☑️Present Perfect Tense
Present Perfect + Simple past
አብዛኞቹ ተማሪዎች present perfect tense ይከብዳል 😫 ይላሉ ነገር ግን እመኑኝ ይቺን አጠር ያለች text ካነበባቹ በሗላ ውሃ💧 ነው ሚሆንላችው🤗።
ከአጠቃቀሙ እንጀምርና :-
1⃣) ከአሁን በፊት የተከናወነ አንድ ድርጊት ከነበርና፡ የዚህ ድርጊት ውጤቱ አሁን ላይ የሚይታይ ወይም ያለ ከሆነ present perfectን እንጠቀማለን
➣ማለትም ድርጊቱ ከአሁን በፊት ያለ ከሆነ past ነው ሚሆነው : ነገር ግን ተከናውኖ ያለቀው የ ድርጊቱ ውጤት አሁን (present) ላይ የሚታይ ከሆነ ይኸን ድርጊት በ present perfect እንገልፀዋለን ማለት ነው።
💠 i.e it describes an event that happened in the past and are still true now because you can see the result.
ለምሳሌ፡ ትናንት ከዛፍ🌴 ላይ ወደክ እንበል ከዛ፡ በመውደቅህ ምክንያት እግርህ ተሰብሮ ዛሬ አልጋ ላይ ተኛህ🛌።
አንድ ሰው መቶ ምን ሆነህ ነው ቢልህ
🚼I have fallen from a tree.
ብለህ ትመልስለታለህ። ትናንት ከዛፍ ላይ መውደቅህ ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት(past) ነው፡ በመውደቅህ ምክንያት እግርህ መሰበሩ🦵 የትናንቱ ድርጊት ዛሬ (present) ላይ የሚታይ ውጤት ነው።
ታዲያ ብዙዎቻችን ድርጊቱ ማለትም ከዛፍ ላይ መውደቁ ትናንት ተከናውኖ ያለቀ ድርጊት ነው፡ ለምን በ simple past አይገለፅም የሚል ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን። አሪፍ ጥያቄ ነው ፡ ነገርግን ማስተዋል ያለብን ነገር በትናንትናው ድርጊት ምክንያት ውጤቱ ማለትም ዛሬ ላይ ታሞ መተኛቱ ነው present perfect እንድንጠቀም ያደረገን። ነገር ግን ትናንት በመውደቁ ምክንያት ዛሬ ላይ ካልታመመ ጤነኛ ከሆነ፡ የትናንቱ ድርጊት አሁን ላይ የሚታይ ውጤት ስለለው በ simple past ይገለፃል።
ልዩነቱ፡-
🔘I have fallen🧎♂ from a tree.
( ከዛፍ ላይ በመውደቄ አሁን ላይ ተሰብሬአለሁ ማለት ሲሆን።)
🔘I fell from a tree.🌴
( ከዛፍ ላይ ወድቄያለው ግን አሁን ላይ አልተሰበርኩም ደህና ነኝ ማለት ነው።)
2⃣) ከትንሽ ደቂቃዎች⏳ በፊት የተከናወነን ድርጊት ለመግለፅ።
💠 to describe an event that happened a few minutes ago.
ማለትም ከ 10, 15 or 20 ደቂቃ በፊት ወዘተ የተከናወኑ ድርጊቶችን ለመግለፅ present perfectን እንጠቀማለን ።
ለምሳሌ፡ የ Arsenal ⚽️ ና chelsea ን ጨዋታ አየህና፡ ጨዋታው በ Arsenal አሸናፊነት ተጠናቀቀ እንበል። ጨዋታው አልቆ ከ 20 ደቂቃ በሗላ ጓደኛህ👬 ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ፡ ድርጊቱ ከትንሽ ደቂቃ(ከ 20 ደቂቃ) በፊት የተከናወነ ስለሆነ በ prsent perfect ትገልፀዋለህ።🤗
🔘Arsenal has won the match.🥇
ነገር ግን ጨዋታው ካለቀ ከ አንድ ቀን ምናምን በሗላ ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምትገልፀው😉።so,
🔘Arsenal won🥇 the match.
3⃣) ከሁን በፊት ሲከናወን የነበረ፡ አሁንም በመከናወን ላይ ያለ ድርጊትን ለመግለፅ።
💠 to describe an event that started in the past and is still happening now.
እዚጋ ታድያ ድርጊቱ ከአሁን በፊት
ለምን ያክል ጊዜ ተከናውኖ እንደነበር ለመግለፅ '
For' ን ስንጠቀም ፡ ከአሁን በፊት ሲከናወን የነበረው ድርጊት ከመቼ ጊዜ
ጀምሮ እንደተከናወነ ለመግለፅ '
Since' ን እጠቀማለን።
Example:
🔘Micky has taught computer science for 6 years.
(ለ 6 አመት computer science አስተምሯል፡ አሁንም እያስተማረ ነው።)
🔘 Micky has taught Computer Science since 2006.
( ከ 2006 ዐ.ም ጀምሮ እስካሁን እያስተማረ መሆኑን ይገልፅልናል።)
እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር Micky ከ 2006 ጀምሮ ለ 6 አመት አስተምሮ አሁን ላይ ግን ሌላ ስራ ይዞ ይኸን ትምህርት የማያስተምር ከሆነ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምንገልፀው።
🔘Million taught Computer Science for 6 years.
(ለ 6 አመት አስተምሮ ነበር ፡ አሁን ላይ ግን እያስተማረ አይደለም።)
Examples:
♦️ I have played football since I was a child.
🔷Solomon has gained numerous experiences since he travelled to london.
-Present perfectን በተለያየ form መጠቀም እንችላለን እነዚም:-
🔰Affirmative form
Subject + has/have + V3
🔰Negative form
Subject + hasn't/haven't+V3.