ልሣነ አምሐራ ሚዲያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ።
ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ደፈጣ በመያዝ የአገዛዙ ሎሌዎችን አመድ አድርጋለች ከአዲስቅዳ ወደ አሸዋ ጉዞ ሴረግ የነበረ ዲሽቃ የጫነ 1 ፓትሮል በኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ልጆች አሸዋ ላይ በደፈጣ ሲመታ መኪናዋ ተገልብጣ 6 ሰዎች  ወደ ላይኛዉ ሲላኩ ዲሽቃዉ ከጥቅም ዉጭ ሁኗል ሲል የብርጌዱ ጦር አዛዥ መቶ አለቃ ለአለም ገልፀዋል


ጠላት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል!!!

ዛሬ በቀን 30/06/2017 ዓ/ም ለሊት 12:00 ስዓት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገው ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በፋ/ለ/ወ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ሻለቃ ፪ ተርቦች ባደረጉት የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን ብዛት ያለዉ  ወራሪ የብርሀኑ ጁላ ጦርን ጨምሮ ገዘኸራ ቀበሌ ላይ የነበረዉ ተመክሮ አይድን ባንዳ አዛይ አድማ ሚሊሻ'ና ፖሊስ ሰራዊት ከእነ ተተኪ ባንዳ አዲስ ምልምል ሰልጣኞቻቸዉ  ሙሉ በሙሉ እንዲደመሰሱ ተደርጓል።

ይህ ከቀናት በፊት ከእየ ቦታዉ ተለቃቅሞ ወደ ፋ/ለ/ወረዳዋ የገጠር ከተማ ገዘኸራ ገብቶ የነበረ የጠላት ሀይል  ዛሬ በቀን 30/06/2017 ዓ/ም ህዝቡን ከቤተ ክርስቲያን መልስ በማስገደድ ገዘኸራ ላይ ብልፅግናን የሚደግፍ ፋኖን የሚያወግዝ ሰልፍ  ለማድረግ አስቦ ሰፊ ስራ እየሰራ የነበረ ሲሆን ይህንን የጠላት እቅድ ቀድመዉ ያወቁት የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በፋ/ለ/ወ ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ዋና ጦር መሪ የመቶ አለቃ ለአለም ጌታነህ በሰጡት ስምሪት መሰረት ወደ ቦታዉ የተንቀሳቀሱት የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ  ሻለቃ ፪ ተርቦች  ሰልፍና ስብሰባህ ከህዝባችን ጋር ሳይሆን ቀደም ሲል በዚህ ብርጌድ ከተሸኙት አለቆችህ ከእነ ሞገሴ እና ብዙ መሰሎቻቸው ጋር ይሁን ሲሎ ሰባ ሶስቱን የጠላት  ሙጃ ሰራዊት ወደ ማይመለስበት ሸኝተዉታል። 

ይች በሀምሳ አለቃ ማስተዋል ታደለ ሀምሳ አለቃ ፈንታሁን እና ፋኖ ዘመን አዲስ እየተመራች ጎህ ሳይቀድ ገዘኸራ ቀበሌ ገብታ  የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት አሳክታ በለሊት ልብ የሚያሞቅ ብስራት ያደረሰችን ተርብ ሻለቃ ከዚህ ቀደም ከ31 ጊዜ በላይ ወደ ቀጠናዋ ተንቀሳቅሶ ከነበረ የጠላት ሀይል ጋር ተፋልማ 31 ጊዜ ሁሉ ከፍተኛ ድል ከማስመዝገቧ በተጨማሪ በክፍለ ጦራችን ስር ከሚገኘዉ ማለትም ከአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በዳንግላ ከተማ የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ጋር በመናበብ በዳንግላ ወረዳ  ጫራ ጊሳና ባርባሺ   አካባቢዎች ሰፍሮ የነበረ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በቀን 28/4/2017 ዓ/ም  ጊሳ አካባቢ ከ100 በላይ የጠላት ጦር የተደመሰሰበትን ኦፕሬሽን ጨምሮ ብዙ ግዳጆችን በታላቅ ጀብድ ያሳካች የብርጌዷ ፈርጥ ናት።

ጠላት ተጨማሪ ጦር ከአዲስ ቅዳም ከተማ ማንቀሳቀስ አስቦ የነበረ ሲሆን የብርጌዷ ዋና ጦር መሪ መቶ አለቃ ለአለም ጌታነህ የመሩት የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ሻለቃ ፩ እረመጥ ጦር ከአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በሳትማ ዳንጊያዉ የቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ግስሎች ጋር በመናበብ  አዲስ ቅዳም ከተማ ድረስ በመግባታቸዉ  ጠላት  አድጓሚ ተራራ ምሽጉ ዉስጥ ተወስኖ  በእዉር ድንብር ተኩስ  ሞርተር'ና ዙ23 ብቻ እየወረወረ በአለበት ቀዝቅዞ እንዲቀመጥ ተደርጓል።

ይህ የቀዘቀዘ የጠላት ጦር አድጓሚ ተራራ ላይ ተቀብሮ በወረወረዉ የሞርተር ቅንቡላ  ዛምበላ ቀበሌ ላይ ህፃን ቀረብሽ አዲሱ የተባለች ህፃንን ጨምሮ የተወሰኑ ግለሰቦች ከባድ'ና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
እንዲሁም  በምዕራቡ አቅጣጫ በእየቦታዉ የወደቀዉን የጠላት ጦር ሰባዊነት አስገድዷቸዉ ለመቅበር በወጡ የገዘኸራና አካባቢዋ ማህበረሰባችን ላይ ከሞት የተረፈ ቁስለኛ የጠላት ሀይል በከፈተዉ የእሩምታ ተኩስ 3 ንፁሀን ወገኖቻችን በግፍ ሲረሸኑ ብዙዎች ቁስለኛ ሁነዋል።

በሌላ በኩል ጫራን አቋርጦ ወደ ገዘኸራ ሊገባ የነበረዉ ጠላት  በአማራ የብረት በሮቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ትንታጎች በለሊት  በመዉጣት መንገዱን እሾህ ስላደረጉበት   የገዘኸራ እቅዱን ዳንግላ ላይ  ሁኖ እንዲያኝከዉ ተገዷል።

አጠቃላይ በዛሬዉ የለሊት ኦፕሬሽን እስከ ጥዋት 1:30 ድረስ የተረጋገጠ 29 ክላሽንኮፍ መሳሪያ የተገኘ ሲሆን  ከ73 በላይ የጠላት ሀይል እስከወዲያኛው ሲሸኝ የተወሰነ ቁስለኛ በምርኮ ተይዟል።  

ከሞተ ከቆሰለና ከተማረከ የጠላት ሀይል  ዉስጥም አብዛኞቹ  የአድማ ምሊሻ እና ፖሊስ አባላት መሆናቸዉን ማረጋገጥ እንደተቻለ  የሻለቃዋ ህ/ግንኙነት ፋኖ ሰናይ ፀጋ ከቦታዉ አረጋግጦልናል።

ፋኖ ተሻገር አደመ ከ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

ይበልጣል የዉነቱ   የክ/ጦሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ


የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ

በሰሜን ጎጃም ሙሉውን በሚባል ደረጃ የሚደረግ የድሮን ቅኝት እንዳለ የባህርዳር ዊክሊክስ ምንጮች ገልፀዋል። በተመሳሳይም በቋሪት ቆላማ ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚደረግ ቅኝትም እንደታሰበ ለማወቅ ተችሏል።


የአደረጃጀት ዜና!

ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ትናንት ከነበረበት ደረጃ ገዝፎ፣ የአደረጃጀት አንድነትን ፈጥሮ፣ በመርኅ መተታገልን አጠናክሮ ከሚጓዝበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ትግላችን የዐይን ብሌናችን ነው፤ ትግላችን ከነፍሳችን ጋር በአቻነት የምንሳሳለት ነው፤ ትግላችን የሕዝባችንን ኅልውና ማረጋገጫችን ነው። ስለሆነም ይህን ትግል በሁሉም ዘርፍ መጠበቅ፦ የሕዝብን አደራ፣ የወጣንለትን ዓላማ፣ የመዳረሻ ግባችንን መጠበቂያ መልኅቃችን መሆኑን በውል መግለጽ እንወዳለን።

ወደ ጫካ የወጣነው፣ ከተመቻቸ ጎጇችን የወጣነው፣ ከልጆቻችን፣ ከወላጆቻችን በነጻ ፈቃዳችን የተለየነው ግፍንና ገፈኞችን ተቃውመን፣ ኅልውናችን መንግሥት መር በሆነ መንገድ አደጋ ውስጥ ገብቶብን፣ ነጻነት፣ ፍትሕና እኩልነት እንደ ሰማይ ርቀውን በአባቶቻችን በፋኖነትና በአርበኝነት ቁጭት እንጅ የግልና የቡድን ፍላጎት ልናስፈጽም አይደለም። በዚህም የፋኖነት ትግል የወል ጉዳይ የአማራን ሕዝብ ኅልውና ማረጋገጥ መሆኑን ለሕዝባችን ለመላው የትግል ጓዳችን አስረግጠን መግለጽ እንወዳለን።

እኛ በንሥር በላሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ውስጥ የምንታገል አርበኞች የትግሉን መራርነት ትናንት በጀግንነት ጠላትን እንደቅጠል ጎዝጉዘው በተሰውት አርበኛ ሳላምላክ ነጋሽ፣ አርበኛ ጉልላት ጸጋዬ እና ሌሎችም ጓዶቻችን በዐይናችን ተመልክተናል። የተሰውለትን የትግል ዓላማም በታማኝነትና በጽናት አንድያ ኅያው ነፍሳችንን ሰጥተን ከዳር ለማድረስ በኅያው እግዚአብሔር ስም መሐላ አለብን።

በዚህ መሠረት ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦርን በመሠረቱት ብርጌዶች ሙሉ ይሁንታነት የወቅቱን የጠላት አሰላለፍ በወጉ ፈትሾ የሚያታግሉ አርበኞችን ወደፊት አምጥቶ ከ10 ቀናት በላይ ውይይቶችንና ሥልጠናዎችንም ጭምር አድርጎ ሪፎርም ሠርቷል። ይህንን ሪፎርምም ተቋማችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በላካቸው የተቋሙ ልኡካን አማካይነት እውቅና ተፈጥሯል።

በዚህ መሠረት፦
1. የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ.............አርበኛ ሙሉቀን ካሳሁን
2. ም/አዛዥ........አርበኛ አብራራው ፀጋዬ
3. የዘመቻ መምሪያ …አርበኛ አበበ ገብሬ
4. ም/ዘመቻ አዛዥ....አርበኛ መሳፍንት ደጉ
                 5.  የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ............ አርበኛ ጣዕማለው ወልዴ
                      6. ም/ፖ/መምሪያ ኃላፊ ...........አርበኛ መላክ ደሳለኝ
                      7. የሕ/ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ........... አርበኛ ሻምበል ኤርሚያስ
                      8. ልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ...........አርበኛ ሙሉቀን ዮሐንስ
                      9. ወታደራዊ አሥተዳደር...........አርበኛ አሠፋ በላይ
                      10."ሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ.............አርበኛ ይግዛው ጥጋቡ
                      11. ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ.............አርበኛ ይበልጣል ምላሽ
                      12. አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ............አርበኛ ማስረሻው አለምነው
                      13. ፋይናንስ አሥተዳደር..............አርበኛ በላይ መልካም
እና ሌሎችን ኃላፊና ምክትል ኃላፊዎችን ያካተተ ሪፎርም ሠርተናል።

በመጨረሻም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር ማስተላለፍ የሚፈልገው ጉዳይ ከጎንዮሽ መጓተት ወጥቶ መሬት ላይ ለሕዝባቸው ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ የትግል ጓዶቻችንን አደራ ከዳር ማድረስ የሚቻለው በቅንነትና በእውነት ሐቀኛውን የአንድነት መንገድ መከተል ብቻ እንደሆነ ጽኑ እምነታችንን። ከምንም በላይ ክ/ጦራችንን በራሳቸው ፍላጎት ያለሠራዊታችን ይሁንታ የአፋሐድ ሚሊሻ ለማድረግ የፕሮፓጋንዳ ሥራ የምትሠሩ ሚዲያዎች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን።

በዚህ መሠረት ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ትናንት በተበታተነ አደረጃጀት የነበረውን ታጋይ ለመሰብሰብ ጎንደርን በአንድ አታጋይ ተቋም የማታገሉ ሰናይ ተግባር እጅጉን ያስደሰተን መሆኑን እየገለጽን የአንድነት ተቋማችንም "የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር" በሚሰጠን አቅጣጫ፣ አሠራርና መርኅ ለመታገል ያለንን ቁርጠኝነት ሳንገልጽ ማለፍ አንፈልግም።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
https://youtu.be/CMYEOQaSYjo?si=HCZXZwUIwkzLj4xk






በዛሬው እለት የስናን አባጅሜ ብርጌድ እና የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ፋኖዎች በጥምረት ጀብድ ፈፅመዋል‼

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር  አባል ብርጌዶች የስናኑ ስናን አባጅሜ ብርጌድ እና የደብረ-ማርቆሱ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ በጋራ በመሆን ከደብረማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡ ገበያ ባለስልጣናቱና ለመሸኘት እና ሬሽን ለማቀበል የተንቀሳቀሰዉን ጠላት አፈር ደቼ አብልተውታል::

በዚህም:

12 ክላሽ
1 ስናይፐር
ከ8 በላይ የወገብ ትጥቅ ከነሙሉ ሎዱ መማረክ የተቻለ ሲሆን 1 ፓትሮል ተቃጥሏል::

በርካታ ቁጥር ያከው የጠላት ሀይል ሲሸኝ የቆሰለውም ብዛት ያለው ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።




#በአዋጅ_ቀን_ጀብድ‼

ልማደኛው #ዘንገና_ብርጌድና #ግዮን_ሰከላ ብርጌድ መብረቁ ሻለቃ ሁለቱ ተናባቢ ነብሮች ጠላትን ምርኮኛ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድልን ተቀዳጅተዋል። ቀኑ አንድነት የተበሰረበት የጠላትን ቅስም የሰበርንበት ድማማ ዲክላሬሽን በመባል የሚታወቅና እየተከበረ ያለበት ታሪካዊ እለት ነዉ።

በዚህ ቀን ነዉ እንግዲህ ከሰከላ ወደ ቲሊሊ ተንቀሳቅሶ ሬሽን ለመቀባበል በማሰብ እንደቄጣማ ሲያረግድ ሲጨነቅ ሲጠበብ ቢዉልም በተያዘበት ደፈጣ ሰተት ብሎ ገብቶ ምርኮኛ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
ከቀኑ 8:00 የጀመረዉ ዉጊያ አድማሱን እያሰፋ ከአሽፋ መገንጠያ እስከ አምቢሲ ዘልቋል።

የኔ ጠላት ያንተ ጠላት ምንለዉ የለንም፤እንደ አማራ ወጠን እንደ አማራ እናሸንፋለን።
በአንድነት ስንሆን እንዲህ ድል በድል ሁነን እንደምቃለን💪

ዝርዝር ምርኮ ከቆጠራ በኋላ የምናደርስ ይሆናል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ




የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የመጀመሪያ ጉባኤውን ማካሄዱ ተገለፀ::

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ቅርንጫፍ የሆነው ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የምዕራብ ወሎ ቀጠና ውስጥ ባሉ 11 ወረዳዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከጃማ እስከ ሳይንት እንድሁም ለጋምቦ እና ከላላ ድረስ ሌሎች ወረዳዎችንም አካሎ ከየአቅጣጫው በተውጣጡ ፋኖዎች የተዋቀረ ክፍለ ጦር ነው ተብሏል::

ክፍለ ጦሩ በኮማንዶዎች እንደሚመራም ነው ለማወቅ የቻልነው::

የጀግኖች ስብስብ የሆነውና በንፁሁ ታጋይ ስም የተሰየመው የዚህ ክፍለ ጦር አንዱ ከፍተኛ አመራር ጥር 6 ቀን 2017 ዓ/ም በርካቶችን ጥሎ መስዋዕትነት ሲከፍል ከ4 ወረዳዎች በውጭጩ የመጣው ጠላት ከ60 በላይ ኃይሉ ተደምስሶበታል::

በጥር ስድስቱ ውጊያ የተወርዋሪ ክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ተመስገን አለምነው መስዋዕትነት የከፈለው ከበባ ሰብሮ እና በርካቶችን በመጣል ጀብዱ ፈጽሞ መሆኑን የምዕራብ ወሎ ኮር ባወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ አስታውቋል::

የምዕራብ ወሎ ኮር አዛዥ አርበኛ አደም አሊ በተገኘበት ጉባኤውን ያካሄደው ተወርዋሪ ክፍለ ጦሩ በጎደሉ አመራሮች ቦታ አዳዲሶችን ተክቷል::

ጎርጎራ ቲቪ - ከእውነት ጋር
የጠብመንጃ አንጋቾች ድምጽ


የመብረቁ ተፈራ ኮማንዶና አንደኛ ሻለቃ ጥምር ጦር አራጢ (ወይንውሀ መገንጠያ) ላይ ጠላትን እየረፈረፉት ነው።


የደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጁ!
==============================================

ራሱን መከላከያ እያለ የሚጠራው የፋሽስታዊው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የሽብር ቡድን ደብረ ኤልያስ ከተማ ገብቶ በጀግኖቹ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች መገረፍ ከጀመረ ድፍን ሁለት ወራት አልፈዋል።በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በርካታ የወራሪው ጦር እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።በርካቶችም ቆስለዋል።
ቀደም ብሎ ካስገባው የጠላት ኃይል በተጨማሪ ከሰሞኑ በርካታ ሰራዊት ማስገባቱ ይታወቃል።ይህም የወረዳውን ገጠራማ አካባቢ ለመቆጣጠርና በዋናነት ግን የብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ስላሴ አንድነት ገዳምን በድጋሚ ለማውደም እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ ነው።

ዛሬም ከደብረ ኤልያስ ከተማ ሙሉ ጦሩንና መሳርያዎቹን ጭኖ ወደ ጓይ መገንጠያ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች ከፍተኛ የሆነ ውጊያን በመክፈት ታላቅ ኪሳራን አድርሰውበታል።በአርበኛ ድረስ አለማየሁና አርበኛ ነጋ መኮንን የተመራው ይህ ውጊያ የጠላትን ቅስም የሰበረ ነበር።ጠላት በዙ-23ና በሞርተር የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም ቀስተኞቹ ግን ከምሽጋቸው ፍንክች ሊሉ አልቻሉም።

በዚህ ውጊያ በወገን በኩል ቀላል ቁስለኛ ከሆኑ ጥቂት ፋኖዎቻችን ውጭ የተከፈለ መስዋዕትነት የሌለ ሲሆን በጠላት በኩል ግን 16 አምቡላንስና ፓትሮል በቁጠር ደረጃ ከ112 በላይ ቁስለኛ የተነሳ ሲሆን የሟቹን መጠን ግን በተረጋገጠ መረጃ ማወቅ አልተቻለም።ምክንያቱም በየቦታውና ምሽግ ባደረጉት የሳሰር ቤተ ክርስቲያን ይቀብሩት ስለነበር ነው።ይሁን እንጅ ከቁስለኛው በላይ ሊሆን እንደሚችል ግን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

ጠላት በአሁኑ ሰዓት በጎፍጭማ ታዳጊ ከተማና የቀጋት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚገኝ ሲሆን የትኩረት አቅጣጫውም የብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን በድጋሚ ለማውደም እንደሆነ ይታወቃል።

ደብረ ኤልያስ ግን ጠላትን ውጣ ማስቀረቷን ቀጥላለች ትቀጥላለችም።

ድል ለሕዝባችን!
ክብር ለሰማዕቶቻችን!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ ተሰፋ፣አዲስ አስተሳሰብ!

ፋኖ ኢ/ር ዘመን ባሳዝነው
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር
የቀስተደመና ብርጌድ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

ጥር 19/2017 ዓ.ም




ጀግናው ተሰውቷል:: እኔም የሰማሁት ዘግይቼ ነው!!

ለነገሩ እሱ ቢሰዋም የልቡን ሰርቶ ነው:: በአጠቃላይ ሰሞኑን በአማራ ሳይንት ቀጠና በሰፊው የምዕራብ ወሎ ግንባር ነገሮች በፍጥነት ተቀይረዋል::

2 መከላከያ እና ሚሊሻዎች የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ብርጌድን በመሀል ሳይንት ወረዳ ግንባር ተቀላቅለው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል የሚል መረጃ አሁን ደርሶኛል:: የአትሮንስ ብርጌድ አዛዥ ፋኖ ጎሹ ታረቀኝ የጠላትን አቅም እያሽመደመደው ነው:: ቁልፍ አዋጊዎችን አምጥቶበታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ በአማራ ሳይንት ቀጠና በለጋምቦ ወረዳ ግንባር ገነቴ አቅራቢያ ሰሞኑን ታሪክ ሲሰራ ሰንብቶ ኖሯል:: ጥር 6 ለ7 ሌሊት በተደረገ ጦርነት የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አደራጅ ኮሚቴ አባል እና የክፍለ ጦሩ ስራ አስፈጻሚ የሆነው ኮማንዶ ተመስገን ሳይንቴው ጀብዱ ፈፅሞ በጀግንነት ተሰውቷል::

የኮሩ ጊዜያዊ ኮሚቴው ተሰባስቦ አዳዲስ ስራ አስፈጻሚዎችን በመሰየም በሰራዊቱ ሊያፀድቅ ከየቦታው ተሰባስቦ ለጋምቦ ወረዳ እና ወግዲ ወረዳ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ብስቁልል የምትባል መንደር ውስጥ ከኮሩ አዛዥ አርበኛ አደም አሊ ጋር ውይይት ላይ ሳሉ የኮሩ አዛዥ አጃቢ የነበረና ከቀናት በፊት ከድቶ ወደ መንግስት የገባ የየሹም አካባቢ ተወላጅ ባንዳ ከወግዲ ወረዳ በኩል ጠላትን እየመራ መጥቶ ከሌሎች የጎረቤት ወረዳዎችም ተጨማሪ ኃይል በቦታው በመድረስ ሌሊት ከባባ ቢፈፅምም ጀግኖች በታትነውታል::

ሞት አይፈሬው ሳይንቴ ከ4 ወረዳዎች የጥምር ጦሩ ጊዜያዊ ካምፓች ተውጣጥቶ በመጣ ከ400 የማያንስ መከላከያ እና እልቆ የለሽ አ.ሚ.ፓ. (አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ...አድማ ብተና እና ፓሊስ) ድብልቅ ሰራዊት ጋር በነበረው ትንቅንቅ በርካታ ጠላት ደምስሶ ተሰውቷል::

የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አዛዥ አርበኛ አደም አሊ ጋር ውጊያን በመምራት ላይ ሳለ ነው ኮማንዶ ተመስገን የተሰዋው:: ፊት ለፊት ሲዋጋ ቆይቶ ከበባ ሰብረው እና ጠላትን ከምሽጉ ነቅለው በማስፈርጠጥ ታላቅ ገድል እየፈፀሙ ባሉበት ቅጽበት ነው በድንገት የተመታው::

በዚህ አውደ ውጊያ ከወግዲ በኩል ከመጣው ጥምር ጦር ብቻ 30 በጥይት ቀምሶ 17ቱ ሙት ሲሆን ቀሪው ቆስሏል::

በለጋምቦ በኩልም ከዚህ ያላነሰ ቁጥር ያለው ጠላት ተደምስሶ 20ዎቹ ጊምባ ተቀብረዋል:: ከ5 ቀናት በኋላ ከትናንት በስቲያ አስከሬን ለቀማ ወደ ውጊያው ቀጠና የተጓዘው ጠላት አርሶአደሮችን አፋልጉኝ ብሎ አስገድዶ ሲፈልግ ቆይቶ የ6 ወታደሮችን እግር አግኝቷል::

በብስቁልሉ ኦፕሬሽን በድምሩ ከ60 በላይ ጠላት እንደተመታ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት:: የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ኦርዲናንስ ኃላፊን ጨምሮ አንድ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ክፍለ ጦር ፋኖ መቁሰሉ የተገለፀ ሲሆን ከኮማንዶ ተመስገን ሳይንቴው ጋር መስዋዕትነት የከፈለም ሳይኖር እንዳልቀረ ነው የሰማሁት::

በጥቂት መስዋዕትነት አስገራሚ የሚባል ጀብዱ ተፈፅሟል ኮማንዶ ተመስገን እንደተሰዋም አንቆጥረውም ሲሉ ነው ጓዶቹ የገለፁት:: ሞት አይፈሬው ጀግና የሳይንቴይቱ ልጅ ከአዲስ አበባ ድረስ ወደ ግንባር ከገባ ሁለት ወር አልሆነውም:: የቀኝ አዝማች ይታገሱን ደም የምንመልሰው ህዝባችን ነጻ ሲወጣ ነው ብሎ የወንድሙን ደም ሊመልስ ገብቶ የልቡን ሰርቶ ተሰውቷል:: ለቃሉ ታምኖ የወንድሙንም አደራ ተሸክሞ እስከ ሞት ድረስ በሀቅ ታግሎ አርፏል:: ይህ ወርቃማ ዕድል ነው:: የዚህ ታሪክ ባለቤት ሆኖ ስም አስሮ መሰዋት መታደል ነው እንጅ ሞት አይባልም!!

ለወዳጅ ዘመድ እና ለጓዶቹ በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ!! ነፍስ ይማር!!


የጎንደር ፋኖ አንድ ሆነ✊




ምዕራብ ጎጃም ከቡሬ ከተማ ወጣ ብሎ ደረቋ ላይ ሀይለኛ ጦርነት በመካሄድ ላይ ሲሆን ከቡሬ ከተማ ታንክ እዬሄደ ይገኛል አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መረጃው በአስቸኳይ ይዛመት።


የጣናው መብረቅ ብርጌድ ከባህር ዳር አፍጫ ስር በምትገኘው መሸንቲ ከተማ ውስጥ ትናትን 8 ሰአት ላይ የተሰካ ኦፕሬሽን ሰርቷል::

Показано 20 последних публикаций.