ባህረል ሙገ(غ)የባ (የሳዳቶች ስርፋ)


Гео и язык канала: Эфиопия, Тамильский
Категория: Познавательное



Гео и язык канала
Эфиопия, Тамильский
Статистика
Фильтр публикаций


#ወደ_አላህ_ብቻ

አንዳንድ ጊዜ አላህን ለመታዘዝ እንገራለን፣ ሌላ ጊዜ ደካማነታችን ተጭኖን ወንጀል ላይ እንወድቃለን።አላህን  ከሚያመልኩት ወዳጆቹ መካከል ለመሆንም አልደረሰን ይሆናል። ነገር ግን አላህን እንወደዋለን። ልባችን እርካታ አታገኝም ከወንጀል ወደ እርሱ ንሰሐ (ተውበት) በመግባት እንጂ።

ሷሊሆች በሥራ ስለበለጡን አይደለም ከፍ ያሉት። ዘወትር ደጋግመው ወደርሱ የሚመለስ ልብ ስለነበራቸው እንጂ። ደጋግሞ ወደርሱ መመለስ ለርሱ የሚቀርብ ምስጋና ነው፣ ወደርሱ ማልቀስ እረፍት ነው፣ እርሱን መጠየቅ ደስታ ነው።

ተውበት የምንወፈቅበት ይሁንልን ♥



https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
አላህ ሱ.ወ፡

"ባሪያዬ ሆይ! ፈልገኝ ታገኝኛለህ። እኔን ካገኘህኝ ሁሉ ነገር አግንኝተሃል። እኔን ካጣህ ሁሉን ነገር አጥተሃል። እወቅ ከሁሉም ነገር እኔ እበልጥልሃለው ! ይላል።

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR

ብሩህ ቀን!


🙏🙏🙏ኸሚስ ሙባረክ ውዶቹ🙏🙏🙏

😥ገጠሬው ነቢያችን ሰዐወ ቀብር ዘንድ ቆሞ በመተናነስ እኚህን ታሪክ የማይዘነጋቸውን ቃላት ከአንደበቱ አንቧቧቸው፦

ኢላሂ!!! ይህ ውዱ ነቢይህ ነው፣ (እጁን ወደ ቀብሩ እያመላከተ) እኔ ደግሞ ባሪያህ ነኝ፣ ይህ ሸይጣን ደግሞ ጠላትህ ነው።

እኔን ብትምረኝ ውዱ ነብይህ ይደሰታሉ....፤
ባርያህም በማርታህ እድለኛ ይሆናል....፤
ጠላትህም ይበሳጫል...።
ባትምረኝ ግን ውዱ ነቢይህ ያዝናሉ...፤
ባርያህም ይጠፋል...፤
ጠላትህም ይደሰታል....።

አንተ ደግሞ ውዱን ነቢይህን አሳዝነህ፣ ባሪያህን አጥፍተህ፣ ጠላትህን የምታስደስት አይደለህም።
ኢላሂ!!! የዐረብ ነገዶች እኮ የጎሳ አለቃቸው ሲሞት፤ ለሱ ክብር ብለው ቀብሩ ዘንድ በርካታ ባሪያዎችን ነፃ ያወጣሉ።
ይህ ነብይ ደግሞ የዐለም አለቃ ነው። በቀብሩ ዘንድ የቆመ ባሪያህን ለነብይህ ክብር ነፃ በለው
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ያ       ጀመአ🤚🤚🤚
ነገ ሰኞ ነው ይህንን ቀን መፆም የውዱ ነብያችን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ነው ከዛ በተጨማሪም ስራችን ወደ ሰማይ የሚወጣበት ቀን ነው የቻለ ይፁም ያልቻለም ለሌላው ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁን
ለማስታወስ ያክል ነው ረያን የተባለችዋ የጀነት በር🌸🌸💐🌷 ለፆመኞች ተዘጋጅታለች!!!!!!

👇👇👇ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇


https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


በቂያማ ቀን እጅግ ለበረታው ጥማትህ ምራቅህን የምታረጥብበት አንዲት ጠብታ አስሰህ በምታጣበት ጊዜ ተወዳጁ ምርጡ ነቢይ ﷺ ዝንታለም የማትጠማባትን መጠጥ በጃቸው ያጠጡህ ዘንዳ ሶለዋትና ሰላም በርሳቸው ላይ አውርድ
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين في كل لمحة ونفس عدد ما وسعه علم الله.


አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ሟች መሞቱን በምን ያረጋግጣል⁉️
-------------------------------------------------
✍መጀመሪያ የሞተ ሰው መሞቱን አያቅም። ሞቶ እያለ እራሱን ያያል፣ ሁለት መላኢካዎች ይመጣሉ መልካም ሰሪ ከሆነ ነፍሱን ያፅናኑለታል።

ቀባሪዎች መሬት ውስጥ አስገብተው አፈር ሲከምሩበት ግን ማልቀስ ይጀምራል ይጮኸል ግን ጩኸቱን የሚሰማው የለም፣ ሁሉም ሰው ተበትኖ ብቻውን ሲሆን አላህ ነፍሱን ይመልስለታል።
ቀብረውት ሲሄዱም ሰዎች ሲቀሩ የእርሱን ድምፅ እንስሳዎች ሳይቀሩ ይሰሙታል።

አይኖቹን ከፍቶ ይነቃል። በመጀመሪያ ደስተኛ እና አመስጋኝ ነበር ያጋጠመው ነገር ቅዠት ሆኖበት አሁን ከተኛበት ነቅቷል።

ከዚያም በጨርቅ የተጠቀለለውን ሰውነቱን ይነካካውና ምነው እዚህ ምን አየሰራሁ ነው? እሱ እየተሰማው ያለው ነገር ህልም አይደለም የምርም እንደሞተ ይረዳል።

የቻለውን ያህል ይጮኸል ዘመዶቼ ከሰሙኝ ብሎ ግና ማንም መልስ አይሰጠውም ከዚያም ተስፋው አላህ ብቻ መሆኑን ያስታውሳል።

አያለቀሰ ይቅርታ ይጠይቃል ያረብ አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ በህይወቱ ተሰምቶት የማያቀው አስገራሚ ፍርሃት ይዞት ይጮኸል።

መልካም ሰው ከሆነ መልካም ስራው ፈገግ እያለ ሊያፅናናው አጠገቡ ይቀመጣል።

መጥፎ ሰው ከሆነ አስቀያሚ ስራው አስቀያሚ ሆኖ መቶ ያሰቃየዋል።

አላህ ከቁጣው አድኖ ጀነት ከሚገቡት ባሮቹ ያድርገን‼️

መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር ማድረግ አትርሱ ወደ መልካም ያመላከተ ሰው ያመላከትምተውን ያክል አጅር አለው‼️
:
«በየ ጊዜው የምለቃቸውን ጽሑፎች በቀላሉ ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻነሌን ተቀላቀሉት»።

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


መዉሊድ ለሀገራችን፣ ለእስልምና መስፋፋትና ለሙስሊሞቹ ጥንካሬነት የተጫወተዉ ከፍተኛ ሚና 👇
💚💚💚💚💚🇪🇹🇪🇹🇪🇹💚💚💚💚💚
የነቢዩ ﷺ ልደት መታሰቢያ በሀገራችን በተደራጀ መልኩ ህዝባዊ ከሆነ ከ200 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ብሄራዊ ባዕልነቱ ከታወጀም 4 አሥርት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ጊዚያት ለህዝበ ሙስሊሙ ና ለሀገራችን ያስገኘው ፋይዳ መካከል ጥቂቶቹ :-
1) የዕዉቀትና የዳዕዋ ፋይዳ አስገኝቷል
2) የመገናኛ መድረክ (ኮንፈረንስ) ሆኗል
3) መንፈሳዊ ፋይዳን አስገኝቶል
4) ኪነጥበባዊ ፋይዳ አለው
5) እስላማዊ ቁመናን የመጠበቅ ፋይዳ አለው
6) የመዝናኛ አገልግሎትን ይሰጣል
7) ኢስላማዊ ሜዲያ ይሆናል
8) የትግል ጥሪ መድረኮችን
9) የህክምና አገልግሎት መስጫ ይደረግበታል
10) ደስታና ምስጋና ለማድረስ ሰበብ ይሆናል
11) ነቢዩን ﷺ የማስታወስ ሚናው ከፍተኛ ነው
12) ነቢዩን ﷺ የማስተዋወቅሚናው ከፍተኛ ነው
13) የነቢዩን ﷺ ፍቅር የማስረጽ ሚናው እጅግ የላቀ ነው
14) መንፈስን የማደስ ሚና አለው
15) የዳዕዋና የፈትዋ መድረክ ይሆናል
16) የትዉልድ ድልድይ ይሆናል
17) 9. የታሪካችን አካል ሆኗል ፡- መዉሊድ የኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ አካል ሆኗል፡፡ ጥልቅ ማህበራዊ መሠረት ያለዉ ባህልም ፈጥሯል፡፡የኢትዮጵያን እስልምና ከመሻኢኾች የዒልም ማዕዶች፣እነርሱንም ከመዉሊድ መድረኮቻቸዉ ነጥሎ ማየት የማይቻል ነዉ፡፡ ይህንን ማንነትና ታሪክ ሊያጠፋ ወይንም ሊያበላሽ የሚለፋ አካል ለእስልምና መዳከም ሊሰራ እንጅ ፈፅሞውንም ለእስልምና መስፋፋት ሊሰራ አይችልም ።


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ከዚህ ወዲያ ፍቅር!


በዕድሜ ማለዳ በአበባው የልጅነት ወቅት የሚታደሉት የለመለመ ዓለም ነው።ኣው! ለኔ የሩሔን ፍሰሃ የምቋደስበት ምድረገነቴ ነው።እድሉ ገጥሞት የቀረበ ያደገበት፣ወይም የተጠጋው ያውቀዋል።
የኻዲሞች መተናነስን ከሩቅ እያየን ስንገረም ያደግነበት ሐድራ።ትልቅ ሰዎች ታናናሾቻቸውን ሲካድሙ፣ወጣቶች ተቀምጠው አባቶች ቡና ሲቀዱ፣እሳት ሲያነዱ እያየን እንገረም ነበር።ኻዲሞች የሚለዩት ደግሞ ሻላቸውን ወገባቸው ላይ(ኣንዳንድ ቦታ ደግሞ ከትከሻቸው ላይ) ጠበቅ ኣርገው በማሰር ነው።ለካ ለኺድማው ታጥቂያለው ነው!።
እድሜ እውቅና ሳይገድበው ለታናሽ ማዘንን፣ታላቅን ማክበርን እዚህ በተግባር ይዳሰሳል።አባቶች ከነ ትጥቃቸው ወዲህ ወዲያ ሲሉ ይውላሉ።የኺድማ ተራቸው ሲደርስ ልባቸው በሐሴት የሚደልቅ መሆኑ እርምጃቸው፣ቅልጥፍናቸው፣
ከፊታቸው የሚነበብ ፈገግታ በጉልህ ያሳብቃል።

ልብን በአደብ አስተምሕሮና ማንነትን በዕመነት ቀርፆ፣ ኣስዉቦ ከሚያሰለጥን ስልጣኔ ኹሉ ቀዳሚ የማደርገው ሐድራን ነው።ምናልባትም ዛሬ ብዙዎች ላይ ከሚታየው የመልካም ስነ–ምግባር ነፀብራቅ ጀርባ የዚህኛው ዓለም ጠብታዎች ይኖራሉ።በወንድምነት ሰንሰለት የተጋመደ ሁሉ ሶፉን ደምድሞ
ይቀመጣል።ክብ መጅሊስ መሐል የተቀመጠች የእጣን ማጨሻ እቃ እንኳ በከበቧት አስሃቦች ነሻጣ የነሸጠች ትመስላለች።ሽቅብ የሚምዘገዘግ ጭሷን እያንቦገቦገች ቅጥሩን በመልካም መዓዛ ታውደዋለች።እዚህ ከተሰበሰበው ዙምራ ውስጥ አንድም የግል ፍላጎት ኣይንፀባረቅም።አንድም ሰው "እኔ"ብሎ ሚያብሰለስለው ሐጀት የለውም።
ሁሉም ሁሉንም ይረሳል።ግጣሙ ህብረት እኛነትን ገንብቶ፣እኔነትን ኣጥፍቷል።

ሩህ በኺያል ሲከንፍ ዛት ግራና ቀኝ ይወዘወዛል።ጃሊሶች ሁሉ ህብረት በኳለው ዜማ የሚቀኙት ሰላዋት ላይ ተጠምደዋል።ቀልባቸው ላይ የሚፈስስ ዘምዘም ይኖር ይመስል ፍካትን ተላብሰዋል።እዚህ መደማመጥ እንጂ ረብሻ አይታሰብም።ኢማሙ ቢቻ ወይም ኢማሙን ያስፈቀደ ሰው ብቻ! ለዚያውም ቀልብን የሚያርስ፣የሼኾችን ተርቲብ የጠበቀ ወግ ካለው ያወጋል።ሁሉም በጥሞና ያዳምጣል።

በየ ደውሩ ሶፉን ደምድሞ ከተቀመጠው ሐዲር ላይ የሚነበብ ፍቅር፣የቀልብ ሰላም አለ።የወንድምነት ጥምረቱ ባቀማመጥ ይጌጣል።እግሩን ኣጣጥፎ ከተቀመጠ ወንድም ኣጠገብ ጉልበቱ ከጉልበቱ ጋር የገጠመ ወንድም ከጎኑ አለ።በዚሁ ትስስር ሁሉም ኣንድ ይሆናል።በመሐል ደወሩን የሚመሩት ሼኽ እስካላዘዙ ድረስ ኸልዋው ላይ ፍፁም ሰላማዊ ፀጥታ ይሰፍናል።ምንም ኣይነት ኮሽታ ይጠፋል።ፀጥ ረጭ ያሉ ሓዲሮች ቀልባቸው ወደ ኻሊቅ የኮበለሉ ጅስሞች።
………

ልጅ ሆነን፣ በረንዳ ተቀምጠን ከሩቅ የምንቃኘው እኛ እንኳን ገብቶን ይሁን ሳይገባን ብቻ በንዝረት እንወዛወዝ ነበር።

ጥንፍ የጥንፍፍ ልጅ ባባቱም በናቱ፣
ውልውልም የለው መድሓኒትነቱ፣
እንዴት ናት ወላጁ እንዴት ናት እናቱ፣
የኑር ማኖሪያቱ የኑር ሱንዱቂቱ፣
ያለችው ሴቶቹን አትወልዱም እንደኔ።
አሏሁመሶሊ………ሲሉ ሰሊውን ያቀብላሉ።
ኣሺቁም በህበረት ይቀበላል።

ባንድነት የተዋበ፣ባብሮነት ጣምራ የተጌጠ የፍቅር ዜማ ይንቆረቆራል።ቅጥሩ ዳግም ይጀድዳል።
ሳር ቅጠሉም በመደድ ይገባል።ትዕይንቱ ልባችንን በፍቅር ይሞላዋል።ያኔ የተጋትነውን ፍቅር በሩሓችን አፀድ ላይ ነግሷል።እናም ከዚህ ወዲያ ፍቅር የታለ ያስብለናል!❤️


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
አንዲት ቁራሽ ዳቦ አንድን ደሀ ሊያጠግብ ይችላል
~ከአንተ የምትወጣው አንዲት ንግግር ለሌሎች ተስፉ ትሆናለች
~የአንተ ትንሾ እጅ ለሌሎች ምርኩዝ ትሆናለች
~እራስህን ለማስደሰት ሰወችን ለመርዳት ሞክር
🍁🌹
መልካም ምሽት😘
:¨·.·¨: ❀
" ለበጎነት መስፈርት የለውም "

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


አሰላማለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውዶች እነሆ መውሊዱ እየደረሰ ስለሆነ ሁላችንም ከአሁኑ ዝግጅት ማድረግ አለብን ❤️ ኢንሻአላህ እኛም ብዙ ዝግጅት እኛደርግን ነው በቅርቡ ወደ እናተ የምናደርስ ይሆናል በሆኑም አሁን ላይ በፌስቡክ ላይ አዲስ ቻሌንጅ ጀመረናል ሁለችንም መውሊድ ከመድረሱ በፊት ሰው ለመውሊዱ እንዲዘጋጅ መውሊዱን ለመሳታወስ እና ስለመውሊዱ ትምህርት እንዲኛገኙ የምናደርግበት ቻሌንጅ ነው ስለሆነም ሁላችንም ስለ መውሊዱ ይጠቅማል የምትሉትን ፖስት በመፖሰት ቻሌንጁን ይቀላቀሉ እናም ሁላችኝም ፌስፑክ ላይ ከምንፖስተዎ ፖስት ከላይ መፃፊያው ላይ የመሰላልን ምልክት # ነክተን ከዛም በእንግሊዝኛ #mewlidchallenge ብለን በመፃፍ ቻሌጁን እንቀላቀል በተጨማሪም ምንፖስተው ፖስት ከመውሊድጋ የተያያዘ እና ኢስላማዊ መሆን አለበት ያለግባቹን በውስጥ መስመር ጠይቁን

ለመጠይቅ 👉 @Specialiol

#mewlidchallenge


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ነገ ቅዳሜ የኛ የሙስሊሞች አዲስ አመት ሙሀረም 1 / 1444 ነው

አዲስ እቅድ ! አዲስ ተስፋ ! አዲስ ኸበር!

አላህ ኸይር የምንሰማበት አመት ያድርግልን

በኢስላሚክ ካሌንደር ዛሬ የአመቱ መጨረሻ ነው:: ከታች ያለው ዱዓ በአመተ ሂጅራ መጨረሻ ላይ የሚቀራ ነው:: ከመግሪብ በፊት ብንርቀራው የተሻለ ነበር:: ሳንቀራው ያለፈን ሰዎች አሁንም ቢሆን ሶስት ጊዜ ብንቀራው በረካ ነው::



አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ

ለእናንተ ያዘጋጀናቸው ነገሮች
-አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች
-ቂሷዎች እና ሀዲሶች
-ግጥሞች እና የመንዙማ PDF
-አዲስም ሆነ የቆዩ መንዙማዎችን
-የሀድራ ቅጂዎች
- የመንዙማ ፁሁፎች በፎቶ ለፕሮፉይል የሚሆኑ

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ሌሊት የሚሉት ኸልዋ ሰርተናል፤
መጅሊስ የሚሉት ከሌ አንጥፈናል፤
ወንድም የሚሉት ክላሽ ይዘናል፤
ውዴታ የሚሉት መድፍ አጥምደናል፤
ሀድራ የሚሉት ሰንጋ ጭነናል፤
ሊቃ የሚሉት ክላሽ አዝለናል፤
ቀንበጥ የሚሉት ጥይት ታጥቀናል፤
ያሲን የሚሉት ጨሬ ይዘናል፤
ኢሰጅብለኩም አላህ ብሎናል፤
ለምንድን ብለው ይነካኩናል፤
እንደውም እንደው ሆድ ይብሰናል።


አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ

ለእናንተ ያዘጋጀናቸው ነገሮች
-አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች
-ቂሷዎች እና ሀዲሶች
-ግጥሞች እና የመንዙማ PDF
-አዲስም ሆነ የቆዩ መንዙማዎችን
-የሀድራ ቅጂዎች
- የመንዙማ ፁሁፎች በፎቶ ለፕሮፉይል የሚሆኑ

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ ማስታዋስ ለሙእሚኖች ትጠቅማለችና ብለዋል ሀቢቢና መሀሙድ ስለሏሁ አለይሂ ወስለም😍


አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ

ለእናንተ ያዘጋጀናቸው ነገሮች
-አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች
-ቂሷዎች እና ሀዲሶች
-ግጥሞች እና የመንዙማ PDF
-አዲስም ሆነ የቆዩ መንዙማዎችን
-የሀድራ ቅጂዎች
- የመንዙማ ፁሁፎች በፎቶ ለፕሮፉይል የሚሆኑ

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


https://vm.tiktok.com/ZMNXGYAAw/?k=1

የዒናያ የቲክ ቶክ አካውንት ነው ፎሎ በማድረግ እና ለቻሉት ሰው ሼር በማድረግ ይተባበሩን በቅርቡ አዳዲስ ቻሌንጆችን ይዘን ብቅ እንላለን ኢንሻአላህ


ስምንቱ የእናት «ዉሸቶች»
💐💐💐 🌹 💐💐💐

እናት ውሸት ትናገራለች ብዬ አልጠረጥርም ነበር። ግና በእናቴ ላይ 8 «ውሸቶችን» ካስተዋልኩ በኋላ ጥርጣሪዬ ትክክል እንዳልነበር አረጋገጥኩ። እናት እንዴት «መዋሸት» እንደምትችል ለማሳየት በቀጣይ የሰፈሩትን የገዛ እናቴን ስምንት «ውሸቶች» እንካችሁ ልል ወደድኩ :-

👉 ታሪኩ የሚጀምረው ከልጅነት ዘመኔ አንስቶ ነው። በክፉ ድህነት ለሚሰቃዩት ወላጆቼ አንድያ ልጃቸው ነበርኩ። አብዛኛውን ጊዜ በቤታችን በቂ ምግብ አይገኝም ነበር። ረሃባችንን ለማስታገስ እፍኝ ሩዝ አግኝተን ማዕድ ላይ ስንቀርብ እናቴ ዘወትር ከድርሻዋ እንድመገብ ትሰጠኛለች። በእሷ በኩል ያለውን ሩዝ በሙሉ ወደኔ እየገፋች « ልጄ ሆይ! እኔ ስለጠገብኩ አንተ በደንብ ተመገብ» ትለኛለኛለች።

