ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ
ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር ኤጄንሲ አሳስቧል።
አስተዳደሩ የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፤ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ መሆናቸውን ገልጿል።
በቅርቡም በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ አድራሻዎች የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በይበልጥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አካውንቶችን በመንጠቅ ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ማረጋገጡን አስታውቋል።
እነዚህም ከተለያዩ አካላት በቴሌግራም የሚደርሱ ሊንኮች በርካታ አደጋዎችን የሚይዙ ሲሆን፤ የሚከተሉት አደጋዎች በዋናነት ይገኙበታል።
👉 የግል መረጃ መጠለፍ፦ እንደ የባንክ መለያ ወይም የይለፍ ቃል ያሉ መረጃዎችን መሰረቅ፤
👉የማልዌር ስርጭት፦ ስልኮችን ወይም ኮምፒውተሮችን የሚጎዱ ቫይረሶች፤
👉ማጭበርበሪያ፦ ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ ተስፋዎች (እንደ ውርርድ ወይም ኢንቨስትመንት) መታለል እንደሚገኙበት ገልጿል።
በመሆኑም ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ ያሳሰበው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፤ ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና ማኅበረሰቡ በፍጹም ሊከፍታቸው ከማይገቡ ሊንኮች መካከል ጥቂቶቹን ይፋ አድርጓል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማኅበረሰቡ በቴሌግራሙ ላይ አጠራጣሪ የሆኑ ሊንኮች ሲያጋጥሙት፤ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር e-mail: ethiocert@insa.gov.et
ወይም ነጻ የስልክ መስመር፡ 933 ማሳወቅ የሚችል መሆኑን አስታውቋል።
ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና በፍጹም ልንከፍታቸዉ ከማይገቡ ሊንኮች መካከል ጥቂቶቹ ከላይ በምስሉ ተያይዘዋል።
@Ethiopian_Digital_Library@Ethiopian_Digital_Library