"የትግራይ ህዝብ ከትላንት ቁስሉ ሳያገግም ዛሬም በጦርነት ወሬ በፍርሃት እንዲኖር ሊፈረድበት አይገባም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**************** የትግራይ ህዝብ ከትላንት ቁስሉ ሳያገግም ዛሬም በጦርነት ወሬ በፍርሃትና በሰቀቀን እንዲኖር በፍጹም ሊፈረድበት አይገባም ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን በመፍጠርና በመንከባከብ ውስጥ ያለው ሚና ጥልቅ ነው ብለዋል።
ትግራይ የስልጣኔ መነሻ እና የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ዋልታ ማገር መሆኑንም እንስተዋል::
የትግራይ ህዝብ በማይፋቅ ቀለም የተፃፈ ብሩህ ታሪክ ያለው ህዝብ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የአገሩ ወዳጅ፣ የሰላምና የብልጽግና ወዳጅና ሥራ ወዳጅ ህዝብ ነው ብለዋል።
ትግራይ የመንግስት አስተዳደር እና ሃገረ መንግስት ግንባታ የተጀመረበትና ተጠበቆ የቆየብትም ምድር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ::
የትግራይ ህዝብ ከምንም በላይ ሃገሩን ወዳድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሰላምም ትልቅ ዋጋ የሚሰጥ ህዝብ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው ብለዋል::
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid026YN4Vugb96GMKN94kgo66irGu1Q56nrLkuFjhXDUcQvpB2Pi81jx3gdYizfoNjThl