ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፪
ለካ ትዝ ሲለኝ የፀነስኩት በቅድስት አርሴማ ፀሎት ነው ቶሎ ብዬ ከባሌ ጋር ወደ ለቡ አርሴማ አቀናን እያለቀስኩኝ ወደ ደጇ ገባሁኝ ምነው እናቴ አመስግኜ ሳልጨርስ ብዬ ትንሽ አፈር አፈስ አድርጌ ሆዴን ቀባባሁኝ ወዲያውኑ ሆዴን ይቆርጠኝ ጀመረ በሆዴ ውስጥ ያለው ፅንስ ተገላበጠ በጣም ደነገጥኩኝ ባለቤቴን ልጃችን ተንቀሳቀሰ አልኩት ወዲያው እጆቹን ወደ ሆዴ አደረገ እውነትም ፅንሱ ዘለለ ደስ ተሰኘ በእንባ ቤተመቅደሱን ዞርነው ገና ሆስፒታል እንደደረስን ምጥ ጀመረኝ ማርያም ማርያም እያልኩኝ የአርሴማን ስዕለ አድህኖ ሆዴ ውስጥ አድርጌ በሰላም ወንድ ልጅ ወለድኩኝ ተመስገን ባሌን ልጅ ላሳቅፈው ነው ከማዋለጃ ክፍል ወጥቼ ወደተሰጠኝ ክፍል ስገባ በጣም ደነገጥኩኝ ውዱ ባለቤቴ እግዚአብሔር የሰጠኝ የኔ አዳም በምን ፍጥነት እንደሆነ ባላውቅም ክፍሉን በፅጌረዳ አበባ ሞልቶታል በጂፓስ አይኔን በአይኔ አየሁት … የሚለውን መዝሙር ከፍቶ ከመሀል ደግሞ ትልቅ የቅድስት አርሴማን ስዕል አስቀምጧል እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም አርሴምዬ ምን ይሳንሻል ግን የኔ አዛኝ እያልኩኝ ወደ ጠዋት ላይ ወደቤታችን ሄድን ስንደርስ የኔ አብሮአደጎቼ ልብሰ ስብሐታቸውን ለብሰው በከበሮ እና በመሰንቆ ታጆበው በእልልታና በዝማሬ ተቀበሉኝ ገና ስገባ እናቴና የባለቤቴ እናት ዝቅ ብለው ስለእኛ እግዚአብሔርን አመሰገኑ በነገራችን ላይ እኔም እሱም እህትና ወንድም የለንም ታዲያ ልጅ በሌለበት ቤት ወንድ ልጅ ሲወለድ እንዴት ደስ አይሰኙ አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሃለው እልል እልል… ብቻ ምስጋና እና ዝማሬው የቃና ዘገሊላን ሰርግ ቤት ይመስላል ቀናት በቀናት ላይ እየተደራረቡ ልጃችንን ክርስትና ልናስነሳ ሽርጉድ እያልን ነው ሁሉን ነገር አሰናድተናል ……


ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ

381 0 15 2 30

ለሰው ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ነው።

             ሔኖክ. ፮፥፩

❤ ምሕረቱ ፥ ርኅራኄው ፥ ይቅርታው ባህሪው የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለኛም ምሕረት ይቅርታን ያድለን ዘንድ ከጌታህ አማልደን🙏🙏🙏❤

         ቅዱስ ሚካኤል
        ❤❤❤❤❤


አርሴማን ጥሩልኝ 🥺
ክፍል ፪







ነገ ከምሽቱ 2:00 ይጠብቁን


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🥰 እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል 🙏

🥰በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🥰🥰🥰🥰🥰

1.5k 0 17 15 79

አርሴማን ጥሩልኝ 🥺
ክፍል ፩
ልክ የዛሬ 15 አመት ነበረ ይህ ነገር የሆነው ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን ለምን ልጅ አልሰጠኸኝም ብለው ሲያማርሩ ብሎም ሆስፒታል ሄደው ሲፈላሰፉ አስተውላለሁ እኔና ባለቤቴ ግን አንድም ቀን እንኳን አማረን አናውቅም ልክ መስከረም 28 ቀን በተኛንበት እኔም ባሌም ተመሳሳይ ህልም አየን በጣም የምታምር እንደ ፀሃይ የምታበራዋ ባለዘንባባዋ እናቴ የሚያምር ወንድ ልጅ ይዛ ወደ ቤታችን ስትገባ ባሌ ያየውን ነገረኝ እኔም ስነግረው አላመነም ነበረ ወዲያው ተነሳንና ተጣጥበን የቅድስት አርሴማ እረፍቷን ልናከብር ወደ ለቡ አርሴማ አመራንና እኔም በሆዴ ለአርሴማ ልጅ ከወለድኩኝ ታቦትሽ የሚከብርበትን ጥላ አመጣለሁ ብዬ ባሌም ተስሎ ወደ ቤታችን ቄጤማና የአርሴማን ስዕለ አድህኖ ገዝተን ተመለስን ምግብ እየበላን አስር ጊዜ ሊያስታውከኝ ሲሞክር ምንም ስለማናውቅ ታምሜ መስሎን ወደ ሆስፒታል ጉዞ ጀመርን ወዲያው እንደደረስን ምርመራ ተደርጎልኝ የ2 ወር ነፍሰጡር ነሽ ተባልኩኝ ባሌ ተንሰቀሰቀ እና ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም በደስታ ዘለልን ወዲያውን ለቡ አርሴማ ሄድን የሚገርመው ባሌም ተስሎ የነበረው ጥላ ነበር ከዛ ገዝተን የማታ ጉባኤ ላይ ምስክርነት ሰጠን ዛሬ የ9 ወር ነፍሰጡር ነኝ በቅርቡ የልጅ እናት ልሆን ነው ከኔ በላይ የባሌ ደስታ አስደስቶኛል ከዛ ቀጠሮ ስላለን ወደ ሆስፒታል አመራን ምርመራ ተደረገልኝ ወጤቱ አስደንጋጭ ነበረ ልጁ በህይወት እንደሌለና ኦፕራስዮን ተደርጌ ልጁ መውጣት እንዳለበት ተነገረኝ ባሌ ደስ ብሎት ሳይጨርስ ብዬ አለቀስኩ እሱ ግን የእኔ ደህንነት ነበር ያሳሰበው ቅድስት አርሴማ አለች አይዞሽ ምንም አትሆኝም ደግሞ ሌላ ልጅ ትሰጠናለች አለኝ መንታ እንባዎች በአይኑ እየፈሰሰ ወዲያው ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ

ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ

2.9k 1 51 22 136

ተመረቀ
እልልል😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

2.8k 0 3 24 168

#ኅዳር_7

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት

ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)


"ቁስቋም ማርያም" በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ።

"የህፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ተነስ እናቱንና ህፃኑን ይዘህ ወደ እስራኤል ተመለስ።"ማቴ_2÷19

ልመናዋ ክብሯ የልጇቸርነት በሁላችን በህዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን 👏

3.4k 0 32 17 111

አርሴማን ጥሩልኝ 🥺



በቅርብ
ቀን
ይጠብቁን








✍ ብርሃኑ ባውቄ

3.3k 0 11 19 125

እንደ እባብ ጠቢብ ኹን

እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲል ምን ማለት ነው? እባብ ጭንቅላቱን (ራሱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳት ቢደርስበት ይመርጣል፡፡

ስለዚህ እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲልህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን፣ ዝናህን፣ ጓደኞችህን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ማጣት ካለብህ እንኳን በዚህ ማዘን መቆርቆር የለበህም ሲል ነው፡፡ ሃይማኖትህ ራስህ ነውና - እውነትን የምታውቅበት! እውነት ደግሞ አርነት ያወጣሃል፡፡

ኾኖም እንደ እባብ ጠቢብ መኾን ብቻውን ለእኛ በቂያችን አይደለም፤ እንደ ርግብ ሐቀኞችና የዋሆች መኾንም ያስፈልገናል፡፡ በጎ ምግባር የሚኖረው ጥበብንም የዋህነትንም አስተባብሮ መያዝ ሲቻል ነውና፡፡ ለምን ቢሉ እንደ እባብ ጠቢብ የኾነ ሰው ስለ ሃይማኖቱ ሲል ብዙ መከራዎችን ሊቀበል ይችላል፡፡

መከራ በሚያደርሱበት ላይ ክፉን በክፉ አለመመለስ የሚችለው ግን እንደ ርግብ የዋህ መኾን ሲችል ነው፤ እንደ ርግብ የዋህ መኾን ማለት መከራ በሚያደርሱብን ላይ በበቀል አለመነሣሣት መቻል ማለት ነውና፡፡ የዋህነት በጥበብ ሚዛን ካልተመጣጠነ አንድ ሰው መከራ ሲቀበል መከራ በሚያደርስበት ላይ በበቀል እንዲነሣ ያደርጓልና፡፡ ጥበብ በየዋህነት ሚዛን ካልተመጣጠነም እንደዚሁ አላስፈላጊ ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ ያደርጋልና፡፡

ስለዚህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል እንደ እባብ ጠቢብ ኹን፡፡ አብረህም መከራ በሚያደርስብህ ላይ ላለመበቀል ስትል እንደ ርግብ የዋህ ኹን፡፡ ኹለቱንም አዋሕደህ አስተባብረህ ያዝ!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ነፍሴን። አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ። ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም። ተነሥ፥ አቤቱ፤ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 3 ቁ1-8

🥀
እንዴት ዋላችሁ 🤲☦🧎‍♀

3.9k 0 35 18 147

ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

🌺(የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም)🌺




እግዚአብሔር ይመስገን እሷን ብሎ ማርያም የተሰኘው ልቦለድ ተፈፀመ ቀጣይ ለማቀርብላችሁ ፅሁፍ ያግዘኝ ዘንድ ሀሳብ አስተያየታችሁን እንዲሁም ከፅሁፉ ያተረፋችሁን ፃፉልኝ
❤️
❤️
❤️
❤️
እኔ ደካማ ወንድማችሁን ድክመቴን ሳትንቁ ስለምትሰጡኝ ሃሳብና አስተያየት እግዚአብሔር ያክብርልኝ

3.5k 0 2 21 128

እሷን ብሎ ማርያም🥺
ክፍል ፱
ሲገቡ ትምህርት አልቆ ነበረ እና ወደ አትሮኖሱ ተጠጋች እኔ ዛሬ የእናቴን ተአምር ልናገር ነው ከፊታችሁ የቆምኩት ጥቅምት 27 መድሃኔአለምን አንግሰን ወደ ቤት ልንመለስ ስንል አደንዝዘው በሌላ መኪና ጭነውን የእኔን መኪና ደግሞ ግብረ አበሮቻቸው ወሰዷት ታፍነን ሳለ በጣም ተጨንቄ ነበረ ምክኒያቱም እናቴ ግፊት አለባት ይዘውን ወደማናውቀው ቦታ ወስደው አስቀመጡን መኪናው እንደተጋጨ ሲሰሙ በእናንተ ምክኒያት ነው ብለው ስቃይና መከራ አፀኑብን በጣም ተጎሳቁለን እያለ እመቤቴ አይዟችሁ እኔ እናታችሁ አለሁላችሁ ትለን ነበር በስሙ የዘከራችሁለት ልጄ በፍፁም አይተዋችሁም ትለኛለች ከዚያ ቤቱ ህገወጥ ስራ ይሰራበት ስለነበር ቤቱ ሲፈተሽ እኛ ተገኘን ከዚያ ስም እየጠየቀን እያለ እኔ ብሎ የሱን ስም ሲናገር እማ የልጄ ስም ነው አለች በጣም ደነገጠና የእህት ወንድሞቹን ስም ሲነግራት እማ ተንሰቀሰቀች የጠፉትን ልጆቿን አገኘች ከዚያ ይኸው ዛሬ ልንመሰክር በቃን አለች እልልታው ደመቀ አባትም መጣ እራሱን ሊያጠፋ እንደነበረና ድንግል ማርያም በእለተ ቀኗ እንደደረሰችለት መሰከረ እኔ ማርያምዬን የለመንኳት ሞት ነበረ እሷ ግን ህይወት የሆኑኝን ቤተሰቦቼን ሰጠችኝ ይባስ ብላ ደግሞ ተስፋ የቆረጥኩባቸውን እህትና ወንድሞቼን ሰጠችኝ ስሰድባት ሳንቋሽሻት አንድ ቀን እንኳን አኩርፋኝ አታውቅም
እሷን ብሎ ማርያም እኔ እላለሁኝ
ከማር በላይ ሆና እያስገረመችኝ
እሷን ብሎ ማርያም ዘወትር የምለው
ከማርያም የሚበልጥ ስም ስለሚገባት ነው
አለ ልቡ ተደስቶ
እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ቆርበው በሰላም እየኖሩ ነው


ተፈፀመ!!!
አስጀምሮ ላስጨረሰን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው
ድንግል ማርያም አለው በደስታችሁ አለው በሃዘናችሁ ትበላችሁ

✍ብርሃኑ
ባውቄ

4.1k 0 77 27 152

እሷን ብሎ ማርያም🥺


ክፍል፱




የመጨረሻ ክፍል






ዛሬ ማታ 3:00 ላይ ይጠብቁን


#ማሕሌተ_ጽጌ
ሕዳር ፩

ናሁ ተፈፀመ ፅጌ ማህሌት

🌺🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌼

ቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል

Показано 20 последних публикаций.