ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"አላህ እንዳንተ አይነት መፍጠሩን ቀጥሏል ብዬ አላስብም ነበር፡፡" ኢብኑ ደቂቀል ዒድ
"ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!" ኢብኑል ሐሪሪ

በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏሂ] የተጻፈ መጽሐፍ፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
ችግርህን ለሠው ስታማክር መዘርዘር :ማስረዳት ይጠበቅብሀል ሲቀጥል መፍትሄ ላታገኝ ትችላለህ እናማ ችግርህን ለሀያሉ አምላክ አውራው ምክንያቱም ችግርህን ሊቀርፍልህ የሚችለው እርሱ ብቻ ስለሆነ::
https://t.me/UstazKedirAhmed


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለወሎ መሻይኽ፣ ዱዓት እና ወጣቶች
~
ይህንን እያያችሁ እንዴት እንቅልፍ ይወስዳችኋል? ይሄ ወገን አያሳዝንም ወይ? ይሄው "ታቦታችን" እያሉ ነው። እነዚህ አካላት ከኢስላም ምን ቀራቸው? በጎጣቸው መስጂድ እያቃጠሉ፣ ሙስሊም እየ ~ ^ገደሉ ወሎ ላይ ሲደርስ "ዓለም ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል" የሚሉት እንዲህ አይነቱን ደም እንባ የሚያስለቅስ የማንነት ቀውስ ለማስቀጠል ነው። እንዲህ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡት ያለ ምክንያት እንዳይመስልህ። ወሎ የአፄ ዮሐንስ እና አፄ ምኒልክ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ጥሎት ካለፈበት የማንነት ምስቅልቅል አልወጣም። እንዲወጣም አይፈለግም። ራሱም በምን ዓይነት ጫና እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ውስጥ እንድገባም አያውቅ።

ዱዓት እና ወጣቶች! ይህንን ወገን የማንቃት ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ። "ወሎ የመሻይኽ አገር"፣ "ወሎ አዝሃሩል ሐበሻ" የሚለው ራስን መደለል የትም አያደርስም። ለወገን የማይሆን ስም ቢከፍቱት ተልባ ነው፣ ጉራ ብቻ!
ከበፊቱ አንፃር ሲታይ ለውጥ እንዳለ ይገባኛል። ብዙ አካባቢ ይሄ ችግር ቀንሷል። ነገር ግን የተሻለ የሰው ኃይል ባለበት ደሴና ዙሪያዋ ላይ ይሄን ያህል አሳማሚ ነገር ማየት የመሻይኹን እና የዱዓቱን መተኛት ነው ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: ጃዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የዳዕዋና የቂርዓት ማዕከል {Official Channel }
የደዕዋ ድግስ በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ


ታላቅ የምስራች ለደሴ እና አከባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ  በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 25/05/2017 ዓ·ል  በአላህ ፍቃድ የወሎ መናገሻ እና እንብርት በሆነችው  ደሴ  ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ  ከአድስ አበባ ፣ ከአፋር፣ ከኸሚሴ፣ እና  ከሌሎችም ሀገራት በሚመጡ ብርቅዬ መሻይኾችና ኡስታዞች   ከጧቱ 3:00 ጀምሮ  እጅግ በደመቀ እና ባማረ መልኩ  የደዕዋ ድግስ ተዘጋጅቶ ሲጠብቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው
 
የዕለቱ ተጋባዥ መሻይኾችና ኡስታዞች


① ሸይኽ አወል አህመድ አል ኸሚሴ
ርዕስ:– ረመዷንን እንዴት እንቀበለው

② ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ(አቡ ሒዛም)
ርዕስ:–ሱናን አጥብቆ መያዝና ቢድዓን መራቅ(መጠንቀቅ)

③ ኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ:– የተውሂድ አሳሳቢነትና የሽርክ አደገኝነት እንድሁም በምን ላይ ነው  አንድ የምንሆነው

④ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሙሀመድ አህመድ)
ርዕስ:–ኢልምን በመፈለግ ላይ መበርታት፣የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት እና መልካም ስነ ምግባር

ማሳሰቢያ:–ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ‼

N·B :– የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 

አዘጋጅ፦ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል


URGENT: - የደሴ ከተማና በዙሪያዋ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፕሮግራሙ ዘንድ ትታደሙ ዘንድ ጥሪ አድርገንላችኋል።

ጆይን ይበሉ ቻናል

t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ

https://t.me/yedesse_selfyochi_group


Репост из: Birhan Nega
ለመረጃ ያክል

#Allert #commercialbankofethiopia


Репост из: የቡታጅራ አህለሱና ቂራኣትና ዳዕዋ ቻናል
ታላቅ የዳዕዋ ዝግጅት በቡታጅራ ከተማ!

እነሆ የፊታችን እሁድ ቀን 18/05/2017 በሙሳ ራማሽ (ቆዳና ሌጦ) መስጂድ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ዝሁር የሚቆይ በአይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል። እርሶም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመሆን ይህንን ፕሮግራም ትካፈሉ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች፦
☞ ኡስታዝ ሳዳት ከማል
☞ ኡስታዝ ዐብዱልናስር
☞ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ (መገኘት ከቻለ)

እና ሌሎችም ዱዓቶች ይገኙበታልና ፈፅሞ እንዳያመልጣችሁ።

«ጥሪን ማክበር የኢስላም ግዴታ ነው»


https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቄራ ሰላም መስጂድ ማስተባበያ አውጥቷል። በሌሎች አካላት የተለጠፈ እንደሆነ የመስጂዱ ጀማዐ አባላት የፃፉትን አይቻለሁ። እንዳሉት መረጃው ያላቸው ከሆኑ ቀደም ብለው ማስታወሻ ቢያወጡ መልካም ነበር። የሆነ ሆኖ ስለሰጣችሁት ማስታወሻ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ይቺ ናት ኢትዮጵያi
~
በነገራችን ላይ በሰላም አብሮ መኖር እና መሸለጥለጥ ይለያያሉ። በመስጂድ ስም እንዲህ አይነት ልዩ የማሽቃበጥ ቢድዐ ማስተዋወቅ ያስንቃል እንጂ አያስደንቅም። ለመሆኑ መስጂዱ አባት የለውም እንዴ? ነው ወይስ "የሚሻሉት" ናቸው ይህን ያደረጉት? ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዛሬ የዑምደቱል አሕካም ደርስ እንጀምራለን፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የተጠናቀቀ የአልዐቂደቱል ዋሲጢያህ ኪታብ ደርስ
~
ክፍል 1 - https://t.me/IbnuMunewor/6642
ክፍል 2- https://t.me/IbnuMunewor/6651
ክፍል 3- https://t.me/IbnuMunewor/6657
ክፍል 4- https://t.me/IbnuMunewor/6674
ክፍል 5- https://t.me/IbnuMunewor/6682
ክፍል 6- https://t.me/IbnuMunewor/6690
ክፍል 7- https://t.me/IbnuMunewor/6695
ክፍል 8- https://t.me/IbnuMunewor/6736
ክፍል 9- https://t.me/IbnuMunewor/6753
ክፍል 10- https://t.me/IbnuMunewor/6761
ክፍል 11- https://t.me/IbnuMunewor/6768
ክፍል 12- https://t.me/IbnuMunewor/6773
ክፍል 13- https://t.me/IbnuMunewor/6778
ክፍል 14- https://t.me/IbnuMunewor/6793
ክፍል 15- https://t.me/IbnuMunewor/6800
ክፍል 16- https://t.me/IbnuMunewor/6812
ክፍል 17- https://t.me/IbnuMunewor/6823
ክፍል 18- https://t.me/IbnuMunewor/6834
ክፍል 19- https://t.me/IbnuMunewor/6841
ክፍል 20- https://t.me/IbnuMunewor/6848
ክፍል 21- https://t.me/IbnuMunewor/6854
ክፍል 22- https://t.me/IbnuMunewor/6860
ክፍል 23- https://t.me/IbnuMunewor/6865
ክፍል 24- https://t.me/IbnuMunewor/6872
ክፍል 25- https://t.me/IbnuMunewor/6878


ሁላችንም ጊዜ ጠብቀን ጓዛችንን ሸክበን ወደዚህኛው አለም ነው ጉዟችን ። እንደየ ስራችን መጠን የጓዛችን መለያየት..... አላህ ይዘንልን!!

@IbnTaymiyyahrahimahullah


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
🌿ሴትን መንካት ውዱእ ያፈርሳልን?🌿
~
♻️ ማሳሰቢያ፦
ለወንድ ሴትን መንካቱ ውዱእ ያፈርሳልን? የሚለውን ነጥብ ስናነሳ በተመሳሳይ ለሴት ወንድን መንካት ውዱእ ያፈርሳል ወይ የሚለው ታሳቢ ይደረጋል። ስለዚህ ጉዳዩ በአንዱ ፆታ ላይ የሚገደብ አይደለም።

ተቃራኒን ፆታ መንካት ውዱእ ያፈርሳል ወይስ አያፈርስም በሚለው ላይ ከኢስላም ምሁራን 3 ጎላ ያሉ የተለያዩ አቋሞች ተንፀባርቀዋል።

✅ አቋም አንድ ✅

በየትኛውም ሁኔታ ሴት መንካት ውዱእ ያፈርሳል የሚል ነው። ይሄ የኢማሙ ሻፊዒይ አቋም ሲሆን ማስረጃቸውም ተከታዩዋ የቁርኣን አንቀፅ ነች፦
(أَوْ لاَمَسْتُمُ النِّسَاء)
"ወይም ሴቶችን ብትነኩ (ሶላትን ራቁ)።" [ኒሳእ፡ 43]

ነገር ግን እዚህ ላይ የተጠቀሰው አካላዊ ንክኪ ሳይሆን የግብረ ስጋ ግንኙነት እንደሆነ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ በግልፅ ፈስረውታል። ተፍሲራቸው ከሌሎች የተሻለ ክብደት ይሰጠዋል። ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) "አላህ ሆይ! በዲን ላይ አስገንዝበው። ተፍሲርንም አሳውቀው" ብለው ዱዓእ አድርገውላቸዋልና። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
ኢብኑ ጀሪርም ይህኛውን ተፍሲር ነው የመረጡት። ስለዚህ የተጠቀሰውን ቁርኣናዊ መልእክት በአካላዊ ንክኪ መተርጎም ልክ አይሆንም።

✅ አቋም ሁለት ✅

ሴትን መንካት ከነጭራሹ ውዱእ አያፈርስም የሚል ነው። ይሄ የአቡ ሐኒፋህ አቋም ነው። በዚህ ላይ ያለው ማስረጃም፦

1ኛ፦ ጦሃራን በተመለከተ ግልፅ አፍራሽ እስከሚገኝ ድረስ መነሻ መሰረቱ የተደረገው ውዱእ ባለበት መኖሩ ነው። መጥፋቱን የሚጠቁም ግልፅ ማስረጃ እስከሚቀርብ ድረስ ባለበት ይዘልቃል። ሴትን መንካት ጦሀራን የሚያጠፋ ለመሆኑ ደግሞ ማስረጃ የለም። ስለዚህ ውዱኡ ባለበት ይቆያል ማለት ነው።

2ኛ፦ እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
كُنْتُ أَنَامُ بَيْنَ يَدَيْ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ وَرِجْلَايَ فِي قِبْلَتِهِ فَإِذَا سَجَدَ غَمَزَنِي فَقَبَضْتُ رِجْلَيَّ فَإِذَا قَامَ بَسَطْتُهُمَا
"ከአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ፊት ለፊት እተኛ ነበር። እግሮቼ በቂብላቸው በኩል ይሆናሉ። ሱጁድ ሲወርዱ ይቆነጥጡኛል እግሮቼን እሰበስባለሁ። ሲነሱ አዘራጋቸዋለሁ።" [ቡኻሪ፡ 382]
በነሳኢ ዘገባ ደግሞ "ዊትር ሊያደርጉ ሲያስቡ ጊዜ በእግራቸው ይነኩኛል።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]

3ኛ፦ አሁንም እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
فَقَدْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ لَيْلَةً مِنْ الْفِرَاشِ فَالْتَمَسْتُهُ فَوَقَعَتْ يَدِي عَلَى بَطْنِ قَدَمَيْهِ وَهُوَ فِي الْمَسْجِدِ وَهُمَا مَنْصُوبَتَانِ ...
''የአላህ መልእክተኛን (ﷺ) በአንድ ሌሊት ከመኝታቸው አጣኋቸው። ስፈልጋቸው መስጂድ ውስጥ ሆነው እጄ በውስጥ እግሮቻቸው ላይ አረፈች። እነሱ (እግሮቻቸው) ተተክለው (መሬት ይዘው ቀጥ ብለው) ነው ያሉት። ..." [ሶሒሕ ሙስሊም]

