ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለፈረንሳይኛ ቋንቋ ጋዜጠኝነት ክፍት የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ በፍሪላንሰርነት መቅጠር ይፈልጋል።
በመሆኑም፣ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ሥራ ፈላጊዎች ከማክሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ብሔራዊ አካባቢ ወደሚገኘው የኮርፖሬሽናችን ዋና መሥሪ ቤት 10ኛው ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1020 በመቅረብ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻችሁን ዋናውን ከማይመለስ አንዳንድ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ቀርባችሁ ወይም በተወካይ ልካችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ክፍት የሥራ መደቡ ብዛት፡ - 02
የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- ፈረንሳይኛ ቋንቋ አዘጋጅ ጋዜጠኛ
የቅጥሩ ሁኔታ፡- በፍሪላንሰርነት
የክፍያ ሁኔታ፡- በኮርፖሬሽኑ የፍሪላንሰር ሠራተኞች የቀን ክፍያ ስሌት መሠረት፤
የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፍሪላንሰር አዘጋጅ ጋዜጠኞች መቅጠሪያ መስፈርቶች
1. በፈረንሳይኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች በመናገር፣ በመስማት እና በመሥራት ከፍተኛ ክህሎት እና ልምድ ያላቸው፤ ማስረጃዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ሥራቸውን የመተንተን፤ የማደራጀት እና በአተገባበሩም ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች የመፍታት አቅም ያዳበሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
3. ሥራውን የማቀድ፣ የማስተባበር እና የመከታተል ልምድ እና ብቃቱ ያላቸው መሆን አለባቸው፤
4. በሳምንት ውስጥ ለአምስት የሥራ ቀናት ገብተው ለመሥራት ፍቃደኝነትና ቁርጠኝነት ያላቸው፤
5. የኮርፖሬሽኑን የኤዲቶሪያል ፖሊሲ፤ የኤዲቶሪያሉን የሥራ ድርሻዎች ባገናዘበ የተቀመጡትን የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓታት የሚያከብሩ፤
6. ሙሉ ጊዜያቸውን በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ለተሠማሩበት የሥራ ድርሻ በማዋል የሚሠሩ፤
7. ሙያቸውን ለሌላው ሰው ማሠልጠንና አቅም መገንባት የሚችሉ፤ በቡድን የመሥራት ልምድና ዝንባሌ ያዳበሩ መሆን አለባቸው፤
8. የለውጥ አስተሳሰብ እና ተነሳሽነት ያላቸው፤ በሥራቸው መልካም ባህሪያ እና አርአያነት ያላቸው፤
10. አመልካቾች ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
11. ከውጭ አገር የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በአገር ውስጥ ከሚገኝ ሥልጣኑ ካለው ሕጋዊ ተቋም የአቻ ግመታ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
12. የሥራ ልምድ ማስረጃዎች የደመወዝ መጠንና ሕጋዊ የመንግሥት ግብር የተከፈለባቸው መሆኑን መግለፅ አለባቸው፡፡
13. አመልካቾች ተጨማሪ መረጃዎችን ስትፈልጉ በስልክ ቁጥር 0115 17 25 56 ላይ በመደወል ማግኘት የምትችሉ ሲሆን፤ የፈተና ጊዜም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ብ ሮ ድ ካ ስ ቲ ን ግ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን
Join @Ethiojobs2000