🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


➣ Express love without reciprocation !
➣ Swimming with a pure heart !
➣ Where trust and empathy prevail !
➣ Thinking about people more than your !
➣ Preach love until her last breath !
= +251931374891
= t.me/Abate_Hiwote

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

አዎ ከሆነ ከታች ያለውን 'start' የሚለዉን ይጫኑ👇👇


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ




ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።

#ተፃፈ_በዳዊት
@Davunin

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ሌሎችም ውስጥ...
(ሳሙኤል አለሙ)


መች ኑር ብለሽኝ...
አልኖርም አልኩ፤
መች ሙት ብለሽኝ...
አልሞትም አልኩ፤
በክቡራን'ና ክቡራት
አልታይሽም እየተቀደምኩ።


እንደው...
ታክቶሽ እንጂ ለምስጋናው
ዝለሽ እንጂ ለፍለጋው፤
አታጭኝም ነበር...
ሌሎችም ውስጥ እየተጠጋጋው።

ሳሙኤል አለሙ
    
@Samuelalemuu

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


#ተከታይ_የሌለው_አንድ

መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።
መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለተገዢው ልቤ
ክዳው ለማትገባው።
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።

ቀርበው ሲጠይቁኝ...
አንዱን ልቤን
እያስለካው፤
አንዴ ልየው ሲሉኝ...
አንዱን ልቤን
እያስጠጋው፤

ስኖር...አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
ላንዴ...ስኖር...ስኖር...ስኖር...ስኖር
ስኖር..አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
በስንቱ አንዴ-ዎች
አንዱን ልቤን፥ ላንዴ ሳስሞክረው፤
አለሁኝ በተስፋ
ገዢ እንደቸገረው።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


☀️☀️ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኛ ምን አይነት ስጦታ ልስጥ ብለው አይጨነቁ !

የ ስዕል ( Art ) ስራወችን በስጦታ መስጠት ለምትፈልጉ ከታላቅ  ቅናሽ ጋር አሁኑኑ ይዘዙን ።
ጥራት ያላቸውን ስራወች ሰርተን በፍጠነት እናስረክባለን ።
  

order ለማረግ 👇👇👇

☎️ 
+251912453800
☎️ 
+251931374891
     ይደውሉ 👆👆👆

በቴሌግራም
@Abate_Hiwote ላይ ያናግሩን።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


ውሀ ሞልቶ ባገር ቀድተሽ 'ማትጨርሽው
ምነው በሰው እንባ ሊጡን አቦካሽው

ቢሆን መልካም ነበር ብትሆኝ እንደቃልሽ
እሞትልሽ ነበር እንኳን ልቀየምሽ

እንዳይዘም አንገተሽ ትራስ ሆነሽ ክንዴ
ዘውዱን ስትጭኝ ተረሳሽ ወይ ባንዴ

በሰፊው ልቤ ላይ እኔ ስተክልሽ
በመንደሬ ልብቀል ለምን ትያለሽ

በ 27 አውታር ተቀኝታ ክራሬ
ላንች ስል የሆንኩት ይታይልኝ ሰንበሬ

አርቲስት
#አቡሽ_ዘለቀ 👌
( perfect Ethiopian artist )

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


[ . . . አ ን ድ  ል ጅ  ነ በ ረ  . . . ]
.
.
አንድ አባት ነበረ
አንድ ልጅ ነበረው
ከድህነቱ ጋ ፣ ታግሎ የሚያኖረው
ታዲያ ይሄ አባት
እህል ያልጠገበ ፣ ኮቴው ቶሎ ቶሎ
ጓዳው ያልተዋበ ፣ ልብሱ ዘባተሎ
ሕይወት አያጓጓው ፣ በስቃይ ሲገፋ
ዕድሜ ይለምናል ፣ እስከ ልጁ ተስፋ
.
ሁሌ ተማሪ ቤት
ይህን ልጅ ሲያደርሰው
በሸካራ እጁ እየደባበሰው
እንዲሁ በደምሳሳ
ይንበረከክና ፣ ከዓይኖቹ መሳ
እንደዚህ ይለዋል
“ልጄ ሆይ ሰው ሁን!”
.
ልጁ አይገባውም  ፣ እንዲህ ያለ ተረት
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፣ ሰው ለመሆን ጥረት
ከምን ይጠብቃል? ምን አለው ከለላ ?
ምንድነው ሰው መሆን ፣ ከሰውነት ኋላ ?
.
ይህን እያሰበ ይገባል ከክፍል
መምሕር ቆሞ ከነብሶቱ
“ለሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቱ
ምግብ ልብስ መጠለያ— እነዚህ ሦሥቱ”

ታዲያ በዚህ ሚዛን ፣ ይወድቃል አባቱ
ልጅ ግራ ይጋባል
ምኞቱ ይበልጣል ፣  ሰው ከሰውነቱ ?
.
በልጅ አእምሮው ውስጥ ፣ ሁለቱን ሲያጣጥም
መራብ፣ መጠማት፣  ሜዳ መውጣት
የሚኖረው ጠላት ፣ ከነዚህ አይበልጥም

እንደዚህ ያስባል
ጠግቦ መመገብ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
አበባ መልበስ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
የሳር ጎጆ መሥራት ፣ ይሆናል ሰው መሆን
እንዳባት አለመሆን ፣  ይሆናል ሰው መሆን
.
እንዲህ ያደገው ልጅ
አሁን ወደ ማምሻ
ቁርጥ ሥጋ በልቶ
ውስኪውን ጠጥቶ
ቶክሲዶውን ለብሶ
ከጥሻ ሥር ያድራል
ከሞት አስበልጦ ፣ ሲርበው ይፈራል
የወዙን ክፍያ ፣ መጠጥ ቤት ሲዘራት
`ሚስቅ ይመስለዋል ፣ አባቱ በኩራት
.
እንዲህ ዓይነት ስጋት የሚያንከራትተው
ምኞቱን ይሆናል ፣ ሰው መሆን ያቃተው

©Henock_B___


https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


☀️☀️ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኛ ምን አይነት ስጦታ ልስጥ ብለው አይጨነቁ !

የ ስዕል ( Art ) ስራወችን በስጦታ መስጠት ለምትፈልጉ ከታላቅ  ቅናሽ ጋር አሁኑኑ ይዘዙን ።
ጥራት ያላቸውን ስራወች ሰርተን በፍጠነት እናስረክባለን ።
መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ቅናሽ አድርገናል ።

order ለማረግ 👇👇👇

☎️ 
+251912453800
☎️ 
+251931374891
     ይደውሉ 👆👆👆

በቴሌግራም
@Abate_Hiwote ላይ ያናግሩን።


"በፈጣሪ ልጄን አድኑልኝ" አባት

ይህ ቆንጅዬ ህፃን አሚር የሱፍ  ይባላል! በተወለደ 4ኛ ወሩ ህመም ሲያሰቃየውና እንቅልፍ ሲከለክለው እናትና አባት ወደ ጥቁርአንበሳ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ!
ህፃን አሚር አንድ ወር አልጋ ይዞ ክትትል ካደረገ በኋላ ዶክተሮች "የልብ ክፍተት  ችግር አለበት፣ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል"ተባሉ!

ልጁን ለማሳከም የተጠየቁት 1500000 ብር ነው ከአቅም በላይ ስለሆነ ልጃቸውን ለማዳን እናንተን እየተማፀኑ ነው😭 እባካችሁ #እንድረስላቸው🙏 እናግዛቸው🙏
 "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000304310937-ዩሱፍ ሀምደለ (አባት)
#ስልክ 0705740135

☞አድራሻ ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር
☞ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል

ሁላችሁም የቻላችሁትን ከ 10 ብር ጀምሮ አስተላልፍ ይሄን ብላቴና እንታደገው 🙏 አደራ


#ባቅፈው_ደስ_ይለኛል

ባርፍ ብጠመጠም
ብገባ ከቅፋ፣
ደቂቃዎች ቁመው
ሰአታት ሳይከንፋ፣
ራሴን አስደግፌ
በደረቱ ተርታ፣
ባደምጥ እንደዜማ
የልቡን ትርታ፣

ዝም ብለን ብቻ
ምንም ሳናዎራ፣
አንድ አይነት ስሜትን
አብረን ብንጋራ፣
ክንዱን ተጠልዬ
ናፍቆቴን እንዳልፈው፣
ደስ ይለኝ ነበረ
ሳብ አድርጌ ባቅፈው።

ግን በምን ጀግንነት
በየትኛው ወኔ፣
ስንቱን ሰው አልፌ
አቅፈዋለው እኔ፣
ይሉኝታዬን ሽሬ
ብደርስ እንኳን ከሱ፣
ይመልሰኝ የለ
ያ ግርማ ሞገሱ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


የኔ...

