አልሀምዱሊላህ😍😍😍
ዛሬ ደስ የሚል ዜና ሰማን ይህን ዜና ለመስማት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር ያደርኩት የበሽር አሳድ መንግስት መፍረስ ለመስማት አልሀምዱሊላህ ይሄን ለማየት በቃን፡፡ አሏህ ደግሞ የፍልስጤሞችን ዋይታ ለቅሶ በቃችሁ ብሎ ደስታቸዉን የምንሰማ ያድርገን ያረብ
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር የነጠለው የአላሳድ ሥርወ-መንግስት ነበር፡፡
ከግብፅ በመቀጠል ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትነጠል የአንበሳውን ድርሻ የተጫወተችው ሶሪያ ናት። የጀብሃ (ELF) ጽ/ቤት በመክፈት፣ ዲፕሎማት ፓስፖርት በማቅረብ፣ ትጥቅና ስንቅ እንዲሁም ፖለቲካዊ ድጋፍ በማቅረብ የሶሪያ አጥፊነት ወደር አልነበረውም።
እ.ኤ.አ ከ 1971 እስከ እለተ ሞቱ 2000 የሶሪያ 18ኛ ፕ/ት የነበረውና በፀረ-ኢትዮጵያ አቋሙ ተስተካካይ ያልነበረው አሁን የተሰናበተው የበሽር አላሳድ አባት ሀፌዝ አላሳድ ኢትዮጵያን ለሚያደሙ ቅጥረኞች ሁሉ ዋነኛ ደጋፊ ነበር። ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ለመነጠል በመጀመሪያ የተደራጀው ጀብሃ ከግብፅ በመቀጠል ሁለተኛ ቢሮው ደማስቆ (ሶሪያ) ነበር። የጀብሃ አባላት ፍልስጤም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ያስቻለው ይህ ሰው ነበር። በኋላ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ሻዕቢያ ጀብሃን አክስ'ሞ ሲመሰረት በመጀመሪያ አካባቢ የክርስቲያን ድርጅት ነው በማለት ድጋፍ ለማቋረጥ አንገራግሮ የነበር ቢሆንም ከእራሱ አልፎ ለህወሓትና ለሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅቶች የሚለገስ የተትረፈረፈ ወታደራዊ ድጋፍ (ትጥቅ፣ ስንቅና ስልጠና) በማቅረብ ኢትዮጵያን ያደ'ማ በመጨረሻም ከቀይ ባህር የነጠለ የክፋት ብልቃጥ ነበር። የዚያድባሬ ደጋፊ ሆኖ Elite force የላከ ወራዳ ሰው ነበር።
☞ ከሀዲነቱ ወደር አልነበረዉም በሽር አላሳድ ሲያምነው የነበረውን የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ የሳተላይት ስልክ ቁጥር ለፈረንሳይ ደህንነት (DGSE) አሳልፎ በመስጠት በቁጥሩ መሰረት ጋዳፊ ያለበት ትክክለኛ ቦታ ተለይቶ ለአማጺያን እንዲሰጥ ያደረገ ከሃዲ ሰው ነው። ከግብፅ ጋር ባላቸው ቂም ጋዳፊ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ።
ከአመታት በፊት ሊቢያውያንን በወግ በማእረግ ፡ አስተዳድረው ህዝባቸውን በምቾት ፡ በደስታ ያኖሩ የነበሩት ታላቁ የሊቢያ መሪ ፡ ሙአመር አል ገዳፊ የሊቢያን ወርቅና ነዳጅ ፈልገው ጥርስ ውስጥ በከተቷቸው ምእራባውያን ሴራ በራሳቸው ህዝብ ተቃውሞ ተነሳባቸው ።
............
የአረብ አብዮት እሳት ሊቢያንና ህዝቦቿን ሊበላ ጫፍ ደረሰ ።
በመጨረሻም ደጉ መሪ ሙሀመድ አል ጋዳፊ ቤተመንግስታቸውን ትተው ወደተወለዱበት ከተማ ሲርጥ በመሄድ በሚስጥር ተቀመጡ ።
...................
ምእራባውያንና አሜሪካ ዋና ጠላታቸው የሆነውን ጋዳፊን ፈልጎ ማግኘት አቃታቸው ።
እና የጋዳፊን አድራሻ ማፈላለግ ጀመሩ ። ያሉበትን ቦታ ወይም ይህን ለማወቅ የሚረዳ መረጃ አጥተው በተቸገሩበት ወቅት አንድ ሰው ለፈረንሳይ የፀጥታ ሰወች የሚነግረው ሚስጥር እንዳለ አሳወቃቸው ።
....
ይህ ሰው በጋዳፊ ይታመን የነበረ እና የሳተላይት ስልካቸውን ቁጥር የሚያውቅ ነው ።
ጋዳፊን የሚፈልጉ ሀገራት ይህን ቁጥር ካገኙ ፡ በሲግናል አማካኝነት ያሉበት ቦታ እንደሚታወቅ ያውቃል ።
እናም ይህን በእምነት የተሰጠውን ትልቅ መረጃ ፡ አሳልፎ ለፈረንሳይ የስለላ ድርጅት ሰጠ ።
......
ይህ መረጃ ከተገኘ በኋላ የጋዳፊን መወገድ የሚፈልጉት ምእራባውያን ፡ በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ አወቁ ።
ይህንንም መረጃ ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ ፡ ለጋዳፊ ተቃዋሚዎች ሰጧቸው ። ጋዳፊ , ከድህነት አውጥተው ባበለፀጉት የሀገራቸው ህዝብ በተነሳባቸው ተቃውሞ ፡ በገዛ ሊቢያውያን ተገኝተው በግፍ ተገደሉ ።
....
ጋዳፊን ማን አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው ነገር ጥያቄ ሆኖ ከቆየ በኋላ ግን. . የሰውየው ማንነት ታወቀ ። ይህ ሰው ፡ ይህ ጋዳፊ ከመሸጉበት ቦታ እንዲገኙ ስልክ ቁጥራቸውን አሳልፎ የሰጠው ከሀዲ ሰው ፡ የሶሪያው ፕሬዝደንት በሽር አልአሳድ ነበር ።
.............
አልአሳድ ፡ ይህንን መረጃ የሰጠው የስልጣን ዘመኑን ለማቆየት የሚያስችል ድጋፍ ከፈረንሳይ መንግስት ለማግኘት በማሰብ ነበር ።
.....
አልሀምዱሊላህ ታሪካዊዋ ሶሪያ ደማስቆ የእዉቀት የጀግኖች የሙስሊሞች መስፋፊያ የሆነችዉ ነፃ ሁናለች ኢንሻ አላህ ወደፊት የሙስሊሞች ድል ቅርብ ነዉ💪
ሀያሉ ፈጣሪያችን አላህ ለሶሪያ ህዝብ ፍትሀዊ መሪ እንድሰጣቸውና የተረጋጋች ሀገር ከመሆንም ባሻገር ደማስቆ ወደገናና ኢስላማዊ ታሪኳ ትመለስ ዘንድ ምኞታችንም ዱዓችንም ነው።
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group