🎙| አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያነሷቸው ጉዳዮች!
ስለነገው ጨዋታ?
🗣| ካርሎ አንቾሎቲ
"ቡድኔ ጨዋታውን ለማሸነፍ በጥሩ ተነሳሽነት ላይ ነው፤ እናም ልክ እንደ ሁልጊዜውም የውድድር ዘመኑ ከባድ ጨዋታ እንደሚሆን እናውቃለን፤ነገር ግን ልዩ የሆነ የውድድር ዘመን እንደምናሳልፍም እርግጠኞች ነን። ባለፉት አመታት ማድረግ እንደቻልነው ዘንድሮም ማሳካት የምንፈልጋቸው ህልሞች አሉን፤ ስለዚህ የነገውም ጨዋታ ይህን ለማድረግ የሚፈቅድልን ጨዋታ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።"
"የዘንድሮው 16ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ውድድር ከባለፉት አመታት ውድድሮች አንፃር ሲታይ የተወሳሰበ ቢመስልም እኛ አሁንም ትግላችንን ለመቀጠል ባለን ነገር ሁሉ እርግጠኞች ነን።"
ከአትሌቲኮ ጋር ስለመጫወት?
🗣| ካርሎ አንቾሎቲ
"እኔ እስከማውቀው ድረስ ከዚህ በፊት ከአትሌቲኮ ጋር ያደረግናቸው ጨዋታዎች በሙሉ ተቀራራቢ የሚባል የፉክክር ደረጃ የነበራቸው ጨዋታዎች ነበሩ፤ስለዚህ የነገውም ጨዋታ በትንሽ ዝርርዝር ጉዳዮች የሚወሰን ጨዋታ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።"
ሮድሪጎ ብራሂም እና ሞድሪች ነገ ይጫወታሉ?
🗣 ካርሎ አንቾሎቲ
"ከአስራ አንድ በላይ ተጨዋቾች አሉኝ፤ ማንም ይሁን ለመጫወት ብቁ የሆነ ሰው ጨዋታው ላይ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፤ ይህም ጥሩ የሚባል እና ትልቅ ለውጥ ያመጣልናል ብዬ አስባለሁ።"
በነገው ጨዋታ ላይ ብዙ መሮጥ ወይስ ልዩነት ፈጣሪ መሆን ጠቃሚ ሊሆን ይችላል?
🗣| ካርሎ አንቾሎቲ
"ብዙ የምትሮጥ ከሆነ መሳል ልታበዛ ትችላለህ፤ ነገር ግን በጨዋታው ላይ ልዩነት ፈጣሪ መሆን ከቻልክ አሸንፈህ ትወጣለህ።"😁
#ይቀጥላል
@ETHIO_REAL_MADRID_15@ETHIO_REAL_MADRID_15