👉አጠር ያለ አስተማሪ መልዕክት👈
♥አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ
በመዓበል ተመታና መርከብ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ
ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው
እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብን ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።
♥አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት
ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ,,,,,,,እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዎን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጣሪወን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለክኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ
አማረረ,,,,,,,, ከደቂቃዎች በዋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ
ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ ,,,,,, የመርከብ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ ?
አላቸው ,,,,, መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን
እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭሰ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት።
♥አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ
ነው ትንሻ ጎጆዬን ያፈርሰከው ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው ። አለ
♥አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት
ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን ።
🌹ያጣነውን የሰጠን አንድዬ ! አህምሮችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን !
ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ማድረጎን አይርሱ
🌷መልካም ቆይታ🌷
🌹🌷🌷🌹
🌹
ጎራ በሉ👇👇👇
@TRUTHZONE @TRUTHZONE