Enat Bank


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Экономика


Enat Bank is a private commercial bank in Ethiopia. Enat Bank is established to provide banking service to all clients with special focus for women economy empowerment by providing financial and non-financial services.
ማን እንደ እናት!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Экономика
Статистика
Фильтр публикаций


‘’የዓመቱ ድንቅ እናት’’ እና ‘’ለእናቴ’’ የፅሁፍ ውድድር ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፋርቶችን ያውቃሉ?
= = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = =
የእናት ባንክ በ2017 ዓ.ም ከሁለተኛው "ለእናቴ" ከተሰኝው የጹሑፍ ውድድር በተጨማሪ ‘’የዓመቱ ድንቅ እናት’’ የተሰኝ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል።
ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር፡ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣በደብዳቤ ቅርፅ የሚወዳደሩበት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ ድንቅ እናት” የተሰኘው ውድድር፣ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው በሕይወት ያሉና የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች በጹሑፍ በድምጽና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበት ውድድር ነው።
የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
"ለእናቴ"
1. በሌሎች የኅትመት እና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ያልቀረበ ወጥ፣ አዲስና የተለየ መሆን ይኖርበታል፤
2. ጽሑፉ ግልጽ እና ተነባቢ እንዲሆን በኮምፒውተር ተጽፎ፣ በ12 ፎንት የፊደላት መጠን እና በ1.5 የኅዳግ መስመር መቅረብ አለበት፤
3. በ ኤ ፎር (A4) የወረቀት ምጣኔ፣ ከሦስት /3/ ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤
4. ተወዳዳሪዎች፣ ስማቸውን እና አድራሻቸውን የጽሐፍ ሥራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ ይልቁንም ሥራቸውን በሚያሽጉበት ፖስታ ላይ ብቻ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል።
5. የማስረከቢያ ጊዜ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
"የአመቱ ድንቅ እናት"
1. ለውድድር የሚቀርቡት ባለታሪኮች በሕይወት ያሉ እናቶች መሆን አለባቸው፤
2. ታሪካቸው የሚነገርላቸው እናቶች ግዴታ ወላጅ እናት (የስጋ እናት) መሆን አይጠበቅባቸውም፤ ለምሳሌ አሳዳጊ ወይም ደግሞ በሰፈር አሊያም በጎረቤት ያሉ እናቶችን ታሪክ ማቅረብ ይቻላል።
3. በዚህ ውድድር ላይ ስለ ሚያቀርቡት ታሪኮች በጽሑፍ አሊያም በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሥራዎቻቸውን ቀርፀው ማቅረብ ይችላሉ።
4. የማስረከቢያ ጊዜ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩቡት የውድድር አይነት የሚያቀርቧቸውን ስራዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት አሊያም በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥን እና በኢሜል አድራሻ፡ lenate@enatbankSc.com ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል። ማስታወሻ ፦ ተወዳዳሪዎች ለመወዳዳሪያ ከቀረቡት ሀሳቦች መካከል በአንዱ ብቻ መርጠው መወዳዳር ይኖርባቸዋል፡፡








ጁምዓ ሙባረክ!
**
የእናት ባንክ “ኡሚ”ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አካውንት በመክፈት የባንካችን ቤተሰብ ይሁኑ!
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tik
https://youtube.com/@enatbank
https://instagram.com/enatbank_ins
https://t.me/EnatBank_official
https://www.facebook.com/enatbank.eth
https://twitter.com/bankenat
https://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-c
https://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40E
Website: https://enatbanksc.com






እናት ባንክ በየሺ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ ምርትና አገልግሎቱን በስፋት አስተዋወቀ፡፡
የ2017ዓ.ም የየሺ ጋብቻና እክስፖን  የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ያሜንት ትሬዲንግ   በመተባበር  በአድዋ ድልመታሰቢያና  በወዳጅነት አደባባይ አዘጋጅተውታል፡፡ 
ሥነ ስርዓቱ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን  የተሞሸሩበት ትልቅ አፍሪካዊ ድግስ ነው።
ሥነ-ስርዓቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ለህዝብ  እንዲያስተዋውቁ ትልቅ ዕድልም ፈጥሯል፡፡
ባንካችን በሥነ-ስርዓቱ ላይ ምቹና ዘመናዊ  የባንክ አገልግሎት አማራጮችን በቀጥታና በመገናኛ  ብዙሃን  አማካኝነት ማስተዋወቅ ችሏል፡፡
ባንኩ ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ  ጠቀሜታ  ያላቸውን አዳዲስ የባንክ አገልግሎቶችን ፣የዲጂታል ባንኪግና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን በስፋት  እየሰጠ እንደሚገኝ አስተዋውቋል፡፡
በተጨማሪም ባንካችን አክሲዮን በመሸጥ ላይ መሆኑን ገልጿል።
የባህልና  ስፖርት  ሚኒስትር  ሻዊት  ሻንካ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሺጋብቻና ኤክስፖ  ማህበራዊ እሴትን አጉልቶ ለማሳየትና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማነቃቃት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር  ተናግረዋል፡፡
የሺጋብቻ በርካታ ጥንዶች በአንድ የሚሞሸሩበት ትዳርን የሚያበረታታና ባህላዊ  እሴትን ለአለም ለማስተዋወቅ መልካም እድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የያሜንት  ትሬዲግ መስራችና ፕሬዝዳንት  አቶ አስናቀ አማኑኤል  ድርጅታቸው ሙሽሮችን በመሞሸርና በትዳር ፀንተው እንዲዘልቁ ስልጠና በመስጠት  ለአገር  ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
        ማን እንደ እናት!






