TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
||ሀዲስ ብቻ||

8 Jul 2018, 09:16

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

#P3
لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ
(ላ ኢላሃ ኢለሏህ)
الكفر بالطاغوت
(አል ኩፍሩ ቢጧጉት)
(በጧጉት መካድ)

ባሳለፍነው ክፍል… #ጧጉት ማለት በጥቅሉ ከአላህ ውጭ የሚመለክ አምልኮ ባጠቃላይ፣ #እየወደደ የተመለከ፣ #በማምለክ #በመከተል #በመታዘዝ #ከአላህና #መልእክተኛው ትእዛዝ ውጪ በሆነ መልኩ የአላህን ድምበር ከተላለፉበት ያ አካል #ጧጉት እንደሚባል አይተናል።

#ጠዋጊቶች(ጣዖታቶች) በጣም ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹ #አምስት ናቸው።
=========================
1ኛ #ሸይጧን(ኢብሊስ ነው) ከአላህ ውጭ ያለ አካልን ወደማምለክ የሚጣራው

አላህ እንደተናገረው፦

[۞ أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ]
{{የአደም ልጆች ሆይ! #ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?}} (ያሲን 60)
=========================
2ኛ #እየወደደ የተመለከ።(መመለኩን እየወደደ ከአላህ ውጭ የሚመለክ)

አላህም እንደተናገረው፦

[۞ وَمَن يَقُلْ مِنْهُمْ إِنِّي إِلَٰهٌ مِّن دُونِهِ فَذَٰلِكَ نَجْزِيهِ جَهَنَّمَ ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِي الظَّالِمِينَ]
{{ከእነሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ» #የሚል ያንን #ገሀነምን እንመነዳዋለን፡፡ እንደዚሁ በዳዮችን እንመነዳለን፡፡}} (አንቢያእ 29)
=========================
3ኛ ከአላህ ውጪ #የሩቅ #ሚስጥርን አውቃለሁ ብሎ #የሚጣራና #የሞገተ ነው።

አላህ እንደተናገረው፦

{{عَالِمُ الْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِ أَحَدًا
«(እርሱ) #ሩቁን #ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ #አንድንም #አያሳውቅም፡፡»
إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا
#ከመልክተኛ #ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡}} (አል ጂን 26-27)

በሌላም አንቀፅ ላይ እንዳለው፦
۞ وَعِندَهُ مَفَاتِحُ الْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا هُوَ ۚ ]
{#የሩቅ ነገርም #መክፈቻዎች #እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ #ከእርሱ #በቀር ማንም #አያውቃቸውም፡፡} (አንዓም 59)
=========================
4ኛ #የአላህን #ሸሪዓ(ሕግ) #የቀየረ አምባገነን መሪ።

አላህ እንደተናገረው፦

[[أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ آمَنُوا بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوا إِلَى الطَّاغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوا أَن يَكْفُرُوا بِهِ وَيُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُضِلَّهُمْ ضَلَالًا بَعِيدًا]]
{{ወደ እነዚያ እነርሱ #በአንተ ላይ #በተወረደውና #ከአንተ በፊትም #በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ #አላየህምን? በእርሱ #እንዲክዱ በእርግጥ #የታዘዙ ሲኾኑ #ወደ #ጣዖት #መፋረድን #ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል፡፡}} (ኒሳእ 60)
=========================
5ኛ #አላህ #ካወረደው #ውጭ በሆነ #ሸሪዓ(ሕግ) የሚዳኝ (የሚፈርድ)።

አላህ እንደተናገረው፦
[[وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ]]
{{#አላህም #ባወረደው ነገር #ያልፈረደ ሰው እነዚያ #ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡}} (ማኢዳህ 44)
=========================

#አስተውል፦ ማንኛውም ሰው በቅድሚያ #በጧጉት ካልካደ #በስተቀር ሙእሚን(አማኝ)ሊባል #አይችልም።

(በአላህ #ከማመኑ #በፊት ቅድሚያ ከአላህ ውጭ የሚያመልካቸውን አካላቶች (ጣዖቶች) እርግፍ አድርጎ #መተው አለበት። እነሱንም እያመለከ አላህን ቢያመልክ (አማኝ ነኝ ቢልምኳ) ፈጽሞ #አማኝ #አያደርገውም።)

አላህ እንደተናገረው፦

[[لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ]]
{{በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ #በጣዖትም #የሚክድና #በአላህ #የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን #ጠንካራ #ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡}} (በቀራህ 256)

ጥራት የተገባው አላህ በአላህ #ከማመን በፊት በጣዖት #መካድን አስቀደመ።
=========================
በአሏህ ማመን ማለት……

@Allahu_Rabi
https://t.me/Husnul_Khuluk

885 0 0
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot