💥እንቁ ᴛᴜʙᴇ™💥


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


🎀..ችግሮችህ በሙሉ ሰው ሰራሾች ናቸው ስለዚህም በሰው ይፈታሉ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ችግሮች ከሰው አቅም በላይ ሊሆኑ አይችሉም••🎀

For any comment & cross👇
@KERODINA
ከቆያችሁ ብዙ ነገር ታገኛላችሁ
If you stay, you will find a lot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


❇️𝙾𝚗𝚕𝚒𝚗𝚎 seentanii yeroo keessan balleessaa jirtuu? maallaqa hoo argachuu ni feetuu? akkas taanan maal eegduree, 🔗liinkii kanaa gadi jiru cuqaasuun hiriyoota keessan telegram Haffeera
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+2QOa2QWEMn05MTRk


'https://t.me/addlist/37N4EgSzRtU3YjA0' rel='nofollow'>» Fakkicha Hubannoodhaan Ilaali!
☁️              ☁️                       🛰
         ☁️              ☁️      ☁️             ☁️
                                    ☁️
☁️     ☁️ ☀️  
           ☁️             ✈️
☁️              ☁️☁️  ☁️
     ☁️           🚁      📡 ☁️
🏡🏬🏥🏡🏭.    🏨🏣🏦
                     / | \
     _🚂🚃  /   |   \ 🚩___
       👬🚦 /    |     \ 🚦🚶
        🌳   /      |        \  🌳
              /        |          \    🐐         🎡
     🌳  /  🚔   |  🚔     \ ⛽️       🏟
          /            |             \
  🌵 /      🚖   |  🚘          🚴
      /                |       🚔     \
    /         🚍    |                   \
  /                    |                    
» Konkolaataa diimaa fakkicha irra jiru tuqii garam akka deemu ilaali! Itti Gammadda! Irraa baratta! Just «JOIN» Now!


Waver @FastVipProm


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰3️⃣2️⃣

እንዲሁ ሳስብ አንዱን ሀሳብ ስጥል አንዱን ሳነሳ ሌሊቱ ሊነጋ ሲል እንቅልፍ ወሰደኝ ።

ጠዋት ልዑሌ ቀድሞኝ ተነስቶ ከመሲጋ ባባን አጣጥበው ልብስ ቀያይረውለት እኔንም ለቁርስ ቀሰቀሱኝ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እንዲሁ ምግቡጋ ቀረብኩ እንጂ ።

ልዑሌ ስራ አልገባም ዛሬ ግን በጣም ትልቅ ቀጠሮ አለኝ ላመሽም ቶሎ ልመለስም እችላለሁ አለኝ ::

እንዴት የት ነው ቀጠሮህ ቆይ አምሽተህ ማታቀው ሰውዬ ምታመሸው አልኩት ።

ትልቅ ጉዳይ አለብኝ ሰላሜ በቃ ቻው አለኝና ሁላችንንም ተሰናብቶን   ወጣ ።

ሁኔታው ትንሽ ግራ አጋብቶኛል ግን ነዝናዛ የት ገባህ የት ወጣህ አይነት ሴትን መሆን አልፈልግም ለዛ ብዬ ዝም አልኩት
ቀኑን ሙሉ ውስጤን ሰላም እየተሰማኝ ስላልነበር ተኝቼ ዋልኩኝ ልዑሌ አድርጎት ማያቀውን ቀኑን ሙሉ ሳይደውልልኝ ዋለ ።

ሰአቱ ቀስ እያለ ቀስ እያለ መሸ እንዳልደውልለት ስብሰባ ነኝ ቀጠሮ አለኝ ስላለ እንዳልረብሸው ፈራሁ ማታ 3 ሰአት አካባቢ ሲል ግን የመጨረሻ ስላላስቻለኝ ደወልኩለት ስልኩ ዝግ ነው ደጋግሜ ደወለኩ text ላኩኝ ግን ምንም መልስ የለም ።

ጨነቀኝ ማንጋ ልደውል ማንን አይታችኋል ወይ ልበል ሰአቱ ያለከልካይ ይሮጣል ።

ለ5 ምናምን ጉዳይ ሲል መጣ ።
ሳየው ይበልጥ ንዴቴ ጨመረ ምን ሆነህ ነው በሰላም ነው ቢያንስ ስልክህን ከፍተህ ማደር ከፈለክ ማምሸትስ ከሆነ አትናገርም እንዴ ቆይ ሰው ያስባል አትልም እንዴ ምንድነው ተምረህ እንዳልተማረ ምቶነው ግን ጭንቅላትህን ለማሰብም ተጠቀምበት እንጂ አልኩት ።

የዛኔ እሱም ብስጭት ብሎ ስላልደወልኩልሽ ይቅርታ ግን ጠዋት ላመሽ እንደምችል ነግሬሽ ነበር አደል እንዴ የሰውን ችግር ሳትረጂ ዝም ብለሽ ለመናገር ትቸኩያለሽ ብሎ አልፎኝ ገባ ።

በጣም ብበሳጭም ቻል ለማድረግ ሞክሬ እኔም ዝም ብዬው ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ትንሽ ቆይቶ መጣና ከአልጋው ስር በርከክ ብሎ ሰላም አለኝ የለበስኩትን ብርድ ልብስ እየገለጠኝ አትንካኝ በቃ መተኛት ነው ምፈልገው ብዬ መልሼ ተሸፈንኩ እልህ ይሁን ምን ይሁን እንባ እየተናነቀኝ ነበር::
በድጋሜ ገለጠኝና ሰላም በፈጣሪ ይቅርታ  በቃ እንዴ ይሄን ያህል ምን አጠፋሁ ስላመሸሁ ይቅርታ በቃ አለኝ እየተቅለሰለሰ ።
ምን ማለት ነው አንድ ስልክ ደውለህ ዛሬ አመሻለሁ ማለት ከብዶህ ነው እኔ እዚህ በጭንቀት ስንቱን ነገር አሰብኩት ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ ስናደድ ወይ እልህ ሲይዘኝ እንባ ነው ሚቀድመኝ ።

አረ ሰላሜ ተረጋጊ በቃ እኔኮ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አደለም ካቅም በላይ ሆኖብኝ ነው እንጂ ቆይ እኔ የት ገባህ የት ወጣህ ዛሬ የት አመሸህ በሰላም ነወይ ወይስ ችግር ገጥሞህ ነወይ መባሉን ጠልቼው አደለምኮ እንደውም ይሄ ለኔ ብርቄ ነው ቢያንስ ሰው አለኝ የሚጨነቅልኝ እንድል ያደርገኛል ሰላም በፈጠረሽ በቃ ይቅርታ ሁለተኛ አይደገምም አለኝና ሳመኝ የዛኔ አላስቻለኝም እኔም እቅፍ አድርጌ ስሜው ተቃቅፈን ተኛን .......
ጠዋት እንደተነሳሁ ከመሲጋ ቆንጆ ድባብ ያለው ቁርስ አዘጋጅተን ልዑሌን ቀሰቀስነው ቁርሳችንን በላልተን እንደጨረስን በቃ ስራ ልሂድ ብሎ ተሰናብቶን ወጣ ።

ይሄኛው እርግዝናዬ በጣም ከባድ ነው ።
እንዴት ነው ግን ከባባድ ስራዎችን እየሰሩ እርግዝናቸው ገፍቶ ሁላ እንደልባቸው የሚንቀሳቀሱት አንዳንድ ሰዎች ግርም ይለኛል።

ቀን ላይ ደውዬ ልዑሌን አምሮኛል ይዘህ ና ያልኩት ነገር ልክ ይዞት ሲመጣ ያስጠላኛል ።
ትንሽ ምግብ ከሸተተኝ ምገባበትን ነው ሚያሳጣኝ ያደበላልቀኛል ።

ከቀናቶች ቡሀላ ልዑሌ እንደተለመደው ጠዋት ላመሽ እችላለሁ ብሎኝ ከቤት ወጣ ።
ከባለፈው ሳይማር አመሸ በዛ ላይ ስልኩ እየጠራ አያነሳውም  እንዲሁ እየተብከነከንኩ መሸልኝ እንደለመደው 5 ሰአት ምናምን ላይ መጣ ሲመጣ ፊቱ ቅይይር ብሎ ነበር  ከሱም ብሶ ፊቱ መቀያየሩ ገርሞኝ 2 ቀን አኮረፍኩት እየለመነኝ እንቢ አልኩኝ።
ከ2 ቀን ቡሀላ ግን አላስችልሽ ብሎኝ አናገርኩት ድጋሜ ከደገመው የመጨረሻችን እንደሆነ አስጠነቀቁት እሺ ብሎ ቃል ገባልኝ ። ከምትወዱት ሰውጋ አንድ ቤት  ውስጥ እየኖራችሁ መቀያየም ማለት ውይ ቃል የለኝም በጣም የሚያስጠላ ስሜት ነው ።

በቃ ከልዑሌጋ በምንም አይነት ሁኔታ መቀያየም አልፈልግም   ጠዋት ወጥቶ ማታ እስኪመጣ እንዲናፍቀኝ እንጂ ጠዋት ወጥቶ ማታ ሊመጣ ሲል ውይ ደሞ ሊመጣ ነው ማለት አልፈልግም ትዳር ውስጥ ትልቁ ነገር መከባበር ነው ።

ልዑሌ ከተጋባን ቀን ጀምሮ አንድም ቀን የተለየ ፊት አሳይቶኝ አያውቅም ።

ውስጡ ባዶነት የሞላው ሰው ነው  
ዙሪያው በገንዘብ የተከበበ ሰው ነው ውስጡ ግን ባዶ ነው even ወንድሞቹ እራሱ ይሙት ይኑር አይጠይቁትም።

እኔ እንኳን እናቴ ጠዋት ስራ ከመሄዷ በፊት ምሳ ሰአትና ማታ ከመተኛቷ በፊት ትደውልልኛለች ።

ሰው እንዴት አንድ ከተማ ውስጥ እየኖረ ያውም ወንድምን ያህል ነገር አይጠያየቁም ግራ ይገባኛል ልዑሌ  ሲበዛ ድብቅ ነው ሰውን ተጨንቆ ማስጨነቅ አይፈልግም ሁሌም ደስተኛ እንደሆነ ለማስመሰል ይሞክራል ግን ፈገግታው ውስጥ እራሱ እንባ አለ ..

አንዳንዴ እንዲሁ ዝም ብዬ አየውና ያሳዝነኛል ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም።


🔻ክፍል ሰላሳ ሶስት ነገ ማታ 3️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
       ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


'https://t.me/addlist/37N4EgSzRtU3YjA0' rel='nofollow'>📣አዲስ ጫወታ መዋሸት አይቻልም የስማችሁን የመጀመሪያ ፊደል በመንካት የሚመጣላችሁን ቀላል ጥያቄ መመለስ..   ዳይ ወደ ስራ👇

⚜🄰⚜       ⚜🄱⚜       ⚜🄲⚜

⚜🄳⚜       ⚜🄴⚜       ⚜🄵⚜

⚜🄶⚜       ⚜🄷⚜       ⚜🄸⚜

⚜🄹⚜       ⚜🄺⚜       ⚜🄻⚜

⚜🄼⚜       ⚜🄽⚜       ⚜🄾⚜

⚜🄿⚜       ⚜🅀⚜       ⚜🅁⚜

⚜🅂⚜       ⚜🅃⚜       ⚜🅄⚜

⚜🅅⚜       ⚜🅆⚜       ⚜🅇⚜
      
           ⚜🅈⚜       ⚜🅉⚜

መልካም ጫወታ

Waver @FastVipPro


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰3️⃣1️⃣

ይገባኛል ልዑሌ ግን በቃ አባት ሆነሀል ።
ደስ ስላለህ ደስ ብሎኛል ።
እውነት ለመናገር በጣም ደስ እንደሚልህ ገምቼ ነበር ግን በዚህ ልክ የሚሆን አልመሰለኝም የኔ አባት እንኳን ደስ አለህ አልኩት።

ሰላሜ በጣም እወድሻለሀ ይሄ ለኔ እንደ አዲስ የመወለድ ያህል ነው በጣም አመሰግንሻለሁ እንደ አዲስ ለመኖር እንድጓጓ ስላደረግሽኝ አለ

አረ ልዑሌ አንተ ለኔ ያደረከው መልካም ነገር መልሶ እየከፈለህ ነው ያለው ደሞኮ ይሄ ገና የመጀመሪያችን ነው ገና ደርዘን ነው ምወልድልህ ብዬ አቀፍኩት በቃ አረፍ እንበል እኔም ደክሞኛል አልኩት ።
አንቺ ተኚ እኔ እቆያለሁ አለኝ  እንዴ ለምን እረፍት አድርግ እንጂ ወዴት ነው ምትቆየው ብዬ ስጠይቀው አይ ሰላሜ  በዚህ ሁኔታ እንቅልፌ አይመጣም ተኚ አለ ።
እሺ በቃ አላስጨንቅህ ብዬው እኔ ዝም ብዬ ተኛሁ።

ሌሊት 8 ሰአት አካባቢ ከእንቅልፌ መጥፎ ህልም አይቼ ብንን ብዬ ተነሳሁ ልዑሌ ከጎኔ አልነበረም።

ተነስቼ ወደ ሳሎን ሄድኩኝ ሶፋ ላይ ጉልበቱን አቅፎ ቁጭ ብሎ እያለቀሰ ነበር ሳየው ደነገጥኩ እንዴ ልዑሌ ምን ሆነሀል በፈጠረኽ አምላክ አይንህን አይተኸዋል ሰው የሞተብህኮ ነው ሚመስለው እእእ ሁሉም ነገርኮ ልክ አለው ቆይ ምንድነው እንደዚህ ስሜትህን የነካው አባት መሆንህ ብቻ ነው ወይስ ሌላም ነገር አለ ግራ ተጋብተህ ግራ አታጋባኝ እኔ ስትዘል ስትፈነድቅ ከጣራ በላይ ስትስቅ ማየት ነው ምፈልገው አልኩት ።

እሺ ሰላም አንዳንዴ በቃ አይሆንም አይደረግም ብለሽ ያመንሽው ነገር ድንገት ሆኖ ስታገኚው ቆይ ባንዴ እሺ ብለሽ ትቀበያለሽ ሰላም እኔኮ አደለም ሚስት ማግባት አደለም የልጅ አባት መሆን ይቅርና ሴትን ልጅ ቀርቤ የማውራት ፍላጎትም ሀሳብም ያልነበረኝ ሰው ነኝ እእ ድንገት ቤት የምትጠብቀኝ ሚስት አባዬ ብለው ሚጠሩኝ ልጆችን ሳገኝ ምን እንደሚሰማኝ ገምቺ እስኪ እእእ ......
እሺ በቃ ልክ ነህ አሁን ና ወደክፍላችን እንግባ ባባ ብቻውን ነው የተኛው ብዬ ይዤው ገባሁ በነጋታውም ወደቢሮ ሳይገባ ቤት ዋለ ከራሱጋ አልነበረም ማለት ይቻላል ከደስታው በላይ ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው ።

ብቻ ልዑሌ እርግዝናዬን ከነገርኩት ቀን ጀምሮ ቶሎ ሆድ ሚብሰው ነገር አለ ።
የትኛውም ነገር ላይ ስለ ልጅ ስናወራ እንባ ይቀድመዋል አንዳንዴ በእጁ የያዘውን እቃ እንደ አዲስ ይፈልጋል::

ይኼኛው እርግዝናዬ እንደመጀመሪያው አደለም  በጣም ከባድ ነው የበላሁት ነገር ሆዴ ውስጥ አይቀመጥም እንደዛ ምወደው ቡና ገና ሲሸተኝ ያቅለሸልሸኛል በፍቅር እወዳቸው የነበሩትን ምግቦች አንዳቸውንም አልጠቀምም  ::
በቃ ሰውነቴ በየቀኑ ቅይይር ይላል ::

እናቴጋ ከሄድን ስለቆየን እሁድ ቀን  እናቴም ጠፋችሁ እያለችኝ ስለነበር ሄድን እንደተለመደው እዛ ስንጫወት ቤቱን ስናደምቀው ዋልን  በየመሀሉ እያመመኝ ወደውጪ እየወጣሁ ነበር ማታ አካባቢ ወደቤታችን ለመሄድ ተነሳን እናቴ በሩን አስወጥታን ተመልሳ ገባች።
መሲ ባባን አቅፋ እኔና ልዑሌ ደሞ እጅ ለእጅ ተያይዘን እያወራን እየተሳሳቅን መኪናውጋ ደረስን ልዑሌ እኔንም መሲንም በሩን ከፍቶ  ካስገባን ቡሀላ እኔ ስልኬን እረስቼው ስለወጣሁ ተመልሶ ሄደ ::

መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን ከመሲጋ ስለሰፈራችን እየነገርኳት ማክቤል በፍጥነት እየተራመደ ከፊት ለፊታችን ትንሽ እራቅ ብሎ አስፋልት ሲሻገር አየሁት አስፋልቱን ተሻግሮ ቆሞ ሚጠብቀው መኪና ነበር አይኔን ማመን አስኪያቅተኝ ድረስ እሱ አልመስልሽ አለኝ።

ማክቤል በህይወቱ የጨርቅ ሱሪ  እና ሱፍ ሚባል ነገር አይወድም ነበር ።
ዛሬ ግን አለባበሱ ቢሮ የሚውል በጣም ትልቅ ድርጅት አስተዳዳሪ ነገር ነው ሚመስለው ፂሙን ፀጉሩን ተስተካክሎ አማላይ ሆኗል አረማመዱ ሁላ ልክ ቢዚ እንደሆነ የስራ ሰው ነበር ሳየው ወሬዬን አቋርጬ አፈን ከፍቼ እያስተዋልኩት ወደመኪናው ውስጥ ገብቶ በፍጥነት መኪናው ከዛ አካባቢ ተሰወረ ።

እውነት ለመናገር ገረመኝ እንዲ በዚህ ፍጥነት መቀየሩ ጥያቄ ሆነብኝ ።
ልዑሌ አትዝረክረኪ እሺ እቃሽን የትም እያጋደምሽ እኔን አታልፊኝ ብሎ እየሳቀ ስልኬን ሰጠኝ ተቀበልኩትና ወዲያው ለማክቤል አምሮብሀል እንዲህ ተለውጠህ በማዬቴ ደስ ብሎኛል ኩል ሆነሀል አልኩት ።
ምንም አልመለሰልኝም ከልዑሌጋ እያወራን እየሄድን አስሬ ስልኬን አያለሁ መልስ የለም ።

ወደቤታችን ከደረስን ቡሀላ ልብሳችንን ቀያይረን ባባም ቀን ሙሉ አንዴ እናቴ አንዴ እህት ሲቀባበሉት ደክሞት ስለነበር እንቅልፍ ተኝቶልን ስለነበር እኛም አረፍ አልን::

ማታ 2 ሰአት አካባቢ text ገባልኝ ማክቤል ነበረ አመሰግናለሁ🙏 ብቻ ነበር ያለኝ ።
እውነት ለመናገር ልጁን ካሳየሁት ቡሀላ ከበፊቱ የበለጠ እኔን ማስቸገር ልጄን ልየው እያለ መጨቅጨቅ እንጂ እንዲህ ድራሽ አባቱ መጥፋት ነበረበት እንዴ ቆይ ምን አስቦ ነው  ከረሴጋ እያወራሁ እንቅልፍ ጣለኝ ::

ሌሊት ላይ ባባ ተነስቶ እያለቀሰ ነበር አባብዬ አስተኛሁት እኔ ግን ተመልሶ መተኛት ከበደኝ ።


🔻ክፍል ሰላሳ ሁለት ነገ ማታ 3️⃣🟰3️⃣0️⃣  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
       ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰3️⃣0️⃣

ቤት ከደረስን ቡሀላ ቆንጆ እራት ከመሲጋ አዘገጃጅተን ልዑሌን ቤቱን ፏፏ አድርገን ጠበቅነው::
ቤት ሲገባ ልዑሌ እንደለመደው በደስታ ተሞልቶ ነበር የገባው ።

እራታችንን በላልተን ወደመኝታችን ሄድን ዛሬ እኔ ድክምክም ብሎኝ ስለነበር ባባን የማስተኛት ተራው የልዑሌ ነበር ።
እኔ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው አይኔን ጨፍኜ ተሸፈንኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ጭንቅላቴ ስለማክቤል ከማሰብ ማቆም አልቻለም ነገረ ስራው ሁሉ አሳዘነኝ ።
ቀን ፊቱ ላይ ያነበብኩት የመጎዳት የእውነት ልቡ እንዴት እንደተሰበረ ፊቱ ላይ ይታያል ድርጊቱ ከፊት ከፊቴ እየቀደመ አላስተኛ አለኝ ።

በፍቅር አለም የሆነን ሰው ማፍቀር መውደድ ያለ ነው መፈቀርም እንደዛው ግን በሁለት ሰው መሀል መሆን በጣም ከባድ ነው ካንዱጋ ሆኖ ስለሌኛው ማሰብ ህመም ነው አንድ ልብ ኖሮን ለሁለት ሰው እንደመስጠት ማለት ነው በጣም ያስጠላል ስሜቱ ከማክቤልጋ ስሆን ልዑሌ ያሳዝነኛል ይናፍቀኛል ከልዑልጋ ስሆን ደሞ ማክቤል ያሳዝነኛል🥺

ብቻ ማክቤል ከዛ ቀን ጀምሮ ሳይደውል text ሳይልክ ቆዬ አንዳንዴ ለመደወል ስልኬን አነሳና እራሴ ተወኝ ብዬ ለምኜው እንዴት እደውላለሁ ብዬ እተወዋለሁ ።

በ15 ቀን አንዴ እናቴጋ እንሄዳለን አሁንም መሲንም ጨምሮ ሰብሰብ ብለን ሄደን እሷጋ ዋልን እንደለመድኩት ሰፈር ላይ ማክቤልን አየዋለሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ላየው አልቻልኩም።

እህቴን ቀስ ብዬ ጠራዃትና ማክቤልን አይተሽው ታውቂያለሽ እንዴ አልኳት??

በፊት በፊት ሁሌ ከኛ በር ፊት ለፊት ይቀመጥ ነበር ሰሞኑን ግን አይቼው አላውቅም አለችኝ ።

በውስጤ በሰላም እንዲሆን እየፀለይኩ ሲመሽ ወደቤታችን ተመለስን ማታ ላይ ሁሉም ሲተኙ ስልኬን አንስቼ text ላኩለት 

ሰላም ነህ ይቅርታ ከረበሽኩህ ድምፅህ ሲጠፋ እንዴት እንደሆንክ ልጠይቅህ ብዬ ነው አልኩት ።

ደና ነኝ ብቻ አለኝ
ከዛ እኔም ዝም አልኩት በቃ ከዛ ቡሀላ ለ1 ወር ከምናምን ምንም አይነት text ተላልከን አናውቅም በስልክም አናወራም ዝም አለኝ ዝም አልኩት።

ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ነገሮች እየተቀየሩብኝ ሲመጡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ እንደገመትኩት እርጉዝ ነበርኩ ።

የመጀመሪያው እርግዝናዬ ላይ እንዳረገዝኩ ስሰማ ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ስፀልይ ነበር።

ባሁኑ ግን የደስታ ጥግ ላይ ነበርኩ ከሀኪም ቤት እንደተመለስኩ ለናቴ ደወልኩላት እና በጊዜ ወጥታ እኔጋ እህቴንም ይዛት እንድትመጣ ነገርኳት  እሺ አለችኝ።

እኔና መሲ ቤቱን በአል አስመሰልነው መሲ አስሬ ምን አለ ዛሬ ምን ዛሬ ትለኛለች ማታ ለሁሉም የተዘጋጀ ሰርፕራይዝ እንዳለ ነገርኳት ።

ልዑሌንም ደውዬ ስንት ሰአት እንደሚመጣ ስላረጋገጥኩ ሰርፕራይዙ እንዳሰብኩት ሄደልኝ ።

ማታ ሁላችንም ቤት ተሰባሰብን ሁሉም አስሬ ምንድነው ዛሬ ምንድነው ይሉኛል ምን የረሳነው በአል አለ አንዴ ይጠያየቃሉ እናቴና ልዑሌ  እኔ ከእራት ቡሀላ ነው ምነግራችሁ በቃ ተረጋጉ ብያቸው እራታችንን በላን ።

ሁሉም ልባቸው ተሰቅሎ እንዴት እንደበሉ ብታዩት እያሳቁኝ ነበር ከእራት ቡሀላ ቡናችንን እየጠጣን አሁን ሁላችሁም ተረጋጉና ሰርፕራይዙን ለማየት ተዘጋጁ አልኳቸው መጀመሪያ ግን ባባን ይዞት የነበረው ልዑል ስለነበር ለእህቴ ስጣት እሷ ትያዘው አልኩት ድንገት ስሜታዊ ሆኖ ቢጮህ እንኳን ባባ እንዳይደነግጥ ብዬ ነው እንደዛ ያልኩት ::
የዛኔ የምር ግራ እየተጋባ ባባን ሰጣት እኔ ተነስቼ ወደመኝታ ክፍላችን ገባሁና ቼክ ያደረኩበትን የእርግዝና ማስረጃዬን ይዤ መጣሁና  መጀመሪያ ለልዑሌ ሰጠሁት

ቀስ ብሎ አየውና እኔን ቀና ብሎ አየኝ  ምንድነው ምንድነው ይሄ አለኝ አይኑ እንባ እያቀረረ እርጉዝ ነኝ የልጅ አባት ልትሆን ነው አልኩት::
እናቴ እንዴት እንደተነሳች ባላውቅም ብድግ አለችና የያዘውን ተቀበለችው ።
ልዑሌ እኔን እያየ አላምንሽም ሰላም አውቀሽ ፕራንክ አደረኩህ ልትይኝ ነው አደለ ሰላም ማይልኝ እውነትሽን ነው አለኝ??

አዎ እማዬ ትሙት የምሬን ነው እርጉዝ ነኝ አልኩት የዛኔ በቁሙ መሬት ላይ  ውድቅ ብሎ ተንበረከከ እናቴ እልልታውን አቀለጠችው ።

ሄጄ ልዑሌን አቀፍኩትና ደስ አለህ አልኩት በእጁ ፊቱ ላይ ያለውን እንባ እየጠረገ ሰላም በህልሜ እየመሰለኝ ነው ደግመሽ ማይልኝ አለ።
ማልኩለት የዛኔ እንደለቅሶ ቤት ድምፅ እያወጣ መሬት ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ ከጠበኩት በላይ ሆነብኝ ልዑል በፈጣሪ ተረጋጋ እንጂ እንዴ አልኩት ።

እናቴም ልጄ ተው ደስታ ላይ እንዲህ አይኮንም ጥሩ አደለም ደስታውን በልኩ አድርገው አለችው።

የሱ እንባ ወይ ፍንክች አለ ዝም ብሎ ይፈሳል ።
አንስቶ አሽከረከረኝ ሰላም እውነት እኔም እንደሰው አባት ልሆን ነው እእእ ሰላም እውነት ፈጣሪ እያየኝ ኖሯል አረሳኝም አለ።

የዛኔ እናቴ ግራ ተጋብታ እንደዚህ ስትሆኑ ለሚያያችሁ ሰውኮ የመጀመሪያ ልጃችሁን ገና ልትወልዱ ነው ሚመስለው አለች ።

የዛኔ እኔ ደነገጥኩኝና ልዑሌን አየት አደረኩት ።
ያው እናቴ እሱ ወንድ ነው ቀጣዩ ደሞ ሴት ልትሆን ትችላለች ብሎኮ ነው እንዲህ ደስ ያለው ለሴት ልጅ ያለው ፍቅርኮ ይለያል አልኳት በሉ ተረጋጉና ቁጭ በሉ ልጆቼ ይህን ክብር ይሄን ደስታ ያሳየን አምላካችን ክብሩ አይጓደልበት።

እኔንም ከአንድም ሁለት የል ልጅ እንዳይ የፈቀደልኝ አምላክ ይመስገን የኔ ልጅ አሁንም እንዲሁ ከነፍቅራችሁ ጤናን ሰጥቶ በሰላም ያኑራችሁና ቤታችሁ በልጅ እንዲሞላ ያድርጋችሁ ።
በሉ እኛን ሸኙንና እናንተ ደሞ ደስታችሁን ከዚህ በበለጠ አክብሩ።
የኔ ልጅ እንዲህ በየጊዜው ደስታን እንዳይ እንድሰማ ስላደረግሽኝ አመሰግናለሁ
ፈጣሪ ያላሰብሽውን ፍቅር በረከት መትረፍረፍ ይስጥሽ ላንተም እንደዛው የኔ ልጅ በቃ ተረጋጋ አለችው ተነስታ በነጠላዋ እንባውን እየጠረገችለት::

በቃ ልዑሌ ተነስ እነማዬን እንሸኛቸው መሽቶባቸዋል አንተ እንደሆንክ በዚህ ሁኔታ መኪና መንዳት አትችልም አልኩት ሰውነቱን እራሱ በስርአት ችሎ መቆም አይችልም ነበር::

እነማዬን ሸኝተናቸው ወደ ቤት ተመለስን መሲ እንደታቀፈችው ባባ ተኝቶ ጠበቀን ተቀበልኳትና ቀስ ብዬ አስገብቼ አስተኛሁት ።

ከዛ ልዑሌን እንዲረጋጋ ወደ ማድረጉ ገባሁ እቅፍ አደረኩትና በቃ ተረጋጋ አባት ሆነሀል አባት ደግሞ ቆፍጣና ነው መሆን ያለበት አልኩት።

ሰላም እኔኮ ከዛ ሁላ ነገር ቡሀላ እንደዚህ አይነት ደስታ አለም እንዳለ አላውቅም ነበር አንድም ቀን አባት ስለመሆን ልጅ ስለመውለድ አስቤ አላቅም ::

ሰላም ይሄኮ ለኔ ምን ማለት እንደሆነ ስላልገባሽ ስሜቴን ሚገልፅልኝ ምንም ቃል ስላጣሁ ምንም ልልሽ አልችልም ግን ሰላም አስቢው እስቲ አባት ልሆን ነውኮ አባት አለኝ ፊቴን በሁለት እጆች ጥብቅ አድርጎ ይዞ እያፈጠጠብኝ ።


🔻ክፍል ሰላሳ አንድ ነገ ማታ 3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣9️⃣

ልዑሌ ለምሳ እቤት መጥቶ ልክ እንደወጣ ማክቤልጋ ደወልኩለት ልመጣ ነው።
አልኩት እሺ ቤት እየጠበኩሽ ነው የት ነው ምንገናኘው አለኝ ።
ከሰፈር ትንሽ እራቅ ይበል ሰው የማያየን ቦታ አልኩት እሺ ለምን ቦታችንጋ አንገናኝም አለኝ። የዛኔ በጣም ተናደድኩ ህፃን ልጅ ጫካ ለጫካ ልዙር ለምንድነው ድንጋይ ምቶነው አልኩት።
ይቅርታ እሺ በቃ መቼስ መጠጥ ቤት አልቀጥርሽ ግራ ገብቶኝኮ ነው አለኝ ።
በቃ እናቴ ቤት እንገናኝ ስደርስ እደውልልሀለሁ አልኩና ልጄን አጣጥቤ ቆንጆ ልብስ አለበስኩት እኔም ልብሴን ቀያይሬ ፏ ብዬ ወደናቴ ቤት ሄድኩኝ እናቴ ቤት ስደርስ እህቴ ከትምህርት ቤት ተመልሳለች እናቴ የለችም ስራ ናት ።
ለእህቴ ይሄንን ነገር ለማንም እንዳትናገር ግን ማክቤልን ቤት ልጠራው እንደሆነ አስጠንቅቄ ነገርኳት እሺ አለችኝ።

ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ቶሎ ና እቸኩላለሁ ልዑሌ ቤት መጥቶ ካጣኝ ይናደድብኛል አልኩት እሺ አለኝ ::
ከ 10 ደቂቃ ቡሀላ ቤት መጣ ለእህቴ ባባን አቅፋው ወደ ክፍሏ እንድትገባ ነገርኳት እሱ ቤት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ልክ እንደገባ ብቻሽን የመጣሽው ልጄስ አለኝ??

በምልክት ድምፁን እንዲቀንስ ነገርኩትና ቁጭ በል በመጀመሪያ ትልቅ ላወራህ ምፈልገው ነገር አለኝ በሱ ከተስማማን ብቻ ነው ዛብሎንን ማየት ምትችለው አልኩት ።
ዛብሎን ነው ስሙ አለኝ ፈገግ እያለ
አዎ
በመጀመሪያ ደረጃ  በዚህ እድሜህ ይሄ በየመጠጥ ቤቱ ምታመሸው ምትሰክረውን ነገር ታቆማለህ : ማፈር አለብህ ጠጥተህ ለምትሸናው ነገር አባትህ ደም ተፍቶ ያመጣውን ገንዘብ ስታጠፋ።

በመቀጠል ይሄ ጎዳና ተዳዳሪ ያስመሰለህን ፂምህንና ፀጉርህን ተቆረጥና የአባትህን ፈገግታ መልስልት በየሰፈሩ ሰው ፊት አታስንቀው ተከብረህ አስከብረው እንጂ ።

ሶስተኛው ደሞ ወጥረህ ስራ ጓደኞችህን ምረጥ ሁሌ እንጠጣ ሚሉህን ተውና ሰርተን እንቀየር የሚሉህን ያዝ  በዚህ እድሜህ ያባትል ጡረተኛ መሆን የለብህም ግርሰሪውንም ቢሆን አንተ ሸፍንላቸው እሳቸውን አሳርፋቸው ።

የመጨረሻው ንግግሬ ደሞ እራስህን ቀይረህ ለውጠህ በተግባር አሳየኝ እንጂ በመሸ ቁጥር እየጠጣህ እየደወልክ አትለፋደድብኝ ትዳር አለኝ የባለቤቴንም የኔንም ክብር መጠበቅ አለብኝ።
ልጄን ዛሬ አሳይሀለሁ ከዛ ቡሀላ ግን አሳይኝ አገናኝኝ ማለት አይቻልም እኔ ስፈልግና ሲመቸኝ ሁኔታህን አይቼ ነው ድጋሜ እሱን ማየት ምትችለው ከዛ ውጭ እንደዚህ ሆነህ ሁለተኛ ልጅ አለኝ ብለህ እራሱ እንዳታስብ ምክንያቱም እራሱን መጠበቅ ማይችል ሰው  ሌላው ሰው መጠበቅ አይችልም ጨርሻለሁ አልኩት ።

በጥሞና ሲያዳምጠኝ ከቆየ ቡሀላ እንዴት እንደምቀየር አሳይሻለሁ እኔ ማክቤል ነኝ ለቃሌ እንዴት ሟች እንደሆንኩ ታቂያለሽ አለኝ።

ጥሩ መጣሁ ብዬው ወደ እህቴጋ ሄድኩ ባባን ተቀበልኳትና እሷ እዚሁ ሆና እንድትጠብቀኝ ነገርኳት ።

ማክቤል ልክ ባባን እንዳየው እጁ ተንቀጠቀጠ ካይኑ እንደሴት ልጅ እንባ ፈሰሰ አሳዘነኝ ።
መጀመሪያ ለመረጋጋት ሞክር ከዛ ቀስ ብለህ ታቅፈዋለህ አልኩት ።

እሺ አለኝ ጭንቅላቱን እያወዛወዘ ካይኑ ሚፈሰውን እንባ ጠረገና እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረ እጁን ዘረጋልኝ ባባን ሰጠሁት አቀፈው አየው ምን አይነት እድል ኖሮኝ ነው ግን በራሴ ስተት አብረኸኝ እንዳታድግ ያደረኩት አለ ቀና ብሎ አየኝና ሰላም እውነት ይሄ የኔ ልጅ ነው እውነት እኔ አባት ሆኜ ነው እእ ሰላም አስበሽዋል አባቴምኮ የልጅ ልጅ አየ ማለት ነው ቆይ ከዚህ በላይ ደስታ ምን አለ አለኝ እያለቀሰ አንዴ ባባን አንዴ እኔን እያየ እኔ ዝም ብዬ ቆምኩ ።

ልሳመው እንዴ እእ ችግር የለውም አለኝ??
አዎ ትችላለህ ሳመው አልኩት ።

ልክ ሲስመው ባባ እሪ ብሎ አለቀሰ የማክቤል ፂም በጣም ስላጎፈረ ኮስኩሶት መሰለኝ ደነገጠና ሰላም ያዥው አለቀሰ አለኝ እሺ ብዬ ተቀበልኩትና አባባልኩት።

ይበቃል የቀረውን ደግሞ የምር ተቀይረህ አሳየኝ በኔ በኩል ጨርሻለሁ አልኩት።

እሺ ለመጨረሻ ጊዜ አንዴ ብቻ ልቀፈውና እወጣለሁ አለኝ ።
ሰጠሁት አቀፈው አየው መልሶ ሰጠኝና በሹራቡ እንባውን እየጠረገ ከቤት ወጣ እኔም እህቴን ቻው ብያት ለናቴ እንደመጣሁ እንዳትናገር አስጠንቂቂያት ወደቤቴ ከልጄጋ ተመልስኩ ።


🔻ክፍል ሰላሳ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለዉን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፈራ ኑና እዩ።
ማቴዎስ 28÷5

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁልን።
ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላምን ያድርግልን።🙏🙏


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣8️⃣

ትንሽ ከተኛሁ ቡሀላ ተነስቼ ልጄን አጣጥቤ ልብሱን ቀያይሬለት አብሬው ለመተኛት ሞከርኩ ።
ለራሴ ምን ያህል የህፃን ስራ እንደሰራሁ በጣም ሞኝ እንደሆንኩ  እየነገርኩት ነበር።
ለማክቤል ልጁ የሱ እንደሆነ ከነገርኩት ቡሀላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ በራሱ ከበደኝ ቀጥታ sms ሲሆን ወይ መደለት አልችል ግራ ገባኝ

ፈጣሪዬ ሆይ ማታ ሰክሮ ስልኩን ጥሎት በገባ ብዬ ፀለይኩ ከእንቅልፉ ሲነቃ ደውሎ ምን ሊለኝ እንደሚችል ማሰብ በራሱ ከበደኝ ከዛ ሽሽት ስልኬን አጠፋሁ።

ምሳ ሰአት ላይ ልዑሌ መጥቶ ቆንጆ ምሳ በላን ያው እኔ እንኳን ጭንቀቱ ሊያፈነዳኝ ትንሽ ነበር የቀረኝ አንብቦት ይሆን ካነበበው ቡሀላስ ምን ይወስን ይሆን ሄዶ ለናቴ ቢነግራትስ ብቻ  ምን የማላስበው አለ  ስልኬን ልክፈተው አልክፈተው ግራ ገባኝ ልክ እንደከፈትኩት ቢደውልልኝስ አንስቼ ምን አወራለሁ ።

ማታ አካባቢ በቃ የፈለገው ይምጣ ብዬ ከፈትኩት እንደፈራሁት ልክ እንደከፈትኩት ማክቤል ደወለ ።
ከእንቅልፌ ከተነሳሁበት ሰአት ጀምሮ ስደውልልሽ ስልክሽ ዝግ ነው አለኝ ።
አዎ ዝግ ነበር ምነው ለምን ፈለከኝ አልኩት ልክ ምንም  እንዳልተፈጠረ ነገር
  
አሁን ካንቺ በላይ ልጄ ነው ሚያስፈልገኝ ደሞኮ ታውቆኝ ገበር ካስታወሽ ጠይቄሽ ገበር አንች ዋሸሽኝ እንጂ አለ

ማታ በችኮላ የሆነ ነገር እራስህ ላይ እነሰዳታደርግ ስለፈራሁ ነው ያን ሁላ ውሸት የቀባጠርኩት እንጂ የምሬን አደለም ልጁ የልዑል ነው የሌለ ነገር ስላወራሁ ይቅርታ አድርግልኝ ቻው ብዬ ዘጋሁበት።

መልሶ ደወለ
በቃ ውሸቴን ነው አልኩህ አደል እየደወልክ አትጨቅጭቀኝ አልኩት ።
እሱ ግን ምንም ሳያፍር ማታ ያንን text ስልክልሽ  ካንቺ የጠበኩት 1 ነገር ያንተ ልጅ ነው ለልጅህ ስትል ኑርለት እንድትይኝ ነበር ያልኩት አልቀረም  የጠቀኩትን text ላክሽልኝ አንቺ በዛ ፍጥነት ከልዑልጋ  አብረሽ አድረሽ ልታረግዢ አትችይም አቅሻለሁኮ አለኝ ።
የዛኔ በጣሞ ተናደድኩ ታዲያ ምን ይጠበስ ልጁ ያንተ  ቢሆንስ ምን አገባህ በቃ እኔም ልጄም እንደሞትን ቁጠረው ልዑሌ ነው አፍርሶ የሰራን ትናት ምክንያትህን እንኳን ንገረኝ እያልኩ  ስለምንህ ዞረህ እንኳን አላየኸኝምኮ ቢያንስ አባቴ እንዲህ እንዲህ አለኝ ለትንሽ ጊዜ እንለያይ አብረን መፍትሄ እንፈልግ መች አልከኝ  ።
የ6 አመት ፍቅሬን እንደቆሻሻ አውጥተህ ጣልከው መች ለኔ ስሜት ተጨነክ ያንን ሁላ ሴት አጠገቤ እያመጣህ ስትስም ስትለፋደድ አልነበር ዛሬ ደርሶ ምን አፍቃሪ አፍቃሪ ያጫውትሀል ልዑሌ እየመጣ ስለሆነ ስልኬ ላይ ደግመህ እንዳትደውል እንዲደብረው አልፈልግም እኔንም ልጄኝ አትበጥብጠን አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት።
ፈጣሪ  ያክብረው ደግሞ አልደወለም ።
ማታ ልዑሌ መጥቶ እራታችንን በላልተን ባባ ተኝቶ ስለነበር ፊልም ማየት ጀመርን ስንጨርስ በረንዳ ላይ ወጥተን አንድ ጋቢ ለሁለት ለብሰን ጨረቃዋን እያየን ማውራት ጀመርን ።

ልዑሌ ምናለ ከሁለትና ከሶስት አመት በፊት ባወኩሽ ኖሮ አለኝ ።
እንዴ ለምን አልኩት ??
በቃ የዛኔ አውቄሽ ቢሆን ህይወት ላይ ተስፋ አልቆርጥም ነበር አለኝ
እንዴ ቆርጠህ ነበር እንዴ ሆ ሰው እንዴት ህይወት ላይ ተስፋ ይቆርጣል ግን ለምን እንደዛ አልክ አልኩት።

በቃ ታቂያለሽ እኔ ብዙ ታሪክ አለኝ ያልነገርኩሽ ግን አንቺንና ልጄን ከመተዋወቄ በፊት በነበረው ህይወቴ ውስጥ ተስፋ ቆርጬ ነበር ማታ ስተኛ ጠዋት ከእንቅልፌ ስለመነሳት አላስብም ነበር በየትኛውም አጋጣሚ ብሞት አይጨንቀኝም አንድም ቀን ለህይወቴ ሰግቼ አላውቅም ነበር ።

ይቀጥላል
ከወደዳችሁት like ካልተመቻችሁ dislike አድርጉ
share እያደረጋችሁ ቻናሉን
ምርትና አግልግሎቶን ለማስተዋወቅ ያናግሩኝ !!!
አሁን ግን በቃ እኔጃ ብቻ ላንቺ ቃል የለኝም ብሎ አቅፎ ሳመኝ ትንሽ ከቆየን ቡሀላ ወደውስጥ ገብተን አረፍ አልን ።
ያው ባባ ቀን ቀን ስለሚተኛ ሌሊት በጣም ያስቸግራል አንዴ እኔ አንዴ ልዑሌ እየሆንን እንይዘዋለን ።
ዛሬ ግን ልዑሌ እንቅልፍ ስለወሰደው ብቻዬን ባባን አቅፌ ማጫወት ጀመርኩ እንደለመደው ሌሊት አካባቢ ላይ ማክቤል ደወለ ዝም ብዬ አንስቼ ስልኩን ጆሮዬ ላይ አደረኩት እልም ያለ ጫጫታ ውስጥ ነበር።
ዝም ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ ።
አፉ ሁላ ተሳስሮ ነበር ።
ህይወቴን በሰላም እንድኖርና የድሮውን ማክቤልን ማግኘት ከፈለግሽ ላንዴ ብቻ ልጄን አሳይኝ ምን እንደሚመስል አንዴ ብቻ ነው ማየት ምፈልገው ከዛ ቡሀላ አጠገብሽ አልደርስም አለኝ ።
አላስቸግርሽም ካንቺ እርቄ አባቴንና እራሴን የሚጠቅም ስራ እሰራለሁ መጀመሪያ ግን አይኑን አሳይኝ አለ ።

ዝም ብዬ ስልኩን ዘጋሁትና text ፃፍኩለት አሁን ወደቤትህ ግባና ሲነጋ እናወራለን አልኩት ።

ጠዋት እኔ በተራዬ እንቅልፍ ጥሎኝ ባባን እያጫወተው የነበረው ልዑሌ ነበር ስነቃ ቁርስ ቀርቦ እኔን እየጠበቁ ስለነበር ተነስቼ ተጣጠብኩኝና አብረን ቁርስ በላን።

ልዑሌ ወደስራ ሄደ እኔ ቁጭጭ ብዬ tv እያየሁ ማክቤል ደወለ ማታ ያወራነውን ምን አሰብሽ ቃል እገባልሻለሁ ላንዴ ብቻ ነው አይኑን ማየት ምፈልገው ከዛ ድጋሜ አላስቸግርሽም ቃሌ ነው አለኝ።

እሺ አልኩት በቃ ዛሬ ከሰአት ቡሀላ እንገናኝ የት ነው የሚመችሽ አለኝ ።
እኔ ሰፈር እመጣለሁ እዛው እንገናኛለን እደውልልሀለሁ አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት እውነት ለመናገር ብዙ ሰአት ከራሴጋ ታግያለሁ ግን ቢያንስ እሱ ሚቀየር ከሆነ ላንዴ የልጁን አይን ባሳየው ችግር የለውም ብዬ አሰብኩ ።


🔻ክፍል ሀያ ዘጠኝ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣7️⃣

ቡናችንን ጠጣተን : ምሳችንን በላልተን ቀኑን ሙሉ ጨዋታው እንደደራ አመሸንና ወደ 11 ሰአት አካባቢ ወደቤታችን ለመሄድ ወጣን።

ባባን ልዑሌ ነበር ያቀፈው ወደመኪናችን ልንገባ ስንል ልጁን ለኔ ሰጠኝና በዛው ግንባሬን ሳምምም አደረገኝ ።


ወደመኪናችን ገብተን እየሄድን ድንገት ዞርስል ማክቤል በመብራት ፖል ተደብቆ እያየን ነበር::
አስተያየቱ እንደነፍሰ ገዳይ ነው ።
በጣም ያስፈራ ነበር ባላየ ፊቴን አዞርኩኝ።
ከባባጋ እየተጃጃልኩ ልዑሌ ደሞ ዝም ብሎ እኔን እያየ እየሳቀ መንገዳችንን ቀጠልን በነገራችን ላይ የባባ ስም ማን ይመስላችኋል(ዛብሎን ነው ልዑሌ ነው ስሙን ያወጣለት ከኔጋ ይኖራል ማለት ነው) ለምን እንደዛ እንዳለው ባላውቅም የልጄ ስም ግን ዛብሎን ነው እውነት ለመናገር ደስ የሚልና ለየት  ያለ ስለሆነ እኔም ወድጄዋለሁ።

ቤታችን ከደረስን ቡሀላ ሁላችንም ደክሞን ስለነበር ለመተኛት እየሞከርን ነበር ባባ ግን እንቢ አለኝ አንዴ እኔ አንዴ ልዑሌ እያጫወትነው ቆየን ከሌሊቱ 6ሰአት አካባቢ ስልኬ ተደጋጋሚ ጊዜ እየጠራ ነበር ከማክቤል እንደማይዘል ስለገባኝ ቼክ አላደረኩትም ነበር ።
ልዑሌ አይቶ እንዳላየ ዝም አለኝ ሳይለንት አደረኩት ።
ትኝሽ ቆይቶ ባባ ሲተኛ ልዑሌም አብሮት ተኛ የዛኔ ስልኬን አንስቼ ሳየው እውነትም ማክቤል ነበረ 26 ጊዜ ደውሏል ።
10 text ልኮልኝ ነበር ።
መጀመሪያ እንደለመደው እየተጃጃለ ስለመሰለኝ ያን ያህል ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር  textochun ማንበብ ጀመርኩ ።
ema
Enate
Selam
አፈቅርሻለሁ
ናፍቀሽኛል
.........
...........
..........
የመጨረሻው ላይ ተስፋዬ ይሙት(ተስፋዬ አባቱ ነው)
ከዛሬ ጀምሮ አይኔን አታይኝም ካባቴም ካንቺም ካልሆንኩ ማንአለኝ ብዬ እኖራለሁ እራሴን ነው ማጠፋው የዛኔ አንችም ሰላምሽን ታገኛለሽ አባቴም ልጅ አለኝ ብሎ ተስፋ ማድረጉን ያቆማል ለነገሩ አሁንም ተስፋ ቆርጦብኛል ::

አባቴን ባየሁት ቁጥር እንደዛ ሆኖ አሳድጎኝ ዛሬ ባንቺ ምክንያት እንደዚህ ክብሩን ሳሳጣው ያናድደኛል

አንቺን ሳይሽ ደሞ ምናለ የዛኔ አባቴን እንደምንም ብዬ ባሳመንኩት አንቺን ጨክኜ ብመርጥ ኖሮ አባቴ ደስተኛ መሆኔን ሲያይ ሀሳቡን ይቀይር ነበር እላለሁ።
በመሀል ቤት እኔ ባክኜ ቀረሁ ሰላም አንቺ ከኔጋ እንደተለያየሽ ድጋፍ እንዲሆንሽ እንዲያፅናናሽ ልዑልን ላከልሽ ቆይ ለኔስ እእእ ብቻዬን ወይ አልሞትኩ ወይ አልዳንኩ ።
በየቀኑ እየጠጣሁ  እየሰከርኩ አባቴን ከማሰድብ እሱ ከማሳዝን አንችም ባየሽ ቁጥር ከምትሳቀቂ በቃ ቻውውውው:::

textun እንዳነበብኩ እጄ ተንቀጠቀጠ ወደ መታጠቢያ ቤት ገብቼ ደወልኩለት አያነሳም ደግሜ 2/3 ጊዜ ደወልኩ አያነሳም ።
እንደምንም እራሴን አረጋጋሁን text ፃፍኩለት ።
አረ እንደዚህ አታስብ አሁንም ድረስ ለኔም ላባትህም ታስፈልገናለህ ብዬ ላኩለት መልስ የለም።
ደግሜ አሁኑኑ ደውልልኝ በጣም ፈልጌህ ነው ??
አይመልስም ።
የዛኔ የምር የሆነ ነገር የሆነ መስሎኝ ነበር ከመደንገጤ ብዛት ምን እየፃፍኩ እንደነበር እራሱ ማሰቢያ ሰአት አላገኘሁም ።
ብቻ ማክቤል ቢያንስ ለልጅህ ስትል መኖር አለብህ ዛብሎን ያንተ ልጅ ነው ካንተ ስላረገዝኩ ነው ልዑሌ እንደዛ በተፋጠነ ሰርግ ያገባኝ ቢያንስ ለሱ ስትል ኑርለት አልኩት።

መልስ አልሰጠኝም ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር 12 ሰአት ሆነ ።
ዝም ብዬ ተነስቼ ልብሴን ቀየርኩና ከክፍላችን ወጣሁ ።
ለማንም ሳልናገር ስልኬንና የትራንስፖርት ብርብቻ  ይዤ ወጣሁ ።

ቀጥታ ወደነ ማክቤል  ግሮሰሪ ሄድኩኝ ዝግ ነው
ወደቤታቸው አመራሁ ከየት የመጣ ድፍረት እንደሆነ ባላውቅም በሩን በሀይል ደበደብኩት አባቱ መተው ከፈቱልኝ ሲያዩኝ በጣም ደነገጡ የሞት መልአክ እንጂ ሰው ያዩ አይመስሉም ነበር ።

እየተንተባተብኩ ይቅርታ ፋዘር ማ ማ ማክቤልን ፈልጌው ነበር ቤት ነው እንዴ  አልኳቸው ።

አዎ የኔ ልጅ ምነው ይሄን ያህል አስቸኳይ ነው እንዴ ልቀስቅስልሽ ሌሊት ሰክሮ እየተዘላገደ ነው የገባው ነይ ግቢና አንቺ ቀስቅሽው በዛውም ትንሽ መክረሽው ትሄጃለሽ አሉኝ።
የዛኔ ልክ ትልቅ ሸክም ከትከሻዬ ላይ እንደተነሳልኝ ነገር እፎይ አልኩኝ ።

አይ አባባ አመሰግናለሁ ይተውት በቃ ይተኛ ቡሀላ እደውልለታለሁ ብዬ መልሳቸውን እንኳን ሳልጠብቅ ፊቴን አዙሬ በፍጥነት ከዛ አካባቢ ሄድኩኝ ።
ወደቤት እየተመለስኩ ልዑሌ ደወለ ።
ሰላሜ የት ሄደሽ ነው በዚህ በጠዋት አስደነገጥሽኝኮ ??
ይቅርታ ልዑሌ መጥፎ ህልም አይቼ ስለነበር ባባ ሳይነሳ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ልምጣ ብዬኮ ወጥቼ ነው መጣሁ አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት ::

ወደቤት ስደርስ ልዑሌ አይቶኝ በጣም ደነገጠ እንዴ ሰላም አብደሻል እንዴ እንደዚህ ሆነሽ ነው ቤተክርስቲያን ሄድኩ ምትይኝ ወይስ ምንድነው አለኝ ።
አረ ልዑሌ ከእንቅልፌ ስነቃ በጣም ደንግጬ ስለነበር ምን እንደለበስኩ እራሱ አላስተዋልኩትም ነበር  ልክ ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ደርሼ ከተሳለመኩ ቡሀላ ነው የታወቀኝ አልኩት።

አይንሽ እራሱ ቀልቷልኮ አሞሻል እንዴ ??
አይ እየቃዠሁ ስለነበር ለዛ ነው በቃ ትንሽ እንቅልፍ ልተኛ መሲን ባባን አጫውችው በላት ብዬው አልጋው ላይ ተዘረርኩ ።
ልዑሌ ያወራሁት ያደረኩት ምንም አልተዋጠለትም ግን ዝምምም አለኝና ባባን አቅፎ ከክፍል ወጣ ።
ሌሊቱን ያልመጣው እንቅልፌ የማክቤልን ደህና መሆን ከሰማ ቡሀላ  ባንዴ መጣብኝ .....

🔻ክፍል ሀያ ስምንት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣6️⃣

ከሌሊቱ 9 ሰአት  አካባቢ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ አደረኩኝ ።

ልዑሌን ዝም ብዬ ሳስበው እንባዬን ያመጣዋል ሰው እንዴት በዚህ ልክ ይፈጠራል ልቡ ከምንድነው የተሰራው ሌሊቱን ሙሉ ከናቴ በላይ ሲጨነቅ አደረ

የሱ ያልሆነን ልጅ የኔ ነው ብሎ ተቀበለ ከዛም ብሶ ደሞ ልክ ልጄን ሲያየው እንደሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ።
ሰው እንዴት በዚህ ልክ ሰው ይራባል ።
እንዴት በዚህ ልክ የሰው ፍቅር ይኖረዋል ።
ብቻ በሰላም ስለተገላገልኩ ዛሬን ውለሽ መውጣት ትችያለሽ ተባልኩ  ።

ሁላችንም ደስ አለን ታቃላችሁ ግን ምድር ላይ እናት እንደመሆን ያለ ፀጋ  ደስታ አለም የለም ።
እውነት ለመናገር እኔ እናት የመሆን ያን ያህል ጉጉት አልነበረኝም ላስወርደው ሁላ ነበር ፈጣሪ ስላልፈቀደው ሳይሆን ቀረ እንጂ አሁን ልክ እቅፌ ውስጥ ሆኖ ሳየው ግን አደለም ለማስወረድ ሳቅፈው ሁላ እፈራለሁ ።
መሲ ቤቱን ከሚባለው በላይ ፏ አድርጋ ግቢው ሳይቀር በቄጤማ  አስውባ ጠበቀችን እናቴ ልጄን አቅፋ ወደቤታችን ገባን ።

እናትነት ሀ ተብሎ ተጀመረ ማለት ነው። ልዑሌ አይኑን ከልጁ ላይ መንቀል አልቻለም ብቻችንን እስክንሆን ጠብቆ ሰላም ምናለ ይሄን ልጅ ከኔ ቢሆን የወለድሽው እኔም ሰው እሆን ነበር ።

ፈጣሪ ለ1 ቀን አባት መሆንን ቢያሳየኝና በነጋታው ብሞት አይቆጨኝም አለ እያለቀሰ

አረ ልዑሌ ቆይ ይሄ ልጅህ አደለም ማለት ነው ካሁኑ አባቱ አለመሆንህን እያሳወክ ነው እእ አንተ ባትኖርኮ እሱ አይወለድም ነበር ቢወለድም ጎዳና ላይ ነበር ።
አንተ አደለህ እንዴ የሞቀ ቤት እንዲገባ ያደረከው አልኩት ።
ልክ ነሽ ሰላም ልጄ ነው  አለኝ።

ደሞ እንዳንተ ቆንጆ ነው ልጃችን እንዳንተ እንዲሆን ነው ምፈልገው ቆንጆ ጥሩ ልብ ያለው ሀብታም ልክ እንዳንተ ውስጡ ነፁህ እንዲሆን ነው ምፈልገው ብዬ እቅፍ አድርጌ ሳምኩት ።
በጣም ደስ አለው እናቴ በቃ ትንሽ እረፍት አድርጊ አለችኝ  በነገራችን ላይ ብዙ እናቶችን ሚገጥማቸው ግን ደግሞ ማያስተውሉትን ነገር ልንገራችሁ።


ብዙ እናቶች ልጆቻቸው ጡታቸውን ስለሳቡት ብቻ እየጠቡ ያለ ይመስላቸዋል
እኔም ዝም ብሎ ጡቴን ሲስበኝ እየጠባ እንደሆነ አስቤ ነበር ግን ገና ጡቴ አልፈነዳም ነበር የዛኔ ሌሊቱን ሙሉ ሲያለቅስ አደረ በነጋታው ጠዋት ላይ እናቴ ገንፎ ካልበላሽ አለችኝ እኔ ደሞ በተፈጥሮ ገንፎ አጥሚት ሚባል ነገር አልወድም ።
ይሄን ካልበላሽ ጡጥትሽ ወተት አይኖረውም አለችኝ የዛኔ ቼክ ሳደርግ እውነትም ጡቴ ምንም ወተት አልነበረውም ዝም ብዬ ነበር ለካ እየጠባ የመሰለኝ ያው ልዑሌ ተሯሩጦ ከአራስነት ጀምሮ ሚወሰድ ወተት ገዝቶ መጥቶ ሰጠነው እስከ 3ኛው ቀን ጡቴ አልፈነዳም ነበር።

እና እማዬና መሲ ሆነው አንቀባረው አረሱኝ እናቴ ከስራ ያመት ፍቃድ ጠይቃ ስለወጣች ሁሌም እኔጋ ነው ምትሆነው

15 ቀን ምናምን ከሆነኝ ቡሀላ እናቴ ለክርስትናው ጠላ መጥመቅ ጀመረች ።
በነገራችን ላይ ከወለድኩ ጀምሮ ማክቤልን አውርቼው አላውቅም ቢያንስ በቀን 3/4 text ይልክልኛል በየደቂቃው ይደውላል ሲሰለቸኝ ስልኬን ወጋዋለሁ።
ያላወራሁት አንደኛ ልዑሌ ሁሌ አብሮኝ ነው እናቴም እንደዛው
በዛ ላይ እናት ከሆንኩ ቡሀላ ሻወር ወስጄ እስክወጣ እራሱ ልጄ ይናፍቀኛል ዝም ብዬ አይን አይኑን እያየሁ ስስቅ ነው ምውለው ።
ማክቤልን የማስብበት ትርፍ ሰአት የለኝም

እና እንዲያ እንዲያ እያለ ክርስትናችን8 ደረሰ የተጋነነ ድግስ ባይሆንም ቆንጆ ድግስ ተደገሰ እኔና ልዑሌ አንድ አይነት ልብስ አሰርተን አበባ መስለን ልጃችንን ለቅዱስ ሚካኤል ሰተን
ክርስትናችንን አሳለፍን ህዝቡ ክርስትና ሲጠራ መጥቶ በክብር በልቶ ጠጥቶ ከመሄድ ይልቅ አርግዛ ነው እንዴ የተጋቡት ከመቼው ወለደች የሚለው ነገር ነው ሚያሳስባቸው ።

የናቴ ጓደኞች እንኳን ስለምኖርበት ቤት እንጂ የኔ ቶሎ መውለድ ያሳሰባቸው አይመስልም ።
አንዷ ትጠራኝና ስንት ሆናችሁ ነው ምትኖሩት ትለኛለች ሌላኛዋ አስከትላ ግን ቤቱን ሙሉ ዞሬ ልጎብኝ ብል መቼ እጨርሳለሁ ትቀጥላለች ሌላዋ ደሞ አስቲ8 የኛንም ከረፈፍ ልጆች ይሄንን አስማትሽን ንገሪያቸው እዛ ከየሰፈሩ ዱርዬጋ ከሚዘላዘሉ እንዳንቺ አንዱን ሀብታም አግብቶ የኛንም ታሪክ ይቀይሩት ልጅስ ከወለዱ አይቀር እንዳንቺ ነው ይሉኛል ።
በዛ ሰአት እናቴ ኩራት ሲሰማት ፊቷ ላይ የደስታ ሳቅ ሲንቀለቀል አያለሁ የሷን ደስታ ሳይ እኔም ደስ ይለኛል ።
ክርስትናችን በቆንጆ ሁኔታ አለፈ ።
ልዑሌ የደስታ ጥግ ላይ ደርሶ ነበር ደስታ እንደሚያሰክር  በሱ ነው ያየሁት።

እኔና መሲ ባባን አጣጥበን አስተኛነው
አንዴ ከተኛ ደግሞ አይነቃም ሌሊቱን ግን ቁጭ ብሎ ነው ሚያድረው ።

ከመሲጋ ቁጭ ብለን እያወራን ልዑሌ መጣ ።
ልጄ ተኝቶ ነው ብሎ ገብቶ አየውና አንዴ ላወራሽ እፈልጋለሁ የኔ መኝታ ቤት ነይ አለኝ ።
መሲን እያየሽው ጨርቅ ነገር እንዳያፍነው ብያት እኔ ወደውስጥ ገባሁ።

ምነው ልዑሌ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ አልኩት።

አይ የለም ግን ሰላም ልጅ እንድትወልጅልኝ እፈልጋለሁ ።
ሳቄ መጣ ይኸው ወለድኩልህ አደል አልኩት ።

ጉንጮቼን በእጁ እየዳበሰ ሰላም አልቀለድኩም ከምሬ ነው ውለጅልኝ ።
ባባን ልጄ አደለም እያልኩሽ አደለም ግን በቃ ውለጅለኝ እሱን ባየሽ ቁጥር እኔን ታስታውሽኛለሽ  አለኝ።
ቆይ ልዑል ምን ሆነሀል አንተ የት ትሄዳለህ አልኩት ።

የትም እኔ ስራ ስሄድ እንዳልናፍቅሽ እሱን ታያለሸ ለማለት ያህል ነው ብሎ ፈገግ አለ

ሁለተኛ እኔ በሌሌለሁ ጊዜ የሚባለውን ነገር ብታነሳ ልዑሌ ሙት ትጣላኛለህ እንዴ ቆይ  ከኔጋ የመቆየት የመኖር ሀሳብ የለህም እንዴ ትተኸኝ ስለመሄድ ታስባለህ   እንዴ ቆይ እኔና አንተ በምን ልንለያይ እንችላለን ሳላስበው እንባዬ ወረደ አቅፎ አባባለኝ   ሳመኝ ሁለታችንም ወደንና ፈቅደን ለመጀመሪያ ጊዜ ከልዑሌጋ አንሶላ ተጋፈፍን ።
ከዛ ቡሀላ ኖርማል ባልና ሚስትነታችንን አወጅን።

ቀኑ እሁድ ነበር እናቴን ለማየት  መሲንም ጨምሮ ሰብሰብ ብለን በነጭ ልብስ አጊጠን ወደናቴ ቤት ሄድን ።
K

🔻ክፍል ሀያ ሰባት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣5️⃣

ልዑሌ በጣም ከጠበኩት በላይ መረበሹ ግራ አጋባኝ ።
መኪናውን እየነዳ ምንም ከራሱጋ አልሆን አለ አስሬ ልዑሌ ተረጋጋ ልዑሌ ተረጋጋ እለዋለሁ እሱ መስሚያው ጥጥ ነው መጨረሻ ላይ በጣም ጮክ ብዬ ልዑል መኪናውን አቁመው አልኩት ።
ደንግጦ ጥጉን ይዞ ቆመ እንዴ ምን ሆነሀል ቆይ እንዴ ???

በእርግጥ አዎ ታሳዝናለች ግን እርጉዝኮ ነኝ እንዴት እንደዚህ ትነዳለህ አልኩት እየተበሳጨሁ!!
ታቂያለሽ ቁስሌን ነው የነካችው አፍቅሮ ማጣት በዛ ላይ ቤተሰብሽ ካጠገብሽ ሳይኖር ለዛውም ያፈቀርሽውን ሰው የገደለው አባትሽ ሲሆን በጣም ይከብዳል አለኝ??

ልዑሌ ምን ማለትህ ነው እንዴት ነው ቁስልህን የነካችው ካንተጋ ምን አገናኘው ??

ምንም ሰላሜ እንሂድ በቃ ይቅርታ ካስደነገጥኩሽ አለኝና መኪናውን መንዳት ጀመረ ።

ላስጨንቀው ስላልፈለኩ ዝም አልኩ በመሀል ስልኬ ጠራ ሳየው ልቤ ትርትር አለ ማክቤል ነው የደወለው የእህቴ ፍጥነት አስገረመኝ ከመቼው ስልኬን ሰታው ደወለ እያልኩ ዝም ብዬ እስኪዘጋ ጠበኩ።
ልዑሌ ለምን አታነሽውም አለኝ
አይ እማዬ ናት እስካሁን አልገባንም ከምላት ቤት ስገባ አንዳፉን እደውልላታለሁ ብዬው ዝም አልኩኝ
ድጋሜ text ገባልኝ ከማክቤል ነበር
አሁንም ድረስ አልቆረጠልሽም አደል ይላል ።

አነበብኩትና ብቻዬን ፈገግ አልኩ ልዑል ዞር ብሎ አየኝና ዛሬ ደሞ ብቻሽንም የሚያሲቅ text ይገባልሻል ባክሽ አለኝ ።
ምን ባክህ እህቴኮ ናት text እያለከች ምታስቀኝ ይቺ እብድ የሆነች ልጅ ምን እንደሚሻላት ብዬ አስቀየስኩ ።

ቤት ከደረስን ቡሀላ ልዑሌ ገና ከመኪና እንደወረደ መሲን ጭምቅ አድርጎ አቀፋት
በጣም ከመደንገጧ የተነሳ እኔ ላይ አፈጠጠችብኝ
አይዞሽ ጠንካራ ሁኚና ታሪክሽን ነበር ብለሽ ለማውራት ያብቃሽ ብሏት ወደ ውስጥ ገባ ።

ተከትለነው ገባን ።
ልዑል ቀጥታ ገብቶ ተኛ እኔም ገብቼ ለማክቤል text ፃፍኩለት
እስከ 6 ሰአት ድረስ ስናወራ ቆየን ሁለተኛ እንዳያመሽ እንዳይጠጣ ቤት እንዲገባ ካባቱጋ እንዳይጣላ ቃል አስገባሁት ።

ከ6 ሰአት ቡሀላ በጣም ስለደከመኝ ተኛሁ
ጠዋት ልዑሌ ስራ ከመሄዱ በፊት ቀሰቀሰኝ ምነው ማታ አመሸሽ እንዴ እንዴት እስካሁን ቆየሽ አለኝ ።

አረ አላመሸሁም ልዑሌ ብዬ ግግም አልኩኝ።
አብረን ቁርሳችንን በልተን ወደስራው ሄደ።
እሱን ተሰናብቼ ወደ ስልኬ ሮጥኩኝ ማታ ካቆምንበት ቀጠልን ከማክቤልጋ 
እያወራን ሰፈር ካልመጣሽ ወይ ደሞ እናንተ ሰፈር ልምጣና ልይሽ አለኝ
እኔ በፍፁም ብዬ ግግም አልኩኝ ።

