GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ

Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана

ይህ የቴሌግራም ቻናል በኢትዮጽያ ሙሉ ወንጌል አማኛች ቤተክርያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ፣የሚከናወኑና የሚተገበሩ ፕሮግራምዎችን መከታተያ page ነው፡፡
this is official page of goro sefera full gospel believers church...
If you have any question Contact:
@Kirubel76
@pastor_sisay

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций

Репост из: Ethiopian Full Gospel Believers Church
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት !!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

Репост из: Ethiopian Full Gospel Believers Church
#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያንና በፓስተር ዮናታን አክሊሉ በትብብር የሚሰራ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ እንዳለ ተደርጎ እየተሠራጨ ያለው ማስታወቂያ ፍፁም ሀሰትና ማጭበርበር ስለሆነ ቅዱሳን ከዚህ የማታለል ድርጊት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን በነገው እለት ቤተክርስቲያኗ ማብራሪያ የምትሰጥ መሆኑን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።
  👉ለሁሉም እንዲደርስ በአስቸኳይ share share ይደረግ!!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
https://vm.tiktok.com/ZMkkgLdDk/

ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ የጸሎት ቤቱ ጽዳት ሰላለ ሁላችሁም እንድትገኙና እንዳጸዳ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን

Репост из: GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ወንድማችን ቢቂላ ሂካ አባቱ አርፈው ለቀብር ሰለሄዱ ሲመጣ ልቅሶ እንድትደረሱ እና ሰልክም በመደወል እንድታጽናኗቸው በጌታ ፍቅር እናሳስባለን

ሰልክ
091 181 5682

አስሩ ምርጥ ምርጫዎች!

1.  ከመጥላት ይልቅ መውደድን እንምረጥ!

2.  ከመኮሳተር ይልቅ ፈገግታን እንምረጥ!

3.  ከማፍረስ ይልቅ መገንባትን እንምረጥ!

4.  ከማቆም ይልቅ እስከ ግባችን ድረስ መቀጠልን እንምረጥ!

5.  ከማማት ይልቅ ማመስገንን እንምረጥ!

6.  ከማቁሰል ይልቅ መፈወስን እንምረጥ!

7.  ከመውሰድ ይልቅ መስጠትን እንምረጥ!

8.  ከመዘግየት ይልቅ እርምጃን መውሰድ እንምረጥ!

9.  ከመጨነቅ ይልቅ መጸለይን እንምረጥ!

10.  ከመቀየም ይልቅ ይቅርታን እንምረጥ!

ምንጭ ኢዮብ

ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ወንድማችን ቢቂላ ሂካ አባቱ አርፈው ለቀብር ሰለሄዱ ሲመጣ ልቅሶ እንድትደረሱ እና ሰልክም በመደወል እንድታጽናኗቸው በጌታ ፍቅር እናሳስባለን

ሰልክ
091 181 5682

ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ከፊታችን ሰኞ 21/04/2017 ዓም እሰከ 27/2017ዓም ድረስ ጾምና ጸሎት ይኖረናል ሁላችን ተገኝተን በጋራ የእግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ፊት እንድንፈልግ ሰንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን

በጾምና ጸሎት መጨረሻ ቀን ማለትም በ27/04/2017 ዓም እሁድ የጌታ እራት ይኖረናል

ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 2:30 ይጀምራል

የተለያዩ አዋቂዎች የሚነግሩን በጥቂቱ ቢለያይም አንድ ጤናማ ሰው በደቂቃ በአማካኝ በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ ሊተነፍስ ይችላል፡፡

ይህ የመተንፈስ ስጦታ በዚህች ምድር ላይ በሕይወት እንድንኖር ፈጣሪ ከሰጠን ታላላቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው ነው፡፡

ይህንን ሰዎች ከእነሱ እንዳይወሰድባቸው ምንም ነገር ከመክፈል ወደኋላ የማይሉትን በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ የመተንፈስ ስጦታ በየደቂቃው እደጋገመ ከ 20 ጊዜ በላይ ፈጣሪ ከሰጠን፣ ለህልውናችን እምብዛም መዋጮ ለሌላቸው ነገሮች መጨናነቃችንን ትንሽ ቀነስ አድርገነው ወደ ሰራችን ብንሄድ ምን ይመስላችኋል?

መልካም የሰራ ቀን

ምንጭ ዶክተር ኢዮብ

Репост из: GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ
የስህተትን መንፈስ መለየት
2ኛ ዮሐ 1:7-13

  ቤተክርስቲያን በየዘመኑ የገጠማትና ሲፋለማት የኖረው ፣ አሁንም የሚገዳደራት አንድ ነገር ቢኖር የስህተት ትምህርት ነው ። ጌታ በዚህ ጉዳይ አስጠንቅቆአል “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ " ማቴ 7:15 ከዋርያትም መካከል ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ሲያስጠነቅቅ " ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ " ሐዋ 20:29,30 ዮሐንስ ራሱም " ወዳጆች ሆይ ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና " 1ዮሐ 4:1 ብሎአል ። ጴጥሮስም በ2ኛ ጴጥ 2:1 ላይ እንዲሁ ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ ተናግሮአል ። ስለ ሐሰት ትምህርት መረዳት የሚገባን ዋና ነገር ቢኖር አእማድ በሆኑ አስተምህሮቶች ላይ ልዩነት አለመኖሩን ነው እንጂ ከዚያ ውጪ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶች ላይ እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩነት አይኖረውም ማለት አይደለም ነገር ግን የትኛውም ልዩነት ይኑር የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ የምንማር ከሆንን በየትኛውም ወጥመድ አንያዝም ። ስለዚህ ዮሐንስ በዚህ ክፍል ስለ ስህተት አስተምህሮ ይህንን ይላል :-

1. አሳቹ እየሰራ ነው

  " ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል ። እንዲህ ያለ ማንኛውም ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ... በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም ፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው" 2ኛ ዮሐ 1:7,9

  የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አሁን እየሰራ ነው ። ይህ መንፈስ የትኩረት አቅጣጫው ሰወች ስለ ክርስቶስ የተዛባ መረዳት ይኖራቸው ዘንድ ነው ምክንያቱም የድነታችን መሰረቱ የተገነባው ክርስቶስን በተረዳንበት ልክ ላይ መሆኑን ሰይጣን ስለሚያውቅ ነው ። በዮሐንስ ዘመን የነበረው የተሳሳተ አስተምህሮ ክርስቶስ በስጋ አልተገለጠም የሚል ሲሆን በየዘመናቱ እንዲሁም ዛሬ በክርስቶስ ላይ የሚነሱ የስህተት ትምህርቶች ብዙ ናቸው ። ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ብቸኛው መንገድ ሆኖ እያለ በእርሱ ላይ የሚጨመሩ ብዙ ግሳንግሶች ዛሬም አእላፋትን በውጭ እያስቀራቸው ይገኛል ። እንዲህ ዓይነቱ አስተማሪ እንደ ዮሐንስ አገላለጥ አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ። በክርስቶስ ላይ ከሚነሱ ስህተቶች መካከል በስጋ መገለጡን መካድ ፣ ኢየሱስን ሰው ብቻ አድርጎ መለኮትነቱን መካድ ፣ ብቸኛ አዳኝና አማላጅ መሆኑን መካድ ፣ የአብን የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ጨፍልቆ ኢየሱስ ብቻ በማለት የስላሴን ህልውና መካድ ፣ ክርስቶስ በመስቀል አልሞተም ብሎ ሞቱን መካድ ወዘተ ... ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ። ማንም ክርስቶስ ከተሸፈነበት አብም የለውም ምክንያቱም አብ ራሱ ያለ ወልድ ሊታወቅ አይችልምና ነው ጌታ ሲናገር " ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል ፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም፡” አለ " ሉቃ 10:22

2. አለመተባበር

" ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ፣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ፤ ሰላምም አትበሉት ፤ የሚቀበለው ሰው ፣ የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና " 2ኛ ዮሐ 1:10,11

  የክርስቶስን ጤናማ ትምህርት ይዞ ከማናገኝበት ከየትኛውም ሰው መራቅ ፣ ትምህርቶቹንም አለመስማት እጅግ ተገቢ ጉዳይ ነው ። በቀድሞዋ ቤተክርስቲያን የስብሰባ ስፍራቸው ቤት ለቤት ስለ ነበር ይህንን ቀክፍተት በመጠቀም ክፉው እየሾለከ ይገባ ነበር ። ዛሬም በየቤታችንም ሆነ በየመድረኮቻችን የአስተምህሮ አቋሙን ሳናውቅ በሩን መክፈት ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ። ነገር ግን ሰወችን በአስተምህሮታቸው እንጂ በህይወት ድካማቸው መግፋት የለብንም ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ሲናገር " በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት ፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ " ሮሜ 14:1 እንዲሁም በገላትያ  " ወንድሞች ሆይ ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት ... " ገላ 6:1 መባሉን መዘንጋት አይገባም ።

3. ለአገልጋዮች ቦታ በመስጠት

  " የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ፤ ይሁን እንጂ በወረቀትና በቀለም እንዲሆን አልፈልግም ፤ ዳሩ ግን ደስታችን ፍጹም ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ " 2ኛ ዮሐ 1:12

  ሐዋርያው በኤፌሶን አካባቢ ወደ ነበሩት አብያተክርስቲያናት እንዳገለገለ ታሪክ ይናገራል ። ዮሐንስ እጅግ በሰፊው በልቡ ያለውን ይጽፍላቸው ዘንድ አልወደደም ይልቁንም ፊት ለፊት በመገናኘት በክርስቶስ ያገኙትን ደስታ አብሮ ለማጣጣምና በሰፊው ለማስተማር ይፈልጋል ። እንዲሁም እኛ በክርስቶስ ያገኘነውን ደስታ ለመካፈል ያሉንን አገልጋዮች ለመቀበልና ከእነሱም ለመማር የተከፈተ ልብ ልናገኝ ይገባል ። በዚህም መንገድ ከብዙ የተፋለሱ አስተምህሮቶች እንድንጠበቅ ይረዳናል ።

            ምንጭ ወዊ ምንተሰኖት

Luke 5 አማ - ሉቃስ
4: ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፡” አለው።

ኦሪት ዘጸአት 17
Exod 17
1 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም።

1 And all the congregation of the children of Israel journeyed from the wilderness of Sin, after their journeys, according to the commandment of the Lord, and pitched in Rephidim: and there was no water for the people to drink.

2 ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት። የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው።

2 Wherefore the people did chide with Moses, and said, Give us water that we may drink. And Moses said unto them, Why chide ye with me? wherefore do ye tempt the Lord?

3 ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ። እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ።

3 And the people thirsted there for water; and the people murmured against Moses, and said, Wherefore is this that thou hast brought us up out of Egypt, to kill us and our children and our cattle with thirst?

4 ሙሴም፦ ሊወግሩኝ ቀርበዋልና በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።

4 And Moses cried unto the Lord, saying, What shall I do unto this people? they be almost ready to stone me.

5 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ።

5 And the Lord said unto Moses, Go on before the people, and take with thee of the elders of Israel; and thy rod, wherewith thou smotest the river, take in thine hand, and go.

6 እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።

6 Behold, I will stand before thee there upon the rock in Horeb; and thou shalt smite the rock, and there shall come water out of it, that the people may drink. And Moses did so in the sight of the elders of Israel.

