🚨#ጥንቃቄ
ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ ድንገተኛ ፣ ቅፅበታዊ መቼ እንደሚፈጠር መቼስ እንደሚቆም የማይታወቅ ክስተት ነው።
መሬት መንቀጥቀጥ ክስተትን መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን ተመራማሪዎች መተንበይ አይችሉም።
ስለዚህ በየትኛውም ሰዓት፣ ጊዜ ሊከሰት ይችላል ፤ ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ የግድ ይላል።
" አሁንማ እኮ ተለመደ " ተብሎ መዘናጋት አይገባም።
" ፈጣሪ ክፉን ሁሉ ያርቅልን " እያልን መማፀኑ እንዳለ ሆኖ በዚህ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በአግባቡ ማወቅ ያስፈልጋል።
የሰሞነኛው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንዳለ ሆኖ የትላንት ለሊቱ ከፍተኛ የሆነ የማንቂያ ደውል ነው።
ብዙዎች ተኝተው ከነበሩበት ቀስቅሷል ፣ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ብለዋል፣ እቃዎች ከላይ ወደ ታች ወድቀዋል።
ሰዓቱ ለሊት የመኝታ ሰዓት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ያልሰሙት ይሆናል እንጂ ጥንካሬው ከእስከዛሬው ሁሉ የተለየ ፤ " ሰምተን እናውቅም " ያሉ ሰዎች ሁሉ የሰሙት ሆኗል።
አዲስ አበባ ብዙ ህንጻዎች ያሉባት በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።
በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ፍጹም አትዘናጉ ! ፈጣሪያችንን ከክፉ ሁሉ ነገር እንዲጠብቀን እየተማፀንና ሳንደናገጥ ንቁ ሁነን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበር በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆን ይገባናል።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia