ሚንሐጁ ሱንና አንነበዊያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት ወይም አቂዳ ማለት፣
በቁርአን እና ሀዲስ ቀደምትሰለፎች በተገነዘቡት ግንዛቤ ላይ በተመሰረተ መልኩ ከሆነ ብቻ ነው ባረከላህፊኩም ሼር ያርጉ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የህዝቦች የምግብና የልብስ ምርጫ ልዩነት አካባቢን፣ አየር ንብረትን፣ ልማድን፣ ወዘተ መሰረት ያደረገ ነው። ቆለኛና በረኸኛው ሽርጥ መልበስ ይወዳል። ከመውደዱ ጀርባ ሌላ ምንም ሚስጥር የለም። ለሚኖርበት አየር ንብረት ተስማሚ ስለሆነ ነው። በወበቃማ አየር ውስጥ ለሚኖር ሽርጥ ለባሽ ቆለኛ ሱሪ መልበስ አቅማዳ ውስጥ የመግባት ይህን ያስጨንቃል። ለሱሪ ለባሽ ደገኛ ደግሞ ሽርጥ ቢለብስ ልብስ የለበሰ እስከማይመስለው ድረስ ሊቀፈው ይችላል።
ልምድ ተፅእኖው ቀላል አይደለም። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሱሪ ለባሽ ሸይኽ ያየሁት 10ኛ ክፍል ለመማር በወጣሁበት አካባቢ ነው። ራሴ ሱሪ የለበስኩ ከመሆኔ ጋር በጣም ነበር የቀፈፈኝ። እውነቱን ለመናገር ከሱ ዘንድ ቁጭ ብዬ መማር ከብዶኛል። ለነገሩ የሸይኽ ሱሪ ለባሽ ዛሬም ድረስ ምቾት አይሰጠኝም። ሑክም ሳይሆን አብሮ ያደገ ስሜቴን ነው የገለፅኩት።
ምግብ ላይም እንዲሁ ነው። ሰሜኑ ከደቡቡ፣ ምስራቁ ከምዕራቡ የሆነ ያክል የምግብ ወይም የአመጋገብ ልዩነት አለው። እዚሁ ሃገራችን ውስጥ የግመል ስጋ የሚፀየፍ ሰው አለኮ። በሆነ ጉዳይ ወደ ጎረቤት ሃገር ሄጄ ነበር። አንድ እዚያው የተዋወቅኩት ወንድም ጋር ምግብ ቤት ገባን። "ምን እንብላ?" አለኝ። "እኔ የት አውቀዋለሁ? አንተ እዘዝ" አልኩት። አዘዘ። አይቼ የማላውቀው ከምላሴ በፊት አይኔ ያልወደደው ምግብ መጣ። ሲቀርብ ልቤን አጥወለወለኝ። የሱን ስሜት ለመጠበቅ ፈለግኩ። ግን ፈተነኝ። እሱ ለባህሉም፣ ለምግቡም ቅርብ ነው። በጣም ተመችቶታል። "አንዳንድ ሰዎች ይህንን ምግብ ያጣጥላሉ" ብሎ በቅሬታ አነሳ። እንዴት አድርጌ ስሜቴን እንደምገልፅ ተጨነቅኩ። ከተወሰነ ቆይታ በኋላ ስለተረዳኝ እፎይ አልኩ። ከዚያች ሃገር ዜጎች ውስጥ ከኛ ምግቦች ውስጥ ብዙ ግራ የሚያጋባቸው እንደሚኖሩ እጠብቃለሁ።
ማለት የፈለግኩት ምርጫችን የራሳችን ነው። አንዳንድ ምግብና ልብስ ጋር በተያያዘ ባደባባይ የምንሰነዝራቸው ሃሳቦች ግን ሌላ ትርጉም እንዳይኖራቸው ወይም እንዳይስሰጣቸው ብንጠነቀቅ መልካም ነው ለማለት ነው። መቼም ከጥቂት ጓደኞች መሃል የሚወራና ሰፊ ህዝብ የሚከታተለው ወሬ አንድ አይደለም።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ድምቀቶቻችን
~
ጉራጌና ስልጤ የከተማ ጌጦች የዒዳችን ድምቀቶች ናቸው። በዒደል ፊጥርና በዒደል አድሓ ያለውን ልዩነት ላስተዋለ ጎዳናዎቻችንና መስጂዶቻችን አፍ አውጥተው የሚናገሩት መልእክት አለ።
ጉራጌና ስልጤ የከተማ ህይወት ቅመሞች ናቸው። እንደ ሃገር ከትንንሽ እስከ ትልልቅ የቢዝነስ እንቅስቃሴ ውስጥ በሰፊው በመኖራቸው ለኢኮኖሚ መነቃቃትና ለከተሞች እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ አላቸው። ይሄ ለህዝብም ለሃገርም የሚዋል ትልቅ ውለታ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ በአብዛኛው ጉራጌና ስልጤ የሚበዛበት ሰፈር ከሌሎች የተሻለ መነቃቃት አለው።
ጉራጌና ስልጤ የኢትዮጵያ ሙስሊም ንቁ ክፍሎች ናቸው። በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል በሙስሊሙ ላይ ለሚደርስ በደል ድምፃቸው ከቁጥራቸው በላይ ጎልቶ ይሰማል። በየትኛውም መዋጮና አስተዋጽኦ ላይ ከፊት መስመር ይገኛሉ። በየከተሙበት ሁሉ መስጂድ እንዲኖራቸው የሚያደርጉት ጥረት ጠላትን የሚያስቀና ወዳጅን "እንኳን የኔ ሆናችሁ!" የሚያስብል ነው። በኢማን ላይ ኢማን፣ በዓፊያ ላይ ዓፊያ፣ በሃብት ላይ ሃብት ደራርቦ ይስጣችሁ። ኑሩልን።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//IbnuMunewor


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .

የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።

አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።

ጉዞውን የጀመረው ፤ ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት (6) ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።

ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን (UAE) አቆራርጧል።

ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ ?

" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ #መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።

የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  መስጂድ ማየት ነበር።

ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት።

አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል።

አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው።

ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው። ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል።

ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ  ፣ በፍተሻ ጣቢያ ፣ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል። አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ።

በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁ።

ምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ።  ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል። "

Via BBC - Al Jazeera

@tikvahethiopia


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ትልቅ እውነት ከዩሱፍ አልቀረዷዊ
~
ከኢኽዋነል ሙስሊሚን አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ አይን ያወጣ ግነት ነው። በማጠልሸትም በማወደስም ያለ ግነት።

* የሚጠሉትን አካል የፈለገ መልካም እሴት ቢኖረው እንኳ፣ አየን የሚሉት ጥፋት ራሳቸው ዘንድ በሰፊው የሚገኝ ቢሆን እንኳ በተለየ ያጠለሹታል። ሳር ቅጠሉ እንዲጠላው አድርገው ያንቋሹታል። ኢስላምን ለማጥፋት የሚያሴር እንደሆነ አድርገው ያለ ረፍት ደጋግመው በማንቋሸሽ ገፅታውን ጥላሸት ይቀቡታል።
* የወደዱትን ደግሞ የሌለውን ያልተከሰተውን ሁሉ እየፈጠሩ ያደንቁታል። መልካም ስራዎች ካሉትም ለሌሎች የማያደርጉትን ትንሹን አግዝፈው፣ ጥቂቱን አብዝተው ያራግቡለታል። ጥፋቶቹን ይሸፍኑለታል። ማለፊያ ሰበብ ይደረድሩለታል።

ሺዐ፣ ኻሪ -ጂ፣ ወደ ሺርክ የሚጣራ ቁቡሪ፣ ሌላው ቀርቶ ከሃዲ እንኳ ቢሆን የወደዱትን ሰማይ አድርሶ በመስቀል የታወቁ ናቸው። የሙስሊሙ አለኝታ፣ ኢማም፣ ዘመኑን የቀደመ፣ ... እያሉ ሰማይ ያደርሱታል። ከነብይ በላይ ሁሉ አድርገው ሊያደንቁት ይችላሉ። የሚሞግተኝ ካለ ለያንዳንዷ ንግግሬ መረጃ መጥቀስ እችላለሁ።

ይሄ በፍቅርም በጥልም የተጋነነ ስፍር መስፈር እንደ ቡድን የኢኽዋን መታወቂያ እንደሆነ ዩሱፍ አልቀረዷዊ እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦
‌‏"‏وأقول بأسف! لقد كان رجال المباحث أصدق في الحكم علينا من إخواننا الذين عرفناهم وعرفونا وعايشونا وعايشناهم. وهذا مايعاب على كثير من الإخوان، أنهم إذا أحبوا شخصا رفعوه إلى السماء السابعة، وإذا كرهوه هبطوا به إلى الأرض السفلى."
“እያዘንኩ የምናገረው ነገር ቢኖር ከምናውቃቸውና ከሚያውቁን፣ ከተኗኗርናቸውና ከተኗኗሩን ወንድሞቻችን ይልቅ የመንግስት ደህንነት ሰዎች በኛ ላይ የሚናገሩት ይበልጥ እውነተኛ ብይን ነው፡፡ ይህ ብዙ ኢኽዋኖች የሚወቀሱበት ነው፡፡ እነሱ አንድን ሰው ከወደዱት ወደ ሰባተኛው ሰማይ ያነሱታል፡፡ የጠሉት ጊዜ ደግሞ ወደ ሰባተኛው መሬት ያወርዱታል!” [ሲራ ወመሲራ፡ 2/89]
.
ያያያዝኳቸው ምስሎች በቀጠሩ የኳስ ድግስ ላይ የሰለሙ ብለው ያቀረቧቸው ቅጥፈቶች ናቸው። ከስንት አመታት በፊት የወጡ ምስሎችን ፎቶሾፕ እየሰሩ ፕሮፖጋንዳ እየሰሩ ነው። አንዱ የ 2016 ሌላው የ 2018 ምስሎች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢስላምን ለመነገጃነት ከመጠቀም የማያርፍ ቡድን
~
ኢኽዋን ከላይ እስከ ታች እንደ እስስት በማስመሰል የተካነ፣ ሌላው ላይ ሲሆን ያወገዘውን "የኔ" በሚላቸው ላይ ሲታይ ሸፋፍኖ ለማወደስ አይኑን የማያሸ፣ ለነቀዘ ቡድናዊ አላማው ሲል ኢስላምን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የሚጠቀም የለየለት ሃፍረተ ቢስ ቡድን ነው። ኢኽዋን ከሱና ዑለማእ ውጭ ሁሉም ኣካል ወዳጁ ነው። ከሺ0 ጋር፣ ከኢባዲያ ኸዋሪጆች ጋር፣ ከአሕባሽ ጋር ህብረት መስርቷል። ተብሊግን ያወድሳል። ጥቅም ካየበት በሻረል አሰድን ያወድሳል፣ ቀረዳዊ እንዳደረገው። ኔታንያሁን ሳይቀር የሚያወድስ አለ። ብቸኛ ጠላቱ የአህለ ሱና እንቅስቃሴ ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ ምእራቡን የሚያወግዘው እንኳ ፈዛዛ ደጋፊዎቹን ለመያዝ ያክል እንጂ መርህ ላይ የተመሰረተ፣ መሬት የረገጠ አይደለም። የዚህ ቡድን ቁንጮዎች እንደ መውዱዲ፣ ሰይድ ቁጥብ፣ ... ያሉት ሶሻሊዝምን እስከማወደስ የደረሱ ናቸው።
ቡድኑ ስለ ስነ ምግባር ይሰብካል። ነገር ግን በርካታ የቡድኑ ቁንጮዎች ባደባባይ ለመግለፅ በሚሰቀጥጡ የስነ ምግባር ንቅዘቶች የተነከሩ ናቸው። ስለ ዑለማእ ማክበር የሚያወራው ከራሱ የጥመት ቁንጮዎች ለመከላከል ብቻ ነው። ሶሐቦችን ለሚያብጠለጥሉ ሺዐዎች ጭምር ጥብቅና የሚቆመው ይሄ ወል- ጋዳ ቡድን የሱና ዑለማዎችን ለማንቋሸሽ ግን ሁለቴ አያስብም። እንዲያውም ንቃቱን፣ ብቃቱን የሚያሳየው በሳዑዲ መሪዎች በኩል አቆራርጦ ለኢኽዋን ቡድን የማይመቹ ዑለማዎችን በማብጠልጠል ነው። "የሰው ነውር መከታተል ነው ስራችሁ" የሚለው አስመሳይ ቡድን የሱና ዑለማዎችና ዱዓቶች ላይ ሃሰተኛ ውንጀላ መለጠፍ ግን የቀን ከሌት ስራው ነው። ዑለማዎቻችንን ሳያከብር እንድናከብረው ይፈልጋል።