7 ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር። እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።

7 And he called the name of the place Massah, and Meribah, because of the chiding of the children of Israel, and because they tempted the Lord, saying, Is the Lord among us, or not?

8 አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።

8 Then came Amalek, and fought with Israel in Rephidim.

9 ሙሴም ኢያሱን፦ ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው።

9 And Moses said unto Joshua, Choose us out men, and go out, fight with Amalek: to morrow I will stand on the top of the hill with the rod of God in mine hand.

10 ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ።

10 So Joshua did as Moses had said to him, and fought with Amalek: and Moses, Aaron, and Hur went up to the top of the hill.

11 እንዲህም ሆነ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።

11 And it came to pass, when Moses held up his hand, that Israel prevailed: and when he let down his hand, Amalek prevailed.

12 የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ።

12 But Moses' hands were heavy; and they took a stone, and put it under him, and he sat thereon; and Aaron and Hur stayed up his hands, the one on the one side, and the other on the other side; and his hands were steady until the going down of the sun.

13 ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ።

13 And Joshua discomfited Amalek and his people with the edge of the sword.

14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ ተናገር አለው።

14 And the Lord said unto Moses, Write this for a memorial in a book, and rehearse it in the ears of Joshua: for I will utterly put out the remembrance of Amalek from under heaven.

15 ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም ይህዌህ ንሲ ብሎ ጠራው

15 And Moses built an altar, and called the name of it Jehovah–nissi:

16 እርሱም፦ እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ።

16 For he said, Because the Lord hath sworn that the Lord will have war with Amalek from generation to generation.

የስህተትን መንፈስ መለየት
2ኛ ዮሐ 1:7-13

  ቤተክርስቲያን በየዘመኑ የገጠማትና ሲፋለማት የኖረው ፣ አሁንም የሚገዳደራት አንድ ነገር ቢኖር የስህተት ትምህርት ነው ። ጌታ በዚህ ጉዳይ አስጠንቅቆአል “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ " ማቴ 7:15 ከዋርያትም መካከል ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ሲያስጠነቅቅ " ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ " ሐዋ 20:29,30 ዮሐንስ ራሱም " ወዳጆች ሆይ ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና " 1ዮሐ 4:1 ብሎአል ። ጴጥሮስም በ2ኛ ጴጥ 2:1 ላይ እንዲሁ ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ ተናግሮአል ። ስለ ሐሰት ትምህርት መረዳት የሚገባን ዋና ነገር ቢኖር አእማድ በሆኑ አስተምህሮቶች ላይ ልዩነት አለመኖሩን ነው እንጂ ከዚያ ውጪ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶች ላይ እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩነት አይኖረውም ማለት አይደለም ነገር ግን የትኛውም ልዩነት ይኑር የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ የምንማር ከሆንን በየትኛውም ወጥመድ አንያዝም ። ስለዚህ ዮሐንስ በዚህ ክፍል ስለ ስህተት አስተምህሮ ይህንን ይላል :-

1. አሳቹ እየሰራ ነው

  " ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል ። እንዲህ ያለ ማንኛውም ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ... በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም ፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው" 2ኛ ዮሐ 1:7,9

  የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አሁን እየሰራ ነው ። ይህ መንፈስ የትኩረት አቅጣጫው ሰወች ስለ ክርስቶስ የተዛባ መረዳት ይኖራቸው ዘንድ ነው ምክንያቱም የድነታችን መሰረቱ የተገነባው ክርስቶስን በተረዳንበት ልክ ላይ መሆኑን ሰይጣን ስለሚያውቅ ነው ። በዮሐንስ ዘመን የነበረው የተሳሳተ አስተምህሮ ክርስቶስ በስጋ አልተገለጠም የሚል ሲሆን በየዘመናቱ እንዲሁም ዛሬ በክርስቶስ ላይ የሚነሱ የስህተት ትምህርቶች ብዙ ናቸው ። ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ብቸኛው መንገድ ሆኖ እያለ በእርሱ ላይ የሚጨመሩ ብዙ ግሳንግሶች ዛሬም አእላፋትን በውጭ እያስቀራቸው ይገኛል ። እንዲህ ዓይነቱ አስተማሪ እንደ ዮሐንስ አገላለጥ አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ። በክርስቶስ ላይ ከሚነሱ ስህተቶች መካከል በስጋ መገለጡን መካድ ፣ ኢየሱስን ሰው ብቻ አድርጎ መለኮትነቱን መካድ ፣ ብቸኛ አዳኝና አማላጅ መሆኑን መካድ ፣ የአብን የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ጨፍልቆ ኢየሱስ ብቻ በማለት የስላሴን ህልውና መካድ ፣ ክርስቶስ በመስቀል አልሞተም ብሎ ሞቱን መካድ ወዘተ ... ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ። ማንም ክርስቶስ ከተሸፈነበት አብም የለውም ምክንያቱም አብ ራሱ ያለ ወልድ ሊታወቅ አይችልምና ነው ጌታ ሲናገር " ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል ፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም፡” አለ " ሉቃ 10:22

2. አለመተባበር

" ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ፣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ፤ ሰላምም አትበሉት ፤ የሚቀበለው ሰው ፣ የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና " 2ኛ ዮሐ 1:10,11

  የክርስቶስን ጤናማ ትምህርት ይዞ ከማናገኝበት ከየትኛውም ሰው መራቅ ፣ ትምህርቶቹንም አለመስማት እጅግ ተገቢ ጉዳይ ነው ። በቀድሞዋ ቤተክርስቲያን የስብሰባ ስፍራቸው ቤት ለቤት ስለ ነበር ይህንን ቀክፍተት በመጠቀም ክፉው እየሾለከ ይገባ ነበር ። ዛሬም በየቤታችንም ሆነ በየመድረኮቻችን የአስተምህሮ አቋሙን ሳናውቅ በሩን መክፈት ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ። ነገር ግን ሰወችን በአስተምህሮታቸው እንጂ በህይወት ድካማቸው መግፋት የለብንም ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ሲናገር " በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት ፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ " ሮሜ 14:1 እንዲሁም በገላትያ  " ወንድሞች ሆይ ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት ... " ገላ 6:1 መባሉን መዘንጋት አይገባም ።

3. ለአገልጋዮች ቦታ በመስጠት

  " የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ፤ ይሁን እንጂ በወረቀትና በቀለም እንዲሆን አልፈልግም ፤ ዳሩ ግን ደስታችን ፍጹም ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ " 2ኛ ዮሐ 1:12

  ሐዋርያው በኤፌሶን አካባቢ ወደ ነበሩት አብያተክርስቲያናት እንዳገለገለ ታሪክ ይናገራል ። ዮሐንስ እጅግ በሰፊው በልቡ ያለውን ይጽፍላቸው ዘንድ አልወደደም ይልቁንም ፊት ለፊት በመገናኘት በክርስቶስ ያገኙትን ደስታ አብሮ ለማጣጣምና በሰፊው ለማስተማር ይፈልጋል ። እንዲሁም እኛ በክርስቶስ ያገኘነውን ደስታ ለመካፈል ያሉንን አገልጋዮች ለመቀበልና ከእነሱም ለመማር የተከፈተ ልብ ልናገኝ ይገባል ። በዚህም መንገድ ከብዙ የተፋለሱ አስተምህሮቶች እንድንጠበቅ ይረዳናል ።

            ምንጭ ወዊ ምንተሰኖት

#ለመልካም_ሆነልኝ!!

