📚ርዕስ:- አደርገዋለው ( i will )
📝ደራሲ:- ቤን ስዊትላድ
👤ትርጉም:- በለጠ ገዳ
📜ይዘት:- psychology ( ሥነ አእምሮ )
📖የገፅ ብዛት:- 194
📆ዓ.ም:- 1990s
📌አዘጋጅ:-
@enmare✅ድብቁን የአአምሮ ክፍል ታላቅ ሃይል ለመጠቀም የሚያስችል የተግባር መመሪያ!!
➡️#ችግር_ባይኖር_ምን_ትሆን_ነበር?
✅ሁሌም ችግር ያጋጥምሃል፡፡ ከፍ እያልክ በሄድክ ቁጥርም ችግርህ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ ሆኖም በዚህ ጉዞህ ችግሮችን እንደ ፈተና በመውሰድ ችግሮችህን መቆጣጠር እንደምትችል ስለምትረዳ ስጋት አይገባህም፡፡
✅ እንቅፋቶችህ ስለሚያስተምሩህ ልታመሰግናቸው ይገባል፡፡ ችግር የሌለበት ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ለደቂቃዎች አስበው እስቲ፡፡ በጣም ደባሪ ከመሆኑ የተነሳ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ መኖር አትፈልግም፡፡
✅ ሁልጊዜ በቀላሉ የምታሸንፈው ጨዋታ ያስደስትሃል? አይመስለኝም!
ምክንያቱም ችግሮችን ማስወገድ መቻል ነው የአሸናፊነት ስሜትን የሚያመጣው፡፡ ማንኛውንም ነገር ያለ ምንም ጥረት የምታገኘው ቢሆን ኖሮ በሕይወትህ የምትፈልገው ነገር አይኖርም ነበር፡፡
✅ ችግር ሲፈጠር ከችግርህ የበለጥክ በመሆንህና ለበለጠ ዕድገት አጋጣሚውን ስለሚያመቻችልህ ፀሎት አድርግ፡፡ ምክንያቱም ችግሮችን በፈታህ ቁጥር በማደግ ላይ ነህ፡፡ በዙሪያህ ያለውን ችግር ከመቅረፍ በተጨማሪ ወደፊት በተመሳሳይ የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን ማስወገድ ያስችልሃል፡፡
📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIO_PDF_BOOKS1@ETHIO_PDF_BOOKS@YETMHRTPDF@BHERE_TREKA