MLTIM


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram


በዚህ ቻናል ገንቢና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ትምህርቶችና ቪዲዮች የሚሰጡበት ሲሆን ሁላችሁም እንድትጠቀሙበት ጋብዘናል፡፡

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций






እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመታደግ የሰጠው ተስፋ
1 የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።

2 በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።

3 እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችሁና አዳኛችሁ ነኝ፤ እናንተን ለመታደግ ግብጽን፥ ኢትዮጵያውያንንና ሳባን እሰጣለሁ።

4 እናንተ በእኔ ፊት የተወደዳችሁ ናችሁ፤ ስለምወዳችሁ ሕይወታችሁን ለማዳን ሕዝቦችንና መንግሥታችን አሳልፌ እሰጣለሁ።

5 እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍሩ
፤ ኢሳይያስ 43:1-5


የባርኮት ቃል ለሚመለከተዉ ሁሉ

🙏🙏🙏እግዚአብሄር የተቀደሰ ተራራዉን ገንዘቡ በምናደርግበት ጎዳና ሁላችንንም ይምራን!! ያም ጎዳና እርሱን መጠጊያዉ ማድረግ ነዉ!! ስለዚህ እግዚአብሄር ገንዘብ የሚሆነንን የተቀደሰ ጓደኛ፣ የተቀደሰ አገልጋይ፣ የተቀደሰ ዕድል፣ የተቀደሰ በረከት፣ የተቀደሰ ህብረት፣ የተቀደሰ ጉባዔ፣ የተቀደሰ ስራ፣ የተቀደሰ አገልግሎት፣ የተቀደሰ ቤተሰብ፣ የተቀደሰ ጎሮቤት፣ የተቀደሰ ዘመን ፣… በጌታ በኢየሱስ ስም እንደፈቃዱ ይስጠን!! አሜን!!

📡የመልእክቱ ምንጭ፡-
📜“እኔን መጠጊያው ያደረገ ሰው ግን፣ ምድሪቱን ይወርሳል፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ገንዘቡ ያደርገዋል።”” — ኢሳይያስ 57፥13 (አዲሱ መ.ት)
📜“But whoever takes refuge in me will inherit the land and possess my holy mountain.” Isaiah 57:13


🙏🙏🙏ይህ የእግዚአብሄር ቃል በረከት ይህን መልዕክት አሜን ብሎ ለሚቀበል ሁሉ ይሁንለት!! በ2 ነገ 4፡41 ላይ ፣” በምንቸቱ ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም” ተብሎ እንደተፃፈዉ በነገአችሁ፣ በየካቲት ወራችሁ፣ በደማችሁ፣ በቤታችሁ፣ በኑሮአችሁ፣ በሰዉነታችሁ፣ በሰዉነት ስርዓታችሁ፣ በሰፈራችሁ፣ በቤተ-ክርስቲያናችሁ፣ በጤናችሁ፣ በትምህርት ቤታችሁ፣ በከተማችሁ፣ በስብሰባችሁ፣ በህብረታችሁ፣ በስራችሁ፣…ጉዳት የምያስከትል ነገር አልተገኘምና እንኳን ደስ አላችሁ!! ምክንያቱም እግዚአብሄር በዚህ 2016/2024 በኤርምያስ 29፡11 ላይ ለእናንተ ካለዉ 4 ዕቅዱ አንዱ እናንቴን የሚጎዳ አይደለም ብሏልና!!
❤️41ኤልሳዕም፣ “እስቲ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም። 2ነገስት 4፡41
❤️11ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። ኤርምያስ 29፡11


”2ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሓይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም ከጋጥ እንደ ተለቀቀ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ። 3እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።ሚልክያስ 4:2-3


እግዚአብሄር ነፍሳት እርሱን እኛ ጋር እንዳለ የምሰሙበት ምስክርነት ሰጥቶን አብረን ቤተ ክርስቲያን እንሂድ የምሉትን የተለያዩ ሰዎች ይስጠን !!!
“እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በእነዚያም ቀናት ከየወገኑና ከየቋንቋው ዐሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ “ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና አብረን እንሂድ’ ” ይሉታል።” — ዘካርያስ 8፥23 (አዲሱ መ.ት)


መዝሙር 22 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ መከራ እየተቃረበ ነውና፣ የሚረዳኝም የለምና፣ ከእኔ አትራቅ።
¹² ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።
¹³ እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣ አፋቸውን ከፈቱብኝ።
¹⁴ እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።
¹⁵ ጒልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።
¹⁶ ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፎአል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።
¹⁷ ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።
¹⁸ ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
¹⁹ አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ አጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
²⁰ ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።
²¹ ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።


👜በዘዳግም 11፡10-12 መሠረት ልባርካችሁ አሜን ብላችሁ ተቀበሉ!!!👜
🌻በዚህ 2024 ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእናንተና በእናንተ በሆነ ነገር ሁሉ ላይ ይሁን!!!
🌻በተጨማሪም በአምላካችሁ በእግዚአብሄር የሚትጎበኙበት ዓመት ይሁንላችሁ!!!

10 ፤ ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።
11 ፤ ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት አገር ናት፤ በሰማይ ዝናብ ውኃ ትረካለች።
12 ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት አገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው። ዘዳ 11፡10-12




መዝሙር 121፡4-8
4 እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።
5 እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።
6 ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት።
7 እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።




❤️የእግዚአብሄር ምርጦች ከእግዚአብሄር የሚያገኙት ርስቶች ❤️❤️
1.እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሳሪያን ያከሽፍላቸዋል፤ ኢሳ 54፡17
2.የሚከሳቸዉን አንደበት ሁሉ መርታት፤ኢሳ 54፡17
3.እግዚአብሄር ያበለፅጋቸዋል፤መዝ 106፡5
4.እግዚአብሄር በእዉቀት ያሳድጋቸዋል፤ ቲቶ 1፡1
5.እግዚአብሄር ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ሉቃስ 18፡7
6.እግዚአብሄር ከመከራቸዉ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤ መዝ 37፡40
7.እግዚአብሄር ከሰዎች ሴራ በማደሪያዉ ዉስጥ ይሸሽጋቸዋል፤ መዝ 31፡19-20
8.እግዚአብሄር ከአንደበት ጭቅጭቅ በድንኳኑ ዉስጥ ይከልላቸዋል፤ መዝ 31፡19-20
9.እግዚአብሄር መልአኩን በፊታቸዉ ይልክላቸዋል፤ ዘፅ 23፡20
10.እግዚአብሄር በመልካሙ ስፍራ ያሰማራቸዋል፤ ህዝቅ 34፡14
11.እግዚአብሄር ያስመስጋቸዋል፤ ህዝቅ 34፡15
12.እግዚአብሄር ፍሬ በመስጠት የታወቀዉን መሬት ይሰጣቸዋል፤ ህዝቅ 34፡29
13.እግዚአብሄር መልአኩን ከእርሱ ጋር ይልካል፤ ዘፍ 24፡40
14.እግዚአብሄር መልካምነቱን ሁሉ በፊታቸዉ ያሳልፋል፤ ዘፅ 33፡19
15.እግዚአብሄር በፊታቸዉ ይሄድላቸዋል፤ ኢሳ 45፡1-3
16.እግዚአብሄር በተሰወረ ስፍራ የተከማቸዉን ሀብት፣…ይሰጣቸዋል፤ ኢሳ 45፡2-3


🌹8 የተባረከ ሰዉ ርስት፤መዝሙር 127፡2-5 እና ዘዳግም 33፡24🌹🌹
1.እግዚአብሄር ጣፋጭ እንቅልፍን ይሰጠዋል፤ መዝ 127፡2
2.የመከራ እንጀራ አይበላም፤ መዝ 127፡2
3.ምርጥ ስጦታን ያገኛል፤ መዝ 127፡3
4.ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተበረከ ልጅን ያገኛል፤ ዘዳ 33፡24
5.ተወዳጅ ልጅን ያገኛል፤ ዘዳ 33፡24
6.የሆዱ ፍሬ የተባረከ መሆኑ፤ መዝ 127፡3
7.የጎልማሳነት ልጆቹ በሀያል እጅ እንዳሉ ፍላፆች መሆናቸዉ፤ መዝ 127፡4
8.ጠላቶቹን በአደባባይ በሚናገርበት ጊዜ አለማፈሩ፤ መዝ 127፡5


ሞዴል የእግዚአብሄር ምርጦች ባህሪይ
1.መልበስ (ርህራሄን፣ ቸርነትን፣ትህትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግስትን)፤ ቆላ 3፡12-13
2.መቻቻል፤ቆላ 3፡12-13
3.ይቅር መባባል፤ቆላ 3፡12-13
4.ማደግ (በዕምነትና በዕዉቀት)፤ ቲቶ 1፡1-2
5.የእዉነትን ቃል በትክክል ማስረዳት፤ 2ጢሞ 2፡15
6.እ/ርን ከማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ መራቅ፤ 2ጢሞ 2፡16
7.ለመልካም ስራ ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ መሆን፤ 2ጢሞ 2፡21
8.የሁሉ አገልጋይ መሆን፤ ማር 9፡35
9.እጅግ መቀደስ፤ ህዝቅ 43፡12
10.በእግዚአብሄር ድንኳን ዉስጥ ማደር፤ መዝ 15፡1-5
11.በእግዚአብሄር የተቀደሰ ኮረብታ መኖር፤ መዝ 15፡1-5
12. አካሄድን ንፁህ ማድረግ፤መዝ 15፡1-5
13.ፅድቅን ማድረግ፤መዝ 15፡1-5
14.ከልብ እዉነትን መናገር፤መዝ 15፡1-5
15.በምላስ አለመሸንገል፤መዝ 15፡1-5
16.በባለንጀራቸዉ ላይ ክፉ አለመስራት፤መዝ 15፡1-5
17.ወዳጃቸዉን አለማማት፤መዝ 15፡1-5
18.ነዉረኛን በፊታቸዉ መናቅ፤መዝ 15፡1-5
19.እግዚአብሄርን የሚፈሩትን ማክበር፤መዝ 15፡1-5
20.ቃለ መሃላዉን መጠበቅ፤መዝ 15፡1-5
21.ገንዘቡን በአራጣ አለማበደር፤መዝ 15፡1-5
22.በንፁሃን ላይ ጉቦ አለመቀበል፤መዝ 15፡1-5
23.አለመናወጥ፤መዝ 15፡1-5
24.ሰዉነትን ቅዱስና እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ ህያዉ መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ፤ ሮሜ 12፡1
25.ልብሱን ማጠብ፤ ራዕይ 22፡14
26.እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ፤ 1ቆሮ 3፡10
27.ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ መፍጠን፤ ፊልጵ 3፡14
28.ክርስቶስ ኢየሱስ እርሱን የራሱ ያደረገበትን ያን፣ እርሱም የራሱ ለማድረግ መጣጣር፤ ፊልጵ 3፡12
29.ከኋላዉ ያለዉን እየረሳ ከፊቱ ወዳለዉ መዘርጋት፤ ፊልጵ 3፡13
30.ሽልማትን እንደሚቀበል ሰዉ መሮጥ፤ 1ቆሮ 9፡24
31.በሁሉም ነገር ራስን መግዛት፤ 1ቆሮ 9፡25
32.ለዘላለም የማይጠፋዉን አክልል ለማግኘት መድከም፤ 1ቆሮ 9፡25


ሉቃ 2:1-11
1 በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።

2 ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።

3 ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ።

4-5 ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።

6 በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥

7 የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።

8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

9 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።

10 መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤

11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።


ሕዝቅኤል 43 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ኀጢአታቸው ያፍሩ ዘንድ፣ ለእስራኤል ሕዝብ ቤተ መቅደሱን አሳያቸው፤ ንድፉንም ያስተውሉ፤
¹¹ ስላደረጉት ነገር ሁሉ ኀፍረት የሚሰማቸው ከሆነ፣ የቤተ መቅደሱን ንድፍ እንዲያውቁት አድርግ፤ ይኸውም አሠራሩን፣ መውጫና መግቢያውን፣ አጠቃላይ ንድፉን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን ሁሉ ነው። ንድፉንና ሥርዐቱን እንዲጠብቁና እንዲከተሉ እነዚህን ሁሉ እነርሱ ባሉበት ጻፋቸው።
¹² “የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ጫፍ አካባቢ ያለው ስፍራ ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል። የቤተ መቅደሱም ሕግ ይኸው ነው።


ኦሪት ዘፍጥረት 18:1-3

1 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።

2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥እንዲህም አለ፦

3 አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ





Показано 20 последних публикаций.

148

подписчиков
Статистика канала
Популярное в канале