የመጀመሪያው «ውሸት» ይህ ነው ‼

👉 እናቴ ዕድሜዬ ከፍ እያለ ሲመጣ ርሃቤን ለማስታገስ ከቤታችን አቅራቢያ ከሚገኝ ወንዝ ዳር በመውረድ አንዲት አሳ ብትሆን እንኳ አጥምዳ ትመጣለች። እንደመታደል ሆኖ ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት አሳዎች አንጠልጥላ መጣች። ከጠበሰቻቸው በኋላ ሁለቱንም አሳዎች ከፊቴ አቀረበችልኝ። አንዱን አሳ ቀስ እያልኩ መመገብ ጀመርኩ። እናቴ ደግሞ ከጣልኩት የአሳ አጥንትና እሾህ ላይ የቀረውን ትርፍ ስጋ መመገብ ያዘች። ይህን በማየቴ ልቤ ተረበሸ። ሌላኛውን አሳ እንድትመገብ ከፊቷ አስቀመጥኩላት። ወዲያው ወደኔ መለሰችውና «ልጄ ሆይ! በእጄ የያዝኩትንም የምግጠው ደስ እንዲልህ ብዬ እንጂ አሳ እንደማልወድ አታውቅም እንዴ?» አለችኝ።

ይህ ሁለተኛው «ውሸት» ነው ‼

👉 ዕድሜዬ ለትምህርት ደረሰ። ነገር ግን እናቴ ለትምህርት ቤት የሚያስፈልጉኝን ቁሳቁሶች መግዣ እና የትምህርት ወርሃዊ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ አልነበራትም። በሰፈራችን ከሚገኝ ትልቅ ልብስ ቤት የተወሰኑ የሴቶች አልባሳት እየወሰደች በየቤቱ ከቸረቸረች በኋላ የልብሶቹን ዋጋ እንድትከፍል ተስማማች። በዚሁ ስራ የተነሳ አንድ ቀን በጊዜ ወደ ቤት መምጣት አልቻለችም። ወቅቱ ከፍተኛ ዝናብ የሚጥልበት ብርዳማ ምሽት ነበር። አላስችልህ ቢለኝ እሷን ፍለጋ ከቤት ወጣሁ። በሰፈራችን ባሉ ጎዳናዎች ስፈልጋት ድንገት ተገናኘን። በላስቲክ የተጠቀለለ አልባሳት ተሸክማ የነዋሪውን ቤቶች ታንኳኳለች። «እናቴ ! አሁን ስለመሸ አልባሳቱን ነገ ጠዋት ትሸጫለሽ፤ በዚያ ላይ ብርድ ስለሆነ ወደ ቤት እንመለስ» አልኳት። በግንባሯ ላይ የሚፈሰውን የዝናብ ውኃ እየጠረገችና እንደ ወተት የነጡ ጥርሶቿን በፈገግታ እያሳየችኝ «ልጄ ሆይ! አይዞህ ቅንጣት ታህል ድካም አልተሰማኝም» አለችኝ።

ሦስተኛው «ውሸት» ይህ ነው ‼

👉 ትምህርት የሚዘጋበት ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የመጨረሻ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጀሁ እያለ «ወደ ት/ቤት አብረን መሄድ አለብን» አለችኝ። እኔ ፈተናውን አጠናቅቄ እስከምወጣ እሷ ከት/ቤቱ ቅጽር ግቢ ውጭ ጸሃይ እያንቃቃት መምጣቴን በጉጉት ትጠባበቃለች። ፈተናው እንዳለቀ በእቅፏ ውስጥ አስገብታ ሳመቸኝ። መልካም ዕድል ከተመኘችልኝ በኋላ ገዝታልኝ የነበረውን እሽግ ጁስ ሰጠችኝ። ውኃ ጠምቶኝ ስለነበር ጥሜ እስኪቆረጥ ድረስ በፍቅር ጠጣሁት። ፊቷን ስመለከት በግንባሯ ግራና ቀኝ እየተንኳለለ ወደ ጉንጮቿ የሚወርድ ላብ አስተዋልኩ። በእጄ የነበረውን ፈሳሽ ልሰጣት ብሞክርም «ልጄ ሆይ! እኔ አልጠማኝም፤ አንተ ጠጣልኝ» አለችኝ።

ይህ አራተኛው «ውሸት» ነው ‼

አባቴ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለየን እኔ እና እናቴ ብቻችንን ቀረን። የቤቱ ኃላፊነት በሙሉ በትከሻዋ ላይ ወደቀ። የህይወት ጥልፍልፎሽ ከሸረሪት ድር ይበልጥ በረታብን። ከቀድሞው በባሰ ሁኔታ በረሃብ አለንጋ መገረፍ ጀመርን። ከቤታችን በቅርብ ርቀት የሚኖር አንድ ደግ አጎት ነበረኝ። በረሃብ ጠኔ እንዳንጎዳ አቅሙ የፈቀደውን ያህል «ቅመሱ !» እያለ ይልክልን ነበር። ያለንበት የህይወት ተጨባጭ አስከፊ እየሆነ መምጣቱን ያስተዋሉ ጎረቤቶቻችን የእናቴን ወጣትነት ታሳቢ በማድረግ በህይወቷ ሊደግፋት የሚችል አንድ የትዳር አጋር ከጎኗ መቆም እንዳለባት አምርረው መከሯት። ነገር ግን ሃሳባቸውን ውድቅ በማድረግ «ከትዳር ምንም ጉዳይ የለኝም» አለቻቸው።

አምስተኛው «ውሸት» ይህ ነው ‼

👉 ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተመርቄ ጥሩ የሚባል ስራና ደመወዝ አገኘሁ። «ከእንግዲህ እናቴ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ የምትተውበትና በግሌ ሁሉንም ኃላፊነት የምሸከምበት ጊዜ አሁን ይጀምራል» በማለት ለራሴ ቃል ገባሁ። በወቅቱ ሁሌም ጠዋት ጠዋት ጉሊት ላይ አትክልት ዘርግታ ትቸረችር ስለነበር ስራውን እንድታቆምና ከወር ደመወዜ ላይ በያዘችው ሥራ ከምታገኘው ብዙ እጥፍ የሚሆን ገንዘብ እንደምመድብላት ብነግራትም «ውዴ ሆይ! እኔ በቂ የሚባል ገንዘብ አለኝ ፤ ይልቅ አንተ ገንዘብህን በደንብ ያዝ» በማለት ሃሳቤን ሳትቀበል ቀረች።

ስድስተኛው «ውሸት» ይህ ነው ‼

ከስራዬ ጎን ለጎን ሁለተኛ ዲግሪዬን ለመያዝ ትምህርቴን መከታተል ጀመርኩ። ህልሜ ተሳካ። የስራ እና የደመወዝ ዕድገትም አገኘሁ። በጊዜው የምሰራበት የጀርመን ኩባንያ ጀርመን አገር ውስጥ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ የስራ ዕድል ፈጠረልኝ። ውስጤ ልኬት በሌለው ደስታ ተናጠ። ህይወትን እያጣጣምኩ በአዲስ መልኩ ለመኖር ህልም ሰንቅኩ። ወደ ጀርመን አገር ተጉዤ የስራ እና የኑሮዬን ሁኔታ ካመቻቸሁ በኋላ ለእናቴ ስልክ ደውዬ ከእኔ ጋር አብረን እንድንኖር ጠየቅኳት። እሷ ግን እንድጨናነቅ አልፈለገችም። « ልጄ ሆይ! የተትረፈረፈ ህይወት መምራት የለመድኩ ባለመሆኔ ቢቀርብኝ ይሻላል» አለችኝ።

ሰባተኛው «ውሸት» ይህ ነው ‼

እናቴ የእርጅናን ጣሪያ ነካች። በካንሰር በሽታ ተጠቃች። ከጎኗ ቆሞ የሚያስታምማት ሰው አስፈለጋት። በእኔ እና በምሳሳላት እናቴ መካከል አገራት ግርዶ ሆነው ቆሙ። ቢሆንም ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ በመተው እናቴን ለመጠየቅ ወዳለችበት አገሬ ተመለስኩ። ከተደረገላት ቀዶ ጥገና በኋላ የአልጋ ቁራኛ ሆና አገኘኋት። ስትመለከተኝ ለዘመናት ያስለመደችኝን ውብ ፈገግታ ለመስጠት ሞከረች። የከሳ ሰውነቷን ስመለከት ያቺ የማውቃት እናቴ አልመስልህ ብላኝ ልቤ ቁጭት ባፈላው ውሃ ሲሞሸለቅ ተሰማኝ። ዓይኖቼ የእንባ ቋጠሯቸው ተፈታ። ጉንጮቼም በእንባ ጎርፍ ወረዙ። በዚህ መሃል እናቴም «ውዴ ሆይ ! ለምን ታለቅሳለህ ? ምንም አይነት የስቃይ ስሜት አይሰማኝም» በማለት ልታጽናናኝ ሞከረች።

ስምንተኛው «ውሸት» ይህ ነበር ‼

ከዚያ በኋላ የእናቴ ዓይኖች ላይከፈቱ ለወዲያኛው ተከደኑ።

🌻🌻 🌻🌻

ይለናል ... በሙስሊሙ ዓለም ልብ ላይ ታትሞ ዛሬ ድረስ ከነውበቱ መዝለቅ የቻለውን አቻ የለሽ «የአሪሳላ» ፊልም ዳይሬክት በማድረግ ዝነኝነቱን ያስመሰከረው ሶሪያዊው የአሌፖ ፈርጥ ሙስጠፈል ዐቃድ።


