4-3-3 World News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


በምዕራባዊት የጀርመን ከተማ ማንሃይም የጀርመን ካርኒቫል በማክበር ላይ በነበሩ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች ላይ አንድ ግለሰብ መኪናውን በፍጥነት በማሽከርከር በፈጸመው ጥቃት በርካቶች መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በዓሉ ከመካሄዱ በፊት እስላማዊ መንግስት ወይም አይ ኤስ እየተባለ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን በተለይ በኮለንና በኑረምበርግ ጥቃት እንደሚፈጽም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አስጠንቅቆ ነበረ። በመሆኑም በዓሉ በሚከበርባቸው ከተሞች ጠንካራ የጸጥታ ጥበቃ የነበረ ቢሆንም ግለሰቡ መኪናውን በፍጥነት በማሽከርከር ጉዳት ሊያደርስ መቻሉን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።
ስለደረሰው የጉዳት መጠንና ስለጥቃት አድራሹ ማንነት ፖሊስ የሰጠው ዝርዝር መረጃ እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ በጥቃቱ 1 ሰው ሞቷል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የትራምፕ አጋሮች ዜለንስኪ አካሄዳቸውን እንዲቀይሩ ወይም ስልጣን እንዲለቁ ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተነገረ

ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ቅርርብ ያላቸዉ ከፍተኛ የሪፐብሊካን ባለስልጣናት የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮልዲሚር ዘለንስኪን ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት ጦርነት ላይ ያላቸውን አቋም እንዲቀይሩ ወይም ወደ ስልጣን እንዲለቁ በመገፋፋታቸዉ ባለፈው ሳምንት አወዛጋቢው የዋይት ሀውስ ስብሰባ በዩክሬን መሪ ላይ ጫና ፈጥሯል።

የአውሮፓ መሪዎች እሁድ እለት በለንደን በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለዘለንስኪ አጋርነታቸዉን ያሳዩ ሲሆን የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር አጋሮቻቸው የመከላከያ ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በሞላላዉ የዋይት ሀዉስ ጽህፈት ቤታቸዉ ውስጥ ከዘሌንስኪ ጋር ከተጋጩ በኋላ የታቀደዉን የማዕድን ውል ሳይፈርሙ ቀደም ብሎ እንዲሄድ ምክንያት ሆኗል፡፡

ዘሌንስኪ በስብሰባው ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እ.ኤ.አ. በ 2019 የተኩስ አቁም ስምምነትን አላከበሩም እና ገዳይ እና አሸባሪ ናቸዉ ሲሉ ተከራክረዋል ።የትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ ዘለንስኪ ጦርነቱን ለማቆም ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸዉን ለዋሽንግተን አስተዳደር ግልፅ አይደለም ብለዋል። ዋልትዝ የትራምፕን ግብ በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል የግዛት ስምምነትን በማካተት በአውሮፓ የሚመራ የደህንነት ዋስትናን በመተካት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ ዘለንስኪ ከስልጣን እንዲለቁ ይፈልጉ እንደሆነ የተጠየቁት ዋልትዝ "ከእኛ ጋር የሚመክር፣ በመጨረሻም ከሩሲያውያን ጋር እና ይህን ጦርነት የሚያቆም መሪ እንፈልጋለን" ብለዋል።"የፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ግላዊ ወይም ፖለቲካዊ ተነሳሽነት በሀገራቸው ውስጥ ያለውን ውጊያ ከማስቆም የተለየ መሆኑ ከታወቀ፣ በእጃችን ላይ እውነተኛ ጉዳይ ያለን ይመስለኛል" ሲሉ ዋልትዝ አክለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የትራምፕ አጋር እና የዩክሬን ተሟጋች የሆኑት የደቡብ ካሮላይና ሴናተር ሊንሴይ ግራሃም ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት የዋይት ሀውስ ግጭትን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ከዘለንስኪ ጋር መስራት ትችል እንደሆነ ጥያቄ እንደፈጠረባቸዉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ


@Ethionews433 @Ethionews433


በሳዑዲ ዓረቢያና በኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 470 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በዚህ ሳምንት ውስጥ 180 ወንዶች፣ 109 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 302 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 157 ወንዶች 11 ሴቶች በድምሩ 168 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆኑ ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 91 ሺህ 420 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የ2.4 ሚሊዮን ሕፃናትን ሕይወት የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
***

በዓለማችን ከከፍተኛ ደም ለጋሾች አንዱ የሆኑት እና በደማቸው በሚገኘው ፕላዝማ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ጄምስ ሃሪሰን ሕይወታቸው ያለፈው በአውስትራሊያ፣ ኒው ሳውዝ ዌልስ በሚገኝ የእንክብካቤ ማዕከል በእንቅልፍ ላይ ሳሉ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

ሃሪሰን የ88 ዓመት አዛውንት ነበሩ።

‘ባለ ወርቃማ ክንዱ' በሚል በአውስትራሊያ የሚታወቁት ሃሪሰን፣ ደማቸው ውስጥ የሚገኘው ፕላዝማ እምብዛም የማይገኘውንና በደም ውስጥ በሽታ የመከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበትን ‘አንቲ ዲ’ን የያዘ ነበር። ይህ ‘አንቲ ዲ’ የሚለገሰው የገዛ ራሳቸው ደም ፅንሳቸውን ለሚያጠቃባቸው ነፍሰ ጡር ሴቶች ነው።

ፕላዝማ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበት በደም ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ክፍል ነው።

ሃሪሰን ደም ለመለገስ ቃል የገቡት የ14 ዓመት ታዳጊ ሳሉ ቀዶ ሕክምና ሲያደርጉ ደም ከተለገሰላቸው በኋላ እንደነበር የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል የደም አገልግሎት ሃሪሰንን ለመዘከር ባጋራው ጽሑፍ ጠቅሷል።

ከዚያም የ18 ዓመት ወጣት ሳሉ ጀምረው ፕላዝማ መለገስ የጀመሩ ሲሆን፤ እስከ 81 ዓመታቸው ድረስ በየሁለት ሳምንቱ ደማቸውን ሲለግሱ ቆይተዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ፕላዝማ በመለገስ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዘው እስከ 2022 ቆይተዋል። ከዚያ ግን ይህን ክብረ ወሰን በአሜሪካዊ ግለሰብ መነጠቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል።

የሃሪሰን ሴት ልጅ ትሬሲይ ሜሎውሽፕ፣ አባቷ ያለምንም ክፍያ እና ህመም የበርካቶችን ሕይወት ስለታደገ ኩራት እንደሚሰማት ገልጻለች።

"ሁልጊዜም ይህን ማድረጉ ምንም እንደማይጎዳው ይናገር እና ‘የምትታደጊው ሕይወት ያንችም ሊሆን ይችላል' ይል ነበር" ብላለች።

ሜሎውሽፕ እና የሃሪሰን ሁለት የልጅ ልጆች የአንቲ ዲ ተቀባይ ናቸው።

"ይህም ሃሪሰንን ልክ እንደኛ ሁሉ በርካታ ቤተሰቦች በእርሱ ደግነት መኖር በመቻላቸው ደስተኛ ያደርገው ነበር" ብላለች።

@Ethionews433 @Ethionews433


ኢትዮጲያዊቷ የእግር ኳስ ተጫዋች ወንድ ነሽ ቢሉኝም እኔ ግን ሴት ነኝ መገለሉ ይቁም ስትል ተናገረች

(ከአራት ዓመት በፊት የተሰራ ዘገባ)

ለሀዋሳ ከተማ የምትጫወተዉ መሳይ ተመስገን በተያዘዉ የዉድድር ዓመት የሴቶች ፕርሚየር ሊግ በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራች ትገኛለች፡፡

ጾታዋን በተመለከተ በርካቶች ጥያቄን ያነሳሉ አንዳንዶችም ከፍተኛ የመገለል በደል እንደሚያደርሱባት ከጋዜጠኛ ምህረት ተስፋዬ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡

ተጫዋቿ በ2006 ዓመት ባህር ዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረ የክልሎች ሻምፒዮና ጨዋታ ላይ በአንድ ጨዋታ አራት ግቦችን ታስቆጥራለች፡፡ይህ ግን መደነቅ አልነበረም ያተረፈላት ይልቁኑ ይህ ተጫዋች ወንድ ነዉ፤አብሮን ሊጫወት አይገባም የሚሉ ዘለፋና የደጋፊዎች ስድብ ከምቆጣጠረዉ በላይ ስሜቴን የጎዳ ክስተት ነበር ስትል መሳይ ተመስገን ተናግራለች፡፡

በእንዲህ ዓይነት ጫና እና ወከባ የተነሳ ከሶስት ዓመታት በላይ ከዉድድር ራሷ እንድታገል አስገድዷታል፡፡በድጋሚ ወደምትመደዉ ስፖርት እንድትመለስ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ ትልቁን ድጋፍ እንዳደረገላትም ታነሳለች፡፡

እግር ኳስ ፌደሬሽኑ በጠየቀዉ መሰረት ምርመራዉን አከናዉና በምርመራዉ ሴት መሆኗ ተረጋግጦላታል፡፡ምም እንኳን መሳይ በምርመራዉ ሴት መሆኗ ቢረጋገጥም በሜዳና ከሜዳ ዉጪ ስሜቷን የሚጎዱ ዘለፋና መገለል ደርሶባታል፡፡

የሰዉነቴ አቋም እኔ ፈልጌ ያመጣሁት አይደለም፡፡ፈጣሪ የሰዉ ልጆችን ሲፈጥር በምክንያት ነዉ፡፡ ስለ እኔ ብዙ የሚሉ ሰዎች ግጭታቸዉ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር ነው፡፡

መሳይ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ መሆኗን የምትናገር ሲሆን ከወጪ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ ከሀገር ዉስጥ ደግሞ የሽታዬ ሲሳይ አድናቂ መሆኗን የብስራት ሬዲዮ የቀድሞ ዘጋቢ ምህረት ተስፋዬ ተናግራለች፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


እስራኤል የሙስሊም ረመዳን እና የአይሁዶች የፋሲካ በዓል እስኪያልፍ ድረስ በሚል ለቀጣይ ስድስት ሳምንታት የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን በጊዜያዊነት ለማራዘም ወሰነች

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ይህንን ያስታወቀው ቀደም ሲል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ላይ ካበቃ በኋላ ብዙም ሳይዘገይ ነበር።

@Ethionews433 @Ethionews433


ልጆቼ ይቅርታ!

ለልጆቼ የማወርሰው የለኝም፣ የምኖረው በቤት ኪራይ ነው የምሰራው የመንግስት መስሪያ ቤት በሹፌርነት ነው!

ለበርካታ ዓመታት ያጠራቀምኳትን የልጆቼን ውርስ ለመቄዶንያ ለመስጠት ነው የመጣውት!

አካውንቴ ላይ 107ሺህ ብር አለ ያሉት አቶ አብርሃም 100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎልናል!

አቶ አብርሃም ልጆቼ ይቅርታ የማወርሳችሁ ገንዘብ አይደለም
ለእናንተ የሚጠቅማችሁ መቄዶንያን ባወርሳችሁ ነው ብለዋል!