ይሄ ቡድን ማፈሪያ ቢኖረው ኖሮ እጁንም ምላሱንም እንዲሰበስብ የሚያደርጉት እጅግ ብዙ ነውሮች ነበሩት። ግና ለዚያ አልታደለም። ያለ ፊትና መኖር አይችልም።

1- ኢኽዋን ሰዑዲ ውስጥ የሙዚቃ ኮንሰርት ሲዘጋጅ የሚጮኸው ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። ፈፅሞ! ቡድኑ ውስጥ "ሙዚቃ ሐላል ነው" የሚሉት እጅግ ብዙ ናቸው። ከእርቃን ቀረሽ ሴቶች ጋር የሚደንሱ እንደ "ሃሩን የሕያ" ያሉ ጠማ ^ሞችን በማወደስ የታወቁ ናቸው። የቡድኑ መሪዎች ገንዘብ እየከፈሉ የፈረንጅ ዳንስ ሲማሩ እንደነበር ለመናገር አያፍሩም። ይሄው ቀጠር ላይ የሙዚቃ ድግስ እንደተዘጋጀ እያወቁ ቀጠርን ሰማይ አድርሰው እያወደሱ ነው።

2- ሰዑዲያ ውስጥ ሴቶች ከነ ስትር አለባበሳቸው ምክር ቤት ሲገቡ ሸሪዐ ተናደ ብሎ ሲንጫጫ ነበር። የዚህ ሸውራራ ቡድን አባላት ግን ቱኒዚያ ውስጥ በገኑሺ መሪነት ፀጉራቸውን የጣሉ ጨብራራ ሴቶችን ፓርላማ አስገብቷል። ፀረ ሸሪዐ አቋማቸውን በግልፅ ሲያንፀባርቁ ነበር።

3- ይሄ ቡድን የሰዑዲያን መንግስት በንጉሳዊ ስርአቱ የተነሳ ሰርክ የሚተች ነው። ሁሌ የሚቆዝሙበት የአቶማን ተርክ መንግስትኮ ንጉሳዊ ነበር። ዛሬ የሚያጨበጭቡላት ቀጠርኮ ንጉሳዊ ስርአት ነው የምትከተለው።

4- ይሄ ቡድን ሰዑዲ ውስጥ የአሜሪካ ጦር ሰፈረ ብሎ ሲጮህ ነበር። "በካ^ fi ^ ር መታገዝ አይቻልም" እያለ ሲያራግብ ነበር። በመካከላቸው ምስራቅ ትልቁ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ያለውኮ ቀጠር ውስጥ ነው። ቱርክም ውስጥ የአሜሪካ የጦር ቤዝ አለ። የኢኽዋን መንጋ ግን ስለዚህ ትንፍሽ አይልም። እንዲያውም በርካታ የኢኽዋን ሰዎች ሙዐመር ቀዛፊን ለመጣል ከአሜሪካ እርዳታ ሲጠይቁ ነበር። የግብፅ ኢኽዋኖችም የአሜሪካን ሰንደቅ ክራቫት አድርገው ነጩ ቤተመንግስት ድረስ ለተማፅኖ ሄደዋል። ከዚህም በላይ ሑስኒ ሙባረክን ለመጣል ከእስራኤል ጋር ጭምር ሲነጋገሩ ነበር።

5- "ሰዑዲ ውስጥ ሸሪዐ የለም፣ ውስጥ ውስጡን የአልኮል መጠጥ ይሸጣል" እያለ የሚያራግበው የዚህ ቡድን ጀሌ፤ ቀጠር ስታዲየም አካባቢ አልኮል መከልከሏን በሃይለኛ እያራገበ ነው። ያ ጀማዕተል ሐምቓ መጠጥ የተከለከለው በስታዲየሞች ብቻ እንጂ በድፍን ቀጠር አይደለም። ደጋፊዎች በየ ካምፓቸው ሆነው መጠጣት አልተከለከሉም። በርካታ ቡድኖችም ከነ አሳማ ስጋቸው ነው ወደ ቀጠር የገቡት። ቢያንስ እያነበባችሁ።

