𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮𝗻 𝗘𝗱𝘂𝗰𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻 24


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ትምህርት ነክ መረጃዎች📑 የሚያገኙበት ቻነል!
For promotion 📰(#ADS)
☎️ለማስታወቂያ🔍 @milki_g

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


ወደ መቶ ብር ከፍ ያለው የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት የተለየ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም ተባለ

የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 100 ብር ሆነ ማለት ድሮ ተማሪዎች ሲመገቡ ከነበረበት የምግብ አይነት የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት በቀን ከ22 ብር ወደ 100 ብር መሻሻሉን ተከትሎ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ተመኑ ሲያድግ በተቃራኒው ግን የሚቀርበው የምግብ አይነትና መጠን ያነሰ በመሆኑ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ አሐዱም ይሄንን የተማሪዎች ቅሬታ በመያዝ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል።

በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ በሰጡት ምላሽ፤ የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው፣ "የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም" ሲሉ ገልጸዋል።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ እንዳልቆዩ የሚገልጹት ዶ/ር ሰሎሞን፤ "ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል" ብለዋል።

አሐዱም "የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ማሻሻያ በቂ ነው ወይ? አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርስ ተመጣጣኝ ነው?" ሲል ዩኒቨርስቲዎችን ጠይቋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ የትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች የቀን ምግብ 22 ብር ቢመደብ፤ ከዛ በላይ ወጪ እንደበረው እና ተቋማቱ ለሌላ ሥራ የሚያገኙትን ገንዘብ ለምገባ የሚያውሉበት ሁናቴ መኖሩን ገልጸዋል።

"ዩንቨርስቲዎች በሚመደው 22 ብር ብቻ ተማሪዎቻቸውን አይመግቡም ነበር" ሲሉ ዶ/ር ሰሎሞን ያነሱትን ሃሳብ ተጋርተዋል።

"አሁን የተሻሻለው በጀት በተወሰነ ደረጃ ችግርን ይቀርፋል ተብሎ የሚጠብቅ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የተደረገው ማሻሻያ ቁጥሩ ትልቅ ቢመስልም ቀድሞ ሲወጣ ከነበረው ወጪ አንጻር ሲታይ አሁንም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በአንጻሩ ሌላው አሐዱ ያነጋገራቸው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ቶሎሶ ዳኒ፤ "አሁን ካለው የዋጋ ንረት አንጻር 22 ብር ተማሪዎችን መመገብ አይችልም ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት መሰረት ወደ መቶ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ የተመደበው በተማሪ 100 ብር በቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ ከነበረው 22 ብር ወደ መቶ ብር ከፍ መደረጉ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ መሆኑን አንስተዋል።

ዶ/ር ሰሎሞን የዩንቨርስቲዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሃሳብ ሲያጠናክሩ፤ ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ እንደነበረ ጠቅሰው፤ "ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር" ሲሉ አክለዋል።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ሀላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

🎙[ዘገባው የአሀዱ ራዲዮ ነው]

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥር 15 እና 16 /2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት እና ትራንስክሪፕት ከማይመለስ ኮፒ ጋር እንዲሁም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ መያዝ ይኖርናችኋል ተብሏል፡፡

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#AdigratUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዳቹበት ማስራጃዎች፣ ፎቶግራፍ፣ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ እንደሚገባችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#ማስታወቂያ #Private

በድጋሚ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበትን አድራሻ https://register.eaes.et/Online በመጠቀም በበየነ መረብ መመዝገብ ይችላሉ።

ይህ የበይነ መረብ ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ።

ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ተመዝገቢዎች በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አጋዥ ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት


⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#MattuUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፈኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ

Note:
የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በበደሌ ካምፖስ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


በመቐለ ዩንቨርስቲ ከምግብ ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች መኖራቸው ተገለጸ።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሆነው ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ፤ በመቐለ ዩንቨርስቲ የአሪድ ግቢ እና ዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመ የመብት ጥሰትን በተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የቀን የምግብ በጀትን ከ22 ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ካደረገ በኃላ አዲስ የምግብ ዝርዝር ይወጣል ተብሎ ለተማሪዎች የተነገረ ሲሆን፤ በታሕሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲሱ የምግብ ዝርዝር መሰረት በፊት ሁለት ዳቦ የነበረው የተማሪዎች የጥዋት ቁርስ ወደ አንድ ዳቦ ተቀንሶ መቅረቡን ተከትሎ በግቢዎቹ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገልጿል።