@Ethionews433 @Ethionews433


እስራኤል ምንም አይነት የሰብአዊ እርዳታዎች ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገቡ ማስቆሟ ተነገረ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእስራኤልና በሀማስ መካከል ሲተገበር የቆየዉ የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ ለመቀጠል ስምምነት ላይ ሳይደረስ መጠናቀቁ ይታወቃል። ይንንም ተከትሎ ነዉ እስራኤል የሰብአዊ እርዳታዎችን ያስቆመችዉ።

ቀደም ሲል እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ በጋዛ የረመዳን እና የፋሲካ ወቅቶች እስኪያልቁ እንዲራዘም በአሜሪካ የቀረበዉን ሃሳብ እንደምትቀበል አስታውቃ ነበር።

ሃማስ በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እስራኤል የተፈራረመችውን ስምምነት ምዕራፍ ሁለት ተግባራዊ ለማድረግ ያለዉን ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል።

በሌላ በኩል በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን በግዛቲቱ የተከሰተዉን ውድመት ተከትሎ ወደ ጦርነት ሊመልሰን ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀደሰዉ የረመዳን ወር የፆም የመጀመሪያ ቀናቸውን በያዙበት ቀን ገልፀዋል።

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጦርነቱ እስካሁን 48,388 ፍልስጤማውያን መሞታቸውን ሲያረጋግጥ 111,803 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 ቀን 2023 በተጀመረዉ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ቢያንስ 1,139 እስራኤላዉያን ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን ከ200 በላይ በምርኮ ተወስደዋል። ዘገባዉ የአልጀዚራ ነዉ

በ- ሊያ ክብሮም

@Ethionews433 @Ethionews433


#alert

በትግራይ ክልል አብዛኛው ቦታዎች ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበረ መረጃዎች ደርሰውኛል። መቀለ ፣ ዓድዋ ፣ አክሱም ፣ ውቅሮ እና ሌሎች አከባቢዎች ተሰምቷል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል...

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ እና መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡

@Ethionews433 @Ethionews433


“ዘለንስኪ ይቅርታ ይጠይቀኝ“ ትራምፕ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩኬሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በዋይት ሃውስ ያደረጉት ዱላቀረሽ እሰጣገባ አሁንም የዓለምን ትኩረተ እንደሳበ ነዉ።

ይህን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩኬሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በዋይት ሃውስ ላሳየው የማይገባ ድርጊት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃቸው እንደሚፈልጉ ብሉምበርግ አስነብቧል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ማለታቸው ደግሞ በበርካቶች ዘንድ ግርምትን እያጫረ ነዉ።

ዘለንስኪ በኋይት ሀዉስ ባደረገዉ ዉይይት ሰብዓዊ ክብር ተነፍጎታል የቃላት ዉረፋና ጊዜዉን ያልጠበቁ ጥያቄዎች ማስተናገዱ አግባብ አደለም በሚል በርካቶች የሶሻል ሚዲያ ርዕስ አድርገዉታል። ይህ ባልረገበበት ሁኔታ የትራንፕ ጥያቄ ደግሞ ተአምር ማሰኘቱ ተደምጧል።

ዘለንስኪ ከዋይት ሀውስ ከወጡ በኋላ በቀጥታ ያመሩት ወደ እንግሊዝ ሲሆን 2.6 ቢሊዮን ዶላር ተበድረው መመለሳቸውም ተሰምቷል።

የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በመጪው አርብ የ100 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ድጋፍ ለማድረግ አቅዷል ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።

በ-ማህሌት ግርማ

@Ethionews433 @Ethionews433


ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የ129ኛው የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በመርሐ ግብሩ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዓሉ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች እየተከበረ የሚገኘው።

በዚህ መሰረትም በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ተጀምሯል፡፡

በአርበኞች እና በአሁኑ ትውልድ መካከል የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ እንደሚደረግ እና የዓድዋ ድል በዓልን የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብም ተመላክቷል፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


Репост из: 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ፣ ደም ተከፍሎበታል ከደም እና ከአጥንት ...ምስጋና ለነሱ ለአደዋ ጀግኖች ፤ ትናገር አደዋ ትናገር ትመስክር...!!!!!⚔️🎶

እንኳን ለ129ነኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዕለት አደረሳቹ 🇪🇹

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et


የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ለዩክሬን ያላቸዉን ድጋፍ እየገለፁ ነዉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋይት ሀውስ የነበራቸዉን ፍጥጫ ተከትሎ አዉሮፓዉያኑ ከዩክሬን ጎን መሠለፋቸዉን ተናግረዋል።

