ስብዕናችን #Humanity


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Психология


🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Психология
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
✨የትላንት ታሪኮቻችን የሚያስተምሩን ዛሬም ላይ ታሪክ መስራት እንደሚቻል ነው።

ታሪክን መዘከር እና ለትውልድ ማውረስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከትናንት ታሪካችን ጽናትን፣ አብሮነትን እና አገራዊ አንድነትን በመላበስ ዛሬ ላይ የትላንቱን ምኒሊክን መሆን፣ በድህነት ላይ መዝመት፣ ኋላቀርነትን መታገል፣ ለመርህ ተገዥ ሆኖ መተባበር የአሁን አድዋ ድል ነው።

✨ታሪክ በራሱ ነፃ አያወጣም። ታሪክን ተመርኩዞ ጭቆናን አሸንፎ፣ ነፃነትን መቀናጀት ግን ይቻላል። አድዋ ! በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ትልቁ የድል ማማ! ነውና። በአድዋ ጦርነት ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ልዩነቶቻቸውን እና ችግሮቻቸውን ወደ ጎን አድርገው ከ1000 በላይ ኪሎሜትር በእግራቸው በአንድነት ተጉዘው አገራቸውን ከጠላት ወራሪ በመከላከል ታሪካዊ ድል አስመዝግበዋል።

💎ክብር ሃገርን በደም መስዋዕትነት ላቆዩልን ጀግኖች አባቶቻችን።

🌟ይህ ትውልድ የአባቶቹን ጀግንነት ለመድገም የውጭ ወራሪን መጠበቅ የለበትም! እርስ በርስ መፋጀታችንን በማኅበራዊ ሰላም አክመን ÷ኃላቀርነትን በእውቀት ከትበን ÷ ዘመናችንን በይቅር ባይነት በአንድነት በመተሳሰብ አቃንተን፣ የእኛን አደዋን ለመስራት መንቃት አለብን፡፡አንዱ ካንዱ ልብለጥ ማለቱን ይተው፣አንዱ አንዱን ልግፈፍ ማለቱን ይርሳው፣ ያኔ የእኛን አደዋን እንሰራለን ፤ የእኛን አደዋን እናሸንፋለን፡፡

ሁለንተናዊ ኑሮአችን ያስጎመጀ እንዲሆን በማኅበራዊ ፣ በፓለቲካ ፣ በባህል በኢኮኖሚ የእኛን አደዋ ማበጀት አለብን፡፡ ሁላችንም የድል ታሪክን የመድገም ሀላፊነት አለብን።

በድጋሚ እንኳን ለ፻፳፱ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሰን!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity


📍እንኳን ለ129ኛው ለታሪካዊ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት በር ለሆነው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሰን።

@EthioHumanity
@EthioHumanity


♦️እብድ ማለት ከተለመደው ውጪ የሚያስብ እና የሚራመድ  ሳይሆን ከተለመደው ጋር ተጣብቆ እውነተኛ ማንነቱን ክዶ ከተወለደ በኋላ የሰማውን የመጨረሻ እውነት አድርጎ በተወለደበት አካባቢ ታጥሮ ብሄሩን ማንነቱ አድርጎ ሀገሩን ብቻ ሰውነቱ አድርጎ አምኖ የሚኖር ማለት ነው።

☯አንተ ሀገር ብቻ አደለህም አንተ አለም ነህ፣ አንተ ዘር ብቻ አደለህም አንተ የፈጣሪ አምሳል ነህ፣ በፈጠረህ አምላክ ውስጥ ስትሆን የፈጠራቸውን ፍጥረቶች ሁሉ በእኩሌታ ማየት እና ማክበር ትጀምራለህ የሰውነት መለኪያው ይህ ነውና። በዚህ አለም የተፈጠርከው እንደ ካርቦን የተፃፈብህን ለማስተላለፍ ወይንም በጉልቻ መሀል እንደ ተለኮሰ እሳት የተጣደብህን ሁሉ ለማብሰል አይደለም። ከቦክሱ ወጥተህ ለማሰብ  እና አለምን ለማየት ሞክር በስሜት ድልቅታ ጋልበህ እንዳትባክን... አንተ ለሰውነት እንጂ ለማሽንነት አልተጠራህም።

♦️በሀይማኖት አጥር ታጥረህ ሌላውን አትንከስ በዘር ድንቁርና ሰክረህ ሌላውን አታራክስ በግለሰብ ጥፋት እልፎችን አትክሰስ፣ ይልቅ ወደ ልብህ ፍሰስ ተገኝ ወደ ፈጠረህ ንፁህ መቅደስ ወደ ሰራህ ፅኑ መንፈስ ክነፍ፣ በጥላቻ አትቁም ከወንዙ ጋር ፍሰስ ወደ አለም ፍለስ አቋርጥ ገስግስ መሬቴ አፈሬ አትበል አትከለል አለም'ም የአንተ ናት አንተም የአለም ነህ።

💡በሰሀራ በረሀ የሚኖሩ አልኬሚስቶች - ፔራሚዶቹን ከመጎብኘትህ በፊት ፔራሚዶቹን በልብህ ፈልገህ ልታገኛቸው ይገባል አለዛ በፔራሚዶቹ ስፍራም ብትሄድ ፔራሚዶቹን አታገኛቸውም!!'' ይላሉ!  እውነትም በውጪ ያጣችሁት ሁሉ በውስጥ ያልፈለጋችሁት ጉዳይ ነው። አፅናፈ አለም እንዲህ ካሉት ጋር ነው ምትሰራው!

📍አሁን አሁን ሰዎች ከውስጣቸው አለም እየወጡ ከውጪ በሚመጣ የሰዎች አስተያየት ልክ ራሳቸውን ይመለከታሉ... ትክክለኛ የህይወት መስታዎታቹህ ነፍሳቹ ነች እናንተ ግን ከነፍሳቹ ቤት ወታቹህ አለምን ለማትረፍ ትጋጋጣላቹ. የመሰላቸውን በሚናገሩ ሰዎች እይታ የህይወት መልካችሁን ትቀርፃላቹህ።
ቡድሀም ይላል መጥፎ አጋጣሚ ከምዕራብም ሆነ ከምስራቅ አይመጣም። ከውስጥህ ነው የሚፈልቀው።

💎የሰው መልክ ተፈጥሮ ናት የምትነፍሰው እስትንፋስ ከልብህ ድልቅታ ጋር ልትጣመር ይገባል ስትኖር ከልብህ ኑር ፣ አታስመስል!! አለም በህብረት ቢደንስብህ እንኳን፣ አንተ ከነፍስህ በሚወጣው ሙዚቃ ብቻ ተወዛወዝ፣ እብድ ይበሉህ ይህ ማእረግህ ይሁን!

💡ጥላ አልባ ሁን በፍቅር ብርሀን ከነፍስህ ጋር አብራ፣ ጭንብልህን ቅደድ የፈጣሪም ብርሀን ከወስጥህ እንዲፈስ ፍቀድ የተሰመረን አድማቂ ለመሆን አልመጣህም፣ አንተ ካርቦን አይደለህም አንተ ከነበሩትም አሁን ካሉትም ወደፊትም ከሚፈጠሩትም የሰው ፍጥረቶች ሁሉ የተለየህ ነህ። ውስጥህን በታትነህ ከሌሎች ጋር አንድ ለመምሰል አትውተርተር።

✍ Dîž Âb

            ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot




✨አሃ - /Aha Moment/

“What I always want is to have several little ‘aha’ moments where your brain is very happy.” – Scott Kim

ከመቶ ዓመት በፊት በአንዱ ዕለት ነው፣ ሰውየው የሚያማምሩ አበቦች ባሉበት የቤቱ የአትክልት ስፍራ ላይ ተቀምጦ የዕለቱን ጋዜጦች ያገላብጣል። ድንገት… ‘በሞት የተለዩ ሰዎች’ በሚለው አምድ ላይ የአንድን ሰው ዜና እረፍት አየና ክው ብሎ ደነገጠ፣ ጽሑፉን ሲያነብ ጋዜጣው እንደ መርዶ ነጋሪ ሹክክ ብሎ ቤቱ የተገኘ ጥላቢስ እንጂ ተራ ወረቀት አልመስልህ አለው፣ ክውታና ድንዛዜ፣ ደርሶ ጭውውውውው አለበት።

ብንን ብሎ ጋዜጣውን በድጋሚ ተመለከተው፣ አልተሳሳተም፣ በትክክል የሚያነበው የራሱን ዜና እረፍት ነው፣ Dynamite king dies ይላል። ‘የድማሚቱ ንጉስ አረፈ…’ ያ.. ተራራውን ገምሶ.. ቋጥኙን ፈልፍሎ.. አለታቱን ነድሎ መንገድ የሚተልመውን ድማሚት የፈጠረው ሰው አረፈ እያለ ነው… ሰውየው ራሱን ጠየቀ… ‘ይህን ዜና የማነበው በእውኔ ነው በሕልሜ?’ መልስ የለም።

💡ዜናው በዚህ ቢያበቃ ጥሩ አይደል… ስለ ‘ሟቹ’ ሌላም ነገር ይላል፣ And he was the merchant of death…(የሞት ነጋዴ እንደማለት ነው) ሳይሞት ሞተሃል ከመባሉ በላይ እንደ ሙት የሚታሰብበት መንገድ ሰውየውን የበለጠ አስደነገጠው፣ ተንቀጠቀጠ… ሰበበ ሞት ተደርጎ ነዋ የተገለጸው… የጅምላ ፍጅት ምክንያት ተደርጎ ነው የተሳለው… ‘እውነት ሞቼ ቢሆን ሰዎች የሚያስታውሱኝ እንደዚህ እያሉ ነው?’ ሲል ጠየቀ፣ ‘በፍጹም!!! ይህ ቅጽል መፋቅ አለበት!!’

🧨 ይህ ሰው አልፍሬድ ኖቤል ነው። ኖቤል ድማሚትን ‘በመፍጠሩ’ ይታወቃል፣ ግኝቱ ለመንገድ ስራ ያለው አስተዋጽዎ ጎልቶ የሚነገርለት ቢሆንም ኖቤልን ‘ነፍሰ ገዳይ’ ከሚል ስም አላስጣለውም… የፈረንሳይ ጋዜጦች “Le marchand de la mort est mort” (“The merchant of death is dead.”) ብለው ሲዘግቡ ዜናውን በዚያው ወቅት ፈረንሳይ ውስጥ ከሞተው የአልፍሬድ ኖቤል ወንድም ሉድቪግ ጋር አምታተውት ኖሯል፣ ሆኖም አጋጣሚው ኖቤልን ከጥልቅ እንቅልፉ የሚያነቃው ነበር… እናም ይህን ስም ለውጦ ማለፍ እንዳለበት የወሰነው እዚያው ነበር።

💎በፈጠራው ምክንያት ያገኘውን ሳንቲም ሰብስቦ ለበጎ ተግባር እንዲውል ሰጠ፣ በደህናው ዘመን ስለ ድንቅ ጥበቡ የተበረከተች ሳንቲም በችግሩ ጊዜ ስለ ስሙ መታደስ ወጣች፣ ያቺ ሳንቲም በዝታና በርክታ በዓለም ዙሪያ በሳይንስ፣ በስነጽሑፍ፣ በሰላም፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በፊዚክስና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ከፍ ያለ አስተዋጽዎ ለሚያደርጉ ግለሰቦች ሽልማት ሆና የምትቀርብ ሆነች።

ዛሬ ዛሬ የ Nobel Prize Winner መሆን የልዕልና መግለጫ ሆኗል፣ በዙርያችን ‘እከሌ የኖቤል ተሸላሚ ነው’ የሚለው ስያሜ ትልቅ ማዕረግ ሆኗል፣ ብዙ የምናደንቃቸው የዓለማችን ሰዎች የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል፣ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጨምሮ ፣ አዎን… አሁን ኖቤልን ከሞት ጋር አያይዞ ስሙን የሚያነሳ፣ ከውድመት ጋር አቆራኝቶ ስራውን የሚያወሳ አንድ ስንኳ የለም።

ከ’ሞት’ በኋላ በበጎ መታወስ የሚል ቅዥት ሰከንዶችን ተጋርቶኝ አያውቅም፣ ግና ሰው በኑረት ብቻ ሳይሆን በእልፈቱም ለሌሎች መኖር ከቻለ ድንቅነቱ ይገባኛል፣ ያም ሆኖ የበለጠ የሚመስጠው የተረኩ ክፍል ‘በሌሎች ዘንድ የጠለሸን ስም’ ለማደስ የመቁረጡ ጉዳይ ነው።

🔷አስባችሁታል፣ መንግስት ‘ለካ ሕዝብ የሚረዳኝ እንዲህ ነው?’ ብሎ ስሙን ለማደስ ሲተጋ… ፣ ባል በጸጸት ውስጥ ሆኖ ‘ለካ በሚስቴ ዓይን የምመስለው ይህን ነው?’ ብሎ እንከኑን ሲነቅስ… አባት ‘ለካስ ለልጆቼ ጥሩ ወላጅ አልነበርኩም’ ብሎ መንገዱን ለመቀየር ሲወስን… ተቋማት ‘በደንበኞቻችን ዘንድ ያለን ገጽታ ጥሩ አይደለም ለካ’ ብለው ለምርትም ሆነ አገልግሎት መሻሻል ሲሰሩ… ትራፊኮች በአሽከርካሪ ዓይን፣ አሽከርካሪዎች በተሳፋሪ ዓይን…፣ አለቆች በሰራተኛ፣ መምህራን በተማሪ፣ ፍቅረኞች በተፈቃሪያቸው፣ ብቻ ሁሉም በየአንፃራቸው ቦታ ራሳቸውን አስቀምጠው ‘አሃ…’ ቢሉ

🔑አንዳንዴ በሌሎች መስታወት ውስጥ ካላየነው በቀር የማይገለጥ ቁሸት አያጣንም፣ በወዳጅ ምክር ውስጥ ካልሆነ የማይቀና ጉብጠትም እንዲሁ ፣ ‘ለሌሎች’ ሲባል ሁሉ ይፍረስ አይባልም መቼም… ሁሉን ማስደሰት አለመቻል ብቻ ሳይሆን ‘የራስ ጣዕም’ ማጣትም ልክ አይሆንምና

ግን አለ አይደል… ‘በልክ ነኝ’ ካብ ውስጥ ያደፈጠች ክፋት፣ በማናለብኝ ጎሬ ውስጥ የተሸጎጠች ትዕቢት፣ የሌላውን ምቾት የምትነሳ ክርፋት… ምናል.. ‘አሃ…’ እያልን ብናስወግዳት።

ውብ አሁን❤️

✍ ደምስ ሰይፉ

💯 በዚህ ውብ ድልድይ እንሻገር ፣ ሁላችንም ቻናሉን በአብሮነት እንቀላቀል 💯
👇
@BridgeThoughts
@BridgeThoughts

@EthioHumanitybot


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


📍ስለ ህይወት

💡አንድ አባባል አለ በጣም የምወደው ''ቁም ነገሩ ምን ያህል እድሜ ኖረሀል ሳይሆን ምን አይነት ህይወት አሳልፈሀል'' ብዙዎቻችን ካለፍንባቸውን ህይወቶች የምንማረው እሩጫችንን ከጨረስን በኋላ በእርጅና ትናንትን ስንመለከት ነው።  በወጣትነታችን ያለፍንባቸውን የህይወት ዱካዎች አስተውለን ማጥናት ምንችል ቢሆን ግን ነጋችንን ብሩህ የማድረግ ትልቅ እድል ይኖረናል።

"የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ" እንዲል ያገሬ ሰው... የዛሬው ህይወታችን ያለፍንባቸው የህይወት ውጣ ውረዶቻችን ቅጂዎች ናቸው ። እናም ስለ ህይወት የገባኝን ከትናንቶቼ የተማርኳቸውን እንደ አባት ልንገራቹህ.