6- ሰዑዲ በኻሊድ አራሺድ ላይ እስራት ጨመረች ብሎ የሚያለቅሰው የዚህ ቡድን ጭፍራ የቱርክ መንግስት አዛውንቶችን ጭምር አእላፍ ሲያንገላታ ትንፍሽ አይልም። ኻሊድ አራሺድ በዴንማርክ የተፈፀመውን ብልግና በማውገዙ ነው የታሰረው እያሉ ሞኞቻቸው ያስለቅሳሉ። ድርጊቱን ያወገዘው እሱ ብቻ ነበር? መቼም እነ ፈውዛን ቅጥረኞች ናቸው እናንተ ዘንድ። እሺ የምታወድሷቸው እነ ሰልማነል ዐውዳ፣ ሰፈር ሐዋሊ፣ ዐሪፊ፣ ቀርኒስ፣ ... አላውገዙም? ነው እነሱም እንደነ ፈውዛን ቅጥረኞች ናቸው? ከብዙ አውጋዦች መሃል ነው ተነጥሎ ኻሊድ አራሺድ የታሰረው?
ቱርክ ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በኋላ ከፈትሑላህ ጉለን ጋር ንክኪ አላቸው በሚል 3 የዜና ወኪሎችን፣ 23 የሬዲዮ ጣቢያዎችን፣ 18 ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን፣ 15 መፅሔቶችን፣ 45 ጋዜጦችን፣ 15 ዩኒቨርሲቲዎችን፣ 35 ሆስፒታሎችን፣ 104 የወቅፍ ተቋሞችን፣ 1,000 ት/ቤቶችን፣ 1,225 የበጎ አድራጎት ተቋማትን፣ … ስትዘጋ፣ 32 ሺህ ህዝብ ስታስር፣ 40 ሺህ ህዝብ ላይ ምርመራ ስታደርግ፣ ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ሰዎችን ስታስር፣ ከመንግስት ስራዎች ብቻ 60 ሺህ ህዝብ ስታፈናቅል፣ ከ93 ሺህ በላይ ህዝብ አጠቃላይ ከስራ ሲፈናቀል ምድረ ኢኽዋን በደስታ ነበር ሲቦርቅ የቆየው። የባሰ ጉድ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ ዝም፣ ጭጭ የሚሉት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor






Репост из: SadatKemal Abu Meryem
ማስታወቂያ
~
ረመዷን ሊገባ ሲል ተቋርጦ የነበረው አንፎ አካባቢ የሚሰጠው ደርስ ኢንሻአላህ የፊታችን እሁድ ይጀምራል።
.
መልእክቱን አሰራጩልን ባረከላሁ ፊኩም።


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
“የቆንጆ” ቢድዐ ቁርኣናዊ “ማስረጃ”
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በኢስላም የዒባዳ ፈጠራ የተወገዘ እንጂ የተወደሰ ምግባር አይደለም። ነብዩ ﷺ ቢድዐን በተደጋጋሚ ሲያወግዙም “ይሄ ሲቀር” ብለው ነጥለው ያስቀሩት የለም። “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ውድቅ ነው” አሉ እንጂ “በራሳችሁ መደንገግ ትችላላችሁ” አላሉም። “በዚህ (የዲን) ጉዳያችን ላይ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ እሱ ተመላሽ ነው” አሉ እንጂ “የሚያስመነዳ ቢድዐ አለ” አላሉም። “ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ”፣ “የሐጅ አፈፃፀሞቻችሁን ከኔ ውሰዱ”፣ “በኔ ላይ ለእናንተ መልካም ተምሳሌት አለ” አሉ እንጂ “አትጨናነቁ በራሳችሁም መጨመር የምትችሉት ዒባዳ አለ” አላሉም። የሶሐቦችም አካሄድ ይህንን ነው የሚያጠናክረው። ለቢድዐ ቀዳዳና መፈናፈኛ የማይሰጡ በርካታ ከባባድ ንግግሮችን ጥለው አልፈዋል። ይህም ሆኖ ግን ለሚፈፅሙት ቢድዐ “ጥሩ” የሚል ጭምብል የሚያለብሱ አካላት በየዘመኑ ያጋጥማሉ። ለዚህም ምንም እንኳን አዋጭ ባይሆኑም የሚጠቀሟቸው ብዥታዎች አሏቸው። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ተከታዩዋ አንቀፅ ነች፦
(تُدَمِّرُ كُلَّ شَيۡءِۭ بِأَمۡرِ رَبِّهَا فَأَصۡبَحُواْ لَا يُرَىٰٓ إِلَّا مَسَٰكِنُهُمۡۚ) [الأحقاف: 25]
{በጌታዋ ትእዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች። ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ።} [አልአሕቃፍ፡ 25]

አንቀጿ የነብዩ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ህዝቦች ባስተባበሉ ጊዜ ስለተላከችባቸው የቅጣት ነፋስ ነው የምታወራው። የቢድዐ ደጋፊዎች ግን “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” የሚለውን ሐዲሥ ለመገደብ ይህቺን አንቀፅ እንዴት እንደሚተነትኗት ተመልከቱ፡-
“ሁሉም ነገር ከሚለው ገለፃ ውስጥ ሰማይና ምድር፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነትና እሳት፣ መላኢካ፣ ጂን፣ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣ ግኡዛን… ሁሉ ይጠቃለላሉ። በተግባር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች አልወደሙም። አህቃፍ የተባለችው የከሃዲዎች መንደር ብቻ ናት የጠፋችው። የአንቀጿ ገለፃ ዐሙን መኽሱስ ይሰኛል። ገለፃው አጠቃላይ ቢሆንም በተጨባጭ እውነታ የተገደበ ነው። ቢድዐህ ሁሉ ጥመት ነው የምትለዋ ሀዲስም እንደዚሁ ገለፃዋ አጠቃላይና ሁሉንም አዲስ ነገሮች (ቢድዐዎች) የሚያካትት ቢመስልም በሌሎች ሀዲሶችና በሸሪዐው መርሆዎች የተገደበች ናት።”

ግና

1. በአንቀጿ ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል የቢድዐ አጋፋሪዎች የሚዘረዝሩትን ሁሉ የሚያካትት አይደለም። ነፋሷ የተላከችው ወደ አሕቃፍ ነው፣ ወደ ነብዩ ሁድ ሰዎች። በሌላ ቦታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَفِي عَادٍ إِذۡ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلرِّيحَ ٱلۡعَقِيمَ ٤١ مَا تَذَرُ مِن شَيۡءٍ أَتَتۡ عَلَيۡهِ إِلَّا جَعَلَتۡهُ كَٱلرَّمِيمِ) [الذاريات: 41-42]
{በዓድም ህዝብ ላይ አጥፊ የሆነችን ነፋስ በላክን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ።) በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወውም።} [አዛሪያት፡ 41-42]

ስለዚህ ነፋሷ ወደ አሕቃፍ መንደር ነው የተላከችው። ሰማይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነትና እሳት፣ … በአሕቃፍ መንደር አይደለም ያሉት።
2. በዚያ ላይ {በጌታዋ ፈቃድ} የሚል ቃል አለ። ስለዚህ እንድታጠፋ የተፈቀደላትን ብቻ ነው “ሁሉ” ሲል የገለፀው።
3. {ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ} ማለቱን አስተውሉ።
4. ከ21ኛዋ አንቀፅ ጀምራችሁ እያነበባችሁ ብትወርዱ እየተረከ ያለው ስለ ዓድ ህዝቦች እንደሆነ ግልፅ ነው። በዚህ አገባብ ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍንትው ያለ ሆኖ ሳለ ሰማይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፀሀይ፣ ጀነት፣ እሳት፣ መላኢካ፣ ጂን፣ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣… እያሉ ማተራመስ እጅግ የሚደንቅ ነው። “አስራ ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደብረ-ብርሃን ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተገልብጦ በውስጡ የነበሩት ሁሉም ተሳፋሪዎች አለቁ” በሚለው ዜና ውስጥ “ሁሉ” የሚለው ቃል እንደሱፍዮች አረዳድ ከአለም ህዝብም ተሻግሮ ጂንና መላእክትን ሁሉ ይገልፃል ማለት ነው። ከንዲህ አይነት የዛገ አመለካከት አላህ ይጠብቀን።

