❤ፍቅርን ፈልጉ❤


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ፍቅርና ግጥም ስወዳቸው!!
❤❤❤❤❤❤❤❤
Suggest us by @Taachine
Phone (0906368577)

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በሷ ሚዛን ስፈልግ
የውሸት ስፈግግ
አለ ቦታ ሆኜ አለ ስሜት እምኖረው
የእናቴን የሚያህል ፍቅር ባጣ ነው

ብረባ ባልረባ ጠልታኝ በማትተው
በእምዬ አምሳል ጠረን የማሸተው
እውነትና ፍቅርን ፈልጌ እምቋምጥ
ዘላለማዊ ስሜትን በውስጤ ብታስቀምጥ
አልግባባ አልኩ አምሳሏ ቢጠፋ
እማን ባይመስልልኝ ለራሱ ቢሳሳ




@Fikrin_feligu


ሰላም ሰላም እንደምን አላችሁ? የፍቅርን ፈልጉ ቻናል ወዳጆች ሰላምታዬን እንኩ እያልኩ አሁን ላይ በተለያየ መንገድ ትምህርትና የስነልቦና ምክር ወይም የማማከር አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቴን ጨርሻለሁ። አገልግሎቶቹም፦

1... ስለ ፍቅር ግኑኝነት
2...ስለ ማህበራዊ ህይወት
3...ስለ ትምህርት ነክ ጉዳዮች

እነዚህ ከላይ በተዘረዘሩት መካከል መነሳሳት አቃተኝ ምክርና ትምህርት እፈልጋለሁ በምትሉት አንዱን መርጣችሁ በinbox ሆነ በስልክ አሊያም በአካል በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደምትችሉ አሳውቃለሁ።

መልካም የሆነችና ውድ ነፍሶችን ለዓለም መፍጠር ውጥኔ ነው።

Telegram @TameLoveT
E mail melkamugirms@gmail.com
ወይም
በስልክ ቁጥር 0906368577
ፍቅርታም ብላችሁ በመደወል ልታገኙኝ ትችላላችሁ።

@Fikrin_feligu


አዳም አፈር ነበር አንተ ባትመጣ...ስለኛ ባትሞት..
"ኦ አዳም መሬት አንቲ..ወትገቢ ውስተ መሬት"
ለሰው ልጅ መዳን እርሶ ተሰድዶ
እርግማን ተሻረ ...ጌታችን ተወልዶ

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልጀት በዓል (ገና) አደረሳችሁ!



@Fikrin_feligu


ሰላም ሰላም ሰዎች እንደምን አላችሁ?

ከ5-8 ክፍል አስጠኚ የሚፈልግ በውስጥ መስመር ያናግረኝ።
በሚቀጥሉት የትምህርት ጊዜያቶች ተማሪዎች አስጠኚ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ማጥናትና ውጤታማ እንዲሆኑ እናደርጋለን።

@TameLoveT


ከ5-8ኛ ክፍል አስጠኚ የሚፈልግ በውስጥ መስመር ያናግረኝ።
በሚቀጥሉት የትምህርት ጊዜያቶች ተማሪዎች አስጠኚ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ማጥናትና ውጤታማ እንዲሆኑ እናደርጋለን።

@TameLoveT


ማንም ልክ ላይሆን ከአንድ ከሱ በቀር
ልኩን አደረግነው ልክ በእኛ ስንዝር




@Fikrin_feligu


ልታመም ግዴለም ...

ስትመጪ ልወቀው...ኮተ ይኑርሽ
መጣሁ በዪኝ...
ስትሄጂም እንዲሁ ...እንዲዘጋጅበት
ልሄድ ነው በዪኝ..
እውነት መናገርሽ መምጣት መሄድሽን
አከብረዋለሁና የእምነት ቃልሽን

መጥቀም እየመሰለው ተደብቆ ሄደው
ስንቱ መሰለሽ ሰው ያሳበደው
ግልጽነት ፍቅር ነው መራራ እውነት
የጨከኑ ዕለት የሚቀበሉበት

ሄጃለሁ ካላልሽኝ ምኔ ይመንሽ?
መጥተሽ ባይም ይቸግረኛል እንዳምንሽ
ይፋ አውጂ ምናባቱ ስሜቴ
ግራ ይግባው ይበጥበጥ ህይወቴ
ሳቅን ልለየው በሀዘን ልቆራኝ
ልታመም ግዴለም እውነቱን አትደብቂኝ

@Fikrin_feligu


እልፍኝ አስጥዬ በብዙ ደግሼ
ባላስጠራሽም በቤት በአዳራሼ
እማምላክን! የሌለው መጠኑ
እውነት እውነት እልሻለሁ ማፈቀሬ ጥኑ
ቃሌም ቅን ነው
ወረት የማይወርፈው

@Fikrin_feligu


ዐይኑን የጨፈነ ...የማያይ ሰው
ጨለማ ብሎ....ሀቁን አፋለሰው
ማሳመን ችሎ ...ታምኖ በዓለም
ጠቢብና እውቅ....ታላቅ ቢባልም
ራሱ አለማወቁን.. እሱ የሚያውቀው
ብዙ ነገር እንዳለ..
ይነግረን ነበረ...ተወው እንጂ ባንጠይቀው።

@Fikrin_feligu


እውነት የማይመስል እውነት...