ለካ ይታለፋል ማይታለፈው
ከልኩ አያልፍም የሰው ፈተናው
ምጠፋ መስሎኝ ፈራች እንጂ ነፍሴ
ለካ ያስጨነከኝ ለጥቅሜ ለራሴ
በእሳት እያለፍኩ ስፈተን
ወርቅ አደረገው ህይወቴን

ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ
አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ
ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ
አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ
ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ
ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ
ልቤን አጀገነው ቅዱሱ መንፈስ
ቀዝቃዛ ሂወቴ በፈተናው ሞቀ
እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ
ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ
መቼ መሰለኝ የምሰራ
ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ
እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ

ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ (2X)
ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ (2X)
ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ
ለመልካም ሆነልኝ ያስጨነከኝ
ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ
ለበጎ ሆነልኝ ያስጨነከኝ

በመከራ ውስጥ መታዘዝን ተማረ
በስጋው ወራት አንተን አከበረ
እኛ ዳንን እንጂ በእርሱ መከራ
ህይወታችን ጣፍጧል በጠጣው መራራ
እሱ ኃያል ሳለ ምስኪን መሰለ
ከአመፀኞች ጋር ተሰቀለ
በጌታ መከራ ስንቶች ዳኑ
አቀረባቸው ወደ ዙፋኑ
ጌታ ሆይ...

Bereket Tesfaye...

ማክሰኞ 15/04/17

የሁለተኛ ዮሐንስ መልዕክት ( ክፍል 02 )

እውነትና የፍቅር ቁርኝት
2ኛ ዮሐ 1-3

  ዮሐንስ ከጌታ ሐዋርያት መካከል የፍቅር ሐዋርያ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ወንጌሉን ሲጽፍም ኢየሱስ ይወደው የነበረ ደቀመዝሙር በሚል የብዕር ስም ስለራሱ ጽፎአል ። ዮሐንስ እውነት ፣ ፍቅር ፣ ብርሃን ወዘተ የሚሉ ቃላትን በብዙ ይጠቀማል ። ዮሐንስ በወንጌሉ ፣ በሶስቱ መልዕክቶቹና በራዕይ ውስጥ እውነት የሚለውን ቃል 122 ጊዜ ተጠቅሞአል ። ይህ የሚያሳየን ከምንም ነገር በፊት ቀዳሚውና ወሳኙ ጉዳይ እውነት መሆኑን ያሳየናል ። እውነትን ሳንይዝ እርስ በእርስ መዋደድ ፣ በአርነት መመላለስ ፣ በሁሉ አቅጣጫ ድል የሞላው ህይወት መኖር አይቻልም ። ባጠቃላይ እውነት ራሱ ክርስቶስ በመሆኑ እውነት በሌለበት መልካም ነገር የለም ። ዮሐንስ በዚህ በመልዕክቱ መግቢያ ላይ የእርስ በእርስ መዋደድ መሰረቱ እውነት እንደሆነ ፣ እውነት የሚገዛው የሰውን ልብ እንደሆነና መገኛውም ክርስቶስ መሆኑን በማሳየት መልዕክቱን ይጀምራል ።

1. በእውነት መዋደድ

  " ሽማግሌው ፤ በእውነት ለምወዳት እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዷት ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆቿ " 2ኛ ዮሐ 1:1