የተወሰነ ካወራን ቡሀላ ማውራቱ እራሱ አስጠላኝ ድክምክም አለኝ በዛ ላይ በየሰአቱ ስለሚርበኝ ቶሎ ቶሎ ነው ምበላው ።

ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ ልዑሌ ደውሎ ውጪ ምሳ መብላት ከፈለኩ ጠየቀኝ ?
አይ ቤት መተህ አሪፍ ጊዜ እናሳልፋለን ቤት ጠብቅሀለሁ አሁን ወሬ ስለገባ ወጣ ወጣ ማለቱ ለኔ ጥሩ አደለም አልኩት ።

እሺ በቃ መጣሁ ከመሲጋ ቤቱን ፏፏ አድርጋችሁ የበአል ድባብ ፍጠሩና ጠብቁኝ ብሎ ስልኩን ዘጋው ።

እኔና መሲ ቤታችን ስናዘገጃጅ እሷ ስትሰራ እኔ ከስር ከስሯ እየተከተልኩ በወሬ ሳግዛት ቆየን ልዑሌ ብዙ ሚበላሉ ምግቦችን ገዛዝቶ መጣ ።

ገና ከውጪ ሲገባ ድባቡን ሲያየው በጣም ደስ አለው እኔን መሲን አቅፎ ሳመን ።

ምሳችንን እየበላን ስልኬ አስሬ ይደወላል ማክቤል እንደሆነ ስለገባኝ እኔ ዝም አልኩኝ ልዑሌ ግን ስልክሽኮ እየጠራ ነው አታነሺውም እንዴ አለኝ ።

ተነስቼ ሄድኩኝ የማክቤልን ስልክ ዘግቼ ወዲያው ወደናቴ ደወልኩና ምሳኮ እየበላን ሆኖ ነው ከልዑሌጋ ምናምን ብዬ ቀባጠርኩ ።
ስልኬን ሳይለን አድርጌ አስቀምጬው ወደ ምሳችን ተመለስኩ።
ምሳ በልተን እንደጨረስን መሲ ቡና እያፈላች እኛ ቁጭ ብለን ወሬያችንን እያወራን ቆየን
ልዑሌ በቃ ስራ እንዳይረፍድብህ ሂዳ አልኩት ።
አይ ሰላሜ አልሄድም ባክሽ ቢሮ የነበረኝን ስራ ጨራርሼ ነው የመጣሁት
ደሞ አንቺን ካገባሁ ቡሀላ ቢሮ መሆን እራሱ እያስጠላኝ ነው ባገኘሁት አጋጣሚ በሙሉ ወደቤት መምጣት ነው የሚያሰኘኝ።
ሰላም አታምኚም በፊትኮ እዚህ ቤት ምገባው ለመተኛት ብቻ ነበር  ።
ቢሮ እስከ 2/3 ላመሽ እችላለሁ ከዛ ስወጣ ደሞ እራት ልበላ እሄዳለሁ
እራቴን በልቼ ወደቤት መምጣት ከደበረኝ እዛው room ይዤ ላድር እችላለሁ ወደቤቴ እንድመጣ የሚያጓጓኝ ምንም ነገር አልነበረም እንደውም ይጨንቀኛል እረጅም ሰአት ቤቴ ስቀመጥ።

አሁን ግን በቃ ውጪ ስሆን ነው ሚጨንቀኝ ቤቴን እንድናፍቅ ስላደረግሽኝ አመሰግናለሁ የኔ ሚስት ብሎ ግንባሬን ሳም አደረገኝ መሲ እያየችን ፈገግ ትላለች።

እኔም አመሰግናለሁ ጉድለቶቼን ሳታይ ስለወደድከኝ ስላከበርከኝ ቀዳዳዎቼን በሙሉ ስለሞላህልኝ አመሰግንሀለሁ ።

ትናት አንተ ወደ ህይወቴ ባትመጣ ኖሮ እኔ ዛሬ የት እንዳለሁ አላውቅም ነበር እኔንም ልጄን በርህን ከፍተህ ባትቀበለን ኖሮ እስካሁን በህይወት የመኖራችን ነገር እራሱ ጥያቄ ውስጥ ይገባ ነበር አልኩት።

ቡናችንን ጠጥተን ጨራርሰን ቀጣዩ ምሽታችንን እንዴት ብናሳልፍ እንደሚሻል እያሰብን እያለ የማላቀው ስሜት ተሰማኝ ለመነሳት እየሞከርኩ አቃተኝ ባንዴ ሆዴ ግልብጥብጥ አለ  ጮኩኝ ስሜቱ ይሄ ነው ብዬ ማውራት አልችልም ልዑሌ ደነገጠ ከመሲጋ እንደምንም ደግፈው መኪና ውስጥ አስገቡኝና ክትትል ወደማደርግበት ሆስፒታል ወሰዱኝ ።

በጣም ሲያመኝ ደንግጬ ልዑሌን እናቴጋ ደውልልኝ እናቴጋ ደውልልኝ እያልኩ ጮኩበት ።
ሆስፒታል ከደረስን ቡሀላ ዶክተሯ ቼክ ካደረገችኝ ቡሀላ ማህፀንሽ ገና አልከፈተም አለችኝ
እኔ መቋቋም ምችልበት ሁኔታ ውስጥ ስላልሆንኩ ማህፀኔ ካልከፈተ ኦፕራሲዮን አድርጊኝ እኔ ይሄንን ህመም መቋቋም አልችልም አልኳት ።
ዶክተሯ ግን በፍፁም አለች ጤነኛ ሆነሽ ማማጥ ምትችይበት ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ እንዴት ኦፕራሲዮን አደርግሻለሁ አለች።

ህመሙ እየጨመረ እየጨመረ ሄደ እዛው መሸ ልዑልም እናቴም መሲም እዛው ነበሩ ።

ሆስፒታል ማደር የሚችለው 1 ሰው ነው ግዴታ ከሆነ ደግሞ እናቷና ባሏ ናቸው ማደር ሚችሉት ተባለ ልዑሌ በዛ በምሽት መሲን ቤት አድርሷት ተመልሷ መጣ ።
 
በህይወቴ እንደዛ ምሽት አስጨናቂ እረጅም ሌሊት አልነበረም


🔻ክፍል ሀያ ስድስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣4️⃣

እውነት ለመናገር ምንም የማለት ድፍረቱን አላገኘሁም ::
ዝም ብዬ ተነስቼ ወጣሁ አልተከተሉኝም ነበር።
ወደናቴ ቤት ሄድኩኝና ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ጭንቀት: ድብርት: ሀሳብ የሰፈነበት መኝታ ነበር ።

እናቴ የሰሞኑ ሁኔታሽ ምንም ደስ አላለኝም ያስጨነቀሽ ነገር አለ እንዴ አለችኝ ።
እኔ ምንም የለም ብዬ ሽምጥጥ አደረኳት።
ልዑሌ ደውሎ ቤት ልምጣ እንዴ ቢሮ ስራ የለኝም አለ ??
አይ እኔ እናቴጋ ሄጃለሁ ቤት አደለሁም አልኩት ??
በዛውም ማዘርን  አያቸዋለሁ በቃ መጣሁ አለኝና ቤት መጣ ፈጣሪ ይወቀው ለምን እንደሆነ ግን አንዳንዴ ሳየው ልዑል ያናድደኝ ጀምሯል ።

ስለማክቤል ከሰማሁ ቡሀላ ትክክለኛ ስሜቴ ምን እንደሆነ ለማወቅም እየተቸገርኩ ነው ።

ልዑል ቤት ሲመጣ ድምፁን ስሰማ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው አይኔን ጨፈንኩ በቃ ይለፍላት ትተኛ ብሎ በሩን ዘግቶ ከክፍሌ ወጣ።
ሁኔታዬ ለራሴም አስጠላኝ ግራ አጋባኝ ቆይ ልዑል ምን አደረገ ብዬ እራሴን ጠይቃለሁ??
መልሱ ምንም አላደረገም ከውርደት ነው ያዳነሽ የቤቱንም የልቡንም በር ነው የከፈተልሽ የሚል ሆኖ አገኘዋለሁ ።

ልዑሌ እና እናቴ የሞቀ ጨዋታ ይዘው እየተጫወቱ ሳቃቸው  ይሰማል ።
እኔም ልቀላቀላቸው ብዬ ተነስቼ ወጣሁ እየተጫወትን እህቴም መጣች ቤተሰቡ ሰብሰብ ብሎ ሲጫወት እናቴ በጣም ደስ አላት ።
ሲመሽ እኔና ልዑሌ ወደቤት ለመሄድ ወጣን ።
እህቴን ለብቻዋ ጠራኋትና አዲሱን ቁጥሬን ለማክቤል እንድትሰጠው ነገርኳት ግን ለማንም እንዳትናገር አስማልኳት ።

ወደ ቤት እዬሄድን አስር ጊዜ አረ መሲ ብቻዋን እቤት ይደብራታል እለዋለሁ።
ቆይ ምንድነው ከዚች ልጅጋ እንደዚህ የተቀራረብሽው አለኝ ልዑሌ ።
አረ ብታይ ታሪኳንኮ ብታውቅ እንደዚህ አትልም ነበር እንዴት እንደምታሳዝን ።
ንገሪኛ ምንድነው አለኝ ???
እየውልህ መሲ ሀገሬው ላይ ከበርቴ ከሚባሉ የሀብታም ቤተሰቦች ነው የተገኘችው ።
በነሱ ሀገር ባህል መሰረት ደግሞ የሀብታም ቤተሰብ ከሆንክ የምታገባው ሰውም ሀብታም መሆን አለበት።

መሲ ደሞ አንድ ቀን ታቦት ለማንገስ በሄደችበት አንድ ወጣት አይታ በፍቅሩ ወደቀች ።

ከቤተሰቦቿ እየተደበቀች ውሀ መቅጃ  ምን ምን እያለች ምክንያት እያበዛች በድብቅ እሱን ማግኘት ጀመረች ተዋደዱ ማለት ነው እንግዲ።

በዛ መሀል እሷ ቤተሰቦችጋ ሌላ ሰው ሽማግሌ ላከ ያው ሽማግሌ የላከው ልጅ የሀብታም ልጅ ስለሆነ እሺ አሉ ቤተሰቦቿ
መሲ ግን እኔ እሱን አላገባም እራሴ ለምፈልገው ሰው ዳሩኝ ብላ የምትወደውን ልጅ አስተዋወቀቻቸው ።

ቤተሰቦቿ ግን አንቀበልም አሉ ....

እንዴ ለምን እንቢ እሷ ከወደደችው አለኝ?? ልዑሌ

መሲ ምትወደው ልጅ አባት የለውም እናቱ ብቻዋን ነው ያሳደገችው ብዙ መሬትና ሀብት ስለሌላቸው የመሲ ቤተሰቦች አይፈልጉትም ።

መሲ ደሞ ከሱ ውጪ ማሰብም ማግባትም ስለማትፈልግ ከልጁጋ ተነጋግራ በድብቅ ወደ አዲሳባ ጠፍታ መጣችና ትንሽ ቤት ተከራይተው አብረው መኖር ጀመሩ ።

ከዛ የመሲ አባት ደግሞ ሄደና የልጁን እናት ገደላት ።
በተከበርኩበት አገር ልጅሽ ልጄን ይዞ ጠፋ ብሎ ገደላት(በዚህ ሰአት ልዑሌ ደንግጦ መኪናውን አቆመው)

እሺ ቀጥይ አለኝ ለመስማት ጓጉቶ አይን አይኔን እያየኝ ።

ከዛ ቡሀላ ልጁ ይሄንን ሲሰማ ከናቴ ገዳይ ልጅጋ አልኖርም አልፈልግሽም ብሎ መሲን አባረራት ።
ብትለምነውም እንቢ አለ ከጠላቴጋ አልዛመድም አለ።

ከዛ የመሲን አባት እገላለሁ ደሜን እበቀላለሁ ብሎ ጫካ ገባ ።

የመሲ አባት ይሄንን ሲሰማ ልጁን በሽፍታዎች አስገደለው ።

ከዛ በቃ መሲም ተመልሳ ወደናትና አባቷ መሄድ ስለማትችል እዚህ ሰው ቤት እየሰራች ትገኛለች።
ውስጧ በጣም የተጎዳ የተሰበረ ልጅ ናት ለዛ ነው ዝም ምትለው አልኩት።

ልዑሌ ልቡ ተንሰፈሰፈ እንባ ተናነቀው ቆይ ይሄ ምን አይነት ህግ ነው እንዴት እናትና ልጅን የገደለ ሰው በሰላም ይኖራል

የመሲ አባትኮ የሞት ፍርድ እራሱ ይገባው ነበር ።
እንዴት በ21 ክፍለ ዘመን ልጄ ለምን የመረጠችውን አገባች ተብሎ የሰው ነፍስ ያጠፋል አለኝ።

ልክ ነህ ልዑሌ በጣም ሚያሳዝን ታሪክ ነው ያላት ሁሌ ሳያት ውስጤን ትበላኛለች የተሻለ ቦታ ልናደርሳት ይገባል አልኩት።


🔻ክፍል ሀያ አምስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


እንዴት አመሻቸሁ?😌


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣3️⃣

የት ሄዶ ይሆን እያልኩ ወደናቴ ቤት ሄጄ ትንሽ ልረፍ ብዬ ልመለስ ስል የማክቤት አባት የኔ ልጅ የኔ ልጅ እያሉ ከኋላይ እየሮጡ መጡና አስቆሙኝ 5  ደቂቃ ብቻ እንዳወራቸው አጥብቀው ለመኑኝ::

ቅር እያለኝም ቢሆን እሺ አልኳቸው ወደ ውስጥ ገብተን እንቀመጥ አሉኝ እሺ ብዬ ተከተልኳቸው ወንበር አዘጋጅተው አስቀመጡኝ።

ምን ሊያወሩኝ እንደሆነ መገመት አልቻልኩም ግን አሁንም ካጠገቡ እራቂ ሊሉኝ ይሆን እንዴ???

ይቅርታ የኔ ልጅ ምን ይምጣልሽ አሉኝ
ምንም አልፈልግም እቸኩላለሁ ካላስቸገርኮት ማለት የፈለጉቱን ቶሎ ይበሉኝና ልሂድ አልኳቸው ...