አንዳንድ ጊዜ የናቅኩት ሁሉ
ከአፈር የደባለቅኩት የተኛ ከወለሉ
አለ እውነት የማይመስል እውነት
ያልጠበቅኩት በጭራሽ ያላስተዋልኩት

@Fikrin_feligu


እንዳትሄጂ ነው....


የማልወደውን የሆንኩት...
አድርጌ የማላውቀውን ያደረግኩት..

እኔ ልሙት..እንዳትሄጂ ነው
ማርያምን! እንዳንለያይ ነው።

@Fikrin_feligu


ያቅበጠበጠኝ ፍቅርሽ እንጂ...ተፈጥሮዬ መች ሆነ...
ካንቺ በፊት ባየሽኝ ቆፍጣና ሆኜ ልቤ እየደነደነ..




@Fikrin_feligu




ሰንብቺ ደህናውን ...

ሁሉም ቀናት ሁሉም ቅጽበታት
አንድ ቀን ነው ከዕለታት

ለነገም ነገ እየሆነ መልስሽ
ከዕለታቱ መች ነው የማይሽ
እኮ መች ነው የት ነው የማገኝሽ?

አትቅጠሪኝ በቃ ለቀጠርሽው ሳትመጪ
ሰንብቺ ደህናውንን ከልቤ ሳትወጪ

@Fikrin_feligu

....


ትመጫለሽ ግን.....

እየሄድሽ ሳለ እኔን ያስጨነቀኝ
መመለስሽ ሆነ እንዲሁ እያራደኝ

ቃል ገብተሽ እየሄደሽ አሁን
ትመጫለሽ ግን..


@Fikrin_feligu


ያን ጊዜ እንጂ የጨከንኩብሽ
እንዳልሽኝ ከሆነ የደረብኩብሽ

ቃሉ ካንቺው ሲጎብጥ
ስሜቴ ሲበጠበጥ
አውሎ እንዳነፈሰው እንደባህር ሲናወጥ

እኔንም አንቺንም ብዬ ከሚጎዳ
ለመድኩት እንጂ መርጬ ከሰው ባዳ
አንቺው ነበርሽ እኮ መላው ዘመዴ
ምስጢር ገመናና ልዩ አዕማዴ



@Fikrin_feligu


ትመጫለሽ ስል....











እየጠበቅኩሽ ነው...




ትሄጃለሽ ስል ደግሞ







እየፈራሁሽ ነው!


@Fikrin_feligu


.........ሰም ነው እህቱ........

እንዲህ ነው ነገሩ የማዋይሽ ዛሬ
ትዝታን ከርችሜ ስሚኝ እስቲ ማሬ
ጎዳናው በሙሉ ፀጥ ረጭ ብሎ
ድምፅ በጠፋበት ዝምታ ጓጉሎ
እኔ ብቻዬን ከትዝታሽ ጋራ
ያ ያለፈው ጊዜ እግሬኑ ሲመራ
ከተቀመጥንበት ሌላ ደሞ ከዞርንበት
በልፊያ ተዋድቀን አቅፌሽ ከተኛሁበት
ምን እንደጠራኝ አላውቅም ዛሬ ደረስኩበት

ከሄድሽ ወዲያ ተጣልቼው በነበረ
ይቅርታ ልለው ቦታውን አካሌ እየዞረ
ታየሽኝ ምነው እውን ባልሆነ
ትዝታሽ ይመጣል ልብሽ ከጨከነ
ትዝታን ወደድኩት አንቺን ስላሳየኝ
እንዳንቺ ትዝታሽ ስላልጨከነብኝ
የሳምኩት ከንፈርሽ የሌላ ሰው ለምዷል
እኔንም በሌላ ተክቶ ከረሳኝ ቆይቷል
እና በዚህ መሀል የጋራ ንብረቱ
በሰው ባጥበው አይፀዳም ትዝታ ሰም ነው እህቱ

ሁሉ በሚያርፈው በትልቁ ሰንበት
ሀሳቤ ይዘምታል ጠፍቶት ስንብት
ቢያምን ምናለበት መሄድሽን ቢያውቅ
እግዜር ባረፈበት ላንድ ቀን እንኳን ቢለቅ

@Fikrin_feligu


መርሳት የሚያቅተኝ ልረሳሽ ሳስብ ነው። ታዲያልሽ አንደኛዬን አስብሻለሁ፤ ትዝታዬ ነሽና።



@Fikrin_feligu


Definitely, I need you for everything. I believe in you, you also back to me.

@Fikrin_feligu

Показано 20 последних публикаций.