ዩኒቨርሲቲዎች ትክክለኛ የእውቀት መፈለጊያ ሰላማዊ ቦታዎች ሊሆኑ ይገባል፡- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ዩኒቨርሲቲዎች እውነተኛ የመማሪያ፣ የማስተማሪያ እንዲሁም ጥናትና ምርምሮች የሚሰሩባቸው ትክክለኛ የእውቀት መፈለጊያ ሰላማዊ ቦታዎች ሊሆኑ ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በወለጋ ዩኒቨርስቲ ከዩኒቨርስቲው አመራሮችና ማኅበረሰብ ጋር ተወያይተዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ትክክለኛ የእውቀት መፈለጊያ ሰላማዊ ቦታዎች ሊሆኑ እንደሚገባ የገለጹትሚኒስትሩ፤ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ዓላማ ይህን ለማሳካት እንደሆነም ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢያቸውን ፀጋ በመለየት ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ የህብረተሰቡን ህይወት መቀየር እና ለሀገራቸው ችግር መፍትሔ መፈለግ ይገባቸዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤በዚህ ረገድ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በዩኒቨርሲቲው በተደረገ ሱፐርቪዥን በጥንካሬ እና መሻሻል አለባቸው ተብለው በተለዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጎባቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የአመራር ለውጥ ከተደረገለት በኋላ የትምህርት ጥራት ፕሮግራሞች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አክለውም ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ በሚገባው መጠንና ጥራት ለማሳደግ አስተሳሰባችንና አሰራራችንን በማሻሻል ያለንን አቅም አሟጠን መጠቀም ይጠበቅብናል ብለዋል።
አመራሮቹ በነቀምቴ ከተማ በነበራቸው ቆይታ የዩኒቨርሲቲውን ኮምፕሬንሲቭ ሆስፒታል ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
⭐ For ExitExam Questions 👇
@Exit_Exam_Questions@Exit_Exam_Questions