#ክሎሮኩዊን(Chloroquine Phosphate ) እና #አዚትሮማይሲን(Azithromycine )🤔🤔🤔
#ኮቪድ_19
#COVID_19
፨ ሰሞኑን በሰፊው ስለነዚህ የመድኃኒት ዓይነቶች ሲወራና በግልም በርከት ያሉ የማብራሪያ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ስለነበር የተወሰነ ገለፃ ለማድረግ አሰብኩ ።
፨ እነዚህ መድኃኒቶች በዓለምአቀፍ ደረጃ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ለተለያዩ በሽታዎች ህክምና እንዲውሉ ፈቃድ አግኝተው በጤና ባለሙያ ይታዘዛሉ ።
፨ለምሳሌ ፦
1. ክሎሮኩዊን(Chloroquine Phosphate ) ፦ ለወባ በሽታ(Malaria )፣ ለኤስ-ኤል-ሂ(SLE)፣ ሬውማቶይድ-አርትራይተስ(RA)
2. አዚትሮማይሲን(Azithromycine )፦
በዋንኛነት የመተንፈሻ አካላት ላይ ለሚከሰቱ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች ይታዘዛሉ ።
፨ ታዲያ ሰሞኑን ቻይና ውስጥ በተወሰኑ በኮቪድ_19 በተጠቁ ሰዎች ላይ በተደረገ ''Non_Randomized'' ጥናት ላይ ተመስርተው የአሜሪካው FDA የተባለው ተቋምም በጤና ባለሙያ #እንዳስፈላጊነቱ እንዲታዘዝ ፈቃድ ተሰጥቶታል ።
፨ እዚህጋ ማየት ያለብን ቁልፍ ነገሮች አሉ ፦
1. መድኃኒቶቹ በእርግጥም ፈዋሽ ናቸው አልያም መከላከያ እንደሆኑ የሚያረጋግጥ #በማስረጃ_የተደገፈ የጥናት ውጤት እሰካውኗ ደቂቃ ድረስ የለም ።
2. እነዚህ መድኀኒቶች ለኮቪድ_19 ተጠቂዎች መታዘዝ ካለበት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉት ህመሙ #በጣም_ለጠናባቸው በሽተኞች #በባለሙያ_ብቻ ነው ሲታዘዝ ነው ።
3. #በባለሙያ_ብቻ መታዘዝ አለበት የተባለበት ምክንያት ሰሞኑን በመገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው እስከሞት ድረስ የሚያበቃ የጎንዮሽ ውጤት ስላላቸው ነው ።
#ምን_ማለት_ነው፦ የጤና ባለሙያው እነዚህን መድኀኒቶች መውሰድ የሌለባቸውን ግለሰቦች የሚለይበት መመሪያና ቅድመ-ምርመራ አለ ማለት ነው ።
፨ ስለዚህ እነዚህን መድኀኒቶች ያለባለሙያ ትህዛዝና ክትትል መውሰድ ፦አንደኛ ከጥቅሙ ይልቅ እስከሞት ለሚያደርስ ጉዳት ሊዳርግ ይችላል ሌላው አላግባብ የመድኃኒት እጥረት በማስከተል ከመድኀኒቶቹ ቀጥተኛ ተጠቃሚዎችን ለስቃይና ላለባቸው በሽታ ስር መስደድ ምክንያት መሆን ነው ።
፨ በመጨረሻም አስካሁን ድረስ ለኮቪድ_19 ኢንፌክሽን በሙከራ ደረጃ እንጂ ምንም ዓይነት ፍቱን መድኀኒትም ሆነ መከላከያ አልተገኘም ። ስለዚህም #የጤና_ባለሙያዎችና_የሚመለከታቸው_አካላት የሚሰጡንን #የመከላከል_መንገዶችን ያለመሰልቸት እንከተል እላለው ።
ጤና ይስጥልኝ
Dr Elias G
ለማንኛውም አስተያየት @EthioBini_bot
👇👇👇👇
@EthioBini