ተከፍቼ ሳዝን እንደ ወንድም፣
በደስታዬ አብሮነት የማትደክም፣
ስትቆጣኝ እንደ አባት ፣
ስትመክረኝ እንደ እህት ፣
የኔ መልካም የፍቅሬ እናት፣
ለኔ ስትል የማቶነው ምንም የላት።

ምን ልበላት...የኔ ፍቅር ማር ጣፋጬ?
ስም ከንቱ... ይጨነቅበት ስም አውጭው፡
እኔግን የእኔ ብያት፣
በአንዲት ውብ ቃል ልቋጭላት።

@Davunin

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ላገኘው ስል አጣሁት
ላስር ስል ፈታሁት
ሞላ ስለው ሲጎል
ሆነ ስል ሲታጎል

የተቃናው ሲጎብጥ
የተሳካው ሲከሽፍ
ታይታ ሆነ ሁሉም ነገር
ውሸቱም ሸፈኖ ነበር
ወና ሆነ አዲስ ህይወት
ተከደነ ጠፍቶ እምነት

መሰበር ሆነ ጉዟችን
አልቃና አለን ጎጇችን
የያዝነው ወዲው ተበታትነ
የጨበጥነው ከጢስ የቀጠነ
ያመነው ጉም ኖሮ ለካ
መኖራችን መባከን ብቻ
አስመኘኝ አለመኖርን
ከበደኝ መማግ አየርን

ሸተተኝ የሞት መቃብሩ
ከበደኝ ምላስ መንደሩ
ነጫጭ ነው ደግሞም ሠፈሩ
ድምፅ አልባ ነው ዳር ና ዳር አጥሩ
ህልም ሆነ የዚህ ዘመን ኑሮ
ይገላል እያደር ቦርቡሮ

ገጣሚ :- ሙሽራዋ 😍

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ይድረሰ:- ለኩርፊያ
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
የሻማው ብርሃን ደብዝዞ
የንፋስ ሽውታ ጠረገው፤
አፋችኑ ቃላት አርግዞ
አምጦ መውለድ አቃተው፤
ዝም...ዝም...ዝም
ጭልም-ልም-ልም
ገዘፈ ድቅድቁ ጨለማው፤
ቃላችንን ሾተላይ ቀማው።
°
°
እንደ'ኔና እንደ እሷ
ጀምበሩ ሳይነጋ
መሰሎቻችን ጋ
አፋቸውን ሊያዘጋ
ጥድፍ-ድፍ-ድፍ...ሲል
ርብት-ብት-ብት...ሲል
ደርሶ አፋችንን ቆልፎበት።
ደጃፉ ላይ ፥ ስደርስበት።
°
°
ቀኝህን ለሚመታ
ግራውን ስጡት እንዳለው ጌታ
ሳትነፍገው የእግዜሩን ሰላምታ
እንደ ዲዳ ዝም ካለህ
ላፍታም... ላፍታም.... ሳታመንታ
ኩርፊያን
በልልኝ!
°
°
ይኸው እኔና እሷ
ሰርክ ኩርፍ ኩ-ርፍ-ርፍ
ሰርክ እቅፍ እ-ቅፍ-ቅፍ
ይኸው እኔና እሷ
እንደ ቄጤማው ፥ እንደ አውዳመቱ፤
ድንገት ካየኸው ፥ የኩርፊያን ፊቱ፤
ትላንቱ ለምልሞ ፥ ዛሬ ክስመቱ።
°
°
እንደ ጳጉሜ ሶስት ዕለቱ
ዕንባውን አዘነብነው።
የሩፋኤል ፀበል አይደል
ክፋቱን አያድነው።
ከጫጫታው አልፈን
ነጎድጓዱን አክለነው።
ጭቅጭቁን አድ'ምጦ
በዜማ አቀነቀነው።
°
°
ተወው በክረምቱ ፥ ይርገጥ ዳንኪራ
ተወው በዕንባችን ፥ ይስከር ያሽካካ
በፀደዩ ብርሃን ፥ እንደምንፈካ
ዘንግቶታናልና!
°
°
የዛሬዋን ዕድል
ከቆጠረው ከድል
ትርኢት ያዘጋጅ
እንግዳም ይጥራ ፥ ድግሱንም ይደግሰው
እንደ ንጉስ አይዙር ፥ ግማሽ ቀኑን የሚነግሰው
ተወው!

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


☀️☀️ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኛ ምን አይነት ስጦታ ልስጥ ብለው አይጨነቁ !

የ ስዕል ( Art ) ስራወችን በስጦታ መስጠት ለምትፈልጉ ከታላቅ  ቅናሽ ጋር አሁኑኑ ይዘዙን ።
ጥራት ያላቸውን ስራወች ሰርተን በፍጠነት እናስረክባለን ።
መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ቅናሽ አድርገናል ።

order ለማረግ 👇👇👇

☎️ 
+251912453800
☎️ 
+251931374891
     ይደውሉ 👆👆👆

በቴሌግራም
@Abate_Hiwote ላይ ያናግሩን።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

#አትጥቀሰኝ

ሳይሰነዝር 'ሚጥል
ሳይገል የሚረታ፣
አንዳች ጉልበት አለው
ያይንህ ስልምልምታ።

እንኳንስ ጨክነህ
አርገብግበህብኝ፣
ድሮም እኔ ልጅት
ፍርሃት አለብኝ፣
እኒያ ውብ ዓይኖችህ
ወደኔ ካመሩ፣
ይመስሉኛል ውስጤን
የሚመረምሩ፣
ያስጎነብሱኛል እንደ
ጨረር ግለት፣
አንተን ለመጋፈጥ
ያሳጡኛል ጉልበት።

ታዲያ ለምንድን ነው....
እንደምንም ችዬ
ሆኜ እንደጠንካራ፣
ወዳንተው ለማዬት
በድንገት ሳመራ፣
ተዘጋጂ ሳትል
ወይ ሳታሳውቀኝ፣
በአይኖችህ ጠቅሰህ
ቀልቤን የምትሰርቀኝ?

አስበኸው ይሆን
ወይስ ሳታስበው፣
የእኔን ሁለመና
ወዳንተ ምትስበው?

ደጋግሞ እጅ መስጠት
ባይኖችህ ብለምድም፣
በአንተ አይነት ጩልሌ
መሸነፍ አልፈቅድም፣
አካሌ እንደባዳ ልቀቂኝ እያለ
ሁሌ ከሚወቅሰኝ፣
ልለምንህ በቃ በምትወደው ነገር
ተወኝ አትጥቀሰኝ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

