ለተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ፡
ይህ መልዕክት አንድ ሀገሩን ከሚወድ ሀኪም የተፃፈ ነው። እንደሚታወቀው አለማችን በከባድ ፈተና ውስጥ እንደወደቀች ይታወቃል። የተከሰተው ወረረርሽኝ ያደጉ የሚባሉ ሀገሮችን ሳይቀር የተፈታተነ እና አቅም ያሳጣ ከባድ ችግር ነው። በአለማችን ጥሩ የህክምና ደረጃ ላይ የሚገኙትን ሳይቀር በጥበባቸው እንዳይመኩ ያደረገ ከባድ ፈተና ነው። ይህን ወረረሽኝ በአገር ደረጃ አልፎም በአፍሪካ አህጉር ለመቆጣጠር እያሳዩ ያሉትን ቁርጠኝነትና የመምራት ብቃት ሳላደንቅ ማለፍ አልፈልግም። ራሴን ለማስተዋወቅ ያክል ኢትዮጲያን በህክምና ከተመረቀኩበት ቀን ጀምሮ ከገጠር እስከ ከተማ እንዳገለገለ ሀኪም የኢትዮጲያን የጤና አገልግሎትና ተቋማት ከጤና ጣቢያ እስከ እስፔሻላዝድ ሆስፒታል በደንብ አውቀዋለው ። በትንሹም በትልቁም ሀገሬን በታማኝነት አገልግጋለው። ከመማር እስከ ማስተማር ተሳትፊያለው። በወረርሽኝም ባይሆን በአደጋ ጊዜ ጥሪ በተደረገልኝ ሰዓት በደቡብ ኦሞ የጎርፍ አደጋ በኤርቦሬ ወረዳ መሬት ላይ እየተኛው ህዝቤን አግዣለው። ይህን ሁሉ የጠቀስኩበት ምክኒያት ወደ ተነሳሁበት ቁም ነገር ለመድረስ እንደ መንደርደሪያ ስለሚያግዘኝ ነው።
እንደሚታወቀው ሀገራችን በመከላከል ፓሊሲ ለብዙ ዘመን በመቆየቷ ብዙ አመርቂ ውጤቶች አስመዝግባለች ደግሞም ከዘመናዊ ህክምናዎች ዘግይታለች። በዚህም ምክኒያት የጤና ባለሞያው የፓሊሲ ለውጥ እንዲደረግ በቅርብ ጥያቄ ያነሳ መሆኑ ይታወቃል ። ይህ ደግሞ በጊዜ ሂደት የሚመለሰ ጉዳይ እንደሆነ አስባለው ። ዘንድሮ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግን ሁለቱንም የመከላከልና የማዳን ፓሊሲዎች አንድ ላይ ደምረን መሄድ እንዳለብን ያሳየን አጋጣሚ ነው። ይህ ቫይረስ በእድሜ የገፉ እና በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎችን የሚያጠቃ በመሆኑ ሀገራችን ደግሞ በአብዛኛው ወጣት የሚበዛባት በመሆኗ ለመንግስት እና ለጤና ተቋማት በቂ የመዘጋጃት እድልና ጊዜ የሚሰጥ ነው ። ከውጪዎቹ በተለየ ሀገራችን ብዙ የኤች አይ ቪ እና የምግብ እጥረት ያለባቸው ሰዎች ስለሚገኙባት እነዚህን የማህበረሰብ ክፍሎች ያማከለ ስትራቴጂ እንዲነደፍ ማሳሰብ እፈልጋለው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለሚመጡ ታካሚዎች የሚሆን የፅኑ ህሙማን አገልግሎት አቅም እንደሌለን የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ ወረርሽኝ ለተጎዱ የሚሆን ያደጉ ሀገሮች ከሚጠቀሙባቸው የኦክስጅን መስጫ ማሽኖች High flow nasal cannula, Mechanical ventilator, and ECMO መሣሪያዎች ሲሆኑ ፤ እኛ ሁለተኛውን ብቻ የምንጠቀም ሲሆን እርሱም በጣም በብዛት ጥቂት ነው ያለን። ከዛ ባለፈ የበሽተኞቹን የኦክስጅን መጠን ለመለካት ከምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች Pulse oxymeter and Arterial blood gas Analysis አንደኛው አልፎ አልፎ በየሆስፒታሉ የሚገኝ ሲሆን ሁለተኛው ግን የልብ ኦፕራሲዮን የሚሰሩ ሆስፒታሎች ውስጥ ብቻ በጣት የሚቆጠሩ ይገኛሉ። ይህን መረጃ ከእኔ የተሻለ ማቅረብ የሚችሉ ሰዎች ከጎኖ እንዳሉ አውቃለው ነገር ግን ቀጥሎ ለምሰነዝረው ሀሳብ ስለሚጠቅመኝ ነው።
