[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!!

""""""""""""""የመፅሃፉ መቅድም""""""""""""""
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው፣ በእርሱም እታገዛለሁ!።
ምስጋና በጠቅላላ ለዓለማቱ ብቸኛ ለሆነውና በሀይማኖቱ ደንጋጊ (ህግ አውጪ) ለሆነው፤ የሰው ልጆችን እውቀቱ በሌላቸው ነገር ላይ መከተልን የከለከለ ለሆነው፤ ብቸኛ ተመላኪ ለሆነው አምላካችን አላህ የተገባ ነው!!፡፡

የሰው ልጆችን እውቀቱ የሌላቸውን ነገር እንዳይከተሉ እንዲህ በማለት ከልክሏል፡-

﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ  إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ﴾ [الإسراء:٣٦]

ለአንተ በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፤ ማያም፤ ልብም እነዚህ ሁሉ ‹ባለቤታቸው› ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡” አል ኢስራእ 36

ከነፍሳችን ተንኮልና ከብልሹ ስራችን በአላህ እንጠበቃለን፤ አላህ የመራውን የሚያጠመው የለም፤ አላህ ያጠመመውንም የሚያቃናው የለም! ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፤ እርሱም ብቸኛና ምንም ተጋሪ የለውም! ነቢዩ ሙሐመድምﷺ የእርሱ ባሪያና መልእክተኛው መሆናቸውን (በልቤ ያመንኩ ስሆን) የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ፡፡
ከንግግር ሁሉ እውነተኛው ንግግር የአላህ ቃል የሆነው ቁርኣን ነው! ከመንገዶች ሁሉ ትክክለኛው መንገድ (እምነት) የመልዕክተኛው የነቢዩ ሙሐመድ መንገድ (እምነት) ነው፡፡
የነገሮች ሁሉ አደገኛ በሀይማኖት ላይ አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ማምጣት ነው! በሀይማኖት ላይ ፈጠራ (ቢድዓ) ሁሉ “ከነቢዩ ያልተለመደ” መጤ ነው፤ መጤ የተባለ በሙሉ ጥመት ነው፤ የጥመት ጎዳና በሙሉ የእሳት ነው።

ከዚህ በመቀጠል
በዚህን ጊዜ እንደሚታወቀው በብዛት በተጨባጭ እንደሚታየውም በአላህና በመልክተኛው ክልክል የተደረገው እንደተፈቀደ ነገር፤ የተፈቀደው ደግሞ እንደተወገዘ ነገር የሚታይበት ተጨባጭ ነው የሚታውየው። ለዚህም ያለ በቂ እውቀት ዝና እና ተወዳጅነትን ፍለጋ ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ አላዋቂ መሀይማን (ጃሂሎች) ዘንድ ሙፍቲ ተደርገው የተቀመጡ በስሜትና በመሀይማን ጭፍን ድጋፍ ሀቅን ላለመቀበል በትቢት የተወጠሩ፤ ያለ ደረጃቸው በመሀይማን ሸይኽና ኡስታዝ ተብለው የተሰቀሉ ብልሽትን የሚያስፋፉ (የፈሳድ) ሙፍቲዎች አሉ፡፡

ታዲያ እንዲህ ያሉ የጥመት ብይን (ፈትዋ) የሚሰጡ ሰዎችን ሀቅ ፈላጊውን ሚስኪኑን ህዝብ፤ በእንዲህ ያለ ፈትዋቸው ሲያስቱ ዝም ብሎ ማየት የአላህን ሀቅን ግልፅ የማድረግ አማና በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር፤ የተወገዘን ንግግር የሚናገሩና በተወገዘ ነገር ላይ ይፈቀዳል ብለው ያለ እውቀት በድፍረት ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎችን ባለማውገዛችን ከአይሁዶች እንዳንመሳሰል ያሰጋል፡፡ አላህ እነዚያ ከበኒ ኢስራኢል ከሀዲ የሆኑት የተረገሙበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ገልፆልናል፡-

﴿لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَى لِسَانِ دَاوُودَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ  ذَلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ٧٨كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ ﴾ [المائدة: 78-79]

ከኢስራኢል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርያም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከሰሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር፡፡” አልማኢዳ 78-79

ይህ በመሆኑም አንዱ ሲሳሳት ሌላኛው ተው! ማለት ግድ ይለዋል!፡፡ በመሆኑም ነሺዳን በተመለከተ የተሰጠውን የተሳሳተ ፈትዋ በቁርኣንና በሶሂህ ሀዲስ፤ በኢስላም ሊቃውንቶች የጋራ ስምምነት (ኢጅማዕ) ስህተት መሆኑን ለህዝበ ሙስሊሙ በተቻለ መጠን ግልፅ የተደረገ ሲሆን፤ ነሺዳን ሀላል ለማስመሰል የተነሱ ብዥታዎች ላይም አንድ በአንድ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ይህን ሶፍት ኮፒ/PDF አንብበው ለሌሎች በማሰራጨት ሌሎችንም ከነሺዳ ብዥታ ይታደጉ!!
ለአስተያየትና ለጥቆማ የሚከተለውን የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡- Ibn.shifa11@gmail.com
PDFን በዚህ ሊንክም 👇👇 ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/1383

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ነሺዳ-Ibn Shifa.61page.pdf
871.4Кб
ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!! PDF
"""""""
በኢብን ሽፋ ከ 3አመት በፊት ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ
#share #ሼር_አድርጉት!

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የሙነውር ልጅ በመርከዙ ሰዎች ላይ ትችቱ የእውነት ረድ ተፈልጎበት ወይስ ለጠያቂዎች አፍ ማዘጊያ?!
—————
የሙነወር ልጅ፣ ሙሀመድ ሲራጅና ሳዳት ከማል መሰሎቻቸው:- በሱንና ላይ እያሉ፣ ለሱንና ሲታገሉ፣ ከቢድዓና ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ሲያስጠነቅቁ፣ ባጢልን በማርከስ ሐቅን እያነገሱ፣ ለተውሒድና ለሱንና ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የምናከብራቸውና የምንወዳቸው የነበሩ ወንድሞች ናቸው። በእልህ፣ በጀህልና እና በትቢት ተወጥረው በተምይዕ ፊክራ የተዘፈቁት። በተምይዕ ፊክራ ከተዘፈቁ በኋላ ግን (አላህ ይጠብቀንና!) የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ሁሉ በተቃራኒው ማስኬድ ጀመሩ። ከተዘፈቁባቸው አቅጣጫ የሳቱ ነጥቦች ለአብነት ያክል:-
1, የተምይዕን ፊክራ ከተለያዩ የሙመይዐህ ዌብሳይቶች ለቃቅመው እያመጡ በሰለፊዮች መካከል በመበተን ሠለፊዮችን ብዥታ ውስጥ ለመጣል ታገሉ።

2, ቀደም ሲል ሠለፊዮች እንዲጠነቀቋቸው በከፍተኛ ደረጃ ሲያስጠነቅቁ (ከዚህ በኋላ ነጭ ነጯን እንናገራለን…) ብለው ከነበሩት (የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ) ሰዎች በመከላከል የሱንና ሰዎችን ደግሞ በመተቸት ተጠመዱ። ብሎም የመርከዙን ሰዎች ዛሬም ወደፊትም ሰለፊዮች ናቸው በማለት ሞገቱ።

3, እንደ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ግልፅ ለወጡ የቢድዐህ ባለ ቤት (መሻይኾቻቸው) "የበሰሉ ሰዎች ናቸው…" እያሉ የተለያዩ መለሳለሶችን እያንፀባረቁ፣ በተቃራኒው ደግሞ የሱንና መሻይኾችን "የረድ ጉረኞች…" እያሉ በተለያዩ ቃላቶች እየጎነተሉ ሰዎች እንዲርቋቸውና ከሱንና መሻይኾች ት/ት እንዳይወስዱ ሲታገሉ ከርመዋል።

4, ከቢድዐህ ባለ ቤቶች መስራት ክልክል አይደለም ብለው ሲሟገቱና በርካታ ሰለፊይ የነበሩ ወንድም እህቶችም እንዲህ ባሉ ልቅ አካሄዶቻቸው ወርደው ከኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር እንዲቀላቀሉ ሰበብ ሆነዋል።

5, ያለ በቂ እውቀታቸው በእልህና በትቢት ተወጥረው፣ የጀርህና ተዕዲልን ጉዳይ በፈለጉት ልክ ቀደው ሲሰፉት ከርመዋል። ሲፈልጉ "ጀርህና ተዕዲል ለማድረግ በቂ አቅም ያለው መስፈርቱን የሚያሟላ ዓሊም የለም" ሲሉ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ በተቃራኒው "ተብዲዕና ተፍሲቅ ማድረግማ እኔና አንተም ብንሆን የሰውዬውን ሁኔታ አይተን አገሌ ሙብተዲዕ ነው አገሌ ደግሞ ሙብተዲዕ አይደለም ማለት እንችላለን…" እያሉ ተራ የመንደር ወሬ አይነት ነገር አድርገው ሲመለከቱት ተስተውሏል።

6, ግልፅ ማስረጃ የቆመበትን፣ ሸሪዓ ሙብተዲዕ ያለውን ሙብተዲዕ በሉ ሲባሉ "እኛ ሙብተዲዕ ያልነውን ካላላችሁ እያሉ እያስገደዱን ነው" ብለው ማለቃቀሳቸው ሌላኛው ጥፋታቸው ነው። እዚህጋ በጣም የሚደንቀው:- እራሳቸው የሱንና መሻይኾችን "የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች እንዴት ከሱና አይወጡም?" ብለው ሲሟገቷቸው ቆይተው መሻይኾች ደግሞ ስለ መርከዝ ኢብኑ መስዑድ ማስረጃዎችን ከሰበሰቡና ዑዝራቸውን ካስጨረሱ በኋላ "አሁንማ ከሙብተዲዕ ጋር ተቀላቅለዋል፣ ለይቶላቸወል ሙብቲዕ ናቸው" ብለው ብይን በሚሰጡ ጊዜ "መጀመሪያ እኛ እያልናችሁ ለምን ዝም አላችሁ?" ብለው በትቢትና በእልህ ተወጥረው ተብዲዓችሁን አንቀበልም ማለታቸው ነው። የሱንና ዓሊሞች አንድ አካል ላይ ማስረጃ እስኪሰበስቡ ተብዲዕ ተፍሲቅ የአኼራ ጉዳይ እንደመሆኑ በጥንቃቄ አጣርተው ዑዝሩን እስኪያስጨርሱት ድረስ መታገስ የተለመደና የሚወደስ ባህሪያቸው እንጂ የሚተቹበት ነገር አልነበረም። ደግሞ አንተ ስትነግራቸው ግልፅ ሳይሆንላቸው ቆይቶ ግልፅ ከሆነላቸው በኋላ ሐቁን በማስረጃ ማስቀመጣቸው ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው?! ልብ በል! አንድ አካል ሙብተዲዕ በመሆኑ ግልፅ ማስረጃ ከቆመበት በኋላ ሙብተዲዕነቱን መቀበል የሚያስገድዱህ መሻይኾች ሳይሆኑ ሸሪዓዊ ማስረጃው ነው!! የተብዲዑ ጉዳይ አልተገለፀልንም እስኪገለፅልን ዝም እንላለን ባላችሁም ጊዜኮ ያስገደዳችሁ አልነበረም።

7, በተቻለ መጠን ሁሉ በሠለፊይ መሻይኾች፣ ኡስታዞችና ዱዓቶች ደዕዋ ሰለፊያን ለማስፋፋት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመጅሊሱና ከቢድዐህ አንጃዎች ጋር በመታገል በሰፊው የሚደረገውን የሰለፊዮችን ሐቅን ግልፅ ለማድረግ ባጢልን ለማርከስ፣ ተውሒድና ሱንና የበላይ እንዲሆን ቢድዐህ እና ሺርክ እንዲረክስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እየተቹና እያጣጣሉ ለቢድዐህ ባለ ቤቶች እንቅስቃሴና ለሚናገሯቸው ሸሪዓን የሚፃረሩ ንግግሮች ደግሞ ዑዝር እየፈለጉ ከርመዋል።
እነዚህ የጠቀስኳቸው 7 ነጥቦች ከጥፋታቸው በጣም በጥቂቱና አደባባይ ላይ የዋሉ ናቸው።

🔸ዛሬ መለስ ብለው የሙነወር ልጅና አምሳዮቹ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ሰዎች እንደ አዲስ በጨረፍታም ቢሆን ለመተቸት (ረድ) ለማድረግ መሞከራቸው እውነት ከልብ የመመለስ አዝማሚያ ነው ወይስ የተለያዩ ከእነሱ ስር የነበሩ ወንድም እህቶች ጠንከር ያለ ጥያቄ ሲያነሱ ማስተኛ ነው?!

የእውነት ተመልሰው ከቢድዐህ ባለቤቶች ረድና ታህዚር ከጀመሩ፣ ቀደም ሲል ከተውት ሐቅን የበላይ የማድረግ ባጢልንና የባጢልን ባለ ቤቶችን የማራቆት ስራ በመመለሳቸው እጅግ በጣም በልበ ሰፊነት ደስተኞች ነን!! የእውነት ከተመለሱ ከላይ የጠቀስኳቸውንና መሰል ስህተቶችንም በአደባባይ ያርሙ!!። እነዚህን ወንድሞች ከጎናችን ስናጣቸው ከተከፋነው በላይ ከተምይዕ ባህር ወጥተው ከላይ የጠቀስኳቸውንና መሰል… ስህተቶችን አስተካክለው ወደነበሩበት ሐቅ ሲመለሱ እጅግ በጣም ደስተኞች እንሆናለን!! በአላህ ፈቃድ እጅ ለእጅ ተያይዘን በምንችለው ሁሉ ሐቅን የበላይ ለማድረግ እንተጋለን!!
ነገሩ ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች በድብብቆሽ ትተው በግልፅና በአደባባይ ከአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ተከትሎ እነ ኢብኑ ሙነወር በጥሩ አቋም የነበሩ መስሏቸው ለእነ ኢብኑ ሙነወር ሲከላከሉ የነበሩ ወንድም እህቶች "በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ላይ ያላችሁን አቋም በግልፅ ንገሩን? ይሀው ጨርሰው ከኢኽዋን ጋር ተጠቃለዋል ምን ቀራቸው?" ብለው በተለያየ መንገድ በጥያቄ ሲያጣድፏችሁ በመርከዙ ሰዎች አፍ ማዘጊያ ፅፋችሁ ከሆነ ግን ከዚህ በኋላ ሐቅ ፈላጊ ሆኖ የሚሸወድላችሁ አታገኙምና ወደ ራሳችሁ ቆም ብላችሁ ተመልከቱ!! የራሳችሁ ጉዳይ ያሳስባችሁ!! አል-ሀምዱሊላህ! ሐቅ ፈላጊ ሆነው በናንተ ብዥታ ውስጥ የወደቁ እጅግ በጣም ብዙ ወንድም እህቶች ከተለያየ አቅጣጫ እየተመለሱ ነው!!

🔸ይልቅ ለራሳችሁ ስትሉ በእልህና በትቢት ተወጥራችሁ ከገባችሁበት የተምይዕ ዋሻ ውጡና ሐቅን የባለይ ለማድረግ ታገሉ!! በእልህ (በደራ) ገብቶ ሐቅን መሳትና በባጢል መውደቅ የከሃዲያንና የመሀይማን ባህሪ ነው እንጂ ሠለፊያን የሚሞግት የሙስሊም ባህሪ አይደለም!!

إِذْ جَعَلَ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي قُلُوبِهِمُ الْحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ

«እነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ » አል'ፈትህ 26

🔹ሠለፊይነትን የሚሞግት ሙስሊም የሆነ ሰው ሐቅን ከሁሉ ነገሩ በማስበለጥ ለሀቅ እጅ እግሩን ይሰጣል!! በዚህም የበታችነት ሳይሆን የበላይነት ይሰመዋል!!። አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉ፣ ባጢልንም አውቀው ከሚጠነቀቁና በሐቅ ላይ እስከ እለተ ሞታቸው ከሚፀኑ ባሪያዎቹ ያድርገን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




ሶሪህ አስ-ሱንና

⏯ ክፍል 5

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
⏱ቅዳሜና እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ከተዳሰሱ ነጥቦች
- ከሐቅ ጎን መቆም ግዴታ ነው
- ጥቅል ቃላትን የመጠቀም አደጋ
- የባሙሳው ዘገሉ ደዕዋ ኪታብ
- የሙሀመድ አል ኢማም አል ኢባና
- ሪፍቀን አህሉሱንና ቢአህሉሱና ኪታብ
- ኢልያስ አህመድ፣ ኢብኑ ሙነወር፣ ኸድር ከሚሴና ሙሀመድ ሰዒድ
- ከዛም ከዚህም የማይሆኑ ሙዘብዘብ ሰዎች አደገኝነት

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444


Репост из: ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel
የተጠናቀቀ ደርስ

የኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪ ሶሪህ አስ-ሱንና ኪታብ ማብራሪያ
شرح صريح السنة لبن جرير الطبري رحمه الله

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

ከመግቢያ እስከ ክፍል 22

የኪታቡ pdf ⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7781
መግቢያ⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7987
ክፍል 1⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7988
ክፍል 2⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7989
ክፍል 3⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7990
ክፍል 4⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8062
ክፍል 5⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8063
ክፍል 6⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8259
ክፍል 7⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8260
ክፍል 8⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8261
ክፍል 9⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8798
ክፍል 10⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8799
ክፍል 11⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8800
ክፍል 12⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9553
ክፍል 13⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9554
ክፍል 14⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9555
ክፍል 15⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9556
ክፍል 16⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9557
ክፍል 17⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9558
ክፍል 18⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9559
ክፍል 19⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9560
ክፍል 20⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9561
ክፍል 21⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9562
ክፍል 22⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9563


Репост из: Semir Jemal
"አቤት የሰለፎች ኢኽላስ!"
"""""""

ሙሐመድ ቢን ዋሲዕ (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን አለ፦

«...ከሰለፎች አንዱ ሚስቱ (ባለቤቱ) አጠገቡ ሳለች፣እንዲሁም አሷ ምንም ሳታውቅ ለ"20" አመታት ያክል አልቅሷል።»

📚 [ሲየር አዕላሚን ኑበላእ፡ 6/122]
@semirEnglish


Репост из: Bahiru Teka
🎤 የማይታመን የሰለፍያ ማእበል

ክፍል አንድ

ሐቅ የተዳፈነ እሳት ነው ንፋስ አግኝቶ የተቀጣጠለ ቀን ባጠለልን ወሬ ነጋሪ እንዳይኖር አድሮጎ ይፈጀዋል ። ባጢል የፈለገ ቢገን ገናናነቱ ሐቅ እስኪደርስበት ነው ። ሲደርስበት የገባበት ይጠፋል አንገቱን ይደፋል የውርደት ካባ ይከናነባል ።
የሱፍይ የኢኽዋንና ሙመዪዓ ጥምር የባጢል ሀይል እያቅራራና እየፎከረ በኢኽዋን መሪነት ሐቅን ለመቅበርና የሐቅ ባልተቤቶችን ለማንበርከክ መንግስት ነን እኛ ያልፈቀድንለት መኖር አይችልም እስከማለት ደርሶ በቀረርቶና ሽለላ እንደ እንቦሳ በማናለብኝነት ሲፈነጥዝ ብዙዎችን አስፈርቶ ነበር ።
በተቃራኒው የሐቅ ሰዎች እንደ ብረት ሙሶሶ ረግጠው ቆሞው ከቁርኣንና ሐዲስ መርህ ያፈነገጡ ሸሪዓ ደንጋጊዎች ነን የሚሉ የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ያሉት ሰለፍዮች ዛሬ ተአምር እያዩ ነው ። እናንተ የተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደላችሁም ። መመሪያችሁም የተቋም መመሪያ እንጂ የሀገሪቱ ዜጎች የሚተዳደሩበት መመሪያ አይደለም ። እንደ ሀገር ሁሉንም የሚመለከት የዜጎችን የእምነት ነፃነት ያወጀ ህገመንግስት አለ በመሆኑም መብታችን ሊከበር ይገባል ። በናንተ የጭቆናና የአምባገነን መመሪያ አንተዳደርም ብለው በመፅናት ከዳር እስከዳር ሲታገሉ የሐቅ ብርሃን አድማሱን እያሰፋ ደቡብ ፣ ምእራብ ፣ ሰሜን ላይ ጮራውን እየፈነጠቀ የነበረው ሰለፍያ ምስራቁን ክፍል በማይታመን ሁኔታ ባጢልን እያናወጠውና እያሳደደው ነው ።
የፌዴራሉ መጅሊስ መሪ ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከወራት በፊት ምስራቅ ሐረርጌ አመራሮቹን አስከትሎ በመሄድ ሁሉም ዑለሞችና ኢማሞች እንዲሁም ኡስታዞች በግድ እንዲገኙ በማድረግ እኛ ያልፈቀድንለት አይኖርም ። ዝም ስንል የተኛን መሰላችሁ እንደ ውሀ ነን ውሀ ዝም ብሎ የተነሳ ቀን ይበላል ። እኛም ዝም ስንል ያላወቅን እንዳይመስላችሁ እናጠፋችኋለን ። ኬት የመጣ ሰለፍይ ነው ? ሰለፍይ አይደለም ሰለኽይ ነው ። እያለ እያላገጠና እያሸማቀቀ ፎክሮ ከተመለሰ ከጥቂት ወራት በኋላ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ የማይታመን ክስተት ተከሰተ ። ዝም ብለው የነበሩት ዑለሞች በቃ አሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሐቅ መሰከሩ ። ኢኽዋኖቹ የዘመናችን ቡኻሪይ ሲሉዋቸው የነበሩት የእድሜ ባለፀጋው አንጋፋው ሸይኽ አሕመድ ወተሬ ሰለፍያ ሐቅ ነው አሉ ። አላሁ አክበር !!! አላሁ አክበር !!! አላሁ አክበር !!! ሸይኽ አሕመድን የማያውቅ ምስራቅ ሐረርጌያዊ የለም ። በዙህዳቸውና በዒልማቸው የሚታወቁት የእድሜ ባለፀጋው ሸይኽ አሕመድ ኢኽዋኖች ጃኬታቸውን የሚሰቅሉባቸው የኛ የሚሏቸው ነበሩ ።
እኚሁ ታላቅ ዓሊም ከሳቸው ስር የወጡ በርካታ ዑለሞችንና መሻኢኾን ይዘው ኢኽዋንን በቃ አሉት ። እኛ ሰለፍዮች ነን የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ዑለሞች አሉን መመሪያችን ቁርኣንና ሐዲስ በሶሓቦች ግንዛቤ ነው ። የናንተን የሰው ሰራሽ መመሪያ አንፈልግም በቃን አሉ ። ኢኽዋንና ግብረ አበሮቹ ምድር ዞረባቸው ። ስልጣንም ገንዘብም ምንም ማድረግ እንደማይችል አምነው ለመቀበል ተገደዱ ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መንገድ በሚያጨናንቁ የሰለፍዮች ፕሮግራሞች ናላቸው የዞረው የመጅሊስ አመራዞች ምስራቅ ሐረርጌ ላይ በተፈጠረው ነገር እግራቸው ራሳቸውን መሸከም ያቃተው ይመስላል ። በአላህ ፈቃድ የመሻኢኾቹን የአቋም መግለጫ በሚቀጥለው ክፍል የማቀርብላችሁ ይሆናል ። ሁላችሁም ለእነዚህ መሻኢኾች ረዥም እድሜ ከመልካም ፍፃሜ ጋር ለምኑላቸው እላለሁ ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: አቡ አዒሻ العلم نور
   አስደሳች ሰበር ዜና  ለሰለፍዮች

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

كيف نستقبل رمضان☪️

🔊ታላቅ የዳዕዋ  ፕሮግራም ድግስ ተደግሷል በአይነቱ ለየት ያለ የምክር ክትባትና እርጭት ፍቱን ለአማኝ መድሀኒት ስለሆነ ድን መመካከር ነውና  ሁላችሁም ታድማችሆል ኑ ደሮ ግብር

📝 የፊታችን ቅዳሜ ማለትም የካቲት ቀን /15/06/2017/ሁላችሁም  ተጋብዛችኋል

🔍ልዩ ስሟ የቀደምት ከተማ ደሮ ግብር እማ የተባለች ከወልድያ ዝቅ ከመገንጠያ ከፍ ብላ  ያለች በጎራና ትላልቅ ተራራ በመታጀብ ረባዳ የቦታ አቀማመጥ ሁኔታላይ ትገኛለችና ኑ ደሮ ግብር ተውሂድ ይነገር

💫ስለሆናም በአቅራቢያው ያላችሁና ይሄን የዳዕዋ  ጥሪ የሰማችሁ ሰለፍዮች  በሙሉ በተባለው ቦታና ወቅት ሰአት በመገኘት የዳዕዋው ተካፋይና ተቋዳሽ ተጠቃሚ  ይሁኑ

🪑ተጋባዥ የክብር እንግዶቻችን እነሆ ብለናል

➢1.ሸይኽ ሁሴን ከረም ሀራ
➢2.ሸይኽ መሀመድ ሀያት ሀራ
➢3.ሸይኽ ሰይድ ሙሀመድ ሀራ
➢4.ሸይኽ ሙሐመድ ሲራጅ ሀሮ
➢5.ኡስታዝ ሙሀመድ ሰልማን ሀራ
➢6.ኡስታዝ አብዱረህማን መርሳ

🕉እነዚህንና ሌሎችም የክብር ታጋባዥ ዳኢ ዎችና ኡስታዞች  የሚገኙ ይሆናል  ከርሶ የሚጠበቀው በቦታው ላይ በመገኘት ጥሪዎትን ማክበር ብቻ ነው።

🌎በውጭ ለምትገኙ የሱና ወንድሞችና እህቶች ከተቻለ በቀጥታ ስርጭት የ0nlien ሂደት ስለሚኖረን በተባለው ቀንና ወቅት ብቅ ዘለቅ ማለታችሁን እንዳትረሱ አስታውሱ

🕒 የሚጀመርበት ሰአትና ወቅት ከጧቱ 2:30/ሲሆን በአላህ ፍቃድ እስከ 10:00 🕥ድረስ ይዘልቃል ይጠናቀቃል

⚙የፕሮግራም ደጋሽና
አስተናባሪ እንደሁም ጠሪ
የደሮ ግብር ሰለፍያ ወጣት በመተባበር

🗓 የካቲት ቀን/15/06/2017/የፊታችን/ ቅዳሜ/
➷➷➷➷
https://t.me/hussenhas
https://t.me/hussenhas


Репост из: ابو البيان نورأديس بن سراج
ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

እነሁ የፊታችን  እሁድ በቀን 16/06/2017 ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም ለየት ባለና በማረ ሁኔታ እንኳን መቅረት ማርፈድ የሚያስቆጭ ፕሮግራም  አዘገጅተን እንጠብቃቹሃላን።

በዚህ ፕሮግራም በአሏህ ፍቃድ ወሳኝ ርእሶች የሚዳሰሱበት ይሆናል


እንዲሁም በእለተ ቅዳሜ በ-15-06 በኣልቾ ልዩ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቆታል

        ተጋባዥ  እንግዶች:-
1ኛ.ኡስታዝ  ኑራዲስ ስራጅ  ከቡታጅራ

2ኛ.ኡስታዝ አብራር አወል  ከአዲስ አበባ


3ኛ.ኡስታዝ ዶክተር  ሸምሱ ከቡታጅራ


እና ሌሎችም ኡስታዞች በአላህ ፍቃድ ይኖራሉ

አድራሻ:-ኦዶ ከተማ ትንሽ ገባ ብሎ  መስጂደል ወሊደይን/ሸረፈ ሙስጠፈ


ሰዓት:-ልክ 2:30 ይጀምራል።

ለበለጠ መረጀ ስልክ

ጀማል ኑሪ 0916293446 

ኑሪ መሀመድ 0989606180 


መሀመድ የሲን   ጀማል 0982612475 

ሼርርርርርርርር
                ርርርርር
                   ርርርር
እናርግ ከጁሙዓ ቦኋላ  እናሰዉቅ።


https://t.me/+kn_NBJK5YaBkMWZk


"የረመዷን ማስታወሻ!"
  ክፍል-➀

አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን ይላሉ፦ “ፆም ግዴታ የሆነው ከሂጅራው ከሁለተኛው አመት በኃላ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘጠኝ (9) ረመዷኖችን ፆመው ነበር ከዚች ዓለም የተለዩት...” [ዛዱል መዓድ (2/30)]

አል-ኢማም አን-ነወዊ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) በተመሳሳይም እንዲህ ይላሉ፦ “የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሕይወት ሳሉ፣ ዘጠኝ (9) ረመዷኖችን ነበር የፆሙት። ይህ ፆም ግዴታ ሆኖ የተደነገገው ከሒጅራው በሁለተኛው ዓመት በወርሃ «ሸዕባን» ላይ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሕይወታቸው ከዚች ዓለም ያለፈው፣ከሒጅራው በ 11ኛው ዓመት በረቢዑል አውል ላይ ነበር...” [አል-መጅሙዕ (6/250)]

አል-ሃፊዝ ኢብኑ ሐጀር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ ከሂጅራው ሁለተኛው ዓመት «የበድር ጦርነት» የተካሄደበት ጊዜ ነው...” [ተልኺሱል ሀቢር (4/89)]

አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሃመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን ይላሉ፦ “የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዚህ በረመዷን ወር በተለያዩ ዒባዳዎች ያሳልፉ ነበር፤ለምሳሌ ከጂብሪል (ዐለይሂ ሰላም) ጋር ሆነው  ቁርኣንን ይከልሱ ነበር፤ከሌሎች ወራት በተለየ በዚህ ወር ሶደቃን ይለግሱ ነበር፣አንዲሁም ዚክርን ያበዙ ነበር፣ ኢዕቲካፍም ይገቡ ነበር...” [ሙኽተሰር ዛደል መዓድ (135)]

አል-በይሀቂ (ረሂመሁላህ) በሱነናቸው ላይ ከናፊዕ ተይዞ እንደዘገቡት፡ “ዐብዱሏህ  ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) በረመዷን በቤታቸው ሶላትን ይሰግዱ ነበር...ከዚያ ሰዎች ከመስጂድ ከወጡ በኃላ፣ኢብኑ ዑመር በእቃ ውሃ ይዘው ወደ መስጂድ አን-ነበዊ ይሄዳሉ። ከሄዱበት የንጋት ሶላትን ሳይሰግዱ ከመስጂድ አን-ነበዊ አይወጡም ነበር። [አል-በይሀቂ ሱነኑል ኩብራ (2/494)]

ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ፦ “ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ፆማቸውን ከድሆች ጋር እንጂ አያፈጥሩም ነበር። ቤተሰባቸው ከከለከሏቸው ደግሞ ያንን ሌሊት ሳይመገቡ ይውላሉ፤እንዲሁም ኢብኑ ዑመር ምግብን እየተመገቡ፣የቸገረው ችግርተኛ መጥቶ ከጠየቃቸው ከተቀመጡበት ተነስተው ከመዓዱ ያካፍሏቸው ነበር...” [ለጧኢፍ አል-መዓሪፍ (ገፅ: 233)]

📝Authentic & copyright Salafi free PDFs
𝑻𝒓𝒂𝒏𝒔𝒍𝒂𝒕𝒆𝒅 𝒃𝒚: 𝑨𝒃𝒖 𝑯𝒂𝒇𝒔𝒂𝒉
@semirEnglish


قال لي شيخنا: أحمد النجمي رحمه الله

"وقد ثبت لدينا بالتجربة أن هناك أناسٌ يدخلون في السلفية

لامن أجل تكثير سواد السلفيين ونصرة الحق
والتعاون على البر والتقوى

ولكن من أجل إشاعة الفوضى بين السلفيين ،

ونشر بذور الخلافات ، التي لا تنتهي ؛ بل تُزهِّد في اتِّبَاع المنهج السلفي ،

وهذه مكائد يبثها الأعداء من

حدادية

وإخوانية

وسرورية

وقطبية وغيرهم

فاتركوا هؤلاء ، ولا تقبلوا منهم كلاماً ، ولا تعد و هم من السلفيين ؛ ليكون ذلك سبباً في سلامة منهجكم"


قلت:وليحذر العقلاء من نقل السفهاء لهم ما قد يصح وما لا يصح من أجل إغار الصدور وإثارة الفتن فهم كالفيروسات لا ينشطون إلا في الفتن .فتنبه

كتبه شيخنا أبو الفضل محمد الصويعي _ حفظه الله .
منقول


Репост из: قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
الشيخ سليمان الرحيلي يبشرنا بتحسن حالة الشيخ ربيع المدخلي حفظه الله الجميع


ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ በቀን 16/06/2017  ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመድረሳችን አልኢስላሕ ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ እንኳን መቅረት በማርፈድ የሚያስቆጭ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ 

ተጋባዥ እንግዶች፡-

1ኛ.   አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁሏህ)

2ኛ.   አሸይኽ ሐሰን ገላው (ሐፊዘሁሏህ)

3ኛ.   አሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዘሁሏህ)

በተጨማሪ ሎሎችም ኡስታዞች የሚገኙ ይሆናል፡፡

👌 በአሽይኽ ዓብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚይ የሚሰጠው ወርሀዊ ፕሮግራማችን ከፊታችን ጁሙዓህ ከአስር ሰላት በኋላ ጀምሮ በተለመደው ሰአት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

አድራሻ፡-  አልኢስላሕ መድረሳ ፉሪ ኑሪ ሜዳ ባጃጅ  ተራ መጨረሻ

ሰዓት፡- ልክ 2፡30 ይጀምራል፡፡

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!!!



የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah


📲 በባለፈው በ 1446 አ/ሒ ሻዕባን 15 - 17 ላይ በተካሔደው የሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ ታላቁ ኮንፈረንስ በውድ እና ብርቅዬ መሻይኾች፣ አስታዞ እና ዱዓቶች የተደረጉ ሙሀደራዎች ፈትዋዎች ምክሮች ኮርሶች አንደሚከተሉት ታገኛላችው ፋይሎቹን ርእሶቻቸውን ጠቅ በማድረግ ታገኛቸዋላችሁ!

1, ሙሀደራ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ
"ስለ ታማኝነት እና በጎ መዋል ወይም ማሳመር!!"

2, ሙሀደራ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ
“እንግዳን በክብር ማስተናገድ በኢስላም አስተምሮ!!”

3, ሙሀደራ በኡስታዝ ሙሀመድ ኪርማኒይ ሀፊዘሁላህ
“ስለ ቁርአን!!”