💡በዚህ አለም ላይ ቋሚ ነገር የለም።
ዛሬ የወደዱህ ነገ ይጠሉሀል ዛሬ ያከብሩህ ነገ ይንቁሀል ዛሬ እንደ አስፈላጊ የተመለከቱህ ነገ አንተን ረስተው ሌላ ህይወትን ሲጀምሩ ታያለህ አየህ ሁሌም ቢሆን ለሰዎች አብዝተህ መጨነቅ የለብህም! ከሰዎች አብዝተህ መጠበቅ የለብህም! በዚህ አለም ቋሚ ነገር የለምና ያለህባትን ህይወት እና ግዜ ብቻ በተገቢው ማጣጣም እወቅበት!

📍ሰዎች ደስታ እና ሀዘንህን የሚፅፉልህ የህይወትህ ደራሲ እንዲሆኑ አትፍቀድላቸው! እነግርሀለው አሁንም ያለኸው አንተ እና አንተ ብቻ ናቹህ ስትሞትም የሚወዱህ ቀብረውህ ህይወትን ይቀጥላሉ... ሁሉም የመጣው ለህይወት እንጂ ለአንተ እንዳልሆነ ተረዳ!
ስለዚህም ለራስህ ክብርን ግዜን ፍቅርን መስጠት እወቅበት ከህይወት ጋር ተዛመድ!

አንድ እውነትን ተረዳ ማንም ሚወድህም ሆነ ሚንቅህ አንተ ላይ ካየው ነገር ተነስቶ ብቻ ነው ሰዎችን አብዝተህ ከማመንህ በላይ ራስህን እመን! ራስህ ላይ ስራ! ሌላው ከሰዎች የሚሰጡህን መልካም ነገሮችን ውደድላቸው አክብርላቸው ነገር ግን ይሄ የመጣው ለራስህ ካለህ ጥልቅ ክብር እንደሆነ ማስተዋል መቻል አለበህ!

♦️ስለዚህም የምትወዳቸውን ሰዎች እንዳታጣ የምትደውን ማንነትህን አትጣለው! ሌሎች ሰዎች ደግሞ ለአንተ ያሰቡ በመምሰል እነሱ በሚፈልጉት ልክ እንድትራመድ መንገድ ሊያመቻቹልህ ይችላሉ ይህ ማለት በሌላ ቋንቋ
(የግል ባርያዬ ላደርግህ እያሰብኩ ነው) እንደማለት ነው ። አንተም ስለምትወዳቸው ውለታም ስለዋሉልህ እነሱን ካለማጣት እና ለማስደሰት የራስህን ማንነት ትተዋለህ ሰዎችም ዙሪያህን እንደተቆጣጠሩ ሲሰማቸው ጥለውህ ይሄዳሉ ! አየህ በማንነትህ አትደራደር ማንም እንዲ ሁን ሊልህ ቢሞክር ከመስመሩ እንዳታሳልፈው! ሰዎች የአንተን ነገር ማክበር ሚጀምሩት ለራስህ ካለህ ፅኑ እምነት ተነስተው ነው።

💎ይቺን እወቅልኝ ማንም በዚህ አለም ያለምክኒያት አብሮህ ሊሆን አይችልም ''ማንም" ካላመንክ ይወዱኛል ብለህ ያሰብካቸውን ሰዎች ''ለምን ከኔ ጋር ሆንክ/ሽ?" በላቸው የሀገር ምክኒያቶችን ሲደረድሩልህ ትሰማለህ 

💡ያለ አንዳች ምክኒያት አንተን የሚወድህ ፈጣሪህ ብቻ ነው። ሰዎች ሁኔታዊ እንደሆኑ እወቅ የቱንም ያህል ቢወዱህ እነሱ ሊያዩህ ከሚፈልጉበት ቦታ ወርደህ ካዩህ ይለዩሀል በቃ ይሄ የሰዎች ተፈጥሮ ነው። ከነፍስህ ጋር መፋቀርን ልመድ ሰዎች ሳይኖሩ ሙሉ መሆንን ልመድ ሁሉም ትቶህ ሄዶ መፈንደቅን ልመድ በህይወት ጭለማህ ውስጥ ብቻህን መሳቅን ልመድ! ለህይወት ቁስሎችህ ሁነኛ ዶ/ር መሆንን ልመድ!

📍ራስህን በወደድክ ቁጥር ህይወት አንተን በጥልቅ መንፈስ ማፍቀር ትጀምራለች... ሰዎችም የህይወት አንዷ አካል ስለሆኑ ወደ በአንተው መሳብ ይጀምራሉ። በሰዎች አትደገፍ !  በራስህ መቆም እስኪሳንህ ድረስ ለሰዎች ራስህን አሳልፈህ አትስጥ ሰዎችን ውደድ ግን በሰዎች አትደገፍ ዘወር ቢሉ መቆም እንደምትችል አሳያቸው!

💡ስትወድቅ አይቶ ሚያነሳህ ፈጣሪ እንጂ ሰዎች አይደሉም። ሰዎች ሁሌም የተሻለን ነገር በተፈጥሮዋቸው ይፈልጋሉ ስለዚህ አንተ ከነሱ ግዜ ጥሎህ አንሰህ ከተገኘህ ጥለውህ ይሄዳሉ እንዳትረሳ! በመጨረሻም አምላክህን ህይወትህን እና ራስህን አጥብቀህ አፍቅር ! ህይወት ያን ያህል ቀላል ትሆናለች ጀግናው!

✍Dîž Âb

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot




📍ፍቅርን ለመስበክ እንደ ጦርነት መሳሪያ መደርደር ወታደር ማሰለፍ ፤ ግዳይ መጣል አያስፈልገንም ። ቅን እና በፍቅር የተሞላች ልብ ብቻ በቂ ነው ። ከጦርነት በኋላ የምናተርፈው ነገር የፈራረሰ ከተማና ማንነት ነው ። ጀግና ነኝ ብሎ ከሚፎክረው ገዳይ ልብ ውስጥ ጥልቅ ፍርሃት ፣ ጥላቻ ፣ ጥርጣሬና ትምክህት ነው የምታገኙት ።

ጦርነት እምቅ ሀብትን አውዳሚ
እምቅ እውቀትን በታኝ፣እምቅ ሀይል ያለው ትውልድን አጥፊ ስለሆነ አስተዋይ ነኝ የሚል ሰው ሊጫወተው የማይገባ ድራማ ነው።

ምላስ የጦርነቶች ሁሉ እናት ነው፡፡ ምላስ አዳኝ ነው፤ ምላስ ገዳይ ነው፡፡ ለአንዱ ንፁህ የሆነው ለሌላው መርዝ ነው፤ አንዱን የፈወሰው ሌላውን ይገድለዋል፡፡በአለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው በሰላም ለመፍታት ቢሞክር ይህ ሁሉ ባልሆነ ነበር የሚሉ አንድምታ ይፈጥራሉ።እኔ ነኝ ልክ ፣ እኔ ነኝ አሸናፊ በማለት የሚነሳ ትውልድ በእልህ የታነቀ ፣ቂምን ያረገዘ ሰለሆነ የሚመጣውን የሀገር ውድመት አያስተውልም።

የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ናት፡፡

📍እናም ወዳጄ

ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው። 

የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ  የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

💡አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው። በፍቅር የሚለመልም እንጂ የሚወድም ግለሰብም ማህበረሰብም ሆነ ሀገር አላየንም ።በፍቅር የተሞላች ልብ ውስጥ ጥንካሬ ፣ቅንነትና ለሁሉ አሳቢነት በአንድንት ጎጆ ሰርተው በፍቅር ሲኖሩ ታያላችሁ ።

ሰው ከፍቅር ውጭ ሊኖር እንዴት ይቻለዋል ! ስለ ፍቅር ስበክ ፣ ስለ ፍቅር  ኑር !

            ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


🌍ምክር ለወዳጅ

📍ወዳጄ ሆይ

ድንቅ ሕይወት ለመኖርና ሕልምህን ለማሳካት ፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም ። ሕልሙ ያንተ ነው ፤ የታየህም ለአንተ ነው ። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብህ አንተ ራስህ ነህ ። አንተ ለሕልምህ ምንም ዐይነት ዋጋ ሳትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች ለአንተ ሕልም ዋጋ እንዲከፍሉ መጠበቅ የለብህም ። አንተ ለሕልምህ የመጨረሻውን ዋጋ እና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ስትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች መረዳት ይጀምራሉ ። ራስህን ስትቀይር ፣ ሌሎች ሰዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ ።  ራስህን ስትቀይር ፣ ሁሉም ነገር መቀየር ይጀምራል ። ሕይወትህ ፣ ቤተሰብህ ፣ ሥራህ ፣ ገቢህ ፣ ጤንነትህ እንዲሁም የምትፈልገው ነገር ሁሉ እንዲቀየር ፣ በመጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ ። ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው ።

📍ወዳጄ ሆይ

ጓደኛ፣ወዳጅ፣ዘመዴ ያልከው ባስቀመጥከው ቦታ ባታገኘው እንደ ነብር በድንገት ተቆጥተህ እላፊ ነገር ውስጥ ዘለህ አትግባ!... ትርፍ ንግግር ሁሌም ቢሆን ሕሊናን ከማቆሸሽ ያለፈ ውጤት ከቶም የለውም፡፡ ይልቅስ ነገሮች ሁሉ ለበጎ ናቸው የሚባለውን የአባቶች ብሂል አስታውስና ነገሩን ናቅ አድርገህ እለፈው። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም።

📍ወዳጄ ሆይ

ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤ አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣ በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።

📍ወዳጄ ሆይ

አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ።  መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም። መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።

📍ወዳጄ ሆይ

የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል " የሚለውን ስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።

📍ወዳጄ ሆይ

እልህ ከራስ ጋር ገመድ መጓተት ነው ። የማይቀጥሉ ነገሮችን መሬት ላይ አስቀምጣቸው ፤ አየር ላይ ከተበተኑ ጉዳት ያመጣሉ ። “የጨዋ ልጅ ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል” እንዲሉ ። የሃያ ዓመቱም የሰማንያ ዓመቱም ሁለቱም የዕድሜ ስስት አለባቸው ። በምናልባት መኖር ጉልበት ይጨርሳል ። ውሳኔ ማጣትም ዕድሜን ይፈጃል ። መኖርህ አለመኖር እንዳይሆን ተጠንቅ ። እንዳትዋረድ ክፉ ጠባይህን አርቅ እንጂ እንዳያዋርዱኝ ብለህ ግን እግርህን አታሳቅቅ።

📍ወዳጄ ሆይ

ያለ መጠን ማድረግ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን
ውጥረትን ያስከትላል አፍ የሚችለውን እጅ ይመጥነዋል እንዲሉ ለሁሉ ነገር መጠን፣ልክ፣ገደብ አለው፡፡ በርሜል ውስጥ የተጠራቀመ ውሃ ከሞላ መፍሰሱ አይቀርም፡፡ መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ።

💎እናም ወዳጄ

ጎደለብኝ በምንለው ጎን ብቻ ነገሮችን ካየን ህይወት መቼም አትሞላም ! ያለንን የሞላውን ግን በደንብ ስንመለከተው ህይወት በራሷ እርካታን ትሰጠናለች ! ያለን የለንም ከምንለው ሁሉ ይበልጣል፣ የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ። ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot




📍በራስህ ችሎታ እና  አቅም ለመሰራት ፈቃደኛ ከሆንክ፣ በሰሪህም ኃይል እና እርዳታ ካመነክ፣ በሌሎች እርዳታ እና ተግዳሮት ጠቀሜታ ላይም እምነት ካለህ፣ ከሁሉም በላይ በራስህ ላይ ከተማመንክ፣ ከወርቅ እና አልማዝ በላይ ደምቀህ ትታያለህ። እራስህን ሁን!! እራስህን መሆን የፈጠረህን አካል አምንህ መቅበል ነው።

💎አልማዝ ጠንካራ ነው። በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልማዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

💡ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል። አልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው። የተሰሩ ሰዎች አልማዝ ናቸው ጠጠር ጠጠር ነው! ጠጠር ከመሬት በቅርብ ርቀት ይገኛል።  አልማዝ በጥልቀት በጋለ ሙቀት እና በከፍተኛ pressure ላይ ይገኛል። ዋጋው ይታወቃል ፤ ድንጋይን ማን ይፈልጋል?  አልማዝ ግን ይፈለጋል ምክንያቱም አልማዝ ጠንካራ ነው ፤ የእርሱ የሆነውን የሚያደምቅ ነው ፤ ከምንም ነገር በላይ ንፁህ እና ውድ ነው።

🔑 እናም ወዳጄ ሆይ

እንደ አልማዝ ውድና ተፈልገህ የምትገኝ ሁን። እንደ አልማዝ በሰዎች መካከል አብራ ፤ ሰዎችን ተስፋ ለግሳቸው ፤ ከቂም ቆሻሻ ነፃ ሁን፤ ይቅር በል ፤ከዘረኝነት ቆሻሻ ታጠብ፤ ከክፋት፤ ከተንኮል እና ከምቀኝነት ራቅ፣ የልብህን ንፅህናን ጠብቅ። ሁኔታዎች ችግር ፈተናዎች አይስበሩህ። ዋጋህ በጣም ውድ ይሁን።

📍የሰው ልጅ ልክ እንደእርሳስ ነው፡፡ እርሳስ ጠቃሚው ነገሩ ውስጡ ነው ያለው፡፡ ለዚህም ነው የሚቀረፀው፡፡ ተቀርፆ ሲያበቃ ታሪክ መፃፍ ሂሳብ መስራት ስእል መሳል ይችላል፡፡ አንተም እርሳስ ነህ በመከራ በፈተና ተቀርፀህ ስታበቃ ነው ታሪክ መፃፍ አለም ማስደመም የምትችለው፡፡ እርሳስ ያለመቅረጫ ዋጋ የለውም አንተም ያለፈተናዎችህ አንተነትህ አይታወቅም፡፡ አስታውስ ሽቶ አናት አናቱን ጫን ሲሉት ነው መልካም መአዛ የሚያወጣው፡፡ መከራህን ውደደው የሰውነትህን መአዛ የሚሰጥህ እሱ ነውና።

               ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።

💛ይህንን ቀን ስናከብር በአንድነት፣ በርህራሄ የወደቀን የምናነሳበት፣ የታመመን የምንጠይቅበት፣ ለተቸገሩ የምንረዳበት የልግስናን መንፈስ በመቀበል ያገኘነውን በረከት የምናካፍል እንሆን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁን።