ስለዚህ እነዚህ መሣሪያዎች እስኪሟሉ እና የማከም አቅማችን ከፍ እስኪል በመከላከል ፓሊሲያችን ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንዲያሳዩ እጠይቃለው። በህዝቡ ዘንድ የሚታየውን ከፍተኛ መዘናጋት እልባት እንዲያበጁለት ሳይረፍድ እጠይቃለው። በደህና ጊዜ አሰልጥነው ለክፉ ቀን ያስቀመጡዋቸውን የፀጥታ ሀይሎች ተጠቅመው ህዝብ እንዳይሰበሰብ እና በብዛት እንዳይቆም ከነገ ጠዋት ጀምረው ቢያስፈፅሙ ታሪክ ያስታውሶታል። ይህ ሀሳብ በእርሶ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ ሲሆን ወደ አፈፃፀም እንዲሻገር ለመሳሰብ ያክል ነው። የፀጥታ ሀይሎች አድማ እና አመፅ ለመበተን ብቻ እስከ ዛሬ የተጠቀምንባቸው ሲሆን ነገር ግን ለራሱ የጤና ጥቅም ፓሊስና የመከላከያን ሀይል ቢጠቀሙ ህዝቡም ቅር አይሰኝም ፤ እንጭጩ የዲሞክራሲ ባህላችንም አይጎድፍም።
የሚዲያዎችን ድርሻ እዚህ ጋር መግለፅ አስፈላጊ አይመስለኝም። ሁሉም ሚዲያዎች ሰዓት ተከፋፍለው ለህዝቡ መረጃ እንዲያደርሱ ሀላፊነት ቢጣልባቸው መልካም ነው። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በያሉበት ህዝቡን ማስተማር እንዲችሉ በየቋንቋው ብሮሸሮች ተዘጋጅቶ ቢሰጣቸው ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል መድረስ ይቻላል። ከአንድ ቀን በላይ በልቶ ማደር የማይችለው ማህበረሰባችን ነገ የከፋ ሁኔታ ቢመጣ በረሀብ ከሚያልቅ መንግስት አስቀድሞ ለክፉ ቀን መዘጋጀት ቢጀምር መልካም ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የገበያ እንቅስቃሴዎችን መግታት ተገቢ አይደለም። መራራቅን እና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ ህዝቡን መምከርና ማስገደድ በቂ ነው።
በመጨረሻም የሰው ልጆችን ህይወት ለመታደግ ከፊት ተሰልፈው ለመፋለም የተዘጋጁትን የጤና ባለሞያዎች ማነቃቃትና መደገፍ ያለብን ሰዓት አሁን ነው። ነገር ግን ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መሣሪያዎች Personal protective equipmnets በሀገር ውስጥ የሚመረቱበት መንገድ በፍጥነት ማመቻቸት አለብን። ብዙ የልብስና የፕላስቲክ ዕቃዎች ማምረቻ ባለበት ሀገር ከውጪ እርዳታ እርዳታ መጠበቅ የለብንም። የልብስ ዲዛይነሮች በፈቃደኝነት ከሀኪሞች ጋር በመመካከር ተቀራራቢ የሆነ ደረጃውን የጠበቀ መከላከያ መሣሪያዎች መንደፍ እንዲችሉ መጋበዝና ማሳተፍ ያስፈልጋል። ይህን ያልኩበት ዋናው ምክኒያት እነዚህን መሣሪያዎች የሚያመርቱ ሀገሮች ለራሳቸው ለክፉ ቀን የመደበቅ አዛማሚያ ላይ ስላሉ ነው። በተረፈ የሚያስፈልገው ዕቃ ይሟላለት እንጂ የጤና ባለሞያው የእርሶን የብሔራዊ ጥሪ ለመቀበል በተጠንቀቅ ላይ ነው ያለው።
ሰሞኑን ሀገራችን የኮሮናን ቫይረስ ለማከም የሚያገለግል መድሀኒት ለመስራት ሂደት ላይ እንደሆነች የተገለፀ ሲሆን ብዙዎች ደስታቸውን አንዳንዶች ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። እኔ ግን አዕምሮ እንዳለው አንድ ኢትዮጲያዊ ሁለቱንም ስሜት እጋራለው። ደስታዬ ዜናው ሀገሬ ዛሬም ድረስ እንደ እነ ዶ/ር አክሊሉ ለማ ያሉ ባለ ምጡቅ አእዕምሮ ባለቤቶች መሆኗን ስላረጋገጠልኝ ነው ፤ ሀዘኔ ደግሞ ከሀገሬ ህዝብ የመረዳት አቅም አንፃር ይህ ዜና ብዙዎችን ሊያዘናጋ ይችላል ብዬ ስለማስብ ነው። ስለዚህ ምርምሩ እንደቀጠለ ሆኖ እርሶም የተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ለመሙላት የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የተጀመሩ ስራዎች እንዲቀጥሉ ቀጭን ትዕዛዝ ቢያስተላልፉ መልካም ነው እላለው። በመጨረሻም ሀገራችን የጀመረችው የብልፅግና ጉዞ በልጆቿ ጥረት እንደሚሳካ አልጠራጠርም። እኔም የድርሻዬን ለመወጣት ዝግጁነቴን ስገልፅ በደስታ ነው።
ዶ/ር ያሬድ አግደው
የቀዶ ህክምና ሀኪም
የህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና ፌሎ
ሼር ለማንኛውም አስተያየት @EthioBini_bot
👇👇👇👇
@EthioBini