TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ

24 Oct 2017, 19:35

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

#ክፍል_19

ከዚህ በኋላ እዚያው ግብፅ ውስጥ ፊታቸውን ወደ ማስተማር አዞሩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ711 ሂ. የሆኑ ሰዎች መስጂድ ውስጥ ለብቻቸው አድርገው ደበደቧቸው፡፡ ነገሩን የሰማው ብዙ ህዝብ ጦር ይዞ ተነሳ፡፡ ከፊሉ እግረኛ ከፊሉ ደግሞ ፈረሰኛ ነው፡፡ የሰዎቹን ማንነት እንዲነግሯቸው ሸይኹን ጎተጎቱ፡፡ አንዱ መጥቶ "አለቃዬ! ይሄው ይሄ ሁሉ ህዝብ ተሰብስቧል፡፡ ሙሉ ግብፅን እንዲያወድሙ ብታዛቸው ያደርጉታል!!" አለ፡፡ "ለምን ሲባል?" አሉት፡፡ "ላንተ ሲባል" አላቸው፡፡ "ይሄ ተገቢ አይደለም" አሉ፡፡ ሌሎች ተነሱና "እነዚህን የበደሉህን ሰዎች እያንዳንዱን ከቤታቸው እየሄድን እንገድላቸዋልን፤ ቤታቸውንም እናፈርሰዋለን! ምክንያቱም ሰውን በጥብጠዋል፡፡ ይህን ፈተናም ቀስቅሰዋል" አሉ፡፡ "ይሄኮ አይፈቀድም" አሉ እሳቸው፡፡

"ይህስ እነሱ የሰሩት የሚፈቀድ ነው?! ይሄ የምንታገሰው ጉዳይ አይደለም፡፡ የግድ ወደነሱ ሄደን በሰሩት እንጋደላቸዋለን" አሉ፡፡ ኢብኑ ተይሚያ ግን ይከለክሏቸዋል፣ ይቆጧቸዋል፡፡ ሰዎቹ በጣም ሲጎተጉቱ ጊዜ "እንግዲህ ሐቁ ወይ የኔ ነው፤ ወይ የናንተ ነው፣ ወይም ደግሞ የአላህ ነው፡፡ ሐቁ የኔ ከሆነ እኔ ይቅር ብያለሁ፡፡ ሐቁ የናንተ ከሆነና የማትሰሙኝና የማታማክሩኝ ከሆነ የፈለጋችሁትን ስሩ፡፡ ሐቁ የአላህ ከሆነ ግን አላህ ሐቁን ከፈለገ በፈለገው መልኩ ይይዛል" አሉ፡፡

ሰዎቹ "ይሄ ባንተ ላይ የፈፀሙት ለነሱ ሐላል ነው?" አሉ፡፡

ኢብኑ ተይሚህ፡ "ይሄ የፈፀሙት ነገር የሚመነዱበት የሚያገኙበት ነው" አሉ፡፡

ሰዎቹ፦ "አጅር የሚያገኙ ከሆነ አንተ ሐሰት ላይ እነሱ ግን ሐቅ ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ስማቸው፣ በሚሉትም ላይ ተስማማ" አሉ፡፡

ኢብኑ ተይሚያህ፦ "ጉዳዩ እንደምታስቡት አይደለም፡፡ እነሱ ምናልባት ሐቅን ለመርዳት ጥረው በጥረታቸው የተሳሳቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እውነትን ለማግኘት ጥሮ የተሳሳተ ሰው አጅር እንዳለው ይታወቃል" አሉ፡፡

ሰዎቹ፦ "እሺ ተነስና አብረን ወደ ካይሮ እንሂድ" አሉ፡፡

ኢብኑ ተይሚያህ፦ "አይሆንም" አሉ፡፡ የዐስር ወቅት ሲጠይቁ እንደተቃረበ ነገሯቸው፡፡ ለዐስር ሶላት ወደዚያው ወደተደበደቡበት መስጂድ አመሩ፡፡

"አለቃ! ሰዎቹ ሊገድሉህ ወስነዋል፡፡ መስጂድ ውስጥ ደግሞ ከሌላ ቦታ በተለየ ይህን ማድረግ ይመቻቸዋል፡፡ ስለዚህ ባለህበት ስገድ" አላቸው አንዱ፡፡ፈቃደኛ ስላልሆኑ እዚያው ለመስገድ ተነሱ፡፡ ብዙ ህዝብ ተከተላቸው፡፡ መንገዱ ተጨናነቀ፡፡ አንዱ መንገድ ዳር ወዳለ መስጂድ እየጠቆመ "ህዝቡ በግፊ እንዳይሞት ይቀንስ ዘንድ ለአፍታ ከዚህ መስጂድ ገብተህ ተቀመጥማ" አላቸው፡፡ ገቡና ቆሙ፡፡ ሰው ቀለል ሲል ወደጥንታዊው ትልቁ መስጂድ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ መንገዳቸው ላይ ቼዝ የሚጫወቱ ሰዎችን አገኙ፡፡ ቼዙን አንስተው በመገልበጥ በታተኑት፡፡ ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡ ሰዎች ከአሁን አሁን ገደሏቸው እያሉ ነው፡፡ ወይም መስጂድ ሲገቡ ከነጓደኞቻቸው ቆልፈውባቸው ይገድሏቸዋል ብለው ሰግተዋል፡፡ መስጂድ ደረሱ፡፡ ሁለት ረከዐዎችን ሰገዱ፡፡ ዐስር ተሰገደ፡፡ ከዚያም ተነስተው "አልሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን" ብለው ንግግራቸውን ከፈቱ፡፡ ፈተና የተነሳበትን ርእስ አንስተው እስከ መግሪብ አዛን ድረስ ተናገሩ፡፡ እነዚያ የደበደቧቸው የተቀናቃኞቻቸው ተከታዮች እተቆጩ ወጡ፡፡ "ወላሂ በዚህ ሰውየ ላይ በፈፀምነው እርምጃ ተሳስተናል፡፡ የሚናገረው ሐቅ ነው፡፡ ሐቅ ያልሆነ ነገር ቢናገር እስከሚጨርስ ጊዜ አንሰጠውም ነበር፡፡ ይልቁንም እንገድለው ነበር፡፡" አሉ፡፡ ለሁለት ተከፍለው እርስ በርሳቸው መሟገት ያዙ፡፡

በረጀብ ወር 711 ሂ. እንዲሁ አንድ ጠላታቸው ሰው በሌለበት ጠብቆ ጥቃት አደረሰባቸው፡፡ ወታደሮች ሳይቀሩ ብዙ ህዝብ ለበቀል እርምጃ ቢሰበሰቡም እሳቸው ግን "እኔ ለራሴ አልበቀልምን" ብለው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡ ሰውየው ኋላ ላይ በአማላጅና በተማፅኖ ተረፈ፡፡ (አልዑቁድ፡ 301-304)


✍ #from_writer_በዱአ_አትርሱኝ
(ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ ገፅ 44-46)
``ኢንሻአላህ ይቀጥላል``

www.facebook.com/IbnTaymiyyahrahimahullah

https://telegram.me/IbnTaymiyyahrahimahullah
ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ
"አላህ እንዳንተ አይነት መፍጠሩን ቀጥሏል ብዬ አላስብም ነበር፡፡" ኢብኑ ደቂቀል ዒድ "ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!" ኢብኑል ሐሪሪ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዘሁላህ) የተጻፈ መጽሐፍ፡፡

3k 0 2
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot