🌛Halal _Image & Quotes  ሀላል ምስል


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


♻️ በዚህ ቻናል ላይ ፦
💡የቁርኣን አንቀፆች
💡የ ረሱልﷺ ሃዲሶች
💡ሀላል የሆኑ ምስሎችና መረጃዎች እንዲሁም ኢስላማዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ።
📩For any comment & promo👇
@halal_image_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


አላህ ይዉደደን፣ በምሀረቱም ይክበበን፣ ብቸኛ ረዳታችን፣ አጋዣችን፣ ጠባቂያችን፣ የልባችንም ጠጋኝ ይሁነን፣ መልካሙን ሁሉ ይመንዳን፣ ከሸይጣን ተንኮልም ይጠብቀን ፣በሀቅ ከሚያመልኩት፣ ከሚፀፀቱት፣ ወደሱ ከሚመለሱትም፣ ያድርገን መጨረሻችንንም ያሳምርልን።አሚን ጌታችን አለህ ሆይ ስማን


ረመዷን 40 ቀን ብቻ ቀሩት🌙
اللهم بلغنا رمضان🌙


🌙በየወሩ ሶስት ቀናት መፆም🌙
ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “በየወሩ ሶስት ቀናት ፁም ስራዎች በአስር እጥፍ ስለሚፃፉ ይህ ማለት የአንድ አመት ፆም ማለት ነው፡፡”
📚 (አል ቡኻሪ (1976) )

▫️አቡሑረይራም እንዲህ ይላሉ:- “ወዳጄ ሶስትን ነገር መክረውኛል በየወሩ ሶስት ቀናት እንድፆም፣ በጠዋት (ዱሃ) ሁለት ረከዓዎችን እንድንሰግድና ከመተኛቴ በፊት ዊትር እንድሰግድ፡፡”
📚(አል ቡኻሪ (1981) )

🌙 እነዚህ ቀናት ጨረቃ የምትሞላባቸው ማለትም በሂጅራ ወራት አስራ ሶስት(13) አስራ አራትና(14) አስራ አምስትተኛውን(15) ቀናት ቢሆን ይመረጣል፡፡

▫️አቡ ዘር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ከእናንተ መካከል በየወሩ የሚፆም ጨረቃ በምትሞላባቸው ቀኖችን ይፁም”::
📚 (ሙስነድ አህመድ (5/152) ነሳኢይ (4/222) )
..............................................


ሐባን ኢብኑ ሙንቂዝ [ረዐ] እንደዘገቡት:

«አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዱዓዬን ሲሶ(አንድ አራተኛ) ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?»

እርሳቸውም:‐ «ከፈለግክ አዎን!» አሉት።

«ሁለት ሶስተኛውን ላድርገው?» አላቸው።

«አዎን!» በማለት መለሱለት።

«ሁሉንም ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?» ጠየቀ።

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐ «እንደዚያ ከሆነ ያሳሰበህን የዱንያም ሆነ የአኺራን ነገር አላህ ይገላግልሀል።»

📚ሹዐቡል‐ኢማን ላይ በይሀቂይ ዘግበውታል።


አልሃምዱሊላህ
🌙 ረመዳን 100 ቀን ቀረዉ
🌙ለይለቱል ቀድር 120 (ሚጀምርበት)
🌙ኢድ አልፈጥር 130 ቀናት ቀሩት
©azan-app
اللهم بلغنا رمضان 🤲


﴿ وَلَا تَقُولَنَّ لِشَاْيۡءٍ إِنِّي فَاعِلٞ ذَٰلِكَ غَدًا ﴾
ለማንኛውም ነገር «እኔ ይህንን ነገ ሠሪ ነኝም» አትበል፡፡
[Al-Kahf - 23]


💥ከቂያማ መቃረብ ምልክቶች ዉስጥ-
ረሱል (ሰዐወ):-
"ከዚያም አንድም የአረብ ቤት ከመግባት የማይሸሽ መከራ "
"Eegasii Balaa (fitnaa) mana arabaa seenu malee hin dheessine (hin hafne)"

"ثُمَّ فِتْنَةٌ لاَ يَبْقَى بَيْتٌ مِنَ الْعَرَبِ إِلاَّ دَخَلَتْهُ،"
***
عَوْفَ بْنَ مَالِكٍ، قَالَ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزْوَةِ تَبُوكَ، وَهْوَ فِي قُبَّةٍ مِنْ أَدَمٍ فَقَالَ ‏"‏ اعْدُدْ سِتًّا بَيْنَ يَدَىِ السَّاعَةِ، مَوْتِي، ثُمَّ فَتْحُ بَيْتِ الْمَقْدِسِ، ثُمَّ مُوتَانٌ يَأْخُذُ فِيكُمْ كَقُعَاصِ الْغَنَمِ، ثُمَّ اسْتِفَاضَةُ الْمَالِ حَتَّى يُعْطَى الرَّجُلُ مِائَةَ دِينَارٍ فَيَظَلُّ سَاخِطًا، ثُمَّ فِتْنَةٌ لاَ يَبْقَى بَيْتٌ مِنَ الْعَرَبِ إِلاَّ دَخَلَتْهُ، ثُمَّ هُدْنَةٌ تَكُونُ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَ بَنِي الأَصْفَرِ فَيَغْدِرُونَ، فَيَأْتُونَكُمْ تَحْتَ ثَمَانِينَ غَايَةً، تَحْتَ كُلِّ غَايَةٍ اثْنَا عَشَرَ أَلْفًا ‏"
📚Sahih Bukhari /3176/


ግጥም ✨ምነኛ አማረ

ምነኛ አማረ
ነፍሱን ያስከበረ
ለሩሁ ፍላጎት
አጥርን ያጠረ
ገደብን የጣለ
የጌታዉንም ቃል
ህጉን ያከበረ
በትዕዛዙ ያደረ
ስራ የተባለዉን
በፍላጎት እሺ
እሰራለዉ ይላል
ለጌታዉ ቃል ሲባል
ባይወደዉም እንኳን
ተዉ የተባለዉን
ከሩቁ ይርቃል
ትዕዛዙንም ሳይጥስ
በእዉነት ይገዛል
አላህን ያወሳል
በዚህም ተግባሩ
ሰይጣንን ማብረሩ
ህጉን በማክበሩ
ለጌታዉ ማደሩ
በመልካም ትግባሩ
አላህ ይደሰታል
በሁለቱም አለም
በዱንያም በአኬራም
ስኬትን ይሰጣል
የገባዉን ቃልም
ለባርያዉ ያደርጋል
በዚያኛዉ አለምም
በጀነት ያበስራል
በል ተደሰት ዛሬ
ያንተ ቀን ነዉ ይላል
ባሪያወዉም ኢሄን ሳይ
ተገርሞ እንዲህ ይላል
ምንኛ ማማሩ
የገባልኝን ቃል
ጌታዬ ማክበሩ
ብሎ ይደሰታል
የትላንት ትግስቱ
ነፍሱንም መግራቱ
ዛሬ ላይ ጠቅሞታል
ለአላህ በመታዘዝ
ለሽልማት በቅቷል
ሌላኛዉ ሲቀጣ
እሱ ይደሰታል
የዘላለም ኑሮን
በጀነት የይወርሳል።

ግጥም በ D.G
For comment -👇
@halal_image_bot


اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد ﷺ ❤


🌙የሙሐረም ወር ና አሹራ // Ji'a Muharram fi Ashuura

●የአላህ መልዕክተኛ በሐዲሳቸው እንደገለፁት
“ከረመዳን ቀጥሎ በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ፆም ነው”
ሙስሊም ዘግበዉታል

🗓ዐሹራእ

●የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን እለተ ዐሹራእ በመባል ይታወቃል።


💎ዐሹራን በመፆም የሚገኘው ታላቅ ምንዳ

وقال النبي صلى الله عليه وسلم: «صيام يوم عاشوراء، إني أحتسب على الله أن يكفر السنة التي قبله» (رواه مسلم)
ረሱል (ሰዐወ) -
“እለተ ዐሹራእን መፃም አላህ ዘንድ ያለፈውን አንድ ዓመት( ትናንሽ ) ወንጀሎች ያስምራል ብዬ አስባለሁ” በማለት ገልፀዋል።
ሙስሊም ዘግበውታል

🤔 የዘንድሮ አሹራ መች ነዉ ሚውለዉ?
የዘንድሮ (የ1444ዓ.ሂ) ዓሹራ የሚሆነው ውይም ሙሐረም 10 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 2 /2014 ወይም ኦገስት /8/2022 ሲሆን ከፊቱ ማክሰኞ ወይም ከኋላ እሁድን እስከትሎ መጾም ተገቢ ነው።

🤲አላህ ይወፍቀን
🙏share for all muslims

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🌙 Ji'a Muharram

🔘 Ergamaan rabii saw hadiisa isaaniitin akka ibsanitti -
“Ramadaanatti aansuudhan caalaan somaa jia rabbi kan ta'e soomaa Muharramiiti.”
📚muslim gabaase

✨Ashuuraa

🔘 Guyyaan kurnaffaa jia muharram ashuuraa jedhamuun beekama.

💧 Guyyaa ashuuraa soomuun mindaan (ajriin) guddan qabu maalii?

وقال النبي صلى الله عليه وسلم: «صيام يوم عاشوراء، إني أحتسب على الله أن8 يكفر السنة التي قبله» (رواه مسلم)

🔘 Ergamaan rabbii (saw) akkas jedhaniiru- “Guyyaa ashuuraa soomuun Rabbiin biratti Dilii (badii) (xixiqqoo) Wagga darbe tokkoo ni araaramsiisa jedheen yaada”
📚 muslim gabaase

🤔 Guyyan ashuuraa (sooma) baranaa yoomi?
Ashuuraan bara kana kan (1444 a.h) wixata fulduraa akka lakk. Ithopiyati Hagayya 2/2014 ykn 08/8/2022 (a.l.a) yoo ta'u guyya fuuldura kibxata ykn guyyaa duubaa dilbata guyyaa 10ffa (ahuraa) wajji walitti ansanii soomun barbachisa dha.

🤲 Rabbi nu haa waffaqu
🙏Share for all muslims


የመጀመሪያ ጁመዓ የ 1444 ዓ.ሂ አላህ አመቱን ከይር ያድርግልን።

✨ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
(በተለይ ከአስር በኋላ)

@halal_image
@halal_image


Репост из: 🌛Halal _Image & Quotes  ሀላል ምስል
አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

‹‹ የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በመጀመሪያው ሰዓት የተጓዘ ግመል እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ሰዓት የተጓዘ ከብት እንዳቀረበ  ነው፣ በሶተኛው ሰዓት የተጓዘ ቀንዳማ በግ እንዳቀረበ ነው፣በአራተኛው ሰዓት የተጓዘ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፤ በአምስተኛው ሰዓት የሄደ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፤ ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጣ መላእክት ኹጥባ ለማድመጥ ይቀመጣሉ››
📚[ቡኻሪ 881 ሙስሊም 85ዐ]

@halal_image


✨ዒድ ሙባረክ !! ✨Eid Mubarak

እንኳን ለ1443 ዒድ አል አድሓ በዓል በሠላም አደረሰን።

(ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሐል አዕማል)


👉ማስታወሻ ነገ // Yaadachiisa Boru
💧የአረፋ ቀን ፆም ደረጃዉ-
ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”
📚(ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)

💧በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት


🔗የ አረፋ ቀን ነገ ጁምዓ ፣ ሃምሌ 1/2014 ይውላል።
--------------------------------------------
👉Yaadachiisa Boru

💧Sadarkaa guyya Soom and Arafaa
Akka Abii-Qataadan gabaasetti Ergamaan rabbii (asw) wa'ee sooma guyyaa arafaa gaafatamanii akaanas jedhaniiru: -
يكفِّر السنة الماضية والباقية
"Badii (Dilii) waggaa Darbee fi dhufuu ni haqa."
📚(Imam Muslim fi Ahmad Gabaasaniiru)

💧Guyga arafaa ( 9ffa) irratti ibaadawwan jaalataman 3:-
1.Guyyaa Soomanuu
2.Zikrii bay'isuu kessatuu Takbiira
3.Duaa'ii heddumessu

🔗Guyyaan Arafaa boru Adoolessa/ 1/ 2014 oola.

Share🙏


👉ማስታወሻ // Yaadachiisa
ዐረፋ ቀን የጁምዓ እለት ከዋለ፤
የምንፆመው የዓረፋ እለት ስለሆነ እንጂ ጁምዓ ቀን ስለሆነ አይደለምና።መፆሙ ችግር የለውም። ይሁንና ለጥንቃቄ ሲባል ከፊቱ ያለውን ሐሙስ እለት መፆሙ ተመራጭ ነው።
✍(ኢብኑ ባዝ)

💧የአረፋ ቀን ፆም ደረጃዉ-
ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-
يكفِّر السنة الماضية والباقية
“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል።”
📚(ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)
--------------------------------------------
👉Yaadachiisa
Soomni guyya arafaa bara kana 1443 hijrii guyya juma'aa irra oola kanaafuu soomun akkam ilaalama??
Deebii :- Kan soomannu guyyaa arafaa wan ta'eef malee guyya jum'aa waan hin taanef soomun rakko hin qabu.
Haata'uu malee ofegganoof jecha guyyaa dura as aanu kamiisa soomun filatamaadha.
✍(Ibnu baz)

💧Sadarkaa guyya Soom and Arafaa
Akka Abii-Qataadan gabaasetti Ergamaan rabbii (asw) wa'ee sooma guyyaa arafaa gaafatamanii akaanas jedhaniiru: -
يكفِّر السنة الماضية والباقية
"Badii (Dilii) waggaa Darbee fi dhufuu ni haqa."
📚(Imam Muslim fi Ahmad Gabaasaniiru)


የ ዙልሂጃን 10 ቀኖችን መጾም ያልጀመረ ሰው ካሁን ጀምሮ ያሉትን ቀናቶች መጾም ይችላል።

እነዚህ ዉድ ቀናቶች በ ፍጥነት እየገሰገሱ ስለሆነ በተቻለን በ ኸይር ስራ እንሽቀዳደም ።

እንዚህን የ አመቱ ምርጥና ዉድ ቀኖች በ ዋዛ ፈዛዛ አሳልፈን ከ እድለ ቢሶች አንሁን። ምንም እንኳ እነዚህ ዉድ ቀናቶች በየ አመቱ እስከ የዉመል ቂያም ድረስ የሚመላለሱ ቢሆንም እኛ ግን ቀጣይ እንደምናገኛቸው ምንም ዋስትና የለንም። ምናልባትም የመጨረሻ ሊሆን ስለሚችል ይህን አስበን እንበርታ።ምናልባትም ትንሽ ሰርተን ብዙ የምናተርፍበት ሊሆን ይችላል አላህ ይወፍቀን።
እነዚህን ቀሪ ቀኖች የ ወትሮ ስራችንን ገደብ አድርገን በ ኢባዳ ልንበረታም ይገባናል። በ ቀሪዎቹ ቀናቶች ከምንሰራቸው ውድ እና መልካም ስራወች መካከል ፤

♦️ተውበት በማድረግ
♦️ፃም በመፃም
♦️ተክቢራ በማለት
♦️ከወንጀል በመራቅ
♦️ቁርአንን በመቅራት
♦️ሰደቃ በመስጠት
♦️ሌሊት በመቆም
♦️ዚክር በማብዛት
♦️ዱአ በማብዛት
♦️ኢልም በመፈለግ
♦️ዳእዋ በማድረግ
♦️ሱና ሶላቶች በማብዛት
♦️ፈርድ ሶላት በጊዜው በመስገድ
♦️ለእናት አባታችን መልካም በመዋልና ሌሎችም መልካም ስራዎች ላይ እንበርታ።

አላህ ያበርታን ! አሚን ።

©daewa_tv


እኔ ምወዶት
ከማር ከወተት
ከናትም ካባት
ካለኝ አንድ ህይወት....

ሰለላህ አለይከ ያ ሀቢበላህ
اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد ﷺ ❤


በነኚህ ዉድ የዙልሂጃ 10 ቀናት ውስጥ ምን ማድረግ አለብን?

1. ሐጅና ዑምራ ማድረግ

በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ ምርጥ የአምልኮ ሥራዎች ናቸው። ምክኒያቱም የነኚህ አምልኮ ሥራዎች ትክክለኛ ወቅቱ ይህ ነውና። ከአቢሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ አሉ:-

العمرة إلى العمرة كفارة لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة

“አንደኛው ዑምራ እስከ ሌላኛው ዑምራ በመካከላቸው የተሰራ ወንጀልን ያብሣል፤ መብሩር /የተሟላ/ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. በበጎ ሥራዎች ላይ መበርታት

ከዐብዱላህ ኢበብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما مِن عمل أفضل من عمل فى هذه الأيام العشر، قالوا: ولا الجهاد؟ قال ولا الجهاد إلا رجل خرج بماله ونفسه فلم يرجع منه بشيء

“በነኚህ አሥር ቀናት ውስጥ የሚሠራ ሥራን የሚበልጥ ምንም የለም። ‘ጅሃድም ቢሆን?’ አሏቸው። እርሣቸውም ‘አዎን ጅሃድም ቢሆን ገንዘቡንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ያልተመለሰ ሰው ብቻ ሲቀር።’ አሉ።” (ኢማም አህመድና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

እንዲሁ በሌላ ዘገባም:-

لا تطفئوا سرجكم ليالي العشر

“በአሥርቱ ቀናት ለሊቶች ውስጥ መብራታችሁን አታጥፉ።” የሚል ዘገባ የመጣ ሲሆን ይህም ትርጉሙ “በነኚህ ቀናት ውስጥ ቁርዓን ቅሩ፣ በሰላትም በርትታችሁ ቁሙ ለማለት ነው” ተብሏል።

3. ዚክር ማብዛት

ከኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:- ما من أيام أفضل عند الله ولا العمل فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر، فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير وذكر الله، وإن صيام يوم منها يعدل بصيام سنة، والعمل فيهن يضاعف سبعمائة ضعف

“በደረጃቸውም ሆነ በውስጣቸው በሚሠራ ሥራ ከነኚህ አሥር ቀናት የሚበልጥ በአላህ ዘንድ አንድም የለም። በነሱ ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር ማለትንና አላህን ማውሣት አብዙ። ከነሱ ውስጥ አንድ ቀን መፆም የአመት ፆምን ይስተካከላል። በነሱ ውስጥ የሚሠራ ሥራ እስከ ሰባት መቶ ድረስ እጥፍ ድርብ ይሆናል።” (በይሀቂና ኢማም አህመድ ዘግበውታል)

4. በነሱ ውስጥ ተክቢራ ማብዛት

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በአሥርቱ ቀናት ውስጥ “አላሁ አክበር!” እያሉ ወደ ገበያ ይወጣሉ። ሰዎችም የነሱን ተክቢራ እየተቀበሉ “አላሁ አክበር!” ይሉ ነበር። እንዲህም ብለዋል። “ዑመር በሚና በሚገኘው ቁባቸው ውስጥ ተክቢራ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በመስጅድ ውስጥ ያሉ ሰዎችም እርሣቸውን ይሰሙና ‘አላሁ አክበር!’ ይሉ ነበር። ገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም ሚና በተክቢራ እስክትናወጥ ድረስ ‘አሏሁ አክበር!’ ይሉ ነበር።” ብለዋል። (ፈትሁል ገፋር ቀጽ 5፣ ገጽ 379)

5. ሀጅ ሥራ ውስጥ ላልተሠማራ ሰው የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት መፆም

ይህንንም ሀሠን፣ ኢብኑ ሲሪን እና ቀታዳህን የመሣሰሉ ታቢዒዮችን ጨምሮ በርካታ ሰሃቦች ሰርተውታል። ኢማም ነወዊ እንዲህ ብለዋል፡-

ليس في صوم هذه التسعة كراهة بل هي مستحبة استحبابًا شديدًا، لا سيما التاسع منها، وهو يوم عرفة

“አነኚህ ዘጠኝ ቀናት መፆማቸው የሚጠላ አይደለም። ባይሆን እጅግ ተወዳጅ ነገር ነው። በተለይም ዘጠነኛው ቀን። እሱም የዐረፋ ቀን ነው።” (ሸርሁል ሙስሊም ቀጽ 3፣ ገጽ 245)

ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-

يكفِّر السنة الماضية والباقية

“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል።” (ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)

6. ቁርዓንን ማንበብ

ከኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

من قرأ حرفًا من كتاب الله فله به حسنة، والحسنة بعشر أمثالها، لا أقول الم حرف، ولكن ألف حرف، ولام حرف، وميم حرف

“ከአላህ ኪታብ አንድ ፊደል ያነበበ ሰው የመልካም ምንዳ አለው። አንዱ መልካም ምንዳ አሥር ተመሣሣይ እጥፍ ይባዛል። አንድ ሰው ‘አሊፍ-ላም-ሚም’ ያለ እንደሆነ አንድ ፊደል አይደለም። ነገርግን ‘አሊፍ’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ላምም’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ሚምም’ አንድ ፊደል ነው።” (ቡኻሪና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

7. ኡድሂያ ማዘጋጀት

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ [١٠٨:٢]

“ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም።” (አል-ከውሰር 108፤ 3)

ከዓኢሻ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما عمل آدمي من عمل يوم النحر أحب إلى الله من إهراق الدم، وإنها لتأتي يوم القيامة بقرونها وأشعارها وأظلافها، وإن الدم ليقع من الله بمكان قبل أن يقع على الأرض فطيبوا بها نفسًا

“ከነህር /እርድ/ ቀን ሥራዎች ውስጥ የአደም ልጅ ደምን ከማፍሠስ በላይ ወደ አላህ ተወዳጅ የሆነ አንድም ሥራ አልሠራም። እርዷም የቂያማ ቀን ከነፀጉሯና ጥፍሯ ትመጣለች። ደሙም መሬት ላይ ከማረፉ በፊት ከአላህ ዘንድ ቦታ ይይዛል። በዚህም ነፍሣችሁን አስደስቱ (ደስ ይባላችሁ)።” (ቱርሙዚ፣ ሃኪም እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)

ኡድሂያ ማረድ የተዘጋጀ ሰው ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን የሰውነቱን መንካት የለበትም። ከኡሙ ሰለማ (ረ.ዓ) በተላለፈው ሀዲስም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

إِذَا دَخَلَتِ الْعَشْرُ وَأَرَادَ أَحَدُكُمْ أَنْ يُضَحِّيَ فَلا يَمَسَّ مِنْ شَعَرِهِ وَبَشَرِهِ شَيْئًا

“አንዳችሁ ኡድሂያ ለማረድ አስቦ አሥርቱ ቀናት የገቡ እንደሆነ ከፀጉሩም ሆነ ከሰውነቱ አንዳቸም ነገር አይንካ።” ብለዋል። (ሙስሊም እና ነሣኢ ዘግበውታል።)

አላህ እነዚህን ውድ ቀናቶች ከሚጠቀሙት ያድርገን ! አሚን🤲


👌ማስታወሻ
የዙልሂጃ ወር ነገ ሐሙስ ሰኔ 23/2014 አንድ ብሎ ይጀምራል!
ከነገ ሐሙስ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶችን በኢባዳ እናሳልፋቸው!

እነዚህን ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ የሆኑትን ቀኖች አላህ ከሚጠቀሙበት ያድርገን! አሚን🤲


Ergamaan rabbii (asw) akkana jedhniiru

" Guyyoota duniyaa hundaa irraa caalmaa kan qaban , guyyota kurnaan zulhijjati"

📚Albezar fi alhysimiy gabsaniiru.
Albaaninis sahiiha jedhaniru.
(sahiihul jami 1133)

@halal_image

Показано 20 последних публикаций.

391

подписчиков
Статистика канала