🎄በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እንመኛለን።
        
🏑 መልካም የገና  በአል 🏑
❤️ስብዕናችን❤️

@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY


🔴ትላንት ማታ የዓለምን ሚስጥር ይነግረኝ ዘንድ ጠቢቡን ለመንሁት
። ከብዙ እርጋታ በኋላም
“ፀጥ በል!... ምስጢሩ በዝምታ ተጠቅልሏልና ሊናገሩት አይቻልም!” ሲል አንሾካሾከልኝ
                                    -ሩሚ

📍ዝምታ ፈጣኑ እርጋታ ነው። ዝምታ ዝ...ግ ነው ፡ ካለትዕግስት የማይከፈት ምስጢር ፤ ዝምታ ዝቅ ነው ፡ አውቃለሁ የማይል ትሁት፡ ዝምታ ወርቅ ነው ፡ ከልብ ተቆፍሮ የሚገኝ ውድ ሐብት ነው።"

🔆ከውጫዊ ገፅታ የበለጠ ውስጣዊ ማንነት ይኑርህ፤ መልክህ፣አለባበስህ፣የምትነዳው መኪና አልያም የምትኖርበት ቤት ያንተን ዋጋ አይተምኑ። እንኳንስ ቁሳቁስህና ሀብት ንብረትህ ቀርቶ ሥራህ፣ ማእረግና ቤተሰብህ እንኳን ያንተ አይደሉም። የእኔ የሚባል ነገር የለም ፣ እሱ ነው ያጠፋን።

♦️አንተ ወደዚህ አለም ከመምጣትህ በፊት የነበረህ እውነተኛ ማንነት አለ ፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ የዚህ አለም ማንነትህ ሁሉም የውሸት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይህ ሰውነትህ አፈር ነው፡፡ህይወት አይደለም፡፡ስምህም ሰዎች ተስማምተው የሰጡህ ጊዛዊ ታርጋ ነው፡፡ድግሪ ካለህም የሚናገረው ኮሌጅ ውስጥ ያሳለፍከውን ጊዜ ነው፡፡ ዝና፣ ትዳር፣ ስልጣንና እዚህ አለም ላይ እኔ ነኝ ብለህ የምታስባቸው ነገሮች ሁሉ አንተን አይደሉም፡፡

🔶እዚህ አለም ላይ አንተን የሆነ ነገር የለም፡፡ መከበርም፡ መዋረድም.... ድህነትም ፡  ሀብትም.... ዝናም ፡ መረሳትም..መማርም:አለመማር...መውለድም ፡ አለመውለድም ሆኑ ሁሉም የዚህ አለም ነገሮች ጊዛዊ ናቸው፡፡ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ ጊዛዊ ያልሆነ ነገር አለ፡፡እሱን ያዘው፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ እውነተኛ ማንነትህ ይህ ነው፡፡

🔷"ያንን ማንንነት ለማግኘት ከጫጫታ መለየት አለብህ፡፡መጀመርያ አለም የጫነብህን ኮተት ከራስህ ላይ ልታራግፍ ያስፈልጋል፡፡ ትኩረትህን በውስጥህ ወዳለው ፈጣሪ ማይረግ አለብህ፡፡ህይወት አይታይም ፡ አይነካም፡ ቅርጽ የለውም፡ አይሞትም፡ አይገደብም አይገለጽም፡፡ህይወት ራሱ ፈጣሪ ነው፡፡ፈጣሪ አሁን ውስጥ ያለ የማይታይ ግንድ ነው፡፡አንተ ደግሞ የማይታይ ቅርንጫፍ ነህ፡፡ከዚህ ከማይታይ የፈጣሪ ግንድ ጋር ስትገናኝ ያንተ የማይታየው ቅርንጫፍ ያበራል፡፡ያለምንም ነገር መደሰት ትጀምራለህ

🌊በህብረተሰብ የጅምላ ጫጫታ ውስጥ የጠፋውን ግለሰባዊ የስብዕና ማንነትን ፈለገን እናግኝ። ጸጥታ፣ ዝምታ፣ እርጋታ ሀሴትን ፈጣሪ ልዩ ገፀ በረከቶቻችን ናቸው።የውስጥ ሰላሙን ያጣ ሰው፣ ውጫዊው ትርምስ ምኑ ነውን?ጠቢብ ግን ባንቀላፉት  መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይመርጣል ... በእርጋታና በጸጥታ የተሞላች ነፍስ የተመረጠች ነች

የሰከነ ልብ፣ አስተዋይ ልቦናን ፈጣሪ ያድለን!

        ውብ ቅዳሚት ለሁላችን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


🟡ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?

(አሌክስ አብርሃም)

💡ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር!  አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret  ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀

🕯ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው  እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው  መዓዛ ከሞያሌ  የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው  ነበርኮ!  ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።

🔦ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱ ጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ።  ከሆነስ ሆነና  ለምንድነው  በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?

📍የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና  በእነሱ ሙያ  Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።

🔑ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ  "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?!  ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ፣ የራስ ክብር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።

✨የሞራል ተቋሞቻችን  በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ  ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል፤እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆኑ።  አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት))) ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው! 

💎ሰው ክብሬ፣ ገመናየ ፣ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን?  ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ  በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልወሰዱት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ ልሙት እንዴ ታዲያ  በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር ምን ያሻግረዋል?!