በነሳኢይና በይሀቂይ ዘገባ ላይ ደግሞ "እሳቸው ሱጁድ ውስጥ ሆነው" የሚል ጭማሪ አለው።
በነዚህ ሐዲሦች ውስጥ ነብዩ (ﷺ) ሶላት ውስጥ ሆነው ዓኢሻን መንካታቸው ንክኪው ውዱእ አፍራሽ እንዳልሆነ ያሳያል።

♻️ ብዥታ፦
ሻፊዒያዎች ግን እጅ አይሰጡም። "ምናልባት ከቀጥተኛ አካላዊ ንክኪ የሚጠበቅ ነገር (ጨርቅ) ላይስ ቢሆን የነኳት?" ይላሉ። ሸውካኒይ በዚህ ላይ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፦ "ይሄ አጉል መድረቅረቅና ግልፅ ተቃርኖ ያለበት አረዳድ ነው።"

4ኛ፦ አሁንም እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
4- أن النبي ﷺ قَبَّلَ امْرَأَةً مِنْ نِسَائِهِ ثُمَّ خَرَجَ إِلَى الصَّلَاةِ وَلَمْ يَتَوَضَّأْ
"ነብዩ (ﷺ) ከሴቶቻቸው አንዷን ከሳሙ በኋላ ከዚያ ለሶላት ወጡ። ውዱእ አላደረጉም።"
ይህንን መረጃ በርካቶች ከሰነድ አንፃር ደካማ ነው ሲሉ ኢብኑ ጀሪር፣ ኢብኑ ዐብዲልበር፣ ዘይለዒይ እና አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። ዶዒፍ ነው የሚሉ አካላትን ውሳኔ ብናስቀድም እንኳ ያሳለፍናቸው መረጃዎች በቂ ናቸው።

✅ አቋም ሶስት ✅

በስሜት ከነካ ውዱእ ይፈርሳል። በስሜት ካልሆነ ግን አይፈርስም የሚል ነው። ይሄ የማሊኪያና የሐናቢላ አቋም ነው። ያደረጉት የቀደሙትን ሁለት አቋሞች መረጃዎች ለማጣጣም መሞከር ነው። ሴትን መንካት ውዱእ ያፈርሳል የሚሉት ወገኖች የሚያቀርቡት መረጃ ተፍሲራቸው ልክ እንዳልሆነ አሳልፈናል። ስለዚህ ይሄኛው ሃሳብ ልክ የሚሆነው የነዚያኞቹ ተፍሲር ልክ ቢሆን ነበር። ተፍሲሩ ልክ ካልሆነ ይሄኛው አካሄድ ውሃ አያነሳም።
ስለዚህ ሁለተኛው ውዱእ አያፈርስም የሚለው አቋም ያለ ተቃርኖ ይቀራል ማለት ነው። ስለሆነም በስሜትም ሆነ ያለ ስሜት፣ አስቦበትም ሆነ በስህተት፣ ቤተሰብም ትሁን ሩቅ (አጅነቢያህ) በየትኛውም ሁኔታ ሴት መንካት ውዱእ አያፈርስም የሚለው አቋም ትክክለኛ ነው ማለት ነው።

♻️ ማሳሰቢያ፦

1- በስሜት የነካ ሰው ፈሳሽ (መዝይ) ከወጣ በዚህን ጊዜ ውዱኡ ይበላሻል።
2- ንክኪው ብቻውን ውዱእ አያፈርስም ማለት ለወንድ አጅነቢያህ ሴትን ወይም ለሴት አጅነቢይ ወንድን መጨበጥ ይቻላል ማለት አይደለም። ክልክል ነው። ያወራነው ስለ ውዱእ ብቻ ነው።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 6/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: الشباب السلفيين

አስፈሪ ጊዜ ላይ ደርሰናል!!
---------------------------
ይህ እየሆነ ያለው 🇪🇹ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

...እውነት ግን አሏህ ምን ሊለን ፈልጎ ነው⁉️

በሰሞኑ የሚታየውና የሚስተዋለው ጉዳይ ያስፈራል ምድር የተቆጣች "በቃኝ" ያለች ትመስላለች።

በምስሉ እንደምትመለከቱት ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሲስተዋል የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ያለ ማቋረጥ ከቀጠለ በኋላ እነሆ በምታዩት መልኩ
ውሃ፣
ጭስና
እሳት ከምድር ወደ ላይ እየፈነዳ ይገኛል።

➢አሁንስ አንገሰፅም!?
➢አሁንስ ወደ አሏህ አንመለስም!?
➢አሁንስ አንቶብትም!?
➢አሏህ በዚህ ክስተት ሊነግረን የፈለገው ነገር አለ!!
➢ሊያስታውሰን ሊያሳየን የፈለገበት ምክንያት አለው።

ወደ አሏህ እንመለስ ጉዳዩ ሸሪዐዊ መዳኒት እንጂ ሳይንሳዊ መላምት አያስፈልገውም።

🤲አላህ ሆይ ታረቀን🤲
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ቅናት አያረጅም!
~
የአዛንና የሶላት ሰዓት አጭር ነው። በጥላቻ ስትሞላ ግን 5ቱ ደቂቃ አምስት ሰዓት ይሆንብሃል። ሰፈራችን ላይ የሱብሕ አዛን 11፡25 አካባቢ ተደረገ። ሶላቱ ደግሞ ሩብ ጉዳይ አካባቢ። ሁሉም ቢደመር 20 ደቂቃ አይሞላም። ከማዶ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ግን እስካሁን አልተቋረጠም። ይሄ የየሰፈሩ እውነታ ነው። ግን የራስ እንትን አይገማም።

የዚች ሃገር ትልቁ ችግር ቅናት ነው። ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚገፋው አስተማሪ ከክልከላው ጀርባ ያደፈጠው ምክንያቱ ምቀኝነት ነው። ሌላው እንዲሁ ሽፋን ነው። የራሱን ማስለበስ ሲያቅተው። ሌሎች ላይ ይዘምታል። "ለሙስሊሞች ሒጃብ ከተፈቀደ እኛም ነጠላ እንለብሳለን" የሚለው የምቀኛ ሰፈር ልጆች መፈክርም የታወቀው በሽታ ነው፣ ቅናት። "ለሙስሊሞቹ መስገጃ ከተፈቀደ ለኛም መፀለያ ይፈቀድልን" የሚለው የምቀኝነት ልክፍትም የተለመደና ዝነኛ ህመም ነው።

ምቀኝነት እየተጋተ ያደገ አካል አድጎ አርጅቶ፣ በምርኩዝ እየሄደ፣ የሌሎችን ሃገራት ሁኔታ እያየ እንኳ አይለወጥም። እንዲያውም እየባሰበት ይሄዳል። ወደው አይደለም "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም" የሚሉት። በቅናት የገረጣ ፊት በቅባት አይወዛም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የደዕዋ ፕሮግራም
~
ዛሬ ቅዳሜ ቀጥታ ከዙህር ሶላት በኋላ
ቦታ፦ አፍንጮ በር ፣ አቅሷ መስጂድ

ተጋባዥ እንግዶች
አቡል ዐባስ
እና
ኢብኑ ሙነወር

በ 6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማ0 የተሰናዳ


#ክፍል_14

                 الحديث الخامس عشر

#15ኛው_ሐዲሥ: #መልካም_ተናገር፣ #ካልሆነ_ዝም_በል

عن أبي هريرة رضي الله عنه، عن رسول الله ﷺ قال: "من كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليقل خيرا أو ليصمت، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم جاره، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم ضيفه" رواه البخاري ومسلم.


ከአቡ ሁረይራ رضي الله عنه ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው መልካም ይናገር፤ ወይ ዝም ይበል። በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ጎረቤቱን ያክብር። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው እንግዳውን ያክብር።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። [6018] [47]

   #ሐዲሡ_ያለው_የላቀ_ደረጃ፦

  ➡️ ታላቁ የማሊኪያ ኢማም ኢብኑ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ሁሉም ስነ ምግባራት ከአራት ሐዲሦች የሚመነጩ ናቸው። (እነሱም፦) 'በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ መልካም ይናገር፤ ወይ ዝም ይበል' የሚለው የነብዩﷺ ንግግር፤ 'ከአንድ ሰው የኢስላም ውበት የሆነው የማያገባውን መተው ነው' ማለታቸው፤ "አትቆጣ" የሚለው አጭር ምክራቸው እና 'አንዳችሁ ለወንድሙ የሚወደውን ለራሱ እስካልወደደ ድረስ አላመነም' የሚሉት ናቸው።" [ፈትሑል ቀውዩል መቲን፡ 49]

     #ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቀም_ነገሮች፦

✅  ሁሌም መልካምን መናገር የሚበረታታ እንደሆነ፣

✅ ፍሬ ከሌለው ወሬ ዝምታ እንደሚመረጥ፣

✅ መልካም መናገር፣ ጎረቤትንና እንግዳን ማክበር ከኢማን እንደሆነ፣

✅ ኢስላም በሰዎች መካከል መከባበር ያለበት ጤናማ ማህበራዊ ህይወት እንዲኖር የሚያደርግ ውድ ሃይማኖት እንደሆነ ከሐዲሡ እንማራለን።

#ማሳሰቢያ፦
 
    🛑 አንድ ጎረቤት ሙስሊም እና ዘመድ ከሆነ ከጉርብትና ሐቅ በተጨማሪ የኢስላምና የዝምድና ሐቅ አለው። ሙስሊም ግን ባዳ የሆነ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና እና የኢስላም ሐቅ አለው። ሙስሊም ያልሆነ ዘመድ ጎረቤት የጉርብትናና የዝምድና ሐቅ አለው። ሙስሊም ያልሆነ ባዳ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና ሐቅ አለው።

    🛑 ከጎረቤትም በሩ ቅርብ በመሆኑ ወደ ቤት የሚገባውን እየተመለከተ ልቡ የሚንጠለጠል የሆነው ይበልጥ መልካም ሊዋልለት ይገባል። የጎረቤትን ሐቅ ከባድነት ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው፦ "ጂብሪል በጎረቤት ላይ እኔን አደራ ከማለት አልተወገደም፣ ያስወርሰዋል ብየ እስከምጠረጥር ድረስ!!" [ቡኻሪ፡ 6015፣ ሙስሊም፡ 2624]
ታዲያ እንደዚህ ሐቁ ከባድ የሆነን ጎረቤት ማስቸገር፣ ለጎረቤት ስጋት መሆን ኢማንን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከባድ ጥፋት ነው። ነብዩ ﷺ በአንድ ወቅት "ወላሂ አያምንም! ወላሂ አያምንም! ወላሂ አያምንም!" አሉ። "ማነው እሱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ?" ሲሏቸው "ጎረቤቱ ተንኮሉን የማያምነው (የሚሰጋው) ሰው ነው" አሉ። [ቡኻሪ፡ 6016]

   🛑  የእንግዳ ሐቅ ደግሞ ከአቅም በላይ ለሆነ ወጭ ሳይዳረጉ ቤት ያፈራውን በማቅረብ፣ በፈገግታ በመቀበል፣ መልካምን በመናገር እንግዳው ዘና እንዲል እንዳይጨናነቅ ማድረግ ነው።

✍ ኢብኑ ሃሩን ከወላይታ ሶዶ በዱአ አትርሱኝ
  
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏህ] የተዘጋጀ መጽሐፍ።

👉  የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር (ገጽ 38-40)


    ``ኢንሻአላህ ይቀጥላል``

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah


#ክፍል_13

                     الحديث الرابع عشر

#14ኛው_ሐዲሥ፡ #የሙስሊም_ደም_መቼ #ሐላል_ይሆናል?

عَنْ ابْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ "لَا يَحِلُّ دَمُ امْرِئٍ مُسْلِمٍ  يشهد أن لا إله إلا الله، وأني رسول الله إلَّا بِإِحْدَى ثَلَاثٍ: الثَّيِّبُ الزَّانِي، وَالنَّفْسُ بِالنَّفْسِ، وَالتَّارِكُ لِدِينِهِ الْمُفَارِقُ لِلْجَمَاعَةِ". رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ،وَمُسْلِمٌ.


