Exit News 👁️‍🗨️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


This channel is designed to share latest information.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ


ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተን ያለፋችሁ እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል ተመዝግባችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በመጋቢት 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
  
ስለሆነም የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከየካቲት 24 - መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ፈተናውን የምትወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እያሳሰብን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦ 
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

- በጥር 30/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትናቹ ያለፍችሁና በዚህ የብቃት ምዘና ፈተና ለመቀመጥ የተዘጋጃችሁ ነገር ግን ቴምፖረሪ ዲግሪ ከተቋማችሁ ያልደረሰላችሁ ተመዛኞች ከትምርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ ቀጥታ ከሚመለከተው የስራ ክፍል የትብብር ደብዳቤ ማያያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እንሳውቃለን።
#MoH
📄

@officialexit


🚀 አዲስ መድረክ፣ አዲስ ዕድሎች! 
🚀የአባላታችንን በተሳካ ሁኔታ የተደረጉ ገንዘብ ማውጣቶች እናከብራለን!አሁን በAllied Gold ይቀላቀሉ – የእርስዎ የስኬት ታሪክ እዚህ ይጀምራል!
💡 በኦንላይን ገቢ መፍጠር ቀላል ነው!
💡 ከብልጽግና ጋር ተባብረው በወርቅ ይድረሱ!ለምን Allied Gold ን መምረጥ?
✅ 10,000+ በዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የተረጋገጠ
✅ ደህንነቱ �ስተማማ የወርቅ ኢንቨስትመንት ከ24/7 ግልጽነት
✅ በአንድ ጠቅታ ገንዘብ ማውጣት እና ብቸኛ ድጋፍ
👇👇👇
Link:https://alliedgd.cc/register?invitation_code=53084

Official Channel:https://t.me/Allied_Gold


ከታች ያለው ማስታወቂያ ነዉ


Репост из: 🦋Official Exit
#MoE

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።
📄

@officialexit


Репост из: 🦋Official Exit
#ታሪክ
ኢትዮጵያውያን ቅኝ ሊገዛቸው የመጣውን የጣልያንን ጦር ያሸነፉበት የአድዋ ድል ታሪክ በአጭሩ ይህ ነው።

አውሮፓውያን በኢንደስትሪ አብዮት የፈረጠመ ኢኮኖሚያቸውን ይበልጥ ለማስፋፋት የቀኝ ግዛት በትራቸውን ባላደጉና ባልሰለጠኑ ብለው በሚያስቧቸው ህዝቦች ላይ አሳረፉ። በ1885 ዓ.ም እ.ኤ.አ በበርሊን ጀርመን ተሰብስበው የአፍሪቃን መሬት ተቀራመቱ። በዚህም ስብሰባ ተሳታፊ የነበረችው ጣልያን ኢትዮጵያን የኔ ናት አለች። ይህ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ ጣልያኖች አስቀድመው ከያዙት የአሰብ እና የምጽዋ ወደብ በመነሳት ወደ ኤርትራ ደጋማ ስፍራዎች መዝለቅ ጀመሩ።

ከዚያም አልፎ ጣልያኖች ሴራቸውን በማጠናከር በ1889 ዓ.ም. እ.ኤ.አ መዘዘኛውን የውጫሌ ውል ከአፄ ምኒልክ ጋር ተፈራረሙ። በውሉ የተጠቀሰው አንቀፅ 17 ትርጓሜ በሁለቱ ሀገራት መካከል አንባጓሮን አስነሳ።  ይህን የጣልያን ተንኮል የተረዱት የኢትዮጵያ መሪዎች ውሉን ቀደው በጣልያን ላይ ጦርነት አወጁ። በ1896 እ.ኤ.አ ጥር ወር አፄ ምኒልክ በወረ ኢሉ የክተት አዋጅ አውጀው፣ በሺህ የሚቆጠሩ ዘማቾች ታጅበው መረብ ወንዝን አልፎ ወደትግራይ ክፍለ ሀገር ዘልቆ የገባውን የጣልያን ጦር ለመመለስ ወደ ሰሜን ዘመቱ።

እሁድ የካቲት 23፣ 1888 ዓ.ም ጦርነት ተጀመረ። በዚያችም እለት የአለምን ታሪክ የቀየረ ክስተት ሆነ። የኢትዮጵያ ወታደር ከፊቱ የተደቀነውን የመድፍና የጥይት እሩምታ ከጥፉም ሳይቆጥር እየሮጠ ገባበት። በጎራዴና ባልሰለጠነ መሳርያ ሰልጥኛለሁ ያለውን ጣልያን አንኮታኮተው። የጣልያን ኢትዮጵያን ጠቅልሎ የመግዛት ህልምም በአድዋ ተራሮች ቅዠት ሆኖ ቀረ።

#ኢትዮጵያ #ምድረቀደምት #ቼበለው #አድዋ #የካቲት23

#ethiopia #LandOfOrigins #chebelew #adwa #yekatit23

📄

@officialexit


Репост из: 🦋Official Exit
ከማይነማር የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖች የወጡ 800 ኢትዮጵያዊያን እዚያው በኹለት የአገሪቱ አማጺ ቡድኖች እጅ ውስጥ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያዊያኑ ፍልሰተኞች መስማቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ በግዳጅ ከሚሠሩባቸው ካምፖች በቡድን ኾነው የወጡት ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት እንደኾነና ከካምፖች አምጸው እንደወጡ አማጺ ቡድኖች እንደተረከቧቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ኾኖም ኢትዮጵያዊያኑ እስካኹን መንግሥት ለምን ወደ አገራቸው ሊመልሳቸው እንዳልቸለ ሊገባቸው እንዳልቻለ ገልጸዋል ተብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ መንግሥት ከካምፖች ነጻ የወጡ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ለመመለስ ዝግጅት እያደረገ መኾኑን ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረው ነበር።


📄

@officialexit


" በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ላይ ቁማር እየተጫወትክ ነው " - ትራምፕ

ዛሬ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ አሜሪካ ሄደው ከፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተዋል።

" ውይይት አደረጉ " ለማለት በሚያስቸግር ሁኔታ ትራምፕ እና ባለስልጣኖቻቸው ዜሌንስኪን ሲገስጹ ፣ ንግግራቸውን ሲያቋርጡ፣ ሲመክሯቸው ታይተዋል።

ትራምፕ ዜሌንስኪን ከሩስያ ጋር የገቡበት ጦርነት የሚያቆምበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋቸዋል።

" አሁን አንተ የምትወስንበት አቋም ላይ አይደለህም " ሲሉም  ትራምፕ እና ጄዲ ቫንስ ዘለንስኪን ሲገስፁ ነበር።

የገቡበት ጦርነት ያለ ቀድሞው ፕሬዜዳንት ባይደን እና 350 ቢሊዮን ዶላር የአሜሪካ ድጋፍ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ያበቃ ነበር ሲሉም ነግረዋቸዋል።

ትራምፕ " በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ላይ ቁማር እየተጫወትክ ነው። በሶስተኛው የዓለም ጦርነት ቁማር እየተጫወትክ ነው " ሲሉ ዜሌንስኪን ተናግረዋቸዋል።

" ሀገርህ ችግር ላይ ናት "ም ብለዋቸዋል።

" ደግሞ አመስጋኝ አይደለህም ፤ያ ጥሩ ነገር አይደለም " ሲሉም ገስጸዋቸዋል።

" ወይ ስምምነት ፍጠር ካልሆነ እኛ ከዚህ እንወጣለን። አሁን ምንም የቀረህ የምትመዘው ካርድ የለህም " ሲሉም ተናግረዋቸዋል።

ዘለንስኪ ከትራምፕ ጋር ከነበራቸው የጋለ የቃላት ልውውጥ በኋላ አስቀድመው ዋይት ሃውስን ለቀው ወጥተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በጋራ መስጠት የነበረባቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰርዟል።

ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር የጋለ ንግግር ካደረጉ በኋላ በትሩዝ ትስስር ገጻቸው ላይ " ዘለንስኪ ለሰላም ዝግጁ አይደለም። ለሰላም ሲዘጋጅ ተመልሶ መምጣት ይችላል " ብለዋል።