እየውልሽ የኔ ልጅ እኔ ስለልጄ ላወራሽ ነበር አሉኝ ቀና ብለው አይኔን ለማየት እየፈሩ

እንዴት ብዬ አይኔን በጨው አጥቤ ፊትሽ እንደቆምኩ አላውቅም  ግን በቃ ልጄን መልሽልኝ ማክቤልና የአይኔን ማረፊያ አይኔ እያየ አጥቼዋለሁ አሉ እንባ እየተናነቃቸው።

ምነው ማክቤል የሆነው ነገር አለ እንዴ???
(እውነት ለመናገር ደንግጫለሁ )

አዎ ካንቺጋ ከተለያያችሁ ጀምሮ የበፊቱ ማክቤል የለም በስርአት አውርቶኝ አያውቅም ቤትም ሆነ ስራ ቦታ ከስንት አንዴ ብር ሲፈልግ ብቻ ነው ሚመጣው የለበሰው ልብስ እላዩ ላይ ሸቶ እንኳን አይቀይረውም ።

ልጄን አተርፋለሁ ብዬ ገደልኩት
እየውልሽ የኔ ልጅ እኔ ነኝ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ እሱ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ።
ህይወቴን በሙሉ ለፍቼ ሰርቻለሁ ልጄን ለማሳደግ ስል
የልጄ እናት በቂ ገንዘብ ስሌለኝ ከኔና ከልጄጋ በድህነት መኖር ስለማትፈልግ ብቻ ነው እኔንም ማክቤልንም ጥላን የሄደችው ።
እና ቆይ የኔ ልጅ ከኔ በላይ ገንዘብን መውደድ ያለበት ሰው አለ እኔ አንችና እሱ እንድትለያዩ ያደረኩበትና ምክንያቶች ልጥቀስልሽ
በመጀመሪያ እኔ ልጄ የራሱን ቤት በራሱ እስኪገዛ መኪና እስኪኖረው ሀብታም ከሚባሉት ደረጃ እስኪመደብ ድረስ ጠንክሮ እንዲሰራና እንደሱ ሀብታም የሆነችውን መርጦ አግብቶ እኔ እሱን ባሳደኩበት መንገድ ሳይሆን በተለየ መንገድ ነው ልጆቹን እንዲያሳድግ ምፈልገው

ሁለተኛ በቃ ስራ ስራ ነው ማክቤል ብዙ ጊዜ እንዲሰራ ያዘዝኩትን ስራ እየተወ አንቺን ለማግኘት ይመጣል አየሽ ዛሬ ገንዘብ በመስሪያው ሰአት አንቺን አንቺን እያለ ነገ የተሻለ ሀብታም ስታገኚ ጥለሽው ብትሄጂስ ብዬ ፈራሁ

ሶስተኛ አንቺ ስንት አመት ሙሉ እናትሽ ብቻዋን ለፍታ አስተምራሽ ተምረሽ ከተመረቅሽ ቡሀላ ግን እሷ እየሰራች አንቺ የቤት እመቤት ሆንሽ በዛ ሰአት ለልጄ እነደማትሆኚው ወሰንኩ ቢያንስ እንኳን በርሽ ላይ ሱቅ ነገር ከፍተሽ ሻይ ቅጠል መሸጥ ይሻላልኮ በዚህ ወጣትነት እድሜ ስራ እስካገኝ ነው እያሉ ቤት ከመቀመጥ

ግን አሁን የታየኝ ልጄ እናንተጋ ሀብት መስፈርት አልነበረውም ፍቅራችሁ አንዳችሁ አንዳችሁን አምናችሁ ጠብቃችሁ እንድትኖሩ ያደርጋችሁ ነበር ለካ ሁሉም ሴት እንደኔ ሚስት አደለም
እኔ ይቺን ግሮሰሪ ይዤ ለልጄ ሚስትነት ስታንሽብኝ
የሀብታሞች ሀብታሙ መጥቶ በክብር አንደላቆ አገባሽ የዛኔ ነው ሁሉም ነገር የተገለጠልኝ ።

ዛሬ ከረፈደ እንደ እግር እሳት ቢበላኝ ምን ላድርግ
ግን በቃ አንድ የመጨረሻ ነገር የምለምንሽ ማክቤልን እንዴትም አድርገሽ ቢሆን ወደራሱ መልሽልኝ ሚስቱ ባትሆኚ እንኳን እህቱ ሁኚው እባክሽ የኔ ልጅ በኔ ጥፋት እሱ አይቀጣብኝ እንደው በወለደችሽ እናትሽ ይዤሻለሁ ይቺን ብቻ እሺ በይኝ አሉ እንባቸው ካይናቸው እየወረደ
ይቀጥላል ......
ምርትና አግልግሎቶን ለማስተዋወቅ ያናግሩኝ !!!


🔻ክፍል ሀያ አራት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌           ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ እንቁ TUBE ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣2️⃣

ወደ ክፍላችን ገብተን ቁጭ ካልን ቡሀላ ቡናችንን አስፈላንና ፈንድሻችንን እየበላን ፊልም ማየት ጀመርን ::

እኔ ልዑሌን ቀና ብሎ ማየት እራሱ ውርደት እየመሰለኝ ነው ካሁን ካሁን አወቀበኝ ካሁን ካሁን ጠየቀኝ በቃ ወሬ ሊያወራ ሲል ቀድሜ አቋርጠዋለሁ

ሁኔታዬ ግራ ስላጋባው በቃ ወክ እንውጣ ትንሽ እራስሽን እንድታረጋጊ ብሎኝ ወክ ወጣን ...
ልዑሌ ሁሌም የሚያወራቸው ወሬዎች ካፉ የሚወጡት እያንዳንዷ ቃላት ታስገርመኛለች።

እርጋታው ቁንጅናው ምንም ቢለብስ የሚያምርበት ነገር  በተለይ ደሞ ከፈጣሪ የታደለው ንፁህ ልቡ ሁሌ እንዳስገረመኝ ነው።
እናቴ ልክ ናት ምንስ ያህል ይሁዳ ብሆን እንዴት ልዑል ላይ እጨክናለሁ እንዴት ህይወቴን እንዳዲስ ሲሰጠኝ እኔ ክህደትን እመልስለታለሁ እላለሁ ።

አንዱ ልቤ ደሞ ማክቤል ከኔ በላይ ምን ያህል እንደተሰቃየ ይነግረኛል ።
ምንም ቢሆን ከሴትም ከወንድም በታች ሆኖ ያሳደገውን አባቱን ለኔ ሲል መተው የለበትም እላለሁ ።

በስተመጨረሻም ግን ከራሴጋ ሚያስታርቀኝን አንድ ሀሳብ አገኘሁ እሱም
ማክቤል እኔን የሚያፈቅረኝ የእውነት ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ትክክለኛውን ነገር ይነግረኝና አብረን መፍትሄ እንፈልግ ነበር እንደምንም አድርጎ አባቱን አስኪያሳምን ድረስ እኔና እሱ እንደተለያየን ማስመሰል እንችል ነበር ።
በቃ ማክቤል አልሳመኝም በቃ ከጭንቅላቴ መውጣት አለበት ትናት ከነልጄ ጎዳና ላይ ሊጥለኝ የነበረው ማክቤል እንደሆነ ለራሴ ነገርኩት ።

ከልዑሌጋ እንዲሁ አብረን ወክ ወጣን እንጂ ሁለታችንም በራሳችን አለም ከራሳችንጋ ስናወራ ቆይተን ተመለስን ።

ወደ ቤት ከተመለስን ቡሀላ ሁሌም በውስጤ ማስበውን ጥያቄ ለልዑሌ ጠየኩት እንዴት እስካሁን ጓደኛ የለህም በፊትስ ከነበረህ ለምን ተለያያችሁ አልኩት ....

እንደዚህ አይነት እርእስ በድጋሜ እንዳለነሳና ጊዜው አሁን እንዳልሆነ ነገረኝ
እሺ ብዬ ላስጨንቀው ስላልፈለኩ ዝም አልኩ ..

ማክቤል አሁንም ስልኬ ላይ text መላክ መደወል ስላላቆመ ለልዑሌ አዲስ ሲም እንዲያወጣልኝ ነግሬው ሲም ቀየርኩኝ
ወደ እናቴ ቤትም መሄድ ፈራሁ ድጋሜ ማክቤልን ማግኘት ማየት ሀጢያት መስሎ ስለሚሰማኝ እናቴ ናት ወደኔ ምትመጣው እንጂ እኔ አሌድም ።

ልወልድ አካባቢ እናቴ ትንሽ አሟት ስለነበር ብቻዬንም መሄድ ስላልፈለኩ ከልዑሌጋ ወደናቴ ቤት ሄድን  ።

ማክቤል ከዚህ በፊት ያገኘሁት ቦታ ላይ ከቤታችን ፊት ለፊት ቁጭ ብሎ ነበር ከበፊቱ በበለጠ ፂሙ ጉፍ ብሎ አድጎ ነበር  አንድ የጎዳና ተዳዳሪ እንጂ ያ የጫማውን ጫፍ እንኳን አቧራ ነካብኝ ብሎ ሚጨነቀው ማክቤል አይመስልም ፈፅሞ የተለየ ሰው ሆኖ ነበር የለበሰው ልብስ ምን እንደሆነ ሁላ ያስተዋለ አይመስልም ልዑል እጄን ይዞኝ ባጠገቡ ስናልፍ ለምን እንደሆነ አላውቅም ውስጤ ስፍስፍ አለ ።  በፍቅር አለም ውስጥ ስንጎዳ ሁሉ ነገራችን ነው ስብርብር ሚለው  የሰው ፊት አስኪያስጠላን ድረስ ድጋሜ ሰው ማመን ሰው ማፍቀር የምንችል እስከማይመስለን ድረስ ውስጥ ድረስ ገብቶ ድቅቅ ያደርገናል...

የዛን ቀን እናቴን አይተናት ከተመለስን ቡሀላ በድጋሜ ስለ ማክቤል እያሰብኩ አደርኩ ።
በነጋታው ልዑሌ ወደስራ ከሄደ ቡሀላ  እኔም ወጣሁና ወደ ማክቤልጋ ሄድኩ ማለትም ወደቀድሞ ሰፈሬ
እዛ ስደርስ ግን ማክቤል ተከታታይ ቀን ቁጭ ብሎ ያየሁት ቦታ ላይ አልነበረም ።
ምናልባት ካባቱጋ እየሰራ ይሆናል ብዬ ወደ አባቱ ግሮሰሪ ሄድኩኝ ።
እዛም አልነበረም .......


🔻ክፍል ሀያ ሶስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዚህ በፊት አዳዲስ ፊልሞችን Review and recommend ምናደርግበት የ you tube channelachn መዘጋቱ ይታወቃል በመሆኑም አሁንም በድጋሚ በመክፈት ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ወደናንተ አዳዲስ የፊልም መረጃዎች እና የፊልም ዜናዎችን ለማድረስ መተናል በዚህ youtube channel አዳዲስ ፊልም trailers,review recommend best movies for you ይኖራል ከስር ባለው LINK Subscribe አድርጉን
#መልካም ቀን

https://www.youtube.com/@HD_MOVIES_GALLERY
https://www.youtube.com/@HD_MOVIES_GALLERY

ቀድመው ለተቀላቀሉት 30 subscriber randomly መርጠን የምንሸልም ይሆናል


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣1️⃣

ልቀቀኝ እንድትነካኝ አልፈልግም አልኩት
በፈጣሪ አንዴ ብቻ ላናግርሽ  በቃ የልቤን ልንገርሽ እኔ ልፈነዳ ነው ።
አለ እንዴት እንደሆነ አላውቅም እንባው ካይኑ ዝርግፍ አለ ።

ደነገጠኩ ምንድነው ንገረኝ አልኩት ተኮሳትሬ ።
በቃ ቤት ገብተን ላውራሽ እዚህ መንገድ ላይ ቆመን ማውራት አንችልም ላንቺም ለስምሽ ጥሩ አደለም ።
ድል ባሰርግ በተዳርሽ በሳምንቱ ከበፊት ፍቅረኛሽጋ ቆመሽ መታየቱ ምንም ካልመሰለሽ እሺ እኔ ችግር የለበኝም አለኝ ። ሳስበው እውነቱን ነው ።

እሺ ጥሩ ተከተለኝ ብዬ ወደ ቤት ገባሁ በያዝኩት ቁልፍ በሬን ከፍቼ ገባሁ እሱም ገባ ሶፋ ላይ ቀድሞኝ ቁጭ አለ እኔም ቁጭ አልኩ ።
መቀጠል ትችላለህ ፈጠን ብለህ መናገር የፈለከውን አውራና ውጣ ብዬ ካፌ ሳልጨርሰው ።

ሰላም በምትወጃት እናትሽ ይዤሻለሁ አሁን ሳወራ እንዳታቋርጭኝ ዝም ብለሽ ስሚኝ እእ (በሚያሳዝን ፊቱ እያየኝ )
እሺ ቀጥል አላቋርጥህም አልኩት
ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ መጣና አጠገቤ ቁጭ አለ።

እየውልሽ ሰላሜ እኔ የዛኔ የተለየሁሽ ጠልቼሽ አደለም ወይም ንቄሽ እንዳይመስልሽ ሰላም አንቺ ያለ አባት ያሳደገችሽን እናትሽን ምን ያህል እንደምትወጃት ታውቂዋለሽ ።
እኔ ደግሞ እናቴ በቅጡ እንኳን ዳዴ ሳልል ያባቴን ድህነት አይታ ጥላን ጠፋች እእ ከዛ ቡሀላ አባቴ በጀርባው እንደሴት  እያዘለ :
እዚህ ምድር ላይ ያልሰራው ስራ አለ እንዴ እስኪባል ድረስ ተሰቃይቶ ለኔ ለአንድ ልጁ ሲል ሚስት ሴት ምን እንደሆነ ሳያውቅ እድሜ ዘመኑን በሙሉ ለኔ ሰቶኝ አሳደገኝ።

ካንቺጋ የነበረንን ግንኙነት ከበፊቱም አይወደውም ነበር ታቂያለሽ መቼስ።

ሁሉንም ነገር ታዲያ እንዳመረርንና ልንጋባ እንዳሰብን ሲያውቅ ካንቺና ከሱ እንድመርጥ አስገደደኝ ሰላም አንቺን የማገባ ከሆነ የወላድ መሀን ሆኖ እንደሚቀር ከነመፈጠሬ ሊያየኝ እንደማይፈልግና አባትነቱን እንደሚክድ ነገረኝ ።
ቆይ ሰላም ንገሪኝ እስቲ እሱ ለኔ ወንድነቱን ወጣትነቱን እድሜውን ሰቶኝ ዛሬ ሲያልፍልን እሱን ትቼ አንቺን መምረጥ ነበረብኝ እእእ እስኪ በኔ ቦታ ሆነሽ አስቢው እእእ ሰላም በፈጠረሽ በቃ ከማበዴ በፊት ትክክለኛ ፍርዱ የቱ እንደሆነ ንገሪኝ ቆይ አንቺን መርጬ አባቴን መተው ነበረብኝ እንዴ እ??

