EOTC ቤተ መጻሕፍት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ Channel የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ስብከትች እንዲሁም የተለያዩ ለአብነት ትምህርት የሚሆኑ በድምፅ ፤ይሁን በጹሁፍ እንዲሁም በ Video ሚለቀቅበት Channl new
ተጨማሪ ወይም ሚፈልጉትን መፃህፍት
ብለው ይጠይቁን
ማስታወቂያም እንሰራለን በውስጥ መስመር ይጠይቁን
የሰማነዉን እንናገራለን!
ያየነዉን እንመሰክራለን!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት ✅JOIN✅ የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜














እንኳን አደረሳቹሁ
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና )
#እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡
#ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤
#ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤
#ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡
፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና  አባቷ  ወደተቀበሩበት  ወደ ጌቴ  ሴማኒ  ሲወስዷት  አይሁድ  አይተው፤  ልጇ ተነሳ፥ አረገ  እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው  አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ  በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው  ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም)
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡
#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡
*የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ  ያሬድም  ‹‹ሞትሰ  ለመዊት ይደሉ፥  ሞታ  ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
*እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡
**ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል::
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
















እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ
             
Size:-128.8MB
Length:-2:20:43

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5




በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ይጠየቃሉ

በጥምቀት በዓል በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ፣ የትንኮሳ ስብከቶችና አለባበሶችን በማኅበራዊ ሚዲያ ያሠራጩ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ እንደሚጠየቁ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን ግለሰቦችና ቡድኖች ሃይማኖታዊ ቅራኔ እና ጥላቻ ሊፈጥሩ የሚችሉ በቪዲዮ የለቀቁትን አሉታዊ መልእክቶችን እና ተግባራትን በፍጥነት ለማረም በጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ማብራሪያ ለሚዲያ አካላት ሰጥቷል፡፡

በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ  እንዳብራራው ከእምነቱ ሥርዐት ባፈነገጠ መንገድ አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የሌላውን እምነትና ሥርዐት በማንቋሸሽ፣ ክብረ ነክ ተግባራትን በመፈጸም፤ በተለይም በጥምቀት በዓል ታቦተ ሕጉ ላይ በመሳለቅ፤ የኢስላማዊ አለባበስ መገለጫ የሆነውን ጀለቢያ በመልበስ ሙስሊሞች በመምሰል የትንኮሳ ስብከቶችና ዝማሬዎች በማቅረብ፣ የትንኮሳ አለባበሶች ጭምር በመጠቀም በማኅበራዊ ድረገጽ የለቀቁት አጫጭር ቪዲዮችዎች የእምነቱ ተከታዮችን ማስቆጣቱን ያብራራል፡፡

ይህ ዓይነቱ ተግባር በሀገራችን ለዘመናት የዘለቀውን የመከባበር፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽር ድርጊት መሆኑን የገለጸው መግለጫው፤ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ የድፍረት ድርጊት በመሆኑ ይህን የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ፣መጠየቅም መጀመሩን መግለጫው ያስረዳል፡፡ ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሌሎችን መብትና ጥቅም በሚጻረር አግባብነት የሌለውና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት የሚፈጽም ማንኛውም ሕገ ወጥ ተግባር በዝምታና ሊታለፍ እንደማይገባው ይገልጻል፡፡ 

በመጨረሻም ማኅበራዊ ድረገጾችን እና ሚዲያዎችን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮች፣ ትንኮሳዎችና ክብረ ነክ ድርጊቶች የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፡- ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ከፍትሕ የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደሆነ የወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡  አያይዞም ይህ ዓይነቱን ተግባር ለመከላከል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሥርዐት ላይ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የሃይማኖት
ተቋማት ጉባኤ መግለጫ ያስረዳል፡፡

Via ኢኦተቤክ ቴቪ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5



Показано 20 последних публикаций.