የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በድጋሚ ታገደ
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተጣለበት እገዳ ባለፈው ሳምንት ተነስቶለት የነበረው የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በድጋሚ ታገደ።
ሀገር በቀሉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የታገደው፤ በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት “አሰራሩን ባለማስተካከሉ” እና “ከዚህ ቀደም የፈጸማቸውን ጥፋቶች በመቀጠሉ ነው” ሲል ባለስልጣኑ ወንጅሏል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ እነዚህን እና ሌሎችን ውንጀላዎችን ለድርጅቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ መግለጹን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ የተጻፈው በትላንትናው ዕለት ቢሆንም፤ ለካርድ አመራሮች የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።
ደብዳቤው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በካርድ ላይ ባደረገው “የክትትል እና “የግምገማ ስራዎች”፤ ድርጅቱ ፈጽሟቸዋል ያላቸውን “የህግ ጥሰቶች” በመዘርዝር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር አስታውሷል። በዚህ መሰረት ድርጅቱ “በተቋቋመበት ዓላማ መሰረት”፤ “ህጋዊ ሂደትን ጠብቆ እንዲሰራ” “በጥብቅ ማሳሰቡንም” ጠቅሷል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2024/14634/
@EthiopiaInsiderNews