ለማንኛውም የቁርኣን ተንታኞች ስለ አንቀጿ ምን እንደሚሉ እንመልከት፡-

1. ኢብኑ ጀሪር አጦበሪ (310 ዓ.ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
وإنما عنى بقوله (تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا) مما أرسلت بهلاكه
“{በጌታዋ ትእዛዝ ሁሉንም ነገር ታጠፋለች} ሲል ማለት የፈለገው እንድታጠፋው የተፈለገውን ማለት ነው።” [ተፍሲር ኢብኒ ጀሪር፡ 22/129]

2. ቁርጡቢም (671 ዓ. ሂ.) እንዲህ ይላሉ፡-
كُلُّ شَيْءٍ مَرَّتْ عَلَيْهِ مِنْ رِجالِ عَادٍ وَأَمْوَالِهَا. قَالَ ابْنُ عَبَّاسٍ: أَيْ كُلُّ شَيْءٍ بُعِثَتْ إِلَيْهِ
“ያለፈችባቸውን የዓድ ሰዎችና ንብረቶቻቸውን ለማለት ነው። ኢብኑ ዐባስ፡ ‘የተላከችበትን ሁሉ ማለት ነው’ ብሏል።” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 16/206]

ሲጠቃለል በየትኛውም ሁኔታ “ሁሉ” የሚለው ቃል አገባቡን የሚከተል እንጂ የቢድዐ ልክፍተኞች እንደሚሉት ጀነትና እሳት ሳይቀር ከፈጣሪ ውጭ ያለን ነገር በሙሉ የሚያጠቃልል አይደለም። “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” ሲባልም እንዲህ አይነት ልጓም አልባ የሆነ አረዳድ የሚረዳ አንድም የለም። የቢድዐ ፍቅር የማገናዘብ አቅማቸውን ያሽመደመደባቸውን ወገኖቻችንን አላህ ዐቅላቸውን ይመልስላቸው።

ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ሊንክ፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
" ሴት ሰራተኞች አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ " - የካቡል ከንቲባ

የታሊባን አዲሱ የካቡል ከንቲባ [ስማቸው - ሐምዱላህ ኖማኒ] በካቡል የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ሴት ሠራተኞችን 'አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ' ሲሉ ተናገሩ።

ከንቲባው ይህን ያሉት ታሊባን ለጊዜው ሴቶች ሥራ እንዳይሠሩ ማዘዙን በመጥቀስ ነው።

"ክፍት የሥራ መደቦች በወንዶች የማይሞሉ ከሆነ ብቻ ለሥራ ልትመጡ ትችላላችሁ፤ አለበለዚያ ግን አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ" ብለዋል ከንቲባው።

የካቡል አዲሱ ከንቲባ እንዳሉት በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ውስጥ አንድ ሦስተኛው ሴቶች ነበሩ። ቤት እንዲቀመጡ የተነገራቸውም በቁጥር ወደ አንድ ሺህ ይጠጋሉ።

ታሊባኖች ሥልጣን ከያዙበት ዕለት ጀምሮ ሥራ የነበራቸው ሴቶች በሙሉ የአገሪቱ የደኅንነት ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ ቤት እንዲቀመጡ አዟል።

ሕጉን በመቃወ ሰልፍ በወጡ ሴቶች ላይም ድብደባ ፈጽሟል።

ታሊባን የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ያፈረሰ ሲሆን በምትኩ ሐይማኖታዊ ደንቦች መከበራቸውን የሚቆጣጠር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አቋቁሟል።

በዚህ ሳምንት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ቢሆንም ወንድ ተማሪዎች እና ወንድ አስተማሪዎች ብቻ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ነው የተነገራቸው።

