💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


💚💛❤️ኢትዮጵያን እንታዘባለን ያየነውን የሰማነውን እንመሠክራለን እንታዘባለን💚💛❤️

#Join now
# share
💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


❗️ሰበር ደብረብርሃን‼

ከሻሸመኔ የተነሱ 4 ግለሰቦች በቤት መኪና ደብረብርሀን ከደረሱ በኋላ አለም ገነት ሆቴል እንዳረፉ እንቅስቃሲያቸው ጥሩ አልነበረም እና ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተያዙበት ወቅትም ለሽብር ተግባር የሚያገለግላቸውን፦

1) ብዛት ያላቸው በተለያየ ስም የተመዘጉ የመታወቂያ ካርዶች

2) ሁለት ከፍተኛ መጠን ያላቸው ተቀጣጣይ ፈንጅ

3) የ925 ሺህ ብር የቡና ባንክ ቼክ

4) 925 ሺህ ብር ንግድ ባንክ በዛሬው እለት ትራንስፈር የተደረገ ሲሆን ጉዳዩ በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ እየተመረመረ ነው።

#Join now
# share

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


‼️ከስንት ማዋከብ በኋላ ተመልሰናል‼️

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት የተሰጠ መግለጫ!

*

ይሄ የማን መግለጫ ነው ፋኖ ብሎ ለመጥራት የከበደው 🤫?


በሕግ ማስከበር ስም የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችንና ጠያቂዎችን የማጥፋትና ሕዝባችንን አንገት የማስደፋት እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን!

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሕዝብ ተወካይ አባላት የተሰጠ መግለጫ፤)
*
ባለፉት አራት ዓመታት በሕዝባችን ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርስበት ሁሉንአቀፍ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል ቅርጹንና አድማሱን እያሰፋ ተባብሶ ቀጥሏል። ይባስ ብሎም ትሕነግ፣ የቤንሻንጉል ነጻ አውጭና ኦነግ ሸኔ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ይፋዊ ጦርነት ከፍተው ሕዝባችን ኅልውናው አደጋ ላይ ወድቆ በጠላቶቹ ከበባ ሥር ይገኛል።

እኛ የአብን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም መንግስት ትንሹን መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣና የሕዝባችንን ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ስንወተውት ቆይተናል። ሆኖም መንግስት ለማሳሰቢያችን ጀሮ ባለመስጠቱና ስጋታችንን ባለመጋራቱ ሕዝባችን ማንነትን መሰረት ላደረገ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ስደት ከመዳረጉም በላይ ከተሞቹና በዘመናት ሂደት ያፈራው ንብረት ወድሞ ለአካላዊና ሥነልቦናዊ ችግር ተጋልጦ ይገኛል። በዚህም ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ መፈናቀል ከዓለም ቀዳሚ እስከመሆን ደርሳለች፡፡

ይባስ ብሎም የዜጎችን ኹለንተናዊ ደኅንነት ማስጠበቅ፣ ሕግና ሥርዓትን ማንበርና የተሳለጠ አመራር መስጠት ያልቻለው መንግሥት ሕዝባችን በትሕነግና ምስለኔዎቹ ኅልውናው አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ጊዜ በነቁ አማሮች ማለትም በአብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላትና አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ባገለገሉ የጦር መኮነኖች ላይ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የአፈና፣ የሕገ-ወጥ እስር እና የመንግስታዊ እገታ ሥራዎች ላይ መጠመዱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን የሕዝብ ተወካይ አባላትን አሳዝኖናል፡፡

መንግስት የሕዝባችንን ደኅንነት ለማረጋገጥና አገራዊ አንድነትን ለማንበር ከፖለቲካዊ ሴራ በጸዳ አኳኋን ሕግ ቢያስከብር እኛም ከመረጠን ሕዝብ ጋር ሆነን የምንደግፈው ቢሆንም አሁን እየተደረገ ያለው ግን ሕግ ማስከበር ሳይሆን በአማራ ሕዝብ የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችንና ጠያቂዎችን የማጥፋትና ሕዝባችንን አንገት የማስደፋት እንቅስቃሴ ነው። ይኼን ጉዳይ ለሕዝባችን ክብር ካለን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት የተነሳ በቸልታ የማንመለከተውና ከሕዝባችን ጋር ሆነን የምንታገለው ያደረ አማራ ጠል እሳቤ ነው። በመሆኑም እኛ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን የሕዝብ ተወካይ አባላት መንግስት በሕግ ማስከበር ስም እያደረገ ባለው መንግስታዊ እገታና አፈና አሳሳቢነት ላይ ከተወያዬን በኋላ፦

፩. በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮነኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡

፪. መንግስት በሕዝባችን ላይ እየፈፀመ ያለው ማዋከብ የታወቀ ጠላት የሚያደርገው ዓይነት ሲሆን ማዋከቡ በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ አገርና ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀው የአገራዊ ምክክር ከወዲሁ እንዲጨናገፍ የሚያደርግ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን።

፫. ሕግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌድራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም እና የክልሉ መንግስት በፌደራል መንግስቱ ለሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ ተባባሪ ከመሆን ወጥቶ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት እንዲያስከብር እየጠየቅን ጉዳዮቹን በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

፬. በሕግ ማስከበር ሰበብ ከተሞችን የጦር አውድማ የማድረግና ንጹሐንን መግደል መንግስታዊ ሽብር በመሆኑ መንግስት የሚያደርገውን ይሄን ሕገወጥ የሽብር ሥራ በአስቸኳይ አቁሞ ሕዝባችንን በማወያዬት የሕዝብ ፍላጎቶችና ድምጾች እንዲሰሙ እንጠይቃለን፡፡

፭. መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችም መሰል መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ ያወጀውን መንግስታዊ ሽብርና ጦርነት እንዲያቆም መንግስት ላይ ጫና እንድታሳድሩ ለአማራ ሕዝብ ያላቸሁን አጋርነትም በተግባር እንዲያሳዩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

፮. መላው የአማራ ሕዝብ በዚህ ፈታኝ ወቅት ውስጣዊ አንድነቱን እንዲያጠናክር እየጠየቅን በአማራ ስም የተደራጃችሁ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራንና መላው ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የኅልውና አደጋና ከበባ በመቀልበስ ልጆቹን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


💚💛❤️መዳኛየ💚💛❤️

#Join now
# share

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


❗️መንግስታዊ አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️

የአማራ ወጣቶች እና የመላው የአማራ ህዝብ ልሳን የሆኑት ጋዜጠኞች እና ሌሎች የሚዲያው አባላት በአፋኙ መንግስት በዛሬው ዕለት በስራ ላይ እያሉ ታፍነው ተወስደዋል ።
ከእነዚህ መካከል
አሻራ ሚዲያ የታሰሩት ጋዜጠኞችን ስም ዝርዝር ስንመለከት

1) ቀለሙ ገላጋይ አቅኔ የአሻራ ሚዲያ የካሜራ ባለሙያና
ኤዲተር
2) ጋሻየ ንጉሴ ፈረደ ጋዜጠኛ
3) ጌትነት ያለው ጋዜጠኛ
4) ሀብታሙ መለሰ ጋዜጠኛ
5) ዳንኤል መስፍን የካሜራ ባለሙያና ኤዲተር ሲሆኑ የንስር ብሮድካስት የጋዜጠኞች ስም ዝርዝር እንደደረሰን
የምናቀርብ ይሆናል።

# share

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


ፈንጂ 5 ሰዎችን ገደለ!

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ ከተማ ፈንጂ 5 ሰዎች መሞታቸውን የባቲ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሰኢድ ለዶይቼ ቬሌ ዛሬ እንደነገሩት በቅርቡ ከህወሓት ጋር በነበረ ጦርነት ቡድኑ ጥሎት የሄደን ፈንጂ ትናንት አግኝተው ሲነካኩ በመፈንዳቱ በአካባቢው የነበሩ ሠዎችን ጨምሮ 5 ሠዎች ህይወታቸው አልፏል።እንደ አቶ መሐመድ ሌሎች 5 ሠዎች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው በህክምና ላይ ናቸው።ጉዳቱ የደረሰባቸው ሠዎች ከህፃናት እስከ አዋቂ ያሉ እንደሆኑም ጨምረው ተናግረዋል።ሕብረተሰቡ ማነኛውንም ብረት ነገር ሲያገኝ ለፀጥታ አካላት ማሳየት እንጂ በራስ መነካካት ጉዳት ያመጣልም ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ዶይቸ ቬሌ ዘግቧል።


