💡ይህንን አስተውሉ!!💡
"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው"
-ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ የታላላቅ ስኬታማ ሰዎችን በውድቀት የታጀበ የህይወት ታሪካቸውን በጥቂቱ እንዳስሳለን።
🔱 አብርሃም ሊንከን 🔱
የምድራችን የጥረት እና የፅናት ዋነኛ ምሳሌ ቢባል ማጋነን አይሆንም። አብርሃም ሊንከን በድህነት የተወለደና ህይወቱን በሙሉ ብዙ ውድቀቶች አጋጥመውት የነበረ ሰው ነዉ።በ1816 ገና በልጅነቱ ቤተሰቦቹ ከቤታቸው በግድ በመፈናቀላቸው እነርሱን ለመደገፍ ይሰራ ነበር። በ1818 እናቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየች። ሁለት ጊዜ በስራው ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል ። በ1831 ከጓደኛው ገንዘብ ተበድሮ በጀመረው ንግድ ኪሳራ ገጥሞት የህይወቱን ብዙ አመታት እዳውን በመክፈል አሳልፏል። በ1835 በጣም የሚወዳትን እጮኛውን በሞት አጥቷል። በ1836 ታሞ ለ6 ወራት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ነበር። ከ1836-1856 #ለስምንት ጊዜያት ያህል በተለያየ የስልጣን ደረጃ በምርጫ ተወዳድሮ #ተሸንፏል። በመጨረሻም በ1858 የአሜሪካ ኘሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ።
በጣም ብዙ ጊዜ ተስፋ ሊቆርጥ ይችል ነበር፤ ግን ተስፋ አልቆረጠም።ተሰፋ ባለመቁረጡም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ከፈጠሩ መሪዎች ቀዳሚው መሆን ችሏል።
🔱አልበርት አንስታየን🔱
እስከ አራት አመቱ ድረስ አፋን አልፈታም ነበር ሰባት አመት እስኪሆነው ድረስም ማንበብ አይችልም ነበር። አስተማሪውም " አእምሮው ዘገምተኛ ከሰው የማይግባባ ና በጅል ህልሞቹ ለዘላለም የተወሰደ " ሲል ገልፆት ነበር። የሱ እኩያ ተማሪዎችም ኮልታፋና ተብታባ ይሉት ነበር። በትምህርቱም ደካማ ውጤት ነበረው። ከዛም ይልቅ ራሱን በራሱ ማስተማር እና ያልተገለጠለትን መመርመር ይውድ ነበር። ዝቅተኛው የዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ት/ቤት ለመግባት የመግቢያ ፈተናውን በተደጋጋሚ ቢወስድም ማለፍ አልቻልም ነበር። ከበዛ ልፋት በኋላ ኮሌጅ ቢገባም ከተመረቀ በኋላ አስተማሪዎቹ በየትኛውም ተቋምና ኮሌጅ ተቀባይነት እንዳያገኝ የሚከለክል ደብዳቤ ፅፍውበት ነበር። በዚህም ምክንያት ለብዙ ጊዜ ስራ አጥቶ ተቸግሮ የነበር ሲሆን። ልጆች ማስጠናት ሁሉ ሞክሯል።
አብዝቶ መመራመር የሚወደው አልበርት አንስታይን የመጀመሪያዎቹ የሳይንስ ግኝቶች የቀን ቅዠት ናቸው ተብለው ተጥለው ነበር። በመጨረሻም አለምን የቀየሩ እና ዛሬም ድረስ የሳይንስ ገዢ ግኝቶች ባለቤት እንደሆነ አስመስክሯል።
አልበርት በአንድ ቃለ-መጠይቅ እንደዚህ ብሎ ነበር።
"I have not special talent.I am only passionately curious."
🔱ቶማስ ኤድሰን🔱
-በአሜሪካ ታሪክ ምናልባትም ታላቁ የፈጠራ ሰው ሊባል የሚችለው ይህ ሰው በሚችጋን ሁሮን ትምህርት ቤት ሲገባ ፣አስተማሪዎቹ "በጣም ዘገምተኛ" እና "ትምህርት የማይገባው ደደብ ነው" ብለውት ነበር በዚህም ምክንያት እናቱ ልጇን ከትምህርት ቤት አስወጥታ ቤት ውስጥ ልታስተምረው ወሰነች። ትንሹ ኤዲሰን በሳይንስ የተሳበ ነበር።ገና በልጅነቱ የኬምስቲሪ ላብራቶሪ ሰርቶ ነበር። የኤዲሰን ፅናትና ጉብዝና በመጨረሻ ከ1300 በላይ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት እንዲሆን አደረገው። ቶማስ ኤዲሰን አምፖል ሲፈጥር ፣የሚሰራ አምፑል ከማግኘቱ በፊት #1000 ጊዜ ሙከራዎች አድርጐ ነበር።
አንድ ጋዜጠኛ ብዙ ጊዜ መውደቅ ምን ስሜት እንደሚፈጥር ጠይቆት ነበር። ቶማስም ሲመልስ "አንድም ጊዜ አልወደቅኩም ምክንያቱም ስራው የ1000 ደረጃዎች ሂደት ውጤት ነው" ብሏል።
አስተማሪ ታሪክ ነውና ለሌላው ሼር ያድርጉ