የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመከታተል የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
አዳማ፣ ህዳር 21/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በቴክኖሎጂ የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ዙሪያ ለተቋሙ የመገናኛ ብዙኃን ክትትል እና ሚዲያ ጥናት ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሚዲያ እና ማስታወቂያ ክትትል መሪ ስራ አስፈፃሚ፤ አቶ ዴሬሳ ተረፈ፣ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በቀላሉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከታተል ስራ ለማከናወን ቅድሚያ የባለሙያዎችን አቅም መገንባት በማስፈለጉ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልፀው፤ ስልጠናው በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሰራጭ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን ለመከታተል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስገንዝበዋል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በበይነ መረብ እና ማህበራዊ ሚዲያ ክትትል ስልቶች፣ በሃቅ ማጣራት፣ (Content Based Fact Checking Techniques)፣ በበይነ መረብ እና ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ይዘቶች ዙሪያ የሞኒተሪንግ ግኝቶች እና የቀጣይ አሰራር አቅጣጫዎች ቀርበዋል።
*በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ፦
ድረ- ገጽ
www.ema.gov.et
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority