Ethiopian Students


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


This channel is created for Ethiopian students' who want to share ideas and resources together.

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


📢 ማስታወቂያ ፡-

ሰላም @Ethiopian_Students ቻናል አባላት

በያላችሁበት ሰላም ይድረሳችሁ።

እዚህ ቻናል ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ፖስት ባለማድረጋችን ይቅርታ እየጠይቅን በቀጣይ ከእናንተ ጋር በመሆን አስፈላጊ እና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማካፈል እንዲሁም ቻናሉ ለትምህርታችሁ አጋዥ እንዲሆን ለማድረግ አስበናል::

በመሆኑም በእናንተ በኩል ገንቢ አስተያየት ወይም ሂስ ካለ መልዕክቶን ቢያደርሱን, ለመቀበል እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናችን በአክብሮት እንገልፃለን

እናመሰግናለን!


📢 Important Update:

Getting Back on Track!

Hello Members of the @Ethiopian_Students community,

We hope you're doing well.
We apologize for our recent inactivity. Life sometimes brings unexpected events that can cause delays, and we want to express our regret for any inconvenience this may have caused.

But guess what?
We're back and excited to resume sharing valuable content with you! Your dedication to learning continues to inspire us, and we are truly grateful for your unwavering support.

Moving forward, we are committed to providing you with a steady stream of engaging and beneficial information. Our channel thrives on community engagement, and we are determined to enhance it even further.

In the upcoming days and weeks, we will be bringing you exciting updates, valuable resources, and more opportunities to connect. We are also eager to hear your suggestions—please let us know what topics you would like us to cover!

We sincerely appreciate your patience and your enthusiasm for learning. Let's embark on this new chapter together, united in our pursuit of knowledge and growth.

Best wishes😊,

The Channel Administrators


የ 12ኛ ክፍል ፈተና ያለፋችሁ

የዩንቨርስቲ ምደባ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ

https://result.ethernet.edu.et


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል(የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና) አይሰጥም!

10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከዚህ ዓመት (2012 ዓ/ም) ጀምሮ አይሰጥም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ እንደቻለው የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወዲሁ ቅድም ዝግጅት ጀምሯል። በአዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት ቀደም ብሎ በ10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በ12ኛ ክፍል እንዲሰጥ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሳምንታት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde




Репост из: YeneTube
የ2012 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት #የተረጋገጠ
ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያመሩ ተማሪዎች
I. የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ዋናውን እና ሁለት ኮፒዎች፣
• የ8ኛ ክፍል (ሚኒስትሪ) ሰርተፊኬት
• የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬቶች
• ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
II. 8 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ (የቅርብ ጊዜ)
III. አንሶላ እና ብርድ ልብስ
IV. የስፖርት አልባሳት (ጫማን ጨምሮ)
** ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የሚኖራቸውን ቆይታ ሰላማዊ ለማድረግ የተማሪ ወላጆች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የዋስትና ውል እንዲገቡ መደረጉ ይታወቃል።

ስለዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚሄዱበት ወቅት ወላጆቻቸው የተፈራረሙበትን ሰነድ ይዘው እንዲገኙ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ሰነዶቹን ከየሚኖሩበት ወረዳ መውሰድ ይችላሉ።

ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ሲጠሩ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ሲሆን ከታች የተዘረዘሩት ቀናት ላይ የጊዜ ለውጥ ካለም ለውጡን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa


Репост из: YeneTube
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ #ጥቅምት_01 ቀን እና #ጥቅምት_02 ቀን 2012 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣
➡️ ብርድልብስና አንሶላ፣
➡️ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
➡️ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➡️ የስፖርት ትጥቅ

📌 በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
📌 ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
📌 ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://
portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
📌 ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር ውል ተፈራርመው የማረጋገጫ ወረቀት ካላመጡ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል፡፡
📌 በተጨማሪም ባለፈው ስርዓተ ትምህርት መሠረት በመጀመሪያ ዓመት 1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡እንዲሁም መደበኛ የድህረ ምረቃ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 06 2012 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Via አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa


Репост из: TIKVAH-MAGAZINE
የዩኒቨርስቲ መግቢያ ለአዲስ ተማሪዎች እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ ቀናቸውን ያስተካከሉ ሲሆን ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በአንጻሩ ምንም ማስተካከያ ሳይደረግባቸው በዛው የጸኑ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የመግቢያ ቀናቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ያራዘሙና የመግቢያ ቀን ያልጠቀሱ ዩኒቨርስቲዎችን አላካተትንም፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናችሁን ለማረጋገጥ የዩነቨርስቲዎችን ዌብሳይትና ትክክለኛ የፌስቡክ ገጻቸውን ተከታተሉ፡፡ እኛም የደረሱንን መረጃዎች እንደምንጊዜውም በፍጥነት የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

#ማሳሰቢያ| ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ @tikvahethmagazine ውጪ የተማሪዎች መረጃ የሚለቅበት ቻናል የለውም፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethmagazine @emush21


Репост из: TIKVAH-MAGAZINE
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአለባበስ ሕግ ይፋ ሊደረግ ነው!

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የአለባበስ ስነምግባር ደንብን ለመወሰን በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚኒስቴር የተጠናው ጥናት ተጠናቆ ከጥር 2012 ጀምሮ ይፋ ሊደረግ ነው።

ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መደበኛ ተብሎ በጥናት የሚረጋገጠውን አለባበስ፣ ሀይማኖታዊ አለባበስ እና ባህላዊ አለባበሶችን ይደነግጋል የተባለው ይህ መመሪያ እስከዛሬ በየዩኒቨርሲቲው ተበታትኖ የሚገኘውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ይተካል ሲልም ሚኒስቴሩ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

‹‹በርካታ ተማሪዎች ሥነ ምግባር የጎደለው አለባበስ በመጠቀም መማር ማስተማሩን ሲያውኩ ነበር›› በማት ለአዲስ ማለዳ የገለፁት የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር #ደቻሳ_ግሩም ‹‹በተለይም ፀጉራቸውን አንጨባረው የሚመጡ በርካታ ወንድ ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲው ማየት የተለመደ ነው›› ሲሉም ገልፀዋል።

በአዲሱ መመሪያ መሰረትም የፓርቲ አርማ ያለበት ልብስ እና ለግጭት የሚዳርጉ የተለያዩ አለባበሶችን ለብሰው የሚመጡ ተማሪዎችን የሚገድብ እና ችግሩንም የሚፈታ እንደሆነ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07


Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia




In case if you need any information


Here are list of Universities in ethiopia and their official website

No Name Acronym Website
1 AA SCI. & TECH UNIVERSITY AASTU http://www.aastu.edu.et/
2 Adama science & technology University ASTU http://www.astu.edu.et/
3 Addis Ababa University AAU http://www.aau.edu.et/
4 Adigrat University AGU http://www.adu.edu.et/
5 Ambo University AU http://www.ambou.academia.edu/
6 Arba Minch University AMU http://www.amu.edu.et/
7 Arsi University ARU https://www.arsiun.edu.et/
8 ASOSSA UNIVERSITY ASU http://www.asu.edu.et/
9 Axum University AXU http://www.aku.edu.et/
10 Bahir Dar University BDU http://www.bdu.edu.et/
11 BONGA UNIVERSITY BU http://www.bongau.edu.et/
12 BULE HORRA UNIVERSITY BHU http://www.bhu.edu.et/
13 DEBARK UNIVERSITY DKU http://www.dku.edu.et
14 Debrebirhan University DBU http://www.dbu.edu.et/
15 Debremarkos University DMU http://www.dmu.edu.et/
16 DEBRETABOR UNIVERSITY DBTU http://www.dtu.edu.et/
17 DEMBI DOLO UNIVERSITY DeDU http://www.dedu.edu.et
18 Dilla University DU http://www.du.edu.et/
19 Dire Dawa University DDU http://www.ddu.edu.et/
20 Gambella University GMU http://www.gmu.edu.et
21 Gondar University GU http://www.uog.edu.et/en/
22 Haramaya University HRU http://www.haramaya.edu.et/
23 Hawassa University HWU http://www.hu.edu.et/hu/
24 INJIBARA UNIVERSITY IU http://www.inu.edu.et/
25 Jigjiga University JGU https://www.jju.edu.et/
26 Jimma University JU https://www.ju.edu.et/
27 JINKA UNIVERSITY JNU http://www.jnu.et/
28 Kebri Dehar University KDU http://www.kdu.edu.et/
29 Kotebe Metropolitan University KMU http://www.kmu.edu.et/
30 Meda Welabu University MWU http://www.mwu.edu.et/
31 Mekelle University MU http://www.mu.edu.et/
32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY MAU http://www.mau.education/
33 METU UNIVERSITY MEU http://www.meu.edu.et/
34 Mizan-Tepi University MTU http://www.mtu.edu.et/
35 Oda Bultum OBU http://www.odabultum.edu.et
36 RAYA UNIVERSITY RU http://www.rayu.org/
37 Selale University SLU http://www.seu.edu.et
38 Semera University SU https://www.su.edu.et/
39 WACHAMO UNIVERSITY WCU http://www.wachemouniversity.academia.edu/
40 Welketie UNIVERSITY WKU http://www.wku.edu.et
41 WERABE UNIVERSITY WRU http://www.edu.et/
42 Wolayita Sodo University WSU http://www.wsu.edu.et
43 Woldiya University WDU http://www.fh2web.academia.edu
44 Wollega University WU
www.wollegauniversity.edu.et
45 Wollo University WOU http://www.wollo.academia.edu


For more information

Join @Ethiopian_students


ሰላም #EthiopianStudents

በትላንትናው ዕለት ቦታችን ባለመስራቱ ይቅርታ እየጠየቅን : ከአሁን በኃላ ምደባችሁን ማየት ትችላላቹ::

@grade_12_placement_bot
@grade_12_placement_bot @grade_12_placement_bot @grade_12_placement_bot @grade_12_placement_bot @grade_12_placement_bot

Join @Ethiopian_Students for more.


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ስለተጠናቀቀ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ዛሬ ከ11: 30 ሰዓት ጀምሮ በአገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት www.neaea.gov.et በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

መልካም የትምህርት ዘመን!

via የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia


የፈተናዎች ኤጀንሲ 11:30 ላይ የምደባው ውጤት የሚለቀቅ መሆኑ ቢያሳውቅም እስከ አሁን ሰአት ግን ዌብሳይቱ እየሰራ አይደለም።

#እናም ውድ የዩንቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች

እንደተለቀቀ በነፃ ለሁላችሁም በቦታችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።


የ2012 የትምህርት ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ

******************

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪውን የሰው ሃይል ስብጥርን በጠበቀ መልኩ በሀገሪቱ ያለውን የገበያ ፍላጎት መሰረት በማድረግ በየዓመቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የቅበላ መስፈርት የሚያወጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህ ዓመት አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት ተጠናቆ ተግባራዊ እንዲሆን በርካታ የመሸጋገሪያ ተግባራት የሚከናወኑበት መሆኑን የገለፀው ኤጀንሲው ይህንን እና የገበያውን ፍላጎት አንዲሁም የሰው ኃይል አሰላለፍን ከግምጥ ውስጥ በማስገባት የ2012 የትምህርት ዘመን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የቅበላ መስፈርትን አውጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

በደረጃ 1 እና 2

10ኛ ክፍል ላጠናቀቁ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.57 እና ከዚያ በታች
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.43 እና ከዚያ በታች
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.43 እና ከዚያ በታች
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.29 እና ከዚያ በታች
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 1.14 እና ከዚያ በታች

በደረጃ 3 እና 4

የ10ኛ ክፍል ላጠናቀቁ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.71 እና ከዚያ በላይ
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.57 እና ከዚያ በላይ
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.57 እና ከዚያ በላይ
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.43 እና ከዚያ በላይ
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 1.29 እና ከዚያ በላይ

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 129 እና ከዚያ በታች
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 129 እና ከዚያ በታች
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 99 እና ከዚያ በታች

በደረጃ 5

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 130 እና ከዚያ በላይ
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 130 እና ከዚያ በላይ
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 125 እና ከዚያ በላይ
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 100 እና ከዚያ በላይ

በመቁረጫ ነጥቡ ላይ በደረጃ 5 ስር የተመለከተው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ ተብሎ ቢቀመጥም 10ኛ ክፍል ተፈትነው 11ኛ ክፍል የሚያስገባ ነጥብ ያላቸው በተጠቀሰው ደረጃ ላይ መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል፡፡


#source EBC
@Ethiopian_Students


Репост из: TIKVAH-MAGAZINE
#ምደባ!

ምደባን በተመለከተ ጋዜጠኛ ኤልያስ በዛሬው የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ አንስቶት የነበረ ሲሆን የሚመለከተውን አካል በስልክ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጾ ተማሪዎች ምደባው በይፋ እስኪለቀቅ በትዕግስት መጠበቅ እንደሚኖርባቸውና በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጽ በሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች ግራ እንዳይጋቡ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም አዳዲስ መረጃዎችን ለማድረስ ዝግጁ መሆኑን እየገለጸ ተማሪዎች መረጃ የምትከታተሉበት ገጽ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር ገጽ ወይም ትክክለኛው የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ገጽ መሆኑን አጣርታችሁ ተከታተሉ፡፡

https://www.facebook.com/SHE.Ethio/ (የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፌስቡክ ገጽ)

https://www.facebook.com/fdremoe/ ( የትምህርት ሚኒስተር ፌስቡክ ገጽ)

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethmagazine

@emush21 @yeambaye


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ተደረገ!

#ASTU #AASTU

የአዲስ አበበ እና አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲትዎች መግቢያ ነጥብ ዝቅ አለ!

የተማሪዎችን ፍላጎትና በተደጋጋሚ የሚነሳውን የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ይበልልን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ በማስታወቂያ የተገለጸው ለወንድ፡190 እና ለሴት፡185 ከነበረው ዝቅ ተደርጎ

ለወንድ፡ 176 እና
ለሴት፡166

የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን እያሳወቅን እስከ ነገ መስከረም 20/01/2012 ዓ.ም. ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዚህ መስክ መመደብ የምትፈልጉ የ2011ዓ.ም. የዪኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች፤ ለት/ቤታችሁ ፍላጎታችሁን በመግለጽ ምርጫችሁን ት/ቤታችሁ እንዲያስገባላችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

http://app.neaea.gov.et/

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ


@tsegabwolde @tikvahethiopia


Репост из: TIKVAH-MAGAZINE
#Fake_News

የዩኒቨርስቲ ምደባ ተራዘመ በሚል የቲክቫን ስም በመጥቀስ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ውሸት ነው፡፡ እስካሁን በምደባ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫም ሆነ ቲክቫህ ያቀረበው መረጃ የለም፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት ጥረት እያደረግን ሲሆን መረጃው እንደደረሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethmagazine

@emush21 @ambayetsegaye


‼ ለመላው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የፈተና ውጤት #ሰርተፊኬታችሁን ለተለያዩ ጉዳዮች ብትፈልጉም እስካሁን ድረስ የፈተናዎች ኤጀንሲ ለትምህርት ቤቶቻችሁ ያላደረሰ መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን ችግር በመገንዘብም ኤጀንሲው በዌብሳይቱ ጊዜያዊ ሶፍትኮፒ ሰርተፊኬት አዘጋጅቷል። ይህ ሰርተፊኬት ዋናው እስኪመጣ ድረስ ለሚያስፈልጓችሁ አጣዳፊ ጉዳዮች ብቻ የምትጠቀሙበት ሲሆን የኤጀንሲው ማህተም ያረፈበትን ትክክለኛ ሰርተፊኬት የሚተካ አይደለም።

ይህንን #PDF ፋይል እዚሁ ቦት ላይ #download የሚለውን ሊንክ በመጠቀም ማውረድ ትችላላቹ !


@grade_12_placement_bot
@grade_12_placement_bot
@grade_12_placement_bot
@grade_12_placement_bot
@grade_12_placement_bot


@Ethiopian_Students for more


Репост из: TIKVAH-MAGAZINE
4_5791778753164085205.pdf
1.2Мб
#AASTU

ነባር የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዶርም ድልድል ከላይ የምትመለከቱትን ይመስላል፡፡ ሳትጉላሉ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

via @PPogba6

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine

@emush21 @ambayetsegaye

Показано 20 последних публикаций.

14 065

подписчиков
Статистика канала