ተማሪዎች ከተማሪ ተወካዮች ጋር የሚያገናኝ እና ቅሬታቸው የሚገልፁበት 'የተማሪዎች የቴሌግራም ገጽ' ያላቸው ሲሆን፤ ከምግብ ጋር ተያይዞ ያላቸውን ተቃውሞ በተደጋጋሚ ያነሱ ተማሪዎች በገጹ አስተዳዳሪዎቸ ከገጹ መሰረዛቸው ተነስቷል።

በዚህም ከተመራጭ ተማሪ ተወካዮች ቁጥጥር ውጪ የሆነ የራሳቸው 'አማራጭ የቴሌግራም ገጽ' በመክፈት  መወያየት ሲጀምሩ፤ አማራጭ ገጹን ከፈቱ የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ታሕሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ ፀጥታ አካላት ታስረዋል ተብሏል።

"የተማሪ ተወካዮች የምግብ ብልሽት ከሚፈጥሩ የዩንቨርስቲው አመራር እና የምግብ ግብዓቶች አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ጋር ግንኙነት አላቸው" የሚል ጥርጣሬ መኖሩም ተጠቁሟል።

ይህን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞና ረብሻ፤ 14 ተማሪዎች መታሰራቸውን የተነገረ ሲሆን፤ የታሰሩበት ቦታም ዓዲ ሓቂ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን አሐዱ ከሪፖርቱ ለመረዳት ችሏል፡፡

የታሰሩት ተማሪዎች ቤተሰብ ሆነ ሌላ ጠያቂ እንደማያገኛቸው እንዲሁም፤ ከታሰሩት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ስላሉ ሕክምና ማግኘታቸውና አለማግኘታቸው አለመታወቁንም ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ አንስቷል።

ከታሰሩት ተማሪዎች የተለቀቁ ተማሪዎች አሉ የተባለ ሲሆን፤ "ገና ያልተለቀቁ ተማሪዎች ፍ/ቤት መቅረባቸውና አለመቅረባቸው አይታወቅም" ብሏል።

በዚህም "በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 16 መሰረት የተደነገገውን 'ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እና ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ድብደባ፣ አያያዝ ወይም ቅጣት መጠበቅ አለበት' የሚሉ ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃዎች ተጥሰዋል" ሲል ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ከሷል፡፡

የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ይህንን መሰረታዊ በሕገ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች የተደነገጉ መብቶች በመጣስ ከፍተኛ ድብደባ እና ማሰቃየት ያደረሱ የፀጥታ አካላት፣ ትዕዛዝ የሰጡ እና ወደ ግቢው እንዲገቡ የፈቀዱ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ምርመራ እንዲያስጀምርም ተጠይቋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)
⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


Woowww😘 #AASTU

🤳ለአይን ያማራ........ጨርሱት😁

🦜AASTU ምግባችን ይለያል ብሏል። እስቲ አሪፉንም ደባሪውንም እንፖስታለን🙌

እስቲ ለ AASTU 👍⚔️👌 React it!

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#AdigratUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዳቹበት ማስራጃዎች፣ ፎቶግራፍ፣ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ እንደሚገባችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደሴ ግቢ፣
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ኮምቦልቻ ግቢ።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


EXIT EXAM NEW 2016 (1).pdf
615.7Кб
Exit_Exam_Questions
ACCOUNTING AND FINANCE EXIT EXAM QUEE
✨ Share with your  Friends
 ⚡️ለ
ዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#WolaitaSodoUniversity

በ2017 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት
ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)
➫ በዩኒቨርሲቲው ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ (ዳውሮ ታርጫ)

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24


#NGAT_EXAM

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በቀጣይ ወር ይሰጣል።

የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የ NGAT ፈተና ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚሰጠው ፈተና ይመዝገቡ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/login

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24




Репост из: ቀሰም Academy
#Advertisement

Old telegram ግሩፖች ያላችሁ

✍️የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም

✍️በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን


➡️2019
➡️2020
➡️2021
➡️2022

ዋጋ
🟥  🔂አሁን ያለው የ group ዋጋ

✍️2018- 500ብር
✍️2019- 450ብር
✍️2020- 400ብር
✍️2021- 350ብር
✍️2022- 300ብር


2023 jan-may ወር የተከፈተ ካሎት ይምጡ

✔️ክፍያ : 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦

ለመሸጥ ምትፈልጉ  inbox
👉 @dag_arshavin


⚠️ ማሳሰቢያ ❗️

የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ይሁን  ዋጋው እኩል ነው ❗️እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ

two step verification ኦን መሆኑን check አርጉ

     
                                               
    

💗💗💗   💗💗💗💗   @ArshavinStore


#DireDawaUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ ም መሆኑ ተገልጿል።

(በምስሉ የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን ይመልከቱ።)

⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news

https://t.me/Ethio_Education_24

Показано 15 последних публикаций.