✍አሌክስ አብርሃም

        ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


🔴ዛሬ ስለማለት መብት እንናገራለን... የምንለውን እንድንል የሚሉትን እንዲሉ ስለመፍቀድ እናወራለን...

🔷ምንድነው ግን እንዲህ አመክንዮ አልባ ያደረገን? ፣ የማለት በር ይከርቸም.. እኛ ብቻ እናውራ የሚያሰኘን ምን ይሆን?... የሌላውን የማለት መብት እግር ከእግር ተከትለህ ስታብጠለጥል የምትጠቀመውን መብት እኮ ነው ተተቺህ የተጠቀመው ፣ እንዳንተ አለማሰብን ስህተት ያደረገው ማን ነው?... እስኪ አንዳንዴ እንኳን ከተባለው ነገር በፊት ለመባሉ እውቅና ስጥ።......ከዚያ አባባሉን ከግለሰቡ ነጥለህ.. በማስረጃ አስደግፈህ.. ወይም ደግሞ ከእይታህ አዋቅረህ ተች... ገና ለገና 'ሃሳቡ ከሃሳቤ ተጣርሷልና .. ቅኝቱ ከቅኝቴ ተፋልሷልና እገሌ የያዘው የረዘዘው ምንትስ የነካው እንጨት ይሁን' ማለት የእውነት Fair አይደለም።

በግሌ የማለት መብት መጋፋታችን ብቻ አይደለም የሚያሳስበኝ አንዳንዴ ወደላይ ምን ካላልን የምንለው ነገር አለን። ያለሙያችን ፣ ያለሜዳችን... ይሄ እውነተኛን ሂስ በስሜት አረንቋ ውስጥ ይደብቅብናል። በዚህ መሃል ፍሬና ግርዱ ተቃቅፎ ይኖራል ፣  አንዳንዴ አንዳንዶች ራሳቸውን እንዲሰድቡ መፍቀድም ብልህነት ነው...

♦️ሌላ የምንረሳው ነገር ደግሞ ተቺውም ሆነ ተተቺው የትችት ሰበብ የሆነው ፣ ነገሩ ያብብ ..... እርስ በእርስ ያማምር ዘንድ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው። እርስ በርስ ካልተያየን እንዴት ልናድግ እንችላለን?... የኔ ስህተት ባንተ ክህሎት ይቃናል... ያንተ ጥፋት በእርሷ ጥቁምት ይፋቃል እንጂ አትድረሱብኝ በሚል ስሜታዊነት እንዴት ይጎለምሳል?... 'አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ' ለማን ይበጃል?...

🔷የአንዳንድ ነገሮች ድጋፋችን ጭፍን ስሜት ይጫነዋል ፣ ዳንኤል ክብረት አንድ መድረክ ላይ ".. ወጣቱ ባዶ ቅናት ይቀናል..." ሲል ሰምቼዋለሁ... ባዶ ቅናት ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ሳይዙ በጥቅል ስሚያ ላይ ከመመስረት የሚመነጭ ስሜት ነው። አንድ ሳር ቅጠሉ ሆ.. የሚልለትን ሰው/ስራ ሌላው ሰው ሲተች የኛን ድንቅ የማሳየት መንገድ መከተል አይደለም የሚቀናን፣ እንዴት እነካለሁ በሚል ቅኝት መደንፋት እንጂ፣ በዚህም ምክንያት እኛም ስለነገሩ ሳናውቅ.. ተቺውም ከስህተቱ ሳይታረቅ ይቀራል... ከትችቱ ቁምነገር የመገብየቱ ነገርማ አይታሰብም.......።

♦️ምን ለማለት ነው?... የተባለው ነገር ፈጽሞ የማንቀበለው ሊሆን ይችላል... አለመቀበላችን ግን የመባል መብቱን መጋፋት የለበትም... ልክነትና ስህተት በመቀበል/መተዋችን ውስጥ ቦታ የለውም... በነገሩ ተፈጥሮ ውስጥ እንጂ...

🔶 ስለዚህም... 'እንዴት እንዲህ ትላለህ?' ሳይሆን 'እንዲህ ማለትህ ከዚህ ከዚህ አንፃር ስህተት ነበር' ማለትና ለውይይት በር መክፈት የተሻለ ነው... ለምን ቢባል ... አንዳንዴ ተመሳሳይ እሳቤንም በተለያየ ቋንቋ እያወሩ 'የተለያዩ' መምሰል አለ... አንዳንዴ ሽንጥ ገትረው የተሟገቱለትን ጉዳይ አድሮ መተውና በሌላኛው ሰው ጫማ ውስጥ መገኘት አለ... ደግሞ አንዳንዴ የትችቱ መልስ ዝምታ መሆን ተቺውን ወደራሱ እንዲያይ ዕድል ሰጥቶት መግባባት አለ...

📍ፈረንሳዊዉ ቮልቴር ለአንድ ጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ ላይ ለማለት መብት መቆሙን ያሳየበት መንገድ ድንቅ ነበር... እንዲህ ብሏል:
"I disapprove of what you say, but I will defend to the death your right to say it."


ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!❤️

                             ✍ ደምስ ሰይፉ

         ፏ ያለች ቅዳሚት ለሁላችን😉

@BridgeThoughts
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram

Показано 20 последних публикаций.