ደሞኮ ከዛ ሁላ ሴትጋ እየሆንኩ ሳሳይሽ የነበረው አንቺ እንዳትጎጅብኝ ቶሎ እንዲቆርጥልሽ :ቀኔ እንድጨክኚ ብዬ ነበር
ቆይ ሰላም እውነት ልጁ የልዑል ነው በናትሽ እንዳትዋሽኝ ????
የዛኔ ልቤ ስንጥቅ አለ አፈጠጥኩበት: ተኮሳተርኩበት: ምላሴ ተሳሰረ ምን ልመልስ ....
ኮስተር ብዬ አይ እንግዲህ ሲሰሙህ ብዙ ታወራለህ አፍህን አትክፈት  አልኩት።
ማይልኝ በዚህ አጭር  ጊዜ ውስጥ ከልዑልጋ አድረሽ ነዎ ያረገሽው ንገሪኝ ሰላም በፈጠረሽ ?????

አይ እኔ ልዑልን ካወኩት በጣም ቆይቻለሁ ከበፊት ጀምሮ ይወደኝ ነበር ካንተጋ ስለነበርኩ እንቢ እያልኩት ነው እንጂ
ካንተጋ እንደተለያየን አልፈልግሽም ስትለኝ አብሬው አደርኩ ምንድነው ማይመስል ነገር ምትቀባጥረው እንደውም ውጣልኝ ቦዬ ብድግ አልኩ .
አብሮኝ ብድግ አለና ግጥም አድርጎ ከንፈሬን ሳመኝ ።
እውነት ለመናገር እራሴን ለመከላከል አልሞከርኩም ደሞም አልከፋኝም እንዲሁ ድርቅ ብዬ ቆምኩ ።
እናቴ የውጪውን በር ስትከፍት ነበር ሁለታችንም የተላቀቅነው ።
በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ከንፈሬ ሁላ እየተንቀጠቀጠ ነበር እናቴ ስትገባ እጄን አፌ ላይ አድርጌ አቀረቀርኩ ልዑሌ በቃ ልሂድ እናቴ እቸኩላለሁ ብሏት እየተጣደፈ ወጣ ።
እናቴ ሰላም እንኳን ሳትለኝ ግራ በተጋባ ሁኔታ እያየችኝ አለፋኝ ገብታ ቁጭ አለች።
ፊቷ ወዲያው ቅይር ብሎ ነበር ።
እኔም እማ ምነው ሰላም እንኳን አትይኝም እንዴ ምን ሆነሻል አልኳት በጥያቄ አይን እያየኋት ?
ቁጭ በይ ልጄ ዛሬ እንዴት መጣሽ ??
አይ እማ እኔኮ ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ብዬ ነበር የመጣሁት ግን ....

ግን ምን እንዴት ገና የሰርግሽ ድባቡ እንኳን ሳይጠፋ ከሌላ ወንድጋ ብቻሽን አንድ ቤት ውስጥ ትገኛለሽ ??አለችኝ

አረ እማ ምን አስበሽ ነው በአጋጣሚ አጊቼውኮ ነው ማክቤልን እማ ቆይ እንዴት አስበሽው ነው??

አይ እንግዲ ልጄ  እኔ ህፃን ልጅ አደለሁምኮ በአጋጣሚ ያገኘሽው እንደሆነ ቤት ምን ሊሰራ ገባ።

እየውልሽ ልጄ እኔ ማክቤልን እወደዋለሁ መልካም ፀባይ አለው ነገር ግን
አሁን ያንቺ ባል ልዑል ነው
ልጄ ተይ ያጎረሰሽን እጅ እንዳትነክሺ።
ሰላም በሰፈሩ ሰው ፊት እንድኮራ እንድከበር ያደረገኝ ልዑል ነው እንጂ ማክቤል አደለም ።
ለክብሩ ሳይጨነቅ ሀብታም ነኝ እዛ ደሀ ሰፈር አልገባም ሰው ይታዘበኛል ሳይል በኩራት ሚስቱ ያደረገሽ ልዑል እንጂ ማክቤል አደለም ።
መከበርን መወደድን ሚስት መሆንን ያሳየሽ ቤተ መንግስቱን ከፍቶ ያስገባሽ ልዑል ነው ። ፈጣሪ የሰጠሽን ፀጋ አትጋፊ ከሰውም ከፈጣሪም አትቀያየሚ በድጋሜ ከዚህ ልጅጋ ባይሽ ሰላም ሙች እንቀያየማለን አለችኝ ።
እማ እሺ በቃ ሁለተኛ አታይኝም ይቅርታ በቃ የተሰራ ምግብ ካለ እናቅርብና እንብላ ብያት ምሳችንን በላን ።
እሷም ወደስራዋ እኔም ወደቤቴ ሄድኩኝ ።

ቤት ከደረስኩ ቡሀላ በጣም የድካም ስሜት እየተሰማኝ ትንሽ ህመምም ስለነበር ለመሲ ልተኛ እንደሆነ ነግሪያት ልተኛ ገባሁ ነገር ግን ጭራሽ መተኛት አቃተኝ ጭንቅላቴ ማክቤል ከነገረኝ ነገር ውጭ ማሰብ ከበደው ።
ልጁ የሱ እንደሆነ እንዴት ጠረጠረ ብቻ ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ውስጥ ገባሁ ።

ብዙም ሳይቆይ ልዑሌ መጣ ድምፁን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ እንዴት ከአልጋ ላይ እንደወረድኩ ሁላ ሳላውቅ ወረድኩኝ እሱም ወደኔ እየመጣ ስለነበር እኔም የክፍሉን በር ስከፍት እሱም ለመክፈት ሲሞክር ተገጣጠምን
አፈጠጥኩበት አድርጌ የመጣሁትን የሚያውቅብኝ መሰለኝ ተርበተበትኩ አይን አይኑን እያየሁት ቀጥ ብዬ ቆምኩ።

እንዴ ሰላም ምን ሆነሻል ታውቆሻል እጂሽም ከንፈርሽምኮ እየተንቀጠቀጠ ነው አመመሽ እንዴ አለኝ ።
አይ ልዑሌ እንዴት አሁን መጣህ ዛሬ ቆያለሁ ብለኸኝ አልነበር እንዴ አልኩት ?

አይ የነበረን ስብሰባ ሲሰረዝ ካንቺጋ ባመሽ ይሻላል ብዬ መጣሁ ምነው ደስ አላለሽም እንዴ አለ???

አይ ልዑሌ እንኳን መጣኽልኝ ግባ በቃ ቆንጆ ምሽት እናሳልፋለን አልኩትና ወደ ውስጥ ገብተን ቁጭ አልን......


🔻ክፍል ሀያ ሁለት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


Репост из: DT Promotion
❤️Haadha kanaaf like 100 taasisaafii👇


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰2️⃣0️⃣

አዎ ልጃችንን አንድ ቤት ሆነን ማሳደግ እንዳለብን ወስነን ነው አይመስልህም ልጅ ያለናትና አባቱ ማደግ የለበትም ።
እኔ አባቴ ሳይኖር ማደግ ምን እንደሆነ አቀዋለሁ ለዛ ነው በቃ ልሂድ ቻው አልኩት።

ስሄድ እጄን ይዞ አስቆመኝና ሰላም ቆይ ከሰውዬውጋ ከኔ በፊትም አብራችሁ ነበራችሁ እንዴ እእ እንጂ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በፍፁም ከብረሽው እንደማትተኚ አውቃለሁ።
እኔ እንኳን ያን ያህል አመት አብረን ቆይተን  ከስንት ጊዜ ቡሀላ እንደዚህ አይነት ነገር እንደተፈጠረ አቃለሁ ።

ወይስ ቶሎ አርግዘሽ በልጅሽ ልታስሪው ፈልገሽ ነው አብረሽው የተጋደምሽው እእ በዚህ ልክ እርካሽ ወራዳ እንዴት ትሆኛለሽ ቆይ 6 አመት ሙሉ አላውቅሽም ማለት ነው አንባረቀብኝ ...
ዝም ብዬ ካዳመጥኩት ቡሀላ
ምናገባህ አንተ አብሬው ባድር ባላድር..

እኔ ታውቃለህ አንድም ቀን የወንድ ልጅ ፀባዩ እንጂ ሀብትና መልኩ አሳስቦኝ እንደማያውቅ ካንተ በላይ ምስክር የለም
ደሞስ አንተ አስሩን ሴት እየቀያየርክ ባጠገቤ ስታልፍ ስታስተዋውቀኝ አልነበር ለምንድነው ደርሶ እንደፃዲቅ የሚያደርግህ ድጋሜ አፍህን ለመክፈት እንዳትሞክር በዙሪያዬ ላይህ እራሱ አልፈልግም ጥዬው ሄድኩ አልተከተለኝም::


የሰርጌ ቀን ደረሰ ሚዜዎቼ የሰፈሬን 3 ልጆች መርጬ ነበር ያደረኩት ልዑሌም ጓደኛ ስለሌለው ሚዜ ማብዛቱ ምን ይሰራል አለኝ።

እናቴ ድግሱን ስትደግስ 5% እንኳን አይሞላም ያወጣችው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እሱ ነው የሸፈነው ።
የሰርጌ ቀን የናቴ ደስታ ሳቋን በህይወቴ አይቼው አላውቅም እናቴ ምድሩን የጨበጠችው መስሏት ነበር አንድ የሰፈር ሰው አልቀራትም እዛ ሰፈር ግብቶ የማያውቅ የመኪና  አይነት  ነበር የጎረፈው ብቻ በህይወት ቆሜ የናቴን ደስታ በዚህ ልክ ማየቴ ብሞትም አይቆጨኝም እንድል አደረገኝ  ።

አቶ ማክቤልም ሳይጠራ ቀብር እንደሚሄድ ሰው ጥቁር ሱፍ ለብሶ ፊቱን አጥቁሮ መጣ (ሰው ለሰርግ የህፃን ልጅ አሻጉሊት ይሰጣል😂)

ብቻ የሰርጉ ታሪክ ብዙ ስለሆነ ልለፈውና
የሰርጋችን ቀን ማታ ልዑሌ ሌላ ክፍል ሄዶ ተኛ ።
ልዑሌን ሳገባ እኔ የመሰለኝ ሳይሰለቸኝ ሳልሰለቸው
ሳይለየኝ ሳልለየው ዘላለም አብረን እንደምንኖር ነበር ያሰብኩት እና ከልዑሌጋ ከተጋባን ጀምሮ አብረን አድረን አናቅም አንድም ቀን  ለሴትነት ጠይቆኝ አያውቅም ብቻ የሰርጉ ጣጣ እያለቀ ከመጣ ቡሀላ ልዑሌ ጠዋት ተነስቶ ስራ ይሄዳል ቤት ውስጥ ብቻዬን መዋል ይደብረኛል እናቴጋ እንዳልሄድ እናቴም ምሳ ሰአት ካልሆነ ቤት አደለችም
ልዑሌም ሁሌ ምሳ ሰአት ቤት ይመጣል።(እውነት ለመናገር ልዑሌ ሁሌም የውጪ ምግብ ነው ሚበላው እኔ ቤት ስውል ምሳ ሰአት ለመብላት ይመጣል እኔ ሽሮ ምስር ሰላጣ ስጋ ወጥ በቀይ በቃ እኔ የሀብታሞች ምግብ እንዴት እንደሚሰራ ማቀው ነገር ስሌለኝ ሁሌ ለምሳ ቤት በመጣ ቁጥር መሳቀቅ ጀመርኩ ።
ስለዚህ ሰራተኛ ቢቀጠር ጥሩ እንደሆነ ለልዑል ስነግረው ተስማማ በዛውም ቤት ብቻዬን ከምውል ታወራኛለች አልኩት :: መሲ ምትባል በጣም ንፁህ ልብ ያላት ምስኪን ልጅ ገባች ።
እኔ በድህነት የኖርኩ ሰው ስለሆንኩ አንድም ቀን እንደሰራተኛ እንዲሰማት አላደርጋትሞ ልክ እንደጓደኛ ነው ምቀርባት ማወራት በጣም የሚያሳዝን ታሪክ አላት ቀጣይ አጫውታችኋለሁ ባየኋት ቁጥር እንባዬ ይመጣል።


የሆነ ቀን እናቴን ሰርፕራይዝ ለማድረግ ምሳ ሰአት ቤቱን ፏ አዶርጌ ልጠብቃት ወደ ሰፈር ሄድኩ ።
ሰፈር ስደርስ ማክቤል  የቤታችን ፊት ለፊት ትክዝ ብሎ ቁጭ ብሎ አየሁት ።

ጠቋቁሯል እራሱን ጥሏል ተክዟል
እውነት  ለመናገር  ሳየው አሳዘነኝ ።
ግን ማናገርም ማየትም ስላልፈለኩ ባጠገቡ አልፌ ወደቤት ልገባ ስል
ብድግ ብሎ እየሮጠ መጥቶ እጄን ያዘኝ



🔻ክፍል ሀያ አንድ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖

https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

Показано 20 последних публикаций.