4, ኹጥባ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ
“የረመዳን ትሩፋቶች!!”

5, ኮርስ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ
ሹሩጦ ሶላት ወአርካኑሃ ክፍል አንድ

ሹሩጦ ሶላት ወአርካኑሃ ክፍል ሁለት

ሹሩጦ ሶላት ወአርካኑሃ ክፍል ሶስት

6, ሙሀደራ በሸይኽ መህቡብ አስ’ሳንኩሪይ ሀፊዘሁላህ
“ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ ማስጠንቀቅ ከአህሉ ሱና መሰረቶች መካከል አንዱ ነው!!”

7, ሙሀደራ በሸይኽ ሙባረክ አል-ወልቂጢይ ሀፊዘሁላህ
“ስራን ለአላህ መነጠል!!”

8, ሙሀደራ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ
"ስለ ተውሒድ፣ አስማእ ወሲፋት እና ኢስቲዋእ!!”

9, ሙሀደራ በኡስታዝ ሙሀመድ ኪርማኒይ ሀፊዘሁላህ
“ምክር በስልጥኛ!!”

10, ሙሀደራ በሸይኽ መህቡብ አስ’ሳንኩሪይ ሀፊዘሁላህ
“ሱናን አጥብቆ መያዝ በስልጢኛ!!”

11, ሙሀደራ በኡስታዝ ባህሩ ተካ ሀፊዘሁላህ
"ስለ ተውሒድ ማስተማር ከሺርክ ማስጠንቀቅ ክፍል አንድ!!”

"ስለ ተውሒድ ማስተማር ከሺርክ ማስጠንቀቅ ክፍል ሁለት!!”

12, ሙሀደራ በሸይኽ ኑሪ ሀፊዘሁላህ
“ስለ ኢስቲቃማ!!”

13, ፈትዋ በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ ሀፊዘሁላህ

14, “አጭር ምክር በኡስታዝ ሱልጣን አል-አሰሊይ ሀፊዘሁላህ!!"

15, “አጭር ምክር በኡስታዝ ኸድር አል-ሀላቢይ ሀፊዘሁላህ!!"

16, “አጭር ምክር በሸይኽ ኸድር አል-ሀዋሲይ ሀፊዘሁላህ!!"

17, “አጭር ምክር በኡስታዝ ፈጅሩዲን አል-አዳሚይ ሀፊዘሁላህ!!"

18, “አጭር ምክር በኡስታዝ ሙህዪዲን አል-ሆሳኒይ ሀፊዘሁላህ!!"

19, “አጭር ምክር በኡስታዝ ኑራዲስ አል-ቡታጀሪይ ሀፊዘሁላህ!!"

20, “አጭር ምክር በኡስታዝ ዐብዱል መጂድ አድ’ዳሎቺይ ሀፊዘሁላህ!!"

21, "የተከበሩ አዛውንት ምስክርነት!!"

አላህ እንደዚህ አይነት ኮንፈረንሶችን ያብዛልን።


✅ሰበር ዜና  ሰበር ዜና
 السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللّٰه  وَبَرَكَاتُهُ



ታላቅ የሙሐደራ ድግስ  በቀቤና ልዩ ወረዳ በጀብዱ ቀበሌ እና  በእጉማ መንደር  ተሰናድቶ ይጠብቃችኃል

🔴 መቼ ነው   ካለቹን በአላህ ፍቃድ የፊታችን ሐሙስና ጁምዓ ማለትም ከቀን 13/06/2017 ጀምሩ ለሁለት ቀን ተከታታይ የሚቆይ ሲሆን

✅ የሙሀደራው  ብርቅዬ ተጋባዥ እንግዶቻችን

🔷 ብርቅዬና ተናፋቂ ከሆኑ መሻይኾች ውስጥ

🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ  ያሲን (ከለተሞ)
🎙አሸይኽ   ሙባረክ አልወለቅጢ  (ከቀቤና)

ከኡስታዞች

🎙ኡስታዝ ባህሩ ተካ        (ከአዲስ አበባ)
🎙ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ   ( ከአዲስ አበባ)
🎙ኡስታዝ አብዱልቃድር   (ከአዳማ)
🎙ኡስታዝ አብዱልቃድር   (ከድንድላ)
እናም በአላህ ፍቃድ ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ ኢንሻአላህ

ስለዚህ አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል
ከተማ ያላቹህ ወንድም እና እህቶች ቤተሰቦቻችንን በስልክ በመቀስቀስ ጨለማ ከሆነው ሸርክ ወጥተው ብርሀናማ ወደ ሆነው ተወሂድ እንዲገቡ የበኩላቹን አስተዋጾ እንድታረጉ ባአላህ ስም እንጠይቃቸዋለን

እናም ባ4ቱም አቅጣጫ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ለዚ በጣም አጓጊና  ተናፋቂ ለሆነው ሙሀደራ ስንጋብዛቹ በታላቅ ደስታ ነው

አላህ እኛንም እናተንም ቀጥ ወዳለው መንገድ ከሚያመላክቱ ባሮቹ  ያድርገን


⚫️ ኢብኑ ሙነወር፣ኸድር ከሚሴው፣ ሳዳት ከማል፣ አቡ ሙስሊም፣ ሰዒድ ሙሳ፣አቡ ሙዓዝ እነዚህ አካላት :-  ድሮ ስለሙመይዓዎች ይህን ይሉ ነበር ዛሬ  በዚሁ ባስጠነቀቁት የተመዩዕ አደጋ ውስጥ ገብተዋል።

ከራሳቸው አንደበት አድምጡት⬇️

ከክፍል 1 እስከ ክፍል 15  ድረስ በቀላሉ ለማግኘት👇👇👇
👉 ክፍል አንድ አቡ ሙስሊም👇

https://t.me/YusufAsselafy/4248

ክፍል ሁለት አቡ ሙስሊም👇
https://t.me/YusufAsselafy/4253

ክፍል ሶስት ኸድር ከሚሴ👇
https://t.me/YusufAsselafy/4269

ክፍል አራት ኢብኑ ሙነወር👇
https://t.me/YusufAsselafy/4272?single

ክፍል አምስት ኸድር ከሚሴ👇
https://t.me/YusufAsselafy/4332

ክፍል ስድስት አቡ ሙስሊም👇
https://t.me/YusufAsselafy/4345

ክፍል ሰባት ሰዒድ ሙሳ👇
https://t.me/YusufAsselafy/4355

ክፍል ስምንት አቡ ሙዓዝ ሀሰን👇
https://t.me/YusufAsselafy/4363

ክፍል ዘጠኝ ሳዳት ከማል👇
https://t.me/YusufAsselafy/4366

ክፍል አስር ኸድር ከሚሴ👇
https://t.me/YusufAsselafy/4423

ክፍል አስራ አንድ ኢብኑ ሙነወር👇
https://t.me/YusufAsselafy/4432

ክፍል አስራ ሁለት ኢብኑ ሙነወር👇
https://t.me/YusufAsselafy/4436

ክፍል አስራ ሶስት ሳዳት ከማል👇
https://t.me/YusufAsselafy/4443

ክፍል አስራ አራት ኢብኑ ሙነወር👇
https://t.me/YusufAsselafy/4521

ክፍል አስራ አምስት ኢብኑ ሙነወር👇
https://t.me/YusufAsselafy/4529

⚠️ የነ ኢብኑ ሙነወር የድሮ አቋማቸው ይህ ነበር አሁን ተቀይራዋል ተንሸራተዋል ስንል በምክንያት ነው።

እኛ አሁንም የምንለው ትናንትና አናንተ ሰትሉት ወደነበረው አቋም ተመለሱ ነው የምንለው።

ሁላቹም መሪዎቹም ሙሪዶቹም ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።
الحَقُّ أَقْوَى مِنَ الرِّجَالِ
ሐቅ(እውነት) ከግለሰቦች ይበልጣል ።


وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ  سورة طه ٤٧
  ➡️ ሰላም ቀጥተኛውን  መንገድ በተከተለ ላይ ይሁን  ሱረቱ ጧሀ 47


         ✍ አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!
     https://t.me/YusufAsselafy
   
http://t.me/aredualelmumeyia
http://t.me/aredualelmumeyia


ማብራሪያ

የራያ ቆቦ አህሉ ሱና ወልጀማዓ  ግሩፕ  ላይ በመግባት  የቀጥታ ስርጭት(የሊቭ  
የዳዕዋ ፕሮግራም ስለሚኖር ሁላችንም ቀድመን በመገኘት የዳዕዋዉ ተጠቃሚ እንሁን
ዳዕዋዉ  ላይ የሚገኙ ኡስታዞች

1   ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት ከሀራ

2   ሸይኽ ሑሴን ከረም ከሀራ

3 ሸይኻችን ሸይኽ ሁሴን አደም


ናቸው ቢኢዝኒላህ በሰአቱ እንገኝ
ወሰላሙ አለይኩም ወረሕመቱሏህ

የጎብየ አህሉል ሱና ወልጀምዓ የኡስታዝ መዋጮ ጉሩፕ
https://t.me/+BMjspM54MysxOTA8

ንግድ ባንክ  1000676050284
ቡና ባንክ      2409591000256


Репост из: 📚ለሱኒይዎች ብቻ 💐💐💐💐
♻️ بــــشــــرى ســـارة ♻️

አስላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ

🔆  ታላቅ የደስታ ብስራት ለመላው ለሳንኩራና በዙሪያዋ ላላችሁ  ሙስሊሞች በሙሉ

🔆 በብላል ኢብን ረባህ መስጅድ  ታላቅ የደዕዋ ፖሮግራም ተዘጋጀ !!!

🛣  ቦታ  🛣

በመእከላዊ ኢትዮጵያ ክሊል በስልጤ ዞን በዓ/ገበያ ከተማ አስተዳደር በገተም ዚኮ  ቀበሌ ሀጂ ሻፊ መንደር  የፊታችን ሀሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ል

🕰 ሰዐት 🕰

ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት

🕰 ግዜው የታላቁ ረመዷን መቀበያ ስለሆነ ፖሮግራሙም እንዴት እንቀበለው

✈️ ተጋባዥ ከመሸይኾች 🛬

🎙ሸይኽ መሕቡብ ከ ሳንኩራ አለም ገበያ  አለህ ይጠብቃቸው

🚗 ከኡስታዞች 🚗

🎤 ኡስታዝ ኢዘዲን ሲራጅ ከሁልበራግ አለህ ይጠብቃቸው

🎤 ኡስታዝ ነስረዲን ከጉጣንቾ አለህ ይጠብቃቸው

🎤ኡስታዝ ሙሰፋ ከድር ከሳንኩራ
አላህ ይጠብቃቸው

🎤 ኡስታዝ ሙሐባ ሱራጅ ከሻድገር አለህ ይጠብቃቸው

🎤አቡ ፋሩቅ ጀማል አህመድን ከሳንኩራ አላህ ይጠብቃቸው

🎤 አቡ አብዱረህማን በህረዲን ሻፊ ከሀላባ አለህ ይጠብቃቸው

🏍 ከገጣሚዎች 🏍

🎧 1 ወንድማችን ኢብን ኑሪ አለህ ይጠብቀው
እናም እንሻ አላህ ሌሎችም የሱና ኡስታዞች እና ወንድሞች ይገኛሉ።

ይህን የመሰለ የሰለፍያ ፖሮግራም አይደለም መቅረት ማርፈድ ራሱ ያስቆጫል

📚 የፖሮግራሙ አዘጋጅ የመድረሳው ጀመዓ ከሳንኩራ ሰለፍይ ወጣት ጀመዓ ጋ በመተባበር !!!

ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን #ጆይን ይበሉ 👇👇👇
https://t.me/Ibnushaffi
https://t.me/Ibnushaffi
https://t.me/Ibnushaffi

Показано 20 последних публикаций.