ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 13 ደዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙት የተለያዩ ዘደዎች
ይህም ማለት ወህይ፣ቁርኣን ፣ነቢይነት (ኑብዋ)እና መልእክተኛነት (ሪሳላ)የአላህ ችሮታዎች ስለሆኑ ችሮታውን እንዴት እንደሚያከፋፍል፣ የት እንደሚያስቀምጣቸው ፣ለማን እንደሚሰጣቸውና ማንን እንደሚከለክላቸው የሚያውቀው እርሱ አላህ ብቻነው። አላህ እንድህ ይላል፦
اللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۗ١٢٤፡
አላህ መልእክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ይበልጥ አዋቂነው።( አል-አንኣም 6:124)
ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ሌላ ማስመሰያ(ሹብሃ) ተዘዋወሩ። መልእክተኛ(ረሱል) መሆን ያለበት ከምድራዊ ነገስታት አንዱ ነው።በንግስናው ምክንያት ክብርንና ግርማን የተጎናፀፈ፣አገልጋዮች፣አጃቢዎች፣አትክልቶች ገንዘብና የመሳሰሉት ነገሮች ያሉት፣ግብርና ዝና ባላቸው ጠባቂዎችና አጃቢዎች ታጅቦ የሚሄድ መሆን አለበት አሉ።ሙሐመድ ደግሞ የእለት ጉርሻውን ለማግኘት በገበያ ውስጥ ከሰው ጋር እየተጋፋ የሚሄድ የአላህ መልእክተኛ ነኝ ይባላልን?አሉ።
لَوْ لَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكࣱ فَيَكُونَ مَعَهُ نَذِيرًا٧أَوْ يُلْقَیٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُ جَنَتٌّ يَأْكُلُ مِنْهَاۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلࣰا مَسْحُورًا٨
ከርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወርሱ መልአክ (በገሃድ)አይወርድም ኖሯልን?አሉ፦ወይም ወደርሱ ድልብ አይጣልለትንም?ወይም ከርሷ የሚበላላት አትክልት ለርሱ አትኖረውምን?(አሉ)በዳዮችም (ላመኑት)የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም አሉ። (አል ፉርቃን25:7-8)
ነቢዩ (ﷺ)ለሁሉም የሰው ልጅ አይነት፦ለትንሹም ለትልቁም፣ለደካማውም ለጠንካራውም፣ለተራውም ለክብሩም፣ለባሪያውም ለነፃውም (ለጨዋውም)የተላኩ መሆናቸው የሚታወቅነው ከላይ እንደተባለው ግርማ ያላቸውና የሚፈሩ፣በአገልጋዮች፣በአጃቢዎችና በታላላቆች የታጀቡ ቢሆን ኖሮ የኅብረተሰቡን አብዛኛውን ክፍል የሚወክሉት ደካሞችና ትንንሾች ሊጠቀሙባቸው ስለማይችሉ የሐልእክቱ(የሪሳላው)ዋና አላማ ሳይፈፅም ይቀር ነበር።እስካሁን የሚወሳና ሊጠቀስ የሚችል ጠቅም ባላስገኝም ነበር።ስለዚህም ሙሽሪኮች ለዚህ ጥያቄያቸው ሙሐመድ(ﷺ)መልእክተኛ ነው የሚል መልስ ነው የተሰጡት። በርግጥ መልእክተኛ መሆናቸው ሁሉንም የሙሽሪኮች ማምታቻ ጥያቄዎች ፉርሽ ለማድረግ በቂ ነው ።መልእክተኛ እንድኖሩት የጠየቃችሁት መፈራት፣ግርማ፣አጃቢና ገንዘብ ለብዙሃኑ ሕዝብ መልእክት የማድረሱን ኣላማና ተግባር የሚፃረር ጥያቄ ነው።መልእክት እንድደርስ የሚፈለገው ለሁሉምነውና።
በዚህ ሹበሀቸው ላይ መልስ ሲሰጥበት ሌላ እርምጃ ተራመዱ።ለእምቢተኝነትና ነቢዩን ለማታከት ተአምራትን እንድያሳዩአቸው ጠየቁዋቸው። በዚህ ጉዳይ በነቢዩና (ﷺ)በነሱ መካከል ክርክርና ውይይት ተካሄደ።ወደፊት የተወሰኑትን ለማምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላሁ ተዓላ።
ይቀጥላል
https://t.me/Menhaj_Asselefiya