22.3k 0 163 14 124

ትውስታው ገዳይ ነው


ኣንቺን ያየሁሽ ቀን የተሰማኝ ስሜት የተሰማኝ ህመም
ቃላትን ደርድሬ ባፌም ተናግሬ ልገልፀው አልችልም
ካገኘውሽ ወዳ ነግሬሽ ነበረ ለቅሜ ሁሉንም
ኣልገባሽም ብዬ ያረገኝን ሁሉ ፅፌያለሁም ግጥም
መልላ አካላቴ ስላንቺ ያስባል
የሁለት እጆቼ ጣት ኣንቺን በመዘከር ግጥም ይደርሳል
ቢሆንም ሃዊዬ የኔ ያንቺ ነገር ለትዝታ ሲቀር
ትውስታው ገዳይ ነው በናፈቅሽኝና
ባስታወስኩሽ ቁጥር
መገናኛችንን ድልድዩን ተሻግሮ አደረግነውና
በሄድኩ በመጣው የማይሽ ይመስል አንገቴን ሳቃና
የቆምንበት ቦታ ሁሌም ኣየዋለሁ አቱኩሬ በጠና
እንደውም ኣንዳንዴ ያቺ ትልቋ ፖል
ትንሽ ወጣ ብላ በመንገዱ መሀል
ቆማ ምትገኘው በማብራቶቹ ሀይል
የምንደገፋት ወሬያችን ስንቀጥል
ሁሌም አያታለሁ በሄድኩ በመጣው
ኣንቺን ያየሁ ይመስል
እናም ይኽቺ ፖል ኣንቺን ለመዘከር አለች ልቤ መሀል
እድሜ ልካችንን ኣንድ ላይ ባንኖርም
እጅ ተያይዘን ስቀን ባንቦርቅም
ኣንድ ላይ ባንበላ ኣንድ ላይ ባንጠጣም
ያሳለፍነው ጊዜ ለፍቅር አያንስም
ታስታውሺ እንደሆነ ጊዜ የፈተነን
ብዙ እንዳንቆይ ጊዜያችን ጠቦን
ወድያው ስንለያይ ወድያው ተገናኝተን
ፈተና ገጥሞናል ከለታት ኣንድ ቀን
በዛች በአጭር ሳት ቀጠሮ አድርገን
እዛው እኛው ሰፈር መንገድ ተጠፋፍተን
እጅግ ተናደናል ሳንገናኝ ገብተን
በኔው በቤቱ ልጅ ያቺ የያዝሻት ሙድ
እያሳቀችኝ ነው መንገድ ላይ እንደ እብድ
ሰፈሩን የማያውቅ ኣንተን አየሁኝ ወንድ
ለማለት አበቃሽ በኔ ለመያዝ ሙድ
በኔስ መቼ ጠፋኝ የሰፈሬ መንገድ
ተደናብሮ እንጂ ልቤ ባንቺ መውደድ



ሃዊዬ በሚለው የራሳቹን ሰው አርጉ እኔ
ሃዋ / ሄዋን በሚለው ነው የያዝኩት

Semer / Almeshan


https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


😔😔   #መልስህን ንገረኝ  😔😔

ድሮስ የወደደውን መች ሰው ይፈልጋል
የማይፈልገውን ሄዶ ይለምናል።

    እኔም ከነዛ ውስጥ አንዷ ነሽ ብለዋል
    አንተ የኔ እንደሆንክ ማን በቅጡ ያቃል።

እኔ ስፈልግህ አንተስ እርቀሀል
እንዴት የኔ ላርግህ ሌላ ሰው ይዘሀል።

      የኔን ልብ ስሰጥህ መች አንተ ይገባሀል
       ለኔ ያለህን ስሜት ማወቅ ተስኖኛል።

እኔ አንተን ስፈልግ አንተ ስትል ሌላ
የኔ ልብ በስቃይ በሀዘን ተሞላ።

       አሁን የማሳይህ ላይገባህ ይችላል
       ስታቀው ሲገባህ እግርህ ይመልስሀል።

ተስፋ እንዳትቆርጥ ልቤ ይቀበልሀል
ጥላቻንም ገፍቶ ፍቅርን ያለብስሀል።

        በርግጥ አልዋሽህም ልቤ ይፈልግሀል
        በአፍ ባልነግርህም አይኔ አሳይቶሀል።

አልገባኝም ማለት አውቃለው እንደምችል
ግን ጥቅም የለውም አይገባኝም ብትል።

         አውቃለው እንደሌለህ የኔ እምትላት
         እኔ እኮ የለኝም የቅናት ስሜት።

ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እባክህ
ልሂድልህ በቃ ሙሉ ከሆነ ልብህ።

         ልቤ መውደድ ይበቃሀል
         ለእሱ እኔ አለሁ ለኔ ማን ያስብልብኛል።

የሰማዩ ጌታ የኔ ሁን ካላለው
ለኔ የፃፈውን እስኪ ልፈልገው።

         ካንተ ጋር መሆኑን ልቤ ይመኘዋል
          ያላንተ መኖሩን እንዴት ይችለዋል።

አንድ ቀን አስበህው ይገባህ ይሆናል
የሰው ልብ እንዲ ነው በተራው ይመጣል።

          ፈላጊ ነኝ እንጂ ማን ይፈልገኛል
          የሚፈልገኝስ መቼ ፍቅር ያውቃል
          እስኪጠግበኝ ብቻ ከጎኔ ይቆያል።


https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

Показано 19 последних публикаций.