የአብዛኞቹ ዑለማእ አቋም ምን የሚል ነው? አልሀሠሚይ “በሰነዱ ውስጥ ዐብዱረሕማን ብኑ ዚያድ አለበት። አሕመድ ብኑ ሷሊሕ ታማኝ ቢለውም ብዙሃኑ ሊቃውንት ደካማ ነው ብለዋል። ኢብኑ ለሂዐህም አለበት” ብለዋል።
ሌሎቹንም ሐዲሦች እንዳጠቃላይ ብንመለከት ኢብኑ ረጀብ አልሐንበሊይ እንዲህ ይላሉ፦
"وفي فضل ليلة نصف شعبان أحاديث متعددة، وقد اختُلف فيها، فضعّفها الأكثرون، وصحّح ابن حبان بعضها"
"የሸዕባን አጋማሽ ሌሊትን በላጭነት አስመልክቶ በርከት ያሉ ሐዲሦች አሉ። በነሱ ላይ ልዩነት ተንፀባርቋል። አብዛኞቹ (ሊቃውንት) ደካሞች እንደሆኑ በይነዋል። ኢብኑ ሒባን ከፊሎቹን ሶሒሕ አድርገው በይነዋል።" [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 261]
አሁን ይህንን አቋም መምረጥ ያስኮንናል? የሚገርም ነው።
“ከጥንት ጀምሮ ይህንን እለት በተለየ የያዙ የሉም ወይ?” ከተባለ “አዎ ነበሩ” ነው መልሴ። እደግመዋለሁ! አዎ ነበሩ። ዋናውን ነጥብ በመሳት እንዲህ አይነት ማስቀየሻ ሙግት እንዳይከፈት ነው ቀድሜ ይህንን የማስታውሰው። የኔ ትኩረት “የብዙሃኑን ዑለማእ አቋም ያንፀባረቀን አካል በዚህ መልኩ በንቀትና በማንጓጠጥ መግለፅ ለምን?” የሚል ነው። ይሄ ሌሎችን በማጣጣል ራስን የመሰቃቀል ስልት ከዚህ ወንድም ጋር ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ጋር የሚንፀባረቅ ርካሽ አካሄድ ስለሆነ ነው ለመፃፍ የተነሳሁት። አቅሙ ያለው ሰው በስርአት ተንትኖ መሀየስ ይችላል። ታላላቅ ዑለማኦች ያውም ብዙሃን የኢስላም ሊቃውንት የተጓዙበትን መንገድ ካንተ ስሜት ጋር ስላልገጠመ ብቻ አንድ ኪታብ ቀርተው ፊጥ ፊጥ የሚሉ ወጣቶች አቋም እያደረጉ መግለፅ ግን፦
* አንደኛ፦ ድን ^ቁርና የወለደው ድፍረት ነው። በጉዳዩ ላይ የዑለማኦችን ንግግሮች ብዙ ሳይሆን ትንሽ እንኳ ቢፈትሽ ኖሮ ቢያንስ ድፍረቱን ይቀንስ ነበር ብዬ አስባለሁ።
* ሁለተኛ፦ የኺላፍ ርእስ አድርጎ ቢያስበው እንኳ መሰል ጉዳዮች በሚይያዙበት መጠን አይደለም ያቀረበው። አለማወቅ ወይስ የከረመ ቂም ኖሮት ማራገፍ ነው የፈለገው?
* ሶስተኛ፦ ንግግሩ በራሱ ሂሳብ ሲታይ ዑለማእ መዝለፍ አለበት።
ደግሞ በደፈናው “ኒስፉ ሸዕባን አዲስ አይደለም። ከጥንት እስከዛሬ የሚታወቅ ሐዲሥ ነው” ይላል። ወላሂ ይሄ ንግግሩ ስለ ጉዳዩ ጫፍ ይዞ እንጂ የረባ ግንዛቤ እንደሌለው ያጋልጣል። ሲጀመር በጉዳዩ ላይ አንድ ሐዲሥ አይደለም ያለው። ሁለተኛ ተቃውሞው እሱ እንዳስመሰለው ዛሬ ፌስቡክ ከመጣ በኋላ የጀመረ ሳይሆን ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት እነዚህ ሐዲሦች ደካማ እንደሆኑ የገለፁት የሐዲሥ ኢማሞች፣ እለቱን በተለየ መያዝ ቢድዐ እንደሆነና በዚህ ጊዜ የሚፈፀሙ ተግባራትን የሚኮንኑ ንግግሮች የወጡት ጥንት ጀምሮ ነው። ሌላው ሁሉ ይቅር። ቢያንስ በቅጡ ባልፈተሽከው ጉዳይ ላይ ድፍረት ብትቀንስ መልካም ነው። ንቀትና ዘለፋህም ይጎዳሃል። ወላሂ ወንድሜ! የትርጉም ስራህ ጉሩር ውስጥ እየከተተህ እንዳይሆን እሰጋለሁ።
ከብዙሃን ዑለማኦች አቋም ይልቅ የጥቂቶቹ ሃሳብ የተሻለ እንደሆነ ከተሰማህ መረጃ ጠቅሰህ ማስረዳት ይበቃሀል፣ ከቻልክበት። መሳለቁን ምን አመጣው? መሳለቅ ቢፈቀድስ አንተ በምን አቅምህ? ለምን ቀድርህን አታውቅም? አንድ ደደውን በመጥቀስ ድምዳሜ መስራትስ ግልብነት አይደለም ወይ? ኺላፍ ያለበት ርእስ በዚህ መልኩ ነው የሚልለየው? ደግሞም ደደው ያቀረበው ትንታኔ'ኮ ያንተን ነውረኛ የንቀት ድምዳሜ የሚሰጥ አይደለም። ቢያንስ ከመለጠፍህ በፊት “ደሊልህን” በስርአት አዳምጥ እንጂ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor