በኮሮና ቫይረስ ስጋት #በአዳማ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋረጠ‼️⬇️
በአዳማ ከተማ ሦስት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ መደረጉን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
በከተማዋ ውስጥ የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴም በከፊል እንዲቋረጥ መደረጉን የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ በተለይ ለኢቲቪ ገልፀዋል።
በአዳማ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጅ እና ታክሲዎች ስራ እንዲያቆሙ ቢደረግም ከተማውን አቋርጦ የሚያልፍ የትራንስፖርት አገልግሎት ግን እንደቀጠለ መሆኑም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን እና ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተገለፀው ሦስት ሰዎች መካከል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
@Esat_tv1