🌕 ረመዷን መጣ 🌙
ይህን ከንቱ ልቤን ወንጀል እንዳጠረው
ይህን ዝርግ ምላስ ሳልቆጣጠረው
ረመዳን መጣ ጥቂት ቀናት ቀረው
ኢንሻአላህ ጀሊሉ በሰላም አድርሶ
ወንጀሌ በእዝነትህ ከመዝገብ ታብሶ
እንድፆም አድርገህ በኢባዳ በለቅሶ።
ስጋ እየበላሁኝ አማርጨ ከቤት
ደረቅ እንጀራ እንኳን ጠፍቶ ከጎረቤት
ለየቲም ሳልሰድቅ እጀን ሳልዘረጋ
ያምናና ካቻምናው ነበረው አደጋ፡፡
ዘንድሮ ግን ያረብ በሰላም አድርሰህ
አመፀኛ ልቤን ወደአንተ መልሰህ
ከተጠቃሚዎች አርገኝ ከራሴ መልሰህ
እኔ ደካማ ነኝ ሀይል የለኝምና
ያላንተ የሚጓዝ ከሳሪ ነውና
እባክህ ያጀባር ምንም ሰው ሳይጎድል
የአለምን ሙስሊሞች አብቃን ለዚህ እድል ።
t.me/FKR_ESKE_JENET
ይህን ከንቱ ልቤን ወንጀል እንዳጠረው
ይህን ዝርግ ምላስ ሳልቆጣጠረው
ረመዳን መጣ ጥቂት ቀናት ቀረው
ኢንሻአላህ ጀሊሉ በሰላም አድርሶ
ወንጀሌ በእዝነትህ ከመዝገብ ታብሶ
እንድፆም አድርገህ በኢባዳ በለቅሶ።
ስጋ እየበላሁኝ አማርጨ ከቤት
ደረቅ እንጀራ እንኳን ጠፍቶ ከጎረቤት
ለየቲም ሳልሰድቅ እጀን ሳልዘረጋ
ያምናና ካቻምናው ነበረው አደጋ፡፡
ዘንድሮ ግን ያረብ በሰላም አድርሰህ
አመፀኛ ልቤን ወደአንተ መልሰህ
ከተጠቃሚዎች አርገኝ ከራሴ መልሰህ
እኔ ደካማ ነኝ ሀይል የለኝምና
ያላንተ የሚጓዝ ከሳሪ ነውና
እባክህ ያጀባር ምንም ሰው ሳይጎድል
የአለምን ሙስሊሞች አብቃን ለዚህ እድል ።
t.me/FKR_ESKE_JENET