ጁማ ሙባረክ !
ኡሚ የሸሪዓን የፋይናንስ መርሆዎች የተከተለ የእናት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት!! ፈጣንና ዘመናዊ ዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት በምንም አይነት ወለድ መክፈልም ሆነ መቀበል ላይ ያልተመሰረተ ከወለድ ነፃ የባንክ የአገልግልት ለሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚያስገኝ የባንክ አገልግሎት አማራጭ!!
ከወለድ-ነፃ የባንካችን ደንበኛ ሲሆኑ ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነው የባንካችን አገልግሎት የተቀማጭና ተንቀሳቃሽ ቁጠባ ፣ዓለም አቀፍ የባንክ አገለግሎቶች፣የውጭ ምንዛሬ አገለግሎቶች፣፣የዲጂታል ባንኪግ አገልግሎቶችን እንዲሁም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ሀገር የገንዘብ ዝውውር አገልግሎቶችን (የገንዘብ ማስተላለፍና መላላክ) ያገኛሉ፡፡
በባንካችን በሁሉም ቅርንጫፎቻችን በምንታወቅበት እናታዊ መስተግዶ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተቀብለን እያስተናገድን የምንገኝ ሲሆን፤ከወለድ ነፃ የባንካችን ሂሳብ በመክፈት ቤተሰብ ይሁኑ!!
ማን እንደ እናት!

#EnatBank #IFB #Ummi
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tik
https://youtube.com/@enatbank
https://instagram.com/enatbank_ins
https://t.me/EnatBank_official
https://www.facebook.com/enatbank.eth
https://twitter.com/bankenat
https://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-c
https://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40E
Website: https://enatbanksc.com


እናት ባንክ በትብብር ባዘጋጀው ለሁለት ቀናት በቆየው የዲያስፖራ ኤግዚቪሽን ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ፡፡
ኤግዚቪሽኑን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበር ከሮሆቦት ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ያዘጋጀው ሲሆን፣ በዚህም የአገር ውስጥ ምርትና አገልግሎቶች በሰፊው እንዲተዋወቅ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል:፡
ባንካችን በኤግዚቪሽኑ ለዲያስፖራው ምቹና የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስተዋውቋል፡፡
ባንኩ ለዲያስፖራው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የተለያዩ የባንክ አገልግሎት አማራጮች የቁጠባ ሂሳብና ከውጭ ሀገር ገንዘብን በቀላሉ ለመላክ የሚያስችል የዲጂታል ባንክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ በሰፊው አስተዋውቋል፡፡
በተጨማሪም ባንካችን አክሲዮን በመሸጥ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዲያስፖራው አክሲዮን በመግዛት የባንክ ባለቤት እንዲሆን በአክብሮት ተጋብዟል፡፡
ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በኤግዚቪሽኑ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የዲያፖራው ማህበረሰብ የተለያዩ የባንክ አገልግሎት አማራጮችን በመጠቀም የአገር ቤት ቆይታውን በቀለሉ እንዲያሳልፍ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኤግዚቪሽኑ በቀጣይ በካናዳ ቶሮንቶ እንደሚከሄድ ተገልጿል፡፡
ማን እንደ እናት!




መልካም ዜና ከእናት ባንክ
እናት ባንክ ሁለተኛው ለእናቴ የፅሁፍ ውድድር እና የአመቱ ድንቅ እናት የተሰኘውን ውድድር ከታህሳስ 14 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 14 2017 ዓ.ም ባለው የአንድ ወር ጊዜ ተወዳዳሪዎች ስራዎቻችሁን እንድታቀርቡ ብለን የነበረ ሲሆን በብዙ ተወዳደሪዎች ጥያቄ መሰረት እስከ ጥር 30 2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘማችንን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
ስለሆነም “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር፣ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣በደብዳቤ ቅርፅ የሚወዳደሩበት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ ድንቅ እናት” የተሰኘው ውድድር፣ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው በሕይወት ያሉና የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች በጹሑፍ በድምጽና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበት ውድድር ነው።

ማን እንደ እናት !












እንኳን  ለብርሃነ ጥምቀቱ  በሰላም አደረሳችሁ !
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን !
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tik
https://youtube.com/@enatbank
https://instagram.com/enatbank_ins
https://t.me/EnatBank_official
https://www.facebook.com/enatbank.eth
https://twitter.com/bankenat
https://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-c
https://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40E
Website: https://enatbanksc.com

Показано 20 последних публикаций.