...ኢንሻአላህ....
ግራ ሲገባህ ሀሳብህ ሲበተን
በራስህ ጉዳይ ላይ ሲሳንህ መወሰን
የበፊት ህይወትህ እንዳልነበር ሆኖ
በየእርምጃህ መሀል ችግር ተደቅኖ
ያንተ የነበረው ወደሌላ ተበትኖ
ተስፍህ ተቆራርጦ ህልምህ ተበጣጥሶ
እረፍት ቢነሳህም መልሶ መላልሶ
የደፈረሰው ወንዝ አይቀርም መጥራቱ
እንዳዲስ መንጣቱ ኩልል ማለቱ
ቀኑም ቢጨልም አይቀርም መንጋቱ
ዱአ ነው የሰው ልጅ የህሊና እረፍቱ
አላህን ለመቅረብ ዋና መሰረቱ
ብርሀን ይወጣል ታሪክ ይቀየራል
ያንተ የነበረው ወዳንተ ይመጣል
ንቆ የተወህ የራቀህ ይቀርባል
ማያልፍ ቢመስልም ሁሉም ስቃይ ያልፍል
ዳግም ተስተካክሎ በደስታ ይቀየራል
አልቅሰህ የለመንከው ያለማቱ ጌታ
ባየኸው ስቃይ በችግርህ ፍንታ
አብዝቶ ይሰጥሀል በደስታ ላይ ደስታ
በዱንያም ባኺራ የመንፈስ እርካታ
.
.
.ለ አደም ልጅ ሁሉ
@Loveyuolema
ግራ ሲገባህ ሀሳብህ ሲበተን
በራስህ ጉዳይ ላይ ሲሳንህ መወሰን
የበፊት ህይወትህ እንዳልነበር ሆኖ
በየእርምጃህ መሀል ችግር ተደቅኖ
ያንተ የነበረው ወደሌላ ተበትኖ
ተስፍህ ተቆራርጦ ህልምህ ተበጣጥሶ
እረፍት ቢነሳህም መልሶ መላልሶ
የደፈረሰው ወንዝ አይቀርም መጥራቱ
እንዳዲስ መንጣቱ ኩልል ማለቱ
ቀኑም ቢጨልም አይቀርም መንጋቱ
ዱአ ነው የሰው ልጅ የህሊና እረፍቱ
አላህን ለመቅረብ ዋና መሰረቱ
ብርሀን ይወጣል ታሪክ ይቀየራል
ያንተ የነበረው ወዳንተ ይመጣል
ንቆ የተወህ የራቀህ ይቀርባል
ማያልፍ ቢመስልም ሁሉም ስቃይ ያልፍል
ዳግም ተስተካክሎ በደስታ ይቀየራል
አልቅሰህ የለመንከው ያለማቱ ጌታ
ባየኸው ስቃይ በችግርህ ፍንታ
አብዝቶ ይሰጥሀል በደስታ ላይ ደስታ
በዱንያም ባኺራ የመንፈስ እርካታ
.
.
.ለ አደም ልጅ ሁሉ
@Loveyuolema