የጀርመን ፣ የፈረንሳይ ፣ የስፔን ፣ የፖላንድ እና የኔዘርላንድስ መሪዎች ዩክሬንን የሚደግፉ የማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን ካስተላለፉት መካከል ሲሆኑ ዘለንስኪም ለእያንዳንዳቸው
ድጋፍ በቀጥታ የምስጋና ምላሽ ሰጥተዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከኋይት ሀውስ መልስ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለንደን መግባታቸውም ተገልጿል።

ለዩክሬን ድጋፋቸዉን እያሳዩ ከሚገኙት መካከል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "አጥቂ ሩሲያ፤ ተጎጂ ዩክሬን ዩክሬንን መርዳት እና በሩሲያ ላይ ከሶስት አመት በፊት ማዕቀብ መጣላችን ትክክል ነበር" ማለታቸዉ ተሰምቷል።

ለዩክሬን የድጋፍ መልእክቶች ከላኩ ሀገራት ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ ላትቪያ፣ ሊትዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ሞልዶቫ፣ ሮማኒያ፣ ስዊድን እና ስሎቬንያ ተጠቃሽ ናቸዉ።

በዛሬዉ ዕለት የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት ከዋይት ሀውስ ስብሰባ በኋላ ከዘለንስኪ ጋር ሁለት ጊዜ መነጋገራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ።

በ- ሊያ ክብሮም

@Ethionews433 @Ethionews433


ግብ ጠባቂዎች ከ8 ሰከንድ በላይ ኳስ ማቆየት የማይችሉበት አዲስ ህግ ጸደቀ
****

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ (IFAB) ግብ ጠባቂዎችን በተመለከተ አዲስ ህግ አውጥቷል።

ግብ ጠባቂዎች ኳስን እጃቸው ላይ ከ8 ሰከንድ በላይ ካቆዩ ዳኞች ለተቃራኒ ቡድን ማዕዘን (ኮርና) መስጠት የሚችሉበትን ህግ ማጽደቁን ይፋ አድርጓል።

ህጉ ከቀጣይ የውድድር ዓመት ጀምሮ የሚተገበር እንደሆነም ነው የተገለጸው።

አሁን በትግበራ ላይ ያለው ህግ ግብ ጠባቂዎች ኳስን ከ6 ሰከንድ በላይ የሚያቆዩ ከሆነ ማስጠንቀቂያ ካርድ የሚሰጥበትና እንደ ሁኔታው ቀጥተኛ ያልሆነ ቅጣት ምት (indirect free kick ) የሚሰጥበት ነው።

በአንተነህ ሲሳይ

@Ethionews433 @Ethionews433


ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝደንት jd ቫንስ ፡ የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ወደ ዋይት ሀውስ ሲጋብዙት ይህን ያህል ይገዳደረናል ብለው አላሰቡም ነበር ።

እና የዩክሬንን ሀብት ለመዝረፍ የሚያስችላቸው ሰነድ ላይ ለመፈረም እንዳልፈቀደ ሲያውቁ ፡ ሰውየው ምንም ይሁን ምን የዩክሬን ፕሬዝደንት ሆኖ እስከመጣ በክብር እንደማናገር እሱንም ሀገሩንም ፡ መሳደብ እና በዛ መልኩ ማናገር ሲጀምሩ. . በርቀት ሆና ማስታወሻ ትይዝ የነበረች አንድ ሴት በተፈጠረው ነገር አዝና አንገቷን ደፋች ።
......
የሀገሯ እንዲህ በአደባባይ መዋረድ ስሜቷን ነክቶት ጉንጮቿ ቀልተው እንባ ተናነቃት ፡
ይህች ሴት Oksana Markarova ትባላለች በአሜሪካ የዩክሬን አምባሳደር ናት ።
ሀገር ስትዋረድ ፡ ሀገር ስትጠፋ ፕሬዝደንቷ በዚህ መልኩ ክብር ሲያጣ ምን ታርግ ?(ዋሲሁን ተስፋዬ)