ከኢብኑ መስዑድ رضي الله عنه ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አሉ፦
"ከአላህ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአላህ መልእክተኛ እንደሆንኩ የሚመሰክር የሆነ ሙስሊም ደም (ህይወት) ከሶስት ነገሮች በአንዱ እንጂ አይፈቀድም (አይደፈርም)። (እነሱም፦) አግብቶ የሚያውቅ ዝሙተኛ፣ ነፍስ በነፍስ (አውቆ ነፍስ ያጠፋ) እና ሃይማኖቱን ትቶ ከሙስሊሙ ህብረት ያፈነገጠ ናቸው።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። [6878][1676]

#ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቁም_ነገሮች፦

✅  እነዚህ ህይወትን የሚያስከፍሉ ጥፋቶች (ዝሙት፣ ነፍስ ማጥፋትና ከኢስላም ማፈንገጥ) እጅግ ከባባድ ወንጀሎች እንደሆኑ፣

✅ የሙስሊም ህይወቱና ክብሩ በሸሪዐዊ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ፍጹም የማይደፈሩ እጅግ ውድና ጥብቅ እንደሆኑ እንማራለን።

#ማሳሰቢያ፦

🛑 በዚህ ሐዲሥ ከተዘረዘሩት ውጭ በተጨማሪ ሌሎችም ህይወት ላይ የሚያስፈርዱ ወንጀሎች አሉ። ለምሳሌ ያክል፦

1. የግብረ ሰዶም ድርጊት የፈፀመም ይሁን ፈቅዶ የተፈፀመበት ይገደላል። ነብዩ ﷺ "የሉጥ ህዝቦችን ስራ ሲሰራ ያገኛችሁትን ፈፃሚውንም የሚፈፀምበትንም ግደሉ" ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 6589]

2. በእንስሳት ላይ ግንኙነት የፈፀመ ይገደላል። ነብዩ ﷺ "እንስሳትን የተገናኘ ግደሉት። እሷንም ከሱው ጋር ግደሏት" ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5938]

3. ለአንድ መሪ ቃል ከተገባ በኋላ የሚነሳ ሌላ ተቀናቃኝ መሪ ይገደላል። ነብዩ ﷺ "ጉዳያችሁ በአንድ ሰው (መሪ) ላይ ከተሰበሰበ በኋላ ህብረታችሁን ሊበትን የመጣን ማንም ይሁን ማን ግደሉት" ብለዋል። [ሙስሊም፣ 1852]

🛑  በነዚህ ከባባድ ጥፋቶች ላይ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ቢወሰድባቸው ዘር አይቀላቀልም፤ ነፍስ አይጠፋም፤ ስነ ምግባር አይዘቅጥም፤ አስቀያሚ በሽታዎች አይንሰራፉም። ነገር ግን በግለሰብ መብትና በስልጣኔ ስም እነዚህ ከባባድ ጥፋቶችን የሚፈፅሙ አካላት ተገቢውን ቅጣት ባለማግኘታቸው የተነሳ ህይወት እንዲረክስ፣ አባታቸው የማይታውቁ ልጆች እንዲበዙ፣ የአባላዘር በሽታዎች እንደ ሰደድ እሳት እንዲስፋፋ፣ ወንጀለኞች የልብ ልብ እንዲሰማቸው ተደርጓል።

🛑    በዑለማዎች መካከል የተለያዩ ሀሳቦች ቢሰነዘሩባቸውም እንደ ሶላትን መተው፣ ጥንቆላ፣ በሙስሊሞች ላይ ለካፊሮች መሰለል፣... ያሉ ሌሎች ጥፋቶችም ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።


✍ #from_writer_በዱአ_አትርሱኝ

👉  የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር (ገጽ 36-38)

👉 @Twehid12
👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah


የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
ክፍል - 9
~
"የለተሞን ጀርሕ እና ተዕዲል ለምን አልተቀበላችሁም" እያለ የሚጮኸው መንጋ ለተሞን ተከትሎ እነ ሸይኽ ሱለይማን አሩሐይሊን እና እነ ሸይኽ ረዪስን ተብዲዕ አድርጎ ይሆን?
ካላደረጋችሁ የሰውየውን ጀርሕ መቀበል ግዴታ ነው ያላችሁትን ጥላችሁታል ማለት ነው። ይሄ ደግሞ መንሀጃችሁ ላይ ጥቁር ነጥብ ይጥላል። ሚናችሁን ልዩ። ወይ ለተሞን ወይ እነዚህን መሻይኾች አንዱን መጣል ነው።

"ለተሞ ተሳስቷል" ካላችሁ ሰውየው የሱና ዑለማኦችን እያብጠለጠለ ነው ማለት ነው። የሱና ዑለማኦችን "ከመንሀጅ ውጭ ናቸው" እያለ የሚዘባነን ወፈፌ ሑክሙ ምን ነበር? ህጉ ለተሞ ጋ ሲደርስ ይቀየር ይሆን?

ለተሞ ተነካ ብላችሁ ያለ ቦታው ስትጠቅሱት የነበረውን የሰለፎች ንግግር አስታውሱ። ከሙብተዲዕ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የሱና ሰዎችን መንካት ነው። ስለዚህ እነ ሱለይማን አሩሐይሊን ከሱና እያስወጣ ያለው ለተሞ ሑክሙ ምንድነው?

የሰውየውን ደፋርና አስቀያሚ ድምፅ ስሙት።
=
https://t.me/IbnuMunewor




#ክፍል_12

                     الحديث الثالث عشر

#13ኛው_ሐዲሥ፡ #ለራስ_የሚወዱትን_ለወንድም
                          #መውደድ


عَنْ أَبِي حَمْزَةَ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه خَادِمِ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ عَنْ النَّبِيِّ ﷺ قَالَ: "لَا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لِأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ". رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ، وَمُسْلِمٌ.


የአላህ መልእክተኛ ﷺ አገልጋይ ከነበሩት አቡ ሐምዛ አነስ ኢብኑ ማሊክ رضي الله عنه ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "#አንዳችሁ_ለወንድሙ #የሚወደውን_ለራሱ_እስካልወደደ_ድረስ_አላመነም (#እምነቱ_አልተሟላም)።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። [13] [45]

#ማሳሰቢያ፦
 
           ሐዲሡ በሌላ ዘገባ ላይ "#አንዳችሁ #ከመልካም_ነገር_ለወንድሙ_የሚወደውን_ለራሱ #እስካልወደደ_ድረስ_አላመነም" በሚል መልኩ ነው የተላለፈው። [ነሳኢይ፡ 5017] ስለዚህ የተፈለገው መልካም የሆነን ነገር ስለመውደድ ነው። እንጂ ብልሹ የሆነ ሰው ለራሱ የሚወደውን ክፉ አመል፣ ሱስ፣ ጥፋት፣ ... ለወንድሙ ቢወድና ቢተባበር በራሱም በወንድሙም ጥፋት ተጠያቂ ይሆናል እንጂ የሚወደስበት ምግባር አይደለም። ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ይህቺ '#ከመልካም #ነገር' የምትለዋ ጭማሬ ወሳኝ ጭማሬ ናት። የሐዲሡን መልእክት ረቂቅ በሆነ መልኩ ትገድበዋለች። ምክንያቱም '#መልካም' የሚለው ቃል ዱንያዊም ይሁን ኣኺራዊ ትእዛዛትና ፍቁድ ነገሮችን የሚጠቀልል ሲሆን ክልክል ነገሮችን ደግሞ ያወጣል። 'መልካም' የሚለው ቃል አይመለከተውምና። ይሄ ግልፅ ነው። ስለዚህ ከአንድ ሙስሊም ስነ ምግባር ሙሉነት ውስጥ የሚካተተው ለራሱ እንደሚወደው ለሙስሊም ወንድሙ መልካምን መውደድ ነው። ልክ እንዲሁ ለራሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለሙስሊም ወንድሙ መጥላት ነው።..." [አስሶሒሐህ፡ ሐዲሥ ቁ. 73]

           #ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቁም_ነገሮች፦

✅  ሙእሚን ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ ሊወድ እንደሚገባ፣

✅  የኢስላም ወንድምን ወይም እህትን መውደድ ከኢማን እንደሆነ፣

✅  ኢማን መልካም በመስራት እንደሚጨምር፣ ወንጀል በመስራት ደግሞ እንደሚቀንስ ከሐዲሡ እንማራለን።

✅  በዚህ ሐዲሥ መልእክት መስራት እርስ በርሱ የሚዋደድና መተሳሰብ የነገሰበት ህብረተሰብ እንዲኖር ያደርጋል።


✍ #from_writer_በዱአ_አትርሱኝ

👉  የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር (ገጽ 34-36)

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah


Репост из: MuhammedSirage M.Nur.
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አስቲዋእ - በአጭሩ

አላህ ከዓርሹ በላይ ነው - በአጭሩ

https://t.me/Muhammedsirage

Показано 20 последних публикаций.