የሚንስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ 581.9 ቢልዮን ብር በጀት በማፅደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፏል::
ዛሬ በተደርገው የሚንስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከዚህ በፊት ከፀደቀው 1 ትሪልዮን ብር በተጨማሪ 581.9 ቢሊዮን ብር አፅድቋል።
የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል ብሏል ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በመግለጫው፡፡
ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የሂሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ብቁ እና ብዛት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፍራት በመንግስት እና በግል ተቋማት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ሥርዓት በመዘርጋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚኖረው ነው ተብሏል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
Source: stockmarketet
@Ethiopianbusinessdaily