@Ethionews433 @Ethionews433


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ባለመግባባት የተጠናቀቀው የፕሬዚደንት ትራምፕና የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ዘለንስኪ የዋይት ሀውስ ቆይታ።

@Ethionews433 @Ethionews433


ሲጠበቅ የነበረው የትራምፕ እና ዘለንስኪ ውይይት ባለመግባባት ተጠናቀቀ
***

በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮልዲሚር ዘለንስኪ መካከል የተካሄደው የዋይት ሀውሱ ስብሰባ ባለመግባባት ተጠናቋል፡፡

መሪዎቹ በአሜሪካ-ዩክሬን የማዕድን ስምምነት ነጥቦች እና በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መቋጫ የመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ሳይግባቡ ቀርተዋል፡፡

ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት አሜሪካ ያቀረበቻቸውን የማዕድን ስምምነት እና ጦርነቱን የማስቆሚያ ምክረ ሐሳቦች የማይቀበሉ ከሆነ ዩክሬንን ከተመለከቱ ጉዳዮች “ራሳችንን እናገላለን” ብለዋል፡፡

ይህን ሐሳብ በጽኑ የተቃወሙት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ፤ “ስምምነቱ የአሜሪካን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ የዩክሬንን የወደፊት ደህንነት ሊያረጋግጥ ይገባል” ብለዋል፡፡

በመሪዎቹ መካከል የተደረገው በኃይለ ቃላት የታጀበው ስብሰባ በሀገራቱ መካከል ያለውን የደህንነት እና ምጣኔ ሐብት ግንኙነት እንዳያሻክረው ስጋት መፍጠሩን ቢቢሲ እና ዘጋርዲያን ዘግበዋል፡፡

ሴራን ታደሰ

@Ethionews433 @Ethionews433


የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሩሲያ ጥቃት ላይ ዋስትናዎችን ይፈልጋሉ ተባለ፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን ይመክራሉ፡፡ ይህም ለሀገራቸው ወሳኝ ጊዜ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

የፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የልዑካን ቡድን ወደ ዋሽንግተን የሚያደርገው ጉዞ በጦርነት የተጎዳችውን ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ከመሆኑ ባለፈ ታሪካዊ የኢኮኖሚ ስምምነት ከአሜሪካ ጋር ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሶስት አመታት ያስቆጠረውን ጦርነት ለማስቆም እንደ አንድ እርምጃ የሚታየው ስምምነቱ የዩክሬንን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ ቢሆንም በሁለቱ መሪዎች መካከል ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በር ይከፍታል ነው የተባለው፡፡

በርካታ ዩክሬናውያን በችኮላ የሚደረገው የሰላም ስምምነት ለሩሲያ ፍላጎቶች ቅድሚያ የሚሰጥ እንዳይሆን ስጋታቸውን በመግለፅ ስምምነቱ ሞስኮ ኃይሏን ለወደፊት ወረራ እንድታጠናክር ያስችላታል የሚል ፍርሃት እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

ትራምፕ አዲሱን ስምምነት ኬቭ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስር ላሳለፈችው የጦርነት ጊዜ አሜሪካን የምትክስበት እድል አድርገው እንደሚቆጥሩት የተገለፀ ሲሆን ዘለንስኪ ለዩክሬን ደህንነት የሚደረጉ ልዩ ማረጋገጫዎች የዩክሬንን ሀብቶች የሚጠብቁ መሆን አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም እንዳላቸው አይሪሽ ኤግዛማይነር ዘግቧል፡፡

በ-ሊያ ክብሮም


🚨🌙 በሳውዲ አረቢያ ጨረቃ መታየቷን ተከተሎ የታላቁ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል።

ለመላው ሙስሊሞች ከወዲሁ መልካም ፆም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን 🙏

ረመዳን ሙባረክ 🌙

#RAMADAN1446

@Ethionews433 @Ethionews433

Показано 20 последних публикаций.