  እውነት የያዘ ፣ እውነትን የሚናገርና በእውነት የሚኖር ሰው እውነትን የሚወዱ ሁሉ ይወዱታል ። ነገር ግን ዛሬ ዛሬ እውነትን የያዘና በእውነት የሚሄድ ሰው ሳይሆን ተወዳጁ እውነትን የሚያመቻምች ፣ አስመሳይና ውሸታም ፣ እውነትን በአመጻ የሚከለክል ሰው ነው ተቀባይነትና ተከታይ ያለው ። ዮሐንስ የሚጽፍላት ይህች የቤተክርስቲያን መሪ የሆነች ሴት በእውነት ላይ በመቆሟ እንደሚወዳት እሱ ብቻ ሳይሆን እውነት የሚወዱ ሁሉ እንደሚወዱአት ስለ እርስዋ የሚያውቀውን ምስክርነት ይነግራታል ። ይህች ሴት ይህችን ቤተክርስቲያን ለመምራት ያስቻላትና ለዚህ ተግባር የተመረጠች ያደረጋትም እውነትን የያዘችና ለእውነት የቆመች በመሆንዋ ነው ። እውነትና ፍቅር አንዱ ከሌላው ጋር ተቃቅፈው የሚኖሩ ናቸው እውነት ባለበት ፍቅር አለ ፍቅር ባለበት እውነት አለ ጳውሎስ ሲናገር ፍቅር " ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም " 1ኛ ቆሮ 13:6 እንዲሁም በኤፌሶን መልዕክቱ ላይ " ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ " ኤፌ 4:15 ሁለቱ የተጣመሩ ናቸው ። የእርስ በእርስ ያለን ፍቅር እየጎለበተ ሊሄድ የሚችለው በእውቀትና በማስተዋል እያደግን በሄድን ቁጥር ብቻ ነው ስለዚህ ጳውሎስ እንዲህ ይጸልያል "  ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ " ፊል 1:9

2. የእውነት መኖሪያ

  " በውስጣችን ከሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ከሚሆን እውነት የተነሣ " 2ኛ ዮሐ 1:2

  እውነት የሚኖረው በሰው ውስጥ ነው ። የሰው ልብ በእውነት ሲማረክ ፣ እውነት በውስጣችን ሲኖር የለውጥ ጅማሮ ያለው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው  ። አንድ ጊዜ እውነት በውስጣችን ከሰረጸች ማንም ሊያወጣት አይችልም ፣ እውነትን የሚወዱ ሁሉ እውነት የዘላለም ወዳጅ ናት ። ጌታ ኢየሱስ ማርያም ቃሉን ከመስማት ተነስታ እንድታግዛት እንዲያደርግ ማርታ ስትጠይቀው " ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት ፤ “ማርታ ፣ ማርታ ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ ፤ ትዋከቢአለሽም ፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው ፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች ፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም " ሉቃ 10:41,42 እውነት አንድ ጊዜ ውስጣችን ከገባ ማንም ሊወስደው አይችልም ። እውነት የእግዚአብሔር ቃል ነው ጌታ ሲናገር " በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው " ዮሐ 17:17 ቃሎቹ በኛ ካሉ ጸሎታችን እንኳ ውጤታማ ይሆናል " በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል " ዮሐ 15:7 ሰይጣን ተግቶ የሚሰራው እውነት በውስጣችን መኖሪያዋን እንዳታደርግ ነው " የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ ፥ ክፉው ይመጣል ፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል ... " ማቴ 13:19

3. የእውነትና የፍቅር ምንጭ

  " ከእግዚአብሔር አብና የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ፣ ምሕረትና ሰላም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናል " 2ኛ ዮሐ 1:3

  የእውነት መገኛው እግዚአብሔርን በክርስቶስ የሚያውቅና ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የተረዳና ይህ እውነት የተገለጠለት ሰው ብቻ ነው ። አማኝ የክርስቶስ ጸጋና ምህረት ሲገባው ህይወቱ በሰላም ከመትረፍረፉም በላይ እውነትንና ፍቅርን ገላጭ ይሆናል ። ክርስቶስን የተረዳ ሰው እውነትን ወይም ቃሉን በሚገባ የመረዳት ብቃት አለው ክርስቶስን ያለተረዳ ሰው እውነትን አያውቅም የእውነት መገኛዋና ትክክለኛ ስፍራዋ ክርስቶስን በማወቅ ውስጥ ነው ። ጌታ ኢየሱስ ፈሪሳውያን ለምን ቃሉን መስማት እንዳልቻሉ ሲናገር " ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው ? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው ። እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ ... " ዮሐ 8:43,44

ምንጭ ወዊ ምንተስኖት

Показано 20 последних публикаций.