አቡ ዙርዐ'ህ አር-ራዚ'ይ :

[.. ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበል ጋር ነበርኩ ፣ የኢብራሂም ቢን ጧህማን (168 አ.ሂ) ስም ተወሳ ፣ ኢማም አህመድ አሟቸው ደገፍ ብለው ነበር ተነስተው ቁጭ አሉና : " ሷሊሆች እየተወሱ መደገፍ አይገባም " አሉ .. ]

📗 ሲየር አዕላም አንኑበላእ 7/381
•••••••••••••••••••

ሷሊሆችን ማክበርም ስማቸውን እንኳን አክብሮና አልቆ መጥራት የሰለፎች መንገድ ነው::


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
የ አሪፎች በጥበብ የተዋበ አካሔድ!

ሰይዲና ዑመር (ረዲ አሏሁ ኣንሁ) ባንድ ወቅት ከመንገድ ሲያልፉ…እሳት አንድደው ተሰብስበው የተቀመጡ ሰዎችን ተመለከቱ።
«እናንተ የመብራት ሰዎች ሆይ!» በማለት ተጣሩ። ሰይዲና ዑመር…«እናንተ የእሳት ሰዎች ሆይ!»ከማለት የታቀቡት ሰዎቹ ቃሉን ሲሰሙ ቀልባቸው እንዳይጎዳ በመስጋት ነበር።

ሰይዲና ሐሰንና ሑሰይን (ረዲ አሏሁ አንሁም) አንድን ሶሓባ በስህተት ውዱእ ሲያደርግ ተመለከቱ።እና ወደርሱ ተጠጉና እንዲህ ኣሉት።«ከሁለታችን ውዱእ አሳምሮ ማድረግ ማይችለው ማን እንደሆነ በመካከላችን እንድትፈርድ እንፈልጋለን»።ከዚያም ከፊት ለፊቱ ሆነው ውዱእ ማድረግ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ሶሓባው ፈገግ አለ።ሊያስተላልፉት የፈለጉትን መልዕክት ተረዳ።
«በስርዓቱ ማድረግ የማልችለው እኔው ነኝ»በማለት መልሶ ከነሱ በተማረው መልኩ ውዱዑ ማድረጉን ጀመረ።

ታላቁ ሊቀ ሊቃውንት ሰይዲ ኢማም አቡ ሓሚድ አል غዛሊ(ረዐ) ተጠየቁ።
«ያ ኢማም ሶላትን ለዘነጋ ሰው ቅጣቱ ምንድር ነው?»…… ኢማሙም መለሱ፦«ከ እኛው ጋር ወደ መስጂድ ይዘነው መሔድ ነው!»

ወደ channelu ገባ በሉ
https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
«ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ »
ለጌታህ አልቅስ የእንባ ጠብታዎችህን ይመለከታልና: ለእያንዳዱ ችግሮችህ የእርሱን ደጃፍ ቆርቁር ፡ ምድር ለጠበበቻቸው ወንድምና እህቶችህ እጅህን አንስተህ ተማፀን...ግዙፍ የመሰለህ ችግር ይናድልሀል!


አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ

ለእናንተ ያዘጋጀናቸው ነገሮች
-አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች
-ቂሷዎች እና ሀዲሶች
-ግጥሞች እና የመንዙማ PDF
-አዲስም ሆነ የቆዩ መንዙማዎችን
-የሀድራ ቅጂዎች
- የመንዙማ ፁሁፎች በፎቶ ለፕሮፉይል የሚሆኑ

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


........ማስታወቂያ........

ቡታጂራ አካባቢ ለምተገኙ የእስልምና ተከታኞች በሙሉ ነገ ማለትም የኢድ _አል አደሃ (አረፋ) በዓል የሚሰገደው በዝናቡ ምክንያት ሀይ እስኩል ሜዳ መሆኑን ተረገጋጧል እናም ሁላችንም በቻልነው አቅም ላለሰማ እናድርስ
በተጨማሪም ሰላቱ ሚጀመረው 2 : 00 ነው ሁላችንም በጊዜ እንገኝ !!!!

https://t.me/joinchat/U4q9OHoSPqgy3teR


Репост из: Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
ዛሬ ምሽት በኢትዮ ነሺዳ እና መንዙማ (ethioneshidamenzuma)
ይጠብቁን! ⬇️
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma/

Показано 20 последних публикаций.

196

подписчиков
Статистика канала