ኢሎን መስክ በX ገጹ ላይ " ዘለንስኪ በአሜሪካ ሕዝብ ፊት እራሱን አዋርዷል " ሲል ፅፏል።
#SputnikNews

📄

@exitnewss


የንግድ ባንክ አዲስ ህግ‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥጥሩን ጠበቅ አድርጓል‼️
ከየካቲት 17 ጀምሮ ከንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ በተላከው ደብዳቤ መሰረት የባንኩ ቴለሮች/ገንዘብ ከፋዮች/ የባንኩን ደንበኞች ተቀማጭ ቀሪ ገንዘብ መጠን ማየት እንደማይችሉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
የደንበኞችን ቀሪ ሂሳብ ማየት የሚችሉት ከፍተኛ ማኔጅሮች ብቻ ናቸው።
ባንኩ ይህን እርምጃ የወሰደው እየተንሰራፋ የሄደውን የገንዘብ ማጭበርበር ለከት ለማስያዝ እንደሆነ ተጠቁሟል(አዩዘሀበሻ)።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📄

@exitnewss


Kelay yalew mastawkya nw


✨በአዲስ መድረክ ላይ አዲስ  እድል ✨
🥇 ከላይ በምስሉ እንደምታዩት ብዙዎች እያሸነፉ ነው!
🔥ዛሬውኑ የቫሌሮ ኢነርጂን ይቀላቀሉ - ስኬትዎ እዚህ ይጀምራል!🔥
✅ በቀላሉ ኦንላይን ገንዘብ መስራት ይችላሉ!
✅ በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ትክክለኛ እና ታማኝ ነን 
ለምን Valero Energy ን እመርጣለሁ?✔️ ከ300,000+ ኢትዮጵያውያን መርጠውናል ✔️ ደህንነቱ የተጠበቀ ዘይት ኢንቨስትመንት ነው✔️ 24ሰዓት ሳምንቱን ሙሉ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ 
ለሌላው ሲያጋሩ የሚያገኙት ኮሚሽን: 37%በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ: https://www.valerosn.com/?invitation_code=58DC2ቴሌግራም ቻናላችን - https://t.me/Valero1


Ketach yalew mastawekya nw


#Update

የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አመልካቾች ምዝገባ ከነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዝገባ በየካቲት መጀመሪያ ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት አጋጥሟል።

አሁን ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮች መፍትሔ በማግኘታቸው ከነገ ቅዳሜ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት የአመልካቾች ምዝገባ (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) እንደሚደረግ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
📄

@Exitnewss


በቀጣዩ የትምህር ዘመን ለተማሪዎች ትምህርት ቤት ምዝገባ ፋይዳ መታወቂያ መያዝ አስገዳጅ መሆኑ ተገለጸ

በቀጣዩ የ2018 ዓ.ም ትምህር ዘመን የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ፤ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ማስጀመርያ በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ሕጻናት በዘመቻ ምዘገባ እንደሚከናወን ተነግሯል።

ለዚህም የትምህርት ማህበረሰቡን እና የተማሪ ወላጆችን ከሚወክሉ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት በዝግጅት ምዕራፍ መከናወኑ ተመላክቷል።

የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን፤ በከተማው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች የቅጥር እና ዝውውር እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ከምዝገባ ስርዓቱ ጋር እንዲቀናጅ በአስገዳጅ ስርዓትነት ተቀምጧል፡፡

በዚህም መሠረት የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታም እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

ላለፉት ወራት በተፈጠረው የጋራ ንቅናቄ በከተማው ከ2 ነጥብ 1 ሚልዮን በላይ አዲስ ተመዝጋቢ መመዝገብ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 900 ሺሕ የሚጠጋው ምዝገባ በቀጥታ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መዋቅር ጽ/ቤቶች የተደረገ ምዝገባ ተመላክቷል።

