© ከ Atiqa Ahmed Ali Facebook የተወሰድ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
ገላቸው ያሳሳል፤ፊታቸው አሳር መከራን ያስረሳል፤ከጀንበር የሚያበራውን ፊታቸውን ለማዬት አይኖች አይታዘዙም ይጭበረበራሉ እንጂ!
ወዳጆቻቸው ቀና ብለው ሊያዯቸውም አይደፍሩም ፤ አጠገባቸው እያሉም ይናፍቋቸዋል ፤ ህይወት ያለርሳቸው ሞት ነው! ታድያ የማይቀረው ሲመጣ ረሱል ሰ.ዓ.ወ ለቀናት በጣም ታመሙ። የርሳቸው መታመም ለባልደረቦቻቸው የቀን ጨለማ ነው። መስጂዳቸው ድምፃቸው ከራቀው ሰንብቷል። የሰውን ሃቅ ክብደት የሚያውቁት ነብዬ ጨንቋቸው ኖሮ አንድ ቀን ታመው ከተኙበት እንደምንም ተነሱና በሰው ተደግፈው መስጂድ ገቡ ። ሰዎች ሁሉ እንዲሰበሰቡም አዘዙ።
በከተማዋ ያለው ሰው ሁሉ ተሰበሰበ ። ረሱልም ህመማቸውን ዋጥ ስቃያቸውን ቻል አድርገው ሚንበር ላይ ወጡ ።
የርሳቸው መታመም ለሃዘን ቆፈን አጋልጦ የሰጣቸው ሶሃቦቻቸው ረሱልን ሰ.ዓ.ወ ሲያዩ አይኖቻቸው እንባ አቀረሩ ።
የኔ ውድ ነብይ በእጃቸው የያዙትን በትር ተደግፈው ሚንበር ላይ ቆሙና በደከመ ድምፅ "እናንተ ሰዎች ሆይ!የመታሁት ሰው ካለ ይኸው አካሌን ይበቀለኝ ። ንብረቱን የወሰድኩበት ሰው ካለም ይኸው ንብረቴን ይውሰድ ።"አሉ።
መስጂዱ ሰው የሌለበት እስኪመስል ድረስ ፀጥታ ሰፈነበት። እንዴት ፀጥ ረጭ አይል??!! ብርሃን ሆነውት የኖሩት ነብይ ከሞት ጣር ላይ ተነስተው ኑዛዜ መሰል ንግግር ሲያሰሙበት እና ከፊቱ የተደቀነውን ጨለማ ሲያስብ!??
በዚህ መካከል አንድ ሶሃባ "ያረሱለላህ በቀል የሚጠይቁ ከሆነ እኔ ልበቀልዎ እፈልጋለሁ ። የበድር ዘመቻ እለት የወታደሮቻችንን ሰልፍ ሲያስተካክሉ ሆዴን በዱላ መተውኛል።እናም ስላሳመሙኝ ልበቀልዎ እሻለሁ!"አለ።ይሄንን የሰሙት ሌሎች ሶሃቦች ልባቸው ራደ፣ደነገጡ ማመንም መቀበልም ባይችሉ በዬተራ መነሳት ጀመሩ……………….!
ዓሊይ ረ.ዓ ተነሱና "እኔን ምታኝ ለረሱል ሰ.ዓ.ወ መስዋእት እሆናለሁ!"አሉ። ለውዳቸው ለመሞት ራሳቸውን ማመቻቸት የለመዱት ነገር ነው።"ዓልይም በቦታው ላይ ተኛለት ሊሞት!" ተብሎላቸዋል።ሌሎቹም እርሳቸውን አጥተው ከመኖር ለርሳቸው መሞትን በደስታ የሚቀበሉ ናቸው!
ረሱል ሰ.ዓ.ወ ግን "ተወው ከራሴ ይበቀል!" አሏቸውና ዱላ አመላከቱት።
ሶሀባው ዱላውን ያዘና ወደ ሚንበር መሄድ ሲጀምር መስጂዱ በለቅሶ ተናወጠ!!! ከነፍሶች ሁሉ በላይ ውድ የሆኑት ነብያችን፣እንኳን ለመመታት ለመታዬት የሚያሳሱት ሃቢባችን ለዛውም በስቃይ ላይ ሆነው ይህ ሊፈጸምባቸው ሲል ማን ያስችለዋል??ምን አይነት ብርቱ አንጀትስ ይገኛል?
ግና ሚንበሩ ጋር ሲደርስ ሌላ ክስተት ነው የታዬው፤ሶሃባው ዱላውን ጣለና እቅቅቅፍ አደረጋቸው! ያ ሰው ዑካሻ ነበር።ፊቱን ከአካላቸው ጋር እያስተሻሸና እንባውን እያረገፈም እንዲህ አላቸው፦
"አንቱ የአላህ መልእክተኛ አካሌ ለአካልዎ መስዋእት ይሁንልዎ!"ያን ጊዜ እዚህም እዚያም የተቋጠሩ የእንባ ከረጢቶች ተፈቱ፤ፊቶች በድጋሚ በእንባ ይታጠቡ ጀመር! ለካ የእርሱ ምኞት ወዲህ ነበር የጠናበትን ናፍቆት ሊያስታግስ፣ገላውን በሸፍዓውና በመድኃኒቱ ጀሰድ ሊባርክ፣ሰውነቱን ከእሳት ሊጋርድ ነበር የሻው!ሆነለትም!
ማዲሁ
"ቢያድለኝ እንደ ኡካሻ ፣
ብስም ያንቱን ትከሻ።ያሉትም ለዚሁ ነው!
#ሶሉ_ዓለል_ሃቢብ!💚💚💚
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓለይህ!