ጥቂት ነጥቦች፣ ለእውቀት ፈላጊዎች
~~~~~~~~~~~~~~
መቼም የዒልም አንገብጋቢነት ለማናችንም የሚሰወር አይደለም፡፡ በተለይም በዚህ ጅህልና በተንሰራፋበት፣ ውዝግብ በነገሰበት፣ ሺርክና ቢድዐ በተስፋፋበት ዘመን የእውቀት አስፈላጊነት ለማንም አይሰወርም፡፡
ሰው ሁሉ ማወቅን ይመኛል፡፡ ነገር ግን እውቀት በትጋት እንጂ በምኞት አይገኝም፡፡ ምኞታችንን እውን ለማድረግ እንቅፋቶች ይበዙብናል፡፡ ቢሆንም ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም። ስለዚህ:–
1. ቅራ፡-
ቁጭ ብለህ ኪታብ ተማር፡፡ ዒልምን ለመቅሰም ቀዳሚው መንገድ ከሚያስተምር ብቁ ሰው ዘንድ ቁጭ ብሎ መቅራት ነው፡፡ ባይሆን የሚያስተምርህ ሰው በእውቀቱ ብቁ፣ በአካሄዱ ጤነኛ መሆን አለበት፡፡ “ይሄ እውቀት ዲን ነው፡፡ ዲናችሁን ከማን እንደምትወስዱ አስተውሉ” ይላሉ ሐሰኑል በስሪ ረሒመሁላህ፡፡
- ባይሆን ቅደም ተከተል ጠብቅ፡፡ ያላቅምህ ዘለህ ከፍ ያለ ኪታብ አትጀምር፡፡ አቅምህን አገናዝበህ ከስር ጀምረህ ተማር፡፡
- ባይሆን ስትቀራ የለብ ለብ ሳይሆን አድምተህ ቅራ፡፡ “ይህን ኪታብ ጨርሻለሁ” ለማለት ሳይሆን በኢኽላስ ቅራ፡፡ ለሌሎች ለማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ ቅራ፡፡ የቀራሀውን ሙራጀዐ (ጥናት) ማድረግ ይልመድብህ፡፡ የዛሬው ኪታብ በሚገባ ከተያዘ በቀጣይ የምትማረው ኪታብ ክብደት በብዙ ይቀንሳል፡፡ ሙሉ በሙሉ አዲስ አይሆንብህም፡፡ አያያዝህ ለብ ለብ ከሆነ ግን ኢኽላስህን ታጣለህ፡፡ ከሰው ዘንድ ታፍራለህ፡፡ ጊዜህንና ልፋትህን ታባክናለህ፡፡
2. አዳምጥ፡-
ቁጭ ብለህ የምትማርበት በአቋሙ ጤነኛ፣ በእውቀቱ ብቁ ሰው ካላገኘህስ ምን ይሻላል? እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ፡፡ ዘመናችን ዒልም ለሚፈልግ ሰው መንገዶቹ የገሩበት ዘመን ነው፡፡ የታላላቅ ዑለማዎችን ትምህርቶች ከቤትህ ቁጭ ብለህ እያዳመጥክ መከታተል ትችላለህ፡፡ ዐረብኛው የሚቸግርህ ከሆነ የምታምናቸውን ኡስታዞች ትምህርት በተገራልህ ቋንቋ ቤትህ ሆነህ በድምፅ መከታተል ትችላለህ፡፡ ስለዚህ በቴሌግራም፣ በዋትሳፕ፣ … ወይም ከጓደኛ በመቀባበል ወጥረህ ተማር፡፡
ሪኮርድ መከታተልን የሚነቅፉ ሰዎችን ሊገጥሙህ ይችላሉ፡፡ “እርሱኮ ሪኮርድ እንጂ ሸይኽ የለውም” ሊሉህ ይችላሉ፡፡ ለእንዲህ አይነት በሽተኞች ጆሮ አትስጥ፡፡ ከስሜቱ ጋር ያልገጠምክለት ሰው አቃቂር ማውጣቱትን አያቆምም፡፡ ይህን ከሚሉት ውስጥ በተጅሪባ እንዳየነው አብዛኞቹ ለራሳቸውም ሸይኽ የላቸውም፡፡ ከፊሎቹ ደግሞ ሸይኾቻቸው የነሱው ብጤ በሽተኞች ናቸው፡፡ የውንጀላው መነሻ በአመዛኙ አካሄድህ ከአካሄዳቸው አለመግጠሙ ነው፡፡ የነሱን ሰዎች በጭፍን እንድትከትል ለሚሹ አካላት ቅንጣት ታክል ቦታ አትስጣቸው፡፡ በሽተኛ ወይም ብቁ ያልሆነ ሰው ዘንድ ተቀምጠህ ከምትማር ያለ ጥርጥር ሁነኛ የሪኮርድ ደርሶችን ብትከታተል ይመረጣል፡፡
