ኮሮና COVID—19
ሙዕሚን እና ወረርሽኝ
ምንም እንኳን ሰዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በህክምናውና በሌሎችም ዘርፎች የቱንም ያህል ቢመጥቁ ሁሌም የአላህ እገዛ እንደ ሚያስፈልጋቸውና ከርሱ እገዛና እርዳታ እንደማይብቃቁ እንዲረዱ ብሎም እንዳይዘነጉ የአለማቱ ጌታ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይፈትናቸዋል።
ወዳጄ ሆይ!
መከራን የሚያስወግደው አላህ ነው!
ካጋጠመን ፈተናም የሚያወጣን ረበል አለሚን ነው!
ከበሽታ የሚፈውሰንም እርሱ ፈዋሽ የሆነው ጌታችን ነው!
አላህ እንዲህ ይላል:—
﴿ وَإِنْ يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ وَإِنْ يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴾ [الأنعام: 17]
《አላህ አንዳች ጉዳት እንዲያገኝህ ቢያደርግ ከርሱ ውጭ ጉዳቱን የሚያነሳልህ የለም። መልካም ነገር እንዲያገኝህ ቢያደርግም እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነው።》
አል—አንዓም/17
በሌላ አንቀፅም እንዲህ ይለናል:—
﴿ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ ﴾ [الشعراء: 80]
《ስታመምም ፈውስን ይለግሰኛል።》አል—ሹዐራእ/80
ኢስላም ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊትም ይሁን ከተከሰተ በኋላ መፍትሄዎችን አስቀምጧል። ማንኛውም ወረርሽኝ ሲከሰት አንድ ሙዕሚን የሆነ ሰው ወረርሽኙ የተከሰተው በአላህ ውሳኔ መሆኑን ሊያውቅ ይገባዋል። ይህ የአላህ ውሳኔ የመጣው አንድም ለበጎ ይሆናል አሊያም በተቃራኒው ቅጣት ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ከስድስቱ የእምነት ማዕዛናት አንዱ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።
"الإيمان بالقضاء والقدر"
ወዳጄ ሆይ!
በሽታ ከአላህ ነው ፈውስም እንዲሁ ከአላህ ነው!
ህያው የሚያደርገው አላህ ነው ልክ እንደዚሁ ሞትንም የሚወስነው ህያው የሆነው ጌታችን ነው!
አላህ አንድን በሽታ ሲያወርድ አብሮት መድሀኒቱን ያወርዳል ፤ ይህን የሚያውቅ ያውቀዋል የማያውቅ ደግሞ አያውቅ ይሆናል እንጂ። ይህንን በተመለከተ በርካታ ነብያዊ ሀዲሶች ከረሱል ﷺ ደርሰውናል። ለምሳሌ አቡ ሁረይራ ሲናገሩ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ይሉናል:—
【አላህ (ማንኛውንም) በሽታ አላወረደም አብሮት መድሀኒቱን (መፈወሻውን) ያወረደ ቢሆን እንጂ።】ቡኻሪና ሙስሊም
ሀቢቢ!
በበሽታ መፈተንህ ደረጃህን ከፍ ሊያደርግልህ ፤ ጌታህንም ከወንጀል የፀዳህ ሆነህ ትገናኝ ዘንድ ሊሆን እንደሚችል ተረዳ። ምን አልባትም በዚህ ወረርሽኝ ህይወትህ ቢያልፍ እንኳ ምንዳህ ከነዚያ ከሹሀዳኦቹ ጋር እንደሚስተካከል እወቅ። ይህ አላህ ለመረጣቸው ባሮቹ ከሚሰጣቸው ችሮታዎቹም ይመደባል።
ይህንን በተመለከተ ረሱል ﷺ እንዲህ ይሉናል:—
【ወረርሽኝ ( በወረርሽኝ መሞት) ለሙስሊሞች ሁሉ የሰማዕታትን (ደረጃ የሚያስገኝ) ነው።】ቡኻሪና ሙስሊም።
ብዙዎች በዚህ ወረርሽኝ መከሰት ሲደናገጡ ሌሎች ደግሞ በተለያዩ መንገዶች ነገሩን ከሚገባው በላይ በማግዘፍ ሌሎችን ሲያደናብሩና ሰላም ሲያሳጧቸው እንመለከታለን። እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሙስሊሙ አቋም ምን መሆን አለበት!? ከመጠን በላይ በፍርሃት ሊዋጥና ሊደናገጥ ይገባዋልን!?
በጭራሽ!
ሙዕሚን አላህ ከወሰነበት ውሳኔ የትም ቢሄድ የትም ቢሸሸግ እንደማያመልጥ ያውቃል። እንዲህ አይነት ፈተና ሲያጋጥመውም መጀመርያ ሊፈፅመው የሚገባው ትልቁ ስራ ወደ አላህ መመለስና እርሱን መማፀን ሊሆን ይገባል። ከዚህ ውጪ ክስተቱን በማጋነን ወንድሞቹንና እህቶቹን ከማስጨነቅና ከማስደንገጥ ሊቆጠብ ግድ ይላል።
ሰዎችን ማስደንገጡ ከበሽታው ራሱ የከፋ ሊሆን ይችላልና።
ሰዎችን ማስደንገጥና ማደናበር ሀራም እንደሆነና ይህ ከመናፍቃን መገለጫ ባህሪ እንደሆነ ሲያስታውሰን አላህ እንዲህ ይላል:—
{ وَإِذَا جَاءهُمْ أَمْرٌ مِّنَ الأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُواْ بِهِ}
سورة النساء83
《ከሰላም ወይም ከፍርሃት ጋር ግንኙነት ያለው አንዳች ነገር በመጣላቸው ጊዜ (ወሬውን) አጋነው ይረጩታል።》አን_ኒሳዕ/83
ይህ እንዳለ ሆኖ በበሽታው ላለመጠቃት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ኢስላም ያስተምረናል። አላህ ይጠብቀኛል ብሎ እጅ አጥፎ መቀመጥ ከኢስላም አስተምህሮ አይደለም። ይልቁኑስ ረሱል ﷺ ያስተማሩንን አዝካሮችና ዱኣዎችን ማዘውተር እንዲሁም ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡንን ምክሮችና ጥቆማዎችን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ ይሆናል።
ሙዕሚን እራሱም ይሁን ሌሎች በበሽታው እንዳይጠቁ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድራጊ ነው።
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech አቡ ቁዳማ