መዝጋታችን ላይቀር በጊዜ እንዝጋ
~~~~~~~~~~
ያለ ጥርጥር መስጂዶችን መዝጋታችን አይቀሬ ነው። ችግሩ ግን የሆነ አካል ዝጉ እስከሚለን ወይም ደግሞ የችግሩ መጠን ከቁጥጥር ውጭ እስከሚሆን ነው እየጠበቅን ያለነው። ይሄ የሚያሳዝን አካሄድ ነው። ወገኔ ለመሆኑ ስንት ሰው ስንደርስ ነው መስጂዶችን የምንዘጋው? ይልቅ በጊዜ ህዝባችንን ለማዳን የምንችለውን ሰበብ ብናደርስ አይሻልም? ለማንኛውም ለሚሰሙ አካላት! ብዙዎቻችን እንደሰማነው የሳዑዲ የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት በሃገሪቱ ያሉ መስጂዶች እንዲዘጉ ከወሰነ ቀናት ተቆጠሩ። ሌሎችም የበርካታ ሃገራት ኢስላማዊ ተቋማት ተመሳሳይ ፈትዋ ሰጥተዋል። ችግሩ አለማቀፍ ችግር እንደመሆኑ የኛን ከነሱ የሚለየው የለምና የተለየ ነገር አንጠብቅ። እንዲያውም መሬት ላይ ያለው የኛ ነባራዊ ሁኔታ የከፋ ነው።
ስለዚህ ወገኔ ሆይ! አላህ ፈረጃውን እስከሚያመጣ ድረስ በያለህበት መስጂዶችህን ዝጋ። "አይዘጋም" ብሎ የሚገላገል ካለ ከሱ ጋር አተካራ ውስጥ አትግባ። እምነታችን ህይወትን ለሚነጥቅ በሽታ ቀርቶ ለዝናብ እንኳ ከመስጂድ መቅረትን ይፈቅዳልና ከቤትህ ረግተህ ተቀመጥ።
የአላህ ፈቃዱ ከሆነ ነገ ጧት በመጠኑ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።