ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/Holy Trinity University


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций










የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሐዋርያዊ አገልግሎት በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት
-----------------
(ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/ጥር 01ቀን 2017 ዓ.ም)

በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ማኅበረሰብ ዘንድ የአርብቶ አደሮች አባት በመባል የሚጠሩት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በጂንካ ከተማ ያሉ በሀገረ ስብከቱና ገዳማት የተሠሩ የልማት ሥራዎች ጎበኝተዋል። ብፁዕነታቸው በዓለ ልደቱ በድምቀት በሚከበርበት ዳግማዊ ኢየሩሳሌም ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ካከበሩ በኋላ በፍጥነት ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመመለስ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ቀጥለዋል።

ዛሬ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጂንካ ከተማ በመግባት ቡርካመር በሚገኘው የሀገረ ስብከቱ የእርሻ መሬት ላይ የተዘራውን የበቆሎ አዝመራ: እና የጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳምን የጎበኙ ሲሆን በገዳሙ የአብነት ትምህርት የሚማሩ ከ50 በላይ ደቀመዛሙርትን እንዲሁም የከብት እርባታና ሌሎች የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት በሰጡት መመሪያ መሠረት የተሠሩትን በማመስገን ቀሪዎቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጨመሪ መመሪያ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው በማስከተልም ሀገረ ስብከቱ ያመረተውን ቦቆሎ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ከሐዋርያዊ አገልግሎቱ ጎን ለጎን ለልማት ጊዜ መስጠት እንዳለበት የሰጡት መመሪያ መተግበሩን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ነገ ጥር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ብፁዕነታቸው ወደ መሠረቱትና ከ 250 በላይ መናንያን ወደ አሉበት ወደ ኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜናማርቆስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳማት በማቅናት አዲስ የታነጸውን ቤተክርስቲያን የሚባርኩ ሲሆን በተጨማሪም ከ3000 በላይ አዳዲስ አማንያንን አጥምቀው ወደ ሥላሴ ልጅነት ይመልሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት












በወቅታዊ ጉዳይ ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ መግለጫ
______
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ፣ የነገረ ቤተ ክርስቲያን፣ የታሪክ፣ የቅኔያትና የጥንታዊ የቤተ ክርስቲያን መሠረተ ትምህርት የሚራቀቅበትና የሚመሠጠርበት ዓለም አቀፍ ጥናትና ምርምር የሚደረግበት ብቸኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዩኒቨርሲቲና የልሕቀት ማእከል ነው።

ይህ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ደቀመዛሙርት ዘመኑን የዋጁ፣ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ፣ እየሠራ ነው። ይህንን መልካም ተግባር የበለጠ ለማዘመን ተቋሙም ዓለም አቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ የመማርያ ክፍሎች፣ የቤተመጻሕፍት፣ የተማሪዎች ማረፊያ፣ የምርምር ማእከላት፣ ዘመናዊ አዳራሾች፣ ዓለም አቀፋዊ ጉባዔያት ማከናወኛና የእንግዳ መቀበያዎች በማስፈለጋቸው ከፍተኛ ራእይ ሰንቆ መጠነ ሰፊ የማስፋፊያ ሥራዎች እያከናወነ ነው።

ይህ የሕንጻ የማስፋፊያ ሥራ የመሠረት ድንጋይ ከማስቀመጥ ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ አመራር አካላት በየጊዜው በቦታው በመገኘት የግንባታውን ሒደት በመከታተል እያበረታቱ ይገኛሉ።

ሰሞኑን ዩኒቨርሲቲው እያስገነባ ያለውን B+G+8 ሕንጻ በተመለከተ በአንድም በሌላም በተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች የተመለከተናቸው የቤተ ክርስቲያንን ክብር የማይመጥኑ፣ ሐሰተኛና ያልተጣሩ፣ የተዛቡ ዘገባዎች ተሰራጭተዋል። እነዚህ ዘገባዎች የቤተ ክርስቲያንን የውስጥ ጉዳይ በማኅበራዊ ሚዲያ በመደለል ከቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ ወገኖች ዘመቻ ውጤቶች ናቸው። በሚዲያ ዘመቻው የተናፈሱ ወሬዎች የሚያደናግሩ፣ ብዥታ የሚፈጥሩ በመሆናቸው የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን፣ ደቀ መዛሙርት፣ የዩኒቨርሲው ወዳጆች እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ከሚቆረቆሩ ማኅበራት መምህራንና ምእመናን ምላሽ እንድንሰጥ በልዩ ልዩ መልኩ እየጠየቃችሁን መሆኑን እያስታወስን ስለተቆርቋሪነታችሁ የአበው አምላክ ያክብርልን እንላለን።

ዩኒቨርሲቲው የቤተ ክርስቲያንን ችግር ፈቺ አካል እንጂ ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ መሆን ስለሌለበት በተለይም ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ፈታኝ በሆነው በዚህ ወቅት በየሚዲያው የእሰጣገባ ምላሽ መወራወር ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለዩኒቨርሲቲው የማይመጥን፣ የምእመናንና የሊቃውንትን ጊዜ የሚያባክን፣ በመከራ ውስጥ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ሌላ መከራ የሚጨምርና ለጠላት በር የሚከፍት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ነገሮችን ሁሉ በትዕግስት ለማለፍ እየሠራ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው የሕንጻ ግንባታ ሒደትና አፈጻጸሙን በተመለከተ ጥያቄ ላላቸው አካላት ግልጽ ለማደረግ በሕጋዊ መንገድ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ በተመደቡ ብፁዕ ጳጳስ ከሚመሩት አጣሪ ጋር በሙሉ ትብብርና በግልጸኝነት እየሠራ ይገኛል። ውጤቱም ተጠናቆ ውሳኔ ሲያገኝ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ የሥራ ሒደትና የአሠራር አለመግባባቶችን ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ በማዋል፣ ሰድቦ ለሰዳቢ በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር የማይመጥኑ ተግባራት ሲፈጸሙ ማየት የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል። ዩኒቨርሲቲው በፍጹም በዚህ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ዝና የማይመጥን ተግባር ውስጥ ገብቶ የመዳከር ተነሣሽነትና ፍላጎት የለውም። በሰሞኑ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዩኒቨርሲቲውን ከሚመሩት ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ/ ፕሬዝዳንት ጀምሮ የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብና የቤተ ክርስቲያንን ክብር የማይጠብቁና ያልተጣሩ ሐሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። ዩኒቨርሲቲው ለተሰራጩት የሐሰት ወሬዎች ሁሉ በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ መስጠት ይችላል። ነገር ግን ለሐሰት ወሬዎቹ የሚሰጠው ምላሽ ጥያቄ ላላቸው አካላት ግልጽ ለማደረግ የተጀመረው የማጣራት ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው የማጣራት ሒደቱ እስከሚጠናቀቅ ይቆይ ብለናል።

ዩኒቨርሲቲው የተጀመረው የማጣራት ሥራ ተጠናቅቆ በወሳኙ አካል (በቋሚ ሲኖዶስ) ውሳኔ ሲያገኝ ውጤቱን በይፋ ያሳውቃል። ነገር ግን ማናቸውም የዩኒቨርሲቲውን ስም የሚያጎድፍ ሐሰተኛ ወሬ በሚያሰራጩ አካላት ላይ የሕግ ክፍላችን የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ሕጋዊ መንገዶችን ለመሔድ የሚገደድ መሆኑን በአጽንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን።

ከሕንጻ ግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ጥያቄና አስተያየት አለኝ የሚል አካል ካለ ዩኒቨርሲቲው በግልጽ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሓላፊዎች ለማስረዳት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።

ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ ፲፯ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም







Показано 14 последних публикаций.