3. አንብብ፡-
ኪታቦችን አንብብ፡፡ ሹሩሓትን አገላብጥ፡፡ ፈታዋዎችን ተመልከት፡፡ ካለህ በቀጥታ ኪታቦችን ተጠቀም፡፡ ከሌለህ መክተበተ ሻሚላን ተጠቀም፡፡ እንዲያውም መክተበተ ሻሚላ በዚህ ዘመን ትልቅ ኒዕማ ነው፡፡ አጠቃቀሙን ቻልበት፡፡ ከዚህ የተረፈውን ኢንተርኔት ተጠቀም፡፡ ጎግልን ጎልጉል፡፡ ፒዲኤፍ አውርድ፡፡ በዚህ ዘመን ጦለበተል ዒልም ሆኖ አነሰም በዛ እነዚህን የማይጠቀም ለማግኘት ይከብዳል፡፡ በነዚህ ሰበቦች መጠቀምህን ሊያጣጥል የሚሞክር ካለ እራሱን በከንቱ የሚቆልል ግብዝ ነው፡፡
በተቻለ መጠን ንባብ ላይ ብቻ ጥገኛ አትሁን፡፡ ስለዚህ ቀጥታ መማር ስትችል ንባብ ላይ ብቻ አትንጠልጠል፡፡ ቁጭ ብሎ መማር ከተገኘ “ማር ሽጠው ምን ይበሉ?!” ባይሆን ደርስህን እየተከታተልክ ከዚያም ንባብህን እንደማዳበሪያ ተጠቀመው፡፡
ልብ በል! በንባብ ዒልም መቅሰምህን የሚነቅፍ ይገጥምሃል፡፡ እርግጥ ነው ንባብ ቁጭ ብሎ እንደመማር አይደለም፡፡ ይሄ ተጨባጭ ሐቅ ከመሆኑም ባለፈ ዑለማዎች የሚያስረግጡትም እውነት ነው፡፡ ነገር ግን የዑለማዎቹ ሃሳብ “አታንብቡ” ለማለት አይደለም፡፡ ይህ ቢሆን ለምን ኪታብ ይፃፋል? ከንባብ የተኳረፉ ወይም ልብ ወለድ የሚያሳድዱ፣ በእንቶ ፈንቶ የተጠመዱ ሰዎች ንባብህን ስለተቹ ጆሮ አትስጣቸው፡፡ የማውቃቸው ተግባራዊ ምሳሌዎች ስላሉኝ ነው እነዚህን መጥቀሴ፡፡ እንዲያውም በንባብ እውቀትን የሚቀስሙ ሰዎችን የሚያጣጥሉ አካላትን ታዘብማ፡፡ “እኛ ቀጥታ ቀርተናል” የሚል ጉራ ከመንፋት በዘለለ ቁጭ ብለው በስርአት ሲማሩ አታያቸውም፡፡
ባይሆን የምታነበውን እያስተዋልክ፡፡ ጤነኛ ስራዎችን እየመረጥክ፡፡ የበሽተኞችን ስራ በመከታተላቸው የተነሳ ስንቶች አፈንጋጭ አስተሳሰቦች ላይ ወድቀዋል?!
4. ተግብር፡-
የምንማረው ለመስራት ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ እውቀታችንን ለማስረፅ ከሚጠቅሙን ሁነኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ባወቅነው መስራት ነው፡፡ የማይተገበር እውቀት በቀላሉ ይረሳል፡፡ ስለዚህ እውቀትህን በተግባር አጅበው፡፡ በብዙ መልኩ ታተርፍበታለህ፡፡
5. አስተምር፡-
እውቀትን ከሚያሰርፁ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ማስተማር ነው፡፡ በማስተማር ከተማሪዎች በበለጠ የሚጠቀሙት አስተማሪዎች ናቸው፡፡ በተግባር ጀርበው፡፡ የመማርም አንዱ አላማ አውቆ ማሳወቅ ነው፡፡ ስለዚህ ያወቅከውን አካፍል፡፡ ቁርኣን ከቀራህ አስቀራ፡፡ ከዚያ ያለፈ አቅም ካለህ በደርስ፣ በሙሓዶራት፣ በፅህፈት፣… አስተምር፡፡ ታገል፡፡ ያለህን ታዳብራለህ፡፡ ክፍተትህን ለመመልከት እድሉን ታገኛለህ፡፡ ለተሻለ ትነሳሳለህ፡፡ በሐቅ ላይ ጂሃድ ታደርጋለህ፡፡ የልፋትን የማስተማርን ጣእም ታጣጥማለህ፡፡
@IbnuMunewor