ከሳምንታት በፊት ነበር ኦነግ ሸኔ እንደለመደው ከተማ ለማቃጠልና ለመዝረፍ እንዲሁም ሴቶችና ህፃናትን ለመድፈር የአባይ ወንዝ ተሻግሮ በየጁቤ አድርጎ ምስራቅ ጎጃምን የጦር ቀጠና ለማድረግ ዕቅድ ይዞ ትንኮሳውን ጀመረ። ነገር ግን አካባቢው ላይ ባሉ ፋኖወች ቂጡን ተብሎ ፈርጥጦ ተመለሰ። በዚህም የተከፍትና የተናደዱት እነ አሮጊቶቹ ኦፌኮ፣ ኦነግና የኦሆዴድ ባለስልጣናት ፍኖ አሸባሪ ነው እያሉ መግለጫ በመግለጫ ቀወጡት።

የአራት ኪሎ መንገዴ በፋኖ እንዳይደናቀፍብኝ ብላ የምትሰጋው ወያኔና በኦነግሸኔ ሽንፈትና የእቅዳቸው መክሸፍ የተናደዱት ኦፌኮና ኦነግ እንዱሁም የኦህዴድ ባለስልጣናት በአንድነት ተባብረው ፍኖ ሌባ ነው አሸባሪ ነው በማለት ፌደራሉ መንግስት ትጥቅ እንዲፈታ አራት ኪሎ ላይ ሲማፀኑ ቆይተዋል።

ለዚህም ነው አብይ ከነግብረ አበሮቹ እነ ወያኔ ፣ኦነግ ሽኔ፣ ኦፌኮና የኦሆዴድ ባለስልጣናት እንዳየኮርፍት ትናንት ህዝብን ከሌባ ከዘራፊ ከተማ ከሚያወድም ሴትና ህፃናትን ከሚደፍር ክፍ አረመኔ አሸባሪ የታደገውን ፍኖን ሊያፍንና ትጥቅ ሊያስፈታ አፍኙን ቡድን የላከ። እውነታው ይሄ ነው። አለኝታህን መከታህን መዳኛህን ፍኖን የመጠበቅ ያንተ ግዴታ ምክንያቱ ደግሞ መጪው ጊዜ በጣም ከባድ ነውና።


#Join now
# share

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


"…የዐቢይ አሕመድ አሊ መንግሥት ከክረምቱ የወያኔ ወረራ በፊት ከዐማራ ህዝብ ጋር ጦርነት መግጠም ፈልጓል። የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ግን በየትኛውም የዓለም ታሪክ ህዝብን ገጥሞ ያሸነፈ መንግሥት ታይቶም፣ ተሰምቶም፣ ኖሮም ያለማወቁ ነው።

"…ከፊቱ ከፍተኛ የጦርነት ስጋት ያለበትን ህዝብ ከወዲሁ መሳሪያውን መግፈፍ፣ መሪዎቹን፣ አንቂዎቹን መሰወር፣ ማገት፣ መግደል ማለት ምን ማለት ይሆን?

"…ህዝብ አይሸነፍም። ተሸንፎም አያውቅም‼️

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


🩸ሰበር ዜና‼️

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብውሃ አካባቢ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ወደ ሸዋሮቢት በፓትሮል ሲጓዙ በነበሩ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ፈጸመ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብውሃ በሚገኙ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ከበባ በማድረግ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጥቃት ፈጽሟል።

ግንቦት 10/2014 በተፈጸመው ጥቃት አንድ የልዩ ኃይል አባል በመቁሰሉ ቁስለኛውን ይዘው በፓትሮ ወደ ሸዋሮቢት ሲጓዙ ተጨማሪ የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

በጥቃቱም የሶስት የልዩ ኃይል አባላት ህይወት አልፏል፤ መኪናውም በመገልበጡ የቆሰሉ ስለመኖራቸው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከስፍራው የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

ስርዓተ ቀብራቸውም ግንቦት 11/2014 በሸዋሮቢት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙ ተገልጧል።

(አሚማ)

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


መንግስት አደብ መግዛትና የሰራውን ትልቅ ስተት በቶሎ ማረም ካልቻለ በኋላ የማይወጣው መቀመቅ ውስጥ ይቸነከራታል።

ህዝብን እንደ አሸባሪ መፈረጅ ያከስራል እንጂ አያዋጣም። ጥላትን ለማስደሰት ሲባል ህዝብን መካድ ከነውርም በላይ ነውር ነው። እናተ እንደምትሉት ፍኖ ዘራፊ አሸባሪ ቢሆን ኖሮ ህዝቡ እንደዚህ ግልብጥ ብሎ ፍኖን አትንኩብኝ ባላለ ነበር። ፍኖ የሰራውን ገድል እንኳን ፌደራል መንግስቱ ወያኔም እንዴት እንደሚያንቀጠቅጣት ታውቀዋለች ነገር ግን መንግስት ላኮረፋት ቡድን መሸንገያ ይሆነኛል በማለት ባለውለታውን ክዶ ማሳደድ ተያይዞታል።

ህዝብ ደግሞ ጋሻ መከታየን መዳኛየን ፋኖን አሳልፌ አልሰጥም በማለት የአደባባይ ትግል ጀምሯል። መካነ ሰላም፣ ሞጣ፣ አሁን ደግሞ ከላይ እንደሚታየው ግንደወይን ህዝባዊ እምቢተኘነቱ ቀጥሏል።

🩸ማፈንና ደብዛን ማጥፋት ለደርግም ሆነ ለወያኔ አልበጀም ከህዝብ ጋር ጦርነት የትም አያደርስም‼️

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


ደራሲና ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ ግንቦት 10/2014 ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ደብዛቸው እንደጠፋባቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀጋ ሞገስ ተናግረዋል። እስከ ምሽት 2:00 የእጅ ስልካቸው ጥሪ ያስተናግድ ነበር ከዚያ በኋላ ግን ተዘግቷል ። በተለያዩ እስር ቤቶች ፋለጋ ላይ ቢሆኑም እስከ አሁን የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ፀጋ ቤተሰቡ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቋል ብለዋል።

( በለጠ ካሳ )


የአያት መንደር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አያት መንደር የዞን 8 ነዋሪዎች ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ያለ ምንም ማስጠንቀቂና ሕጋዊ ማስረጃ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ፓርኩን ያለሙት የመንደሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ከ15 ዓመት በላይ ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ወይም ፓርክ ከነዋሪዎች በተዋጣ ገንዘብ በአረንጓዴ ልማት የተሸፈነ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ዛሬ ማለዳ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የመጣነው ያሉ ፖሊሶች ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሰራተኞችና አንድ ትራክተር አሰማርተው ፓርኩን እያፈረሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ከ15 በላይ በመናፈሻነት የተጠቀሙት ፓርክ እንደሚፈርስ ምን አይነት ማስጠንቀቂያም ይሁን መረጃ እንዳልተሰጣቸውም ጭምር ነው የተናገሩት፡፡

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የምናፈርሰው ያሉት የመንግሥት አካላት ማዘዣውን ለፓርኩ ባለቤት ለሆኑት ነዋሪዎች እንዲሳዩ ቢጠየቁም የፍርድ ቤት ማዘዣ ማሳየት አልቻሉም ተብሏል፡፡

Via Addis Maleda




🦾ምጣ‼️

🩸ህዝቡ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጧል ጥንቃቄ ይደረግ🩸

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


የአማራ ህዝብ መሪውን ካስበላ በኋላ ስለጀግንነቱ የሚፎክርል የሚዘመር የሚፀፀት ህዝብ ሆኗል። እንደ ምሳሌ ብንመለከት በላይ ዘለቀና አሳምነውን እና ሌሎችን ቆሞ አጨብጭቦ ያስገደለ ህዝብ ዛሬ የበላይ ዘለቀ ዘር፣ የአሳምነው ልጆች እያልን ስንፎክር እንውላለን። እውነት የአሳምነው ልጆች ከሆን በየፌስቡኩ እየተለጠፍ መፎከር ሳይሆን በተግባር ሆኖ መገኜትና የጀነራሉን ሌጋሲ እውን ማድረግ የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው።

ትናንት እኔም ፍኖ ነኝ እያለ የፌስቡክ አርበኛ የነበረ ሁሉ ዛሬ ፌስቡኩን ሎጋውት ብሎ ተደብቋል። ፍኖ ከሆንህ መዳኛህን ክንድህን ጋሻ መከታህን ጠብቅ። የአማራ ህዝብ አሁንም ፍኖን በጉማሪወች አስበልቶ የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆንባቸው መጠንቀቅ አለበት።

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


❗️ድምፅህን አጥፍተህ ተለወጥ!

የራስህን ዋጋ ስታውቀው ዋጋቸውን ያልተረዱ ሰዎች ያሳዝኑሀል፤ አንተ ከልብህ መለወጥ ስትጀምር ሌሎች እንደፈዘዙ ታያለህ፤ መሮጥ ስትጀምር ብዙዎች ቆመው እንደቀሩ ትታዘባለህ። ብትነግራቸው ግን አይሰሙህም፤ ሰዎች ብዙ ርቀት ላልተጓዘ ጆሮ አይሰጡም፤ ለዛ ነው ድምፅህን አጥፈተህ እስከጥግ መለወጥ ያለብህ።

መጀመሪያ አንተ ሳትቀየር ሌሎች እንዲቀየሩ አጠብቅ! ለምትወዳቸው የምትደርሰው አንተ ቆራጥ ሆነህ ያመንክበትን ስታሳካ ነው፤ ያኔ ስኬትህ ጮክ ብሎ ይናገራል!

የተዓምር ሀሙስ ተመኘንላችሁ🙏

ለእናንተው ምርጥ ጓደኛ መልክቱን #ሼር አድርጉለት።

💚💛❤️ ትዝብት😳 ኢትዮጵያ💚💛❤️

@Ethiotzibt
@Ethiotzibt
@Ethiotzibt


አዲስ አበባ —ኮምቦልቻ —ደሴ —ወልዲያ

ትናንት ሌሊት በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማ የነበረው የጥይት ተኩስ ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ በመድረሱ መሆኑን የከተማው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።ይህንን ተከትሎ መንገድ ተዘጋ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰት ናቸው።ምንም አይገናኝም።የእሳት አደጋውን ዝርዝር ጉዳይ አጣርቶ ዛሬ እንደሚያሳውቅም ገልጧል።በዋናው መንገድ ላይ ያጋጠመ የፀጥታ ችግር አለመኖሩን እና አካባቢው ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።


ወገን መንቃት አለብን። ጎጃም ላይ ብዙ ሰላማዊ ወጣቶች እየታፈሱ ነው ምክንያት ደግሞ ፍኖን ትደግፋላቹሁ በሚል የፈሪወች የደመነፍስ ውንጀላ ነው። ህዝብ ለምን በል የታቀደልህን ሴራ በጊዜ አክሽፈው።


ፍኖ ከበባውን በክንዱ እየሰበረ እየወጣ ነው ግን ህዝቡ የት አለ?? ሰሞኑን ምስራቅ ጎጃም ባሶሊበን ኮርክ ፍኖን ለማፈን ባለ ቀይ መለዮ ለባሽ አፋኝ ቡድን ከአዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ የጅቤ ኮርክ በይፍ ሲመላለሱ ታይቷል። ስለዚህ ይሄን የታዘበ ህዝብ ከንፈር ከመምጠጥ ውጪ ምን አደረገ? ፍኖ መከታህን ክንድህን መዳኛህን አለኝታህን ጠብቀው ለኦነጋውያን አሳልፈህ አትስጥ ። የደብረ ማርቆስ የጁቤ ህዝብ ከተኛህበት ንቃ ለምን ብለህ የመጣልህን አፍኝ ቡድን አሳፍረህ መልስ። ሁሉም የፍኖ አደረጃጀቶችን ነቅተህ ጠብቅ።


ገቢው በጦርነቱ ለተጎዳው ከተማ ልማት ይውላል
(የነፃ ማስታወቂያ ነው)

የኮምቦልቻ ከተማ ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ለሊዝ ጨረታ አዘጋጅቷል።የጨረታ ሰነዱ ከግንቦት 11—24/2014 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር 250 በመግዛት ተሳተፉ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

Показано 20 последних публикаций.

3 320

подписчиков
Статистика канала