📄

@Exitnewss


ለመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በርቀት (Distance) በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በ PGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አመልካቾች እስከ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የምታመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከታች መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የማመልከቻ መስፈርት
 በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈት መሰረት ለበለጠ መረጃ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ይመልከቱ፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች
 የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
 የብቃት ማረጋገጫ (COC) (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)
 ኦፊሻል ትራንስክርፒት (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)
 ኮስት ሸሪንግ የተከፈለበት ደረሰኝ (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)
 የስራ ልምድ (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)
 ለማመልከቻ የተከፈለበት ኦርጅናልና አንድ ደረሰኝ እና የማይመለስ 2 ፎቶ ኮፒ ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)

የማመልከቻ ቦታ፣
 በባሕር ዳር፣ጎንደር፣ደሴ፣ደ/ብርሃነ፣ አዲስ አበባ ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ፍኖተ ሰላም እና ሞጣ -እነሴ ማዕከላት (የሁሉም አመልካቾች ምዝገባ በርቀት ትምህርት ማዕከላት ይሆናል፡፡)

ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች፡-
1. ሪሚዲያል በመንግስት ተቋም ተምራችሁ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች፡-
ኦፊሻል ትራንስክርፒት እና ኮስት ሸሪንግ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ይዛችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ

2. ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀርብ የሪሚዲያል ውጤት ተቀባይነት የለውም

3. የቀድሞው ትምህርት ፖሊሲ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የለውም

4. በዲፕሎማ ፣ በሪሚዲያልና ዲግሪ የሚመዘገቡ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክርፕች በፖስታ ሳጥን ቁጥር 79 ማስላክ አለባቸው፣

5. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት ዘርፎች ተቋሙ የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው፡፡ የፈተናው ቀን እና የቅበላ ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ወይም የፌስቡክ ገጽ ወደ ፊት ይገለፃል

6. በቂ የተማሪ ቁጥር የማያመለክትባቸው የትምህርት መስኮች አይከፈቱም

7. ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡት የትምህርት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ አይነት መመዝገብ አይቻልም

8. ለPGDT አመልካቾች በመምህርነት ሙያ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ
📄

@Exitnewss


#ራስ_ገዝ_ዩኒቨርሲቲ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ አስተዳደር ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የሴኔት ሕግ ለማዳበር የተዘጋጀ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል።

በቀጣይ ራስ ገዝ ለመሆን ዝግጅት እያደደረጉ ያሉ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች፦

➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
➫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ።

📄

@Exitnewss


በአክሱም 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በሚል ላለፉት አንድ መቶ ቀናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ተነገረ

በትግራይ ክልል አክሱም የሚገኙ 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ተከልክለዋል በሚል ላለፉት አንድ መቶ ቀናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ተገለጠ ።

በትግራይ ክልል በዋነኝነት በሴቶች መብት ጉዳይ ዙርያ የሚሠሩ ስድስት ሲቪክ ተቋማት ሕገወጥ ያሉትን ይህን የትምህርት ክልከላ ተቃውመዋል ። የአክሱም ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በዚህ ጉዳይ ዙርያ ምላሽ መስጠት አልቻለም ።

ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በሚከለክል የአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች መመርያ ምክንያት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ እስካሁን 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከትምህር ገበታ ውጪ ሆነው እንዳለ  የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ይገልፃል ።

ጉዳዩን አስመልክቶ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ መመርያ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ይህ መመርያ በትምህርት ቤቶች መጣሱን፣ ከዚህ በተጨማሪ የፍርድ ቤት ውሳኔም ጭምር አለመተግበሩን የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤቱ ይገልፃል።

በዚህ በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ርምጃ ምክንያትም ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ መሆናቸው ተገልጿል። 

#DW
📄

@Exitnewss


Репост из: Channel owner's
🎉🎉Instant Withdraw Bot
⭐️⭐️UniCoin Airdrop

▶️Bot Link https://t.me/UniCoinApp_bot?start=ref_72097356

Instant Payment & Withdraw

➡️Minimum Withdraw 1$USDT
💎100K Token Convert = 1$USDT
Payment Verified

✍️ አሰራሩ ቀላል ነው tap tap ነው እና task አለ ሞክሩት
https://t.me/UniCoinApp_bot?start=ref_72097356

Показано 17 последних публикаций.