ሴት ተማሪዎቸና አስተማሪዎች ግን ለጊዜው ቤት እንዲቆዩ ተደርጓል።

ታሊባን ለሴቶች የተለየ ትምህርት ቤቶችን እያዘጋጀሁ ነው ብሏል።

መረጃው ከቢቢሲ ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia


Репост из: Bahiru Teka
🚫 ገጠሬ መስሎ አታላዮች
በአሁን ጊዜ በሰበታ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን የሚያታልሉ ገጠሬ መሳዮች መጥተዋልና ተጠንቀቁ ።
እነዚህ አታላዮች በዘንቢል ቅቤ ይዘው ከገጠር በትእዛዝ የመጡ በማስመሰል ስልካቸው ከነ ተሰጣቸው የስልክ ቁጥር የጠፋባቸው እንደሆነና መግቢያ አጥተው ሲንከራተቱ አንድ ሙተነቂብ እንዳስጠጋቻቸው እያስመሰለች ሌላ ቦታ ደግሞ ወንድ በማድረግ ለትራንስፖርት እንዲሆናቸው በእርካሽ እየሸጡ ነው በሚል ህዝቡ እየተሽቀዳደመ እንዲገዛ ይደረጋል ። ገጠሬዎቹ ሶስት ናቸው ኩርምት ብለው ይቀመጣሉ ቋንቋ አያውቁም ይባላል ። በዚህ መልኩ አንድ አካባቢ ካታለሉ በኋላ ወደ ሌላ አካባቢ? ይሄዳሉ ። ይህ በትእዛዝ መጣ የሚባለው ቅቤ ምን እንደሆነ አይታወቅም ላዩ በጣም ንፁህ ለጋ ቅቤ ይቀባል ።
ውስጡ ያለው ግን ምን እንደሆነ አላህ ይወቀው ።
የገዙ ሰዎች እቤት ወስደው ሲያነጥሩት ግማሾቹ አይረጋም ውሃ ነው ይላሉ ሌሎች ደግሞ ይረጋል ግን መልኩ ይቀየራል ምን እንደሆነ አይታወቅም ይላሉ አብዛኞች የሚታለሉት ሙተነቂቧ በምትተርከው አሳዛኝ ታሪክ ነው ። አላህን የማይፈሩ በኒቃብ ሰውን ያታልላሉ የኢስላምንም ገፅታ ያጠለሻሉ በመሆኑም እነዚህን አታላዮች ተጠንቀቁዋቸው ።
አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ።
http://t.me/bahruteka


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ዚል-ቀዕደህ 21/1442 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: Ibnu Ahmed
የጁመዓ ቀን ሱናዎች
=========

📌 ገላን መታጠብ

📌 ንፁሕ ልብስ መልበስ

📌 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)

📌 በጊዜ ወደ መስጂድ መሔድ

📌 ሱረቱል ካህፍ መቅራት

📌 ዱዓ ማድረግ ማብዛት

📌 በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ.....

t.me/IsmaelAhmed


Репост из: Ibnu Ahmed
አሏሁ አክበር !!

አል አሚር ሙሀመድ ቢን ሰልማን ከሼኽ ሷሊህ አል ሸይኽ ጋር በመሆን ፡ የጊዜያችን ታላቅ የሱና አሊም የሆኑትን (ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛንን) ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሂደው እየዘየሯቸው ፡ ለሼኽ ፈውዛን ምን አይነት ክብር እንደሚሰጣቸው ተመልከት !!

- እወቅ !! እነዚህ ንጉሶች ፡ - የተውሒድና ሱና ዑለማወችን እንዲህ ያከብራሉ ፡ የኸዋሪጅን ፊክራ ለማራመድ የሚፈልግን ዲንና ሀገር የማፈራረስ ጥም ያለበትን ኢኽዋኒ ደግሞ ወደ ወህኒ ቤት ይወረውራሉ ፡ !

አሏህ ሆይ ! የተውሐድ ሀገር የሆነችዋን ሳዑዲን እና መሪዎቿን እንዲሁም የሱና ኡለማወቿን አንተ ጠብቃቸው .... አሚን
t.me/IsmaelAhmed/146


Репост из: Ibnu Ahmed
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
t.me/IsmaelAhmed/146


Репост из: Ibnu Ahmed
🔴 መንገድ ላይ የጠፋ ብር ያገኘ ሰው ምን ማድረግ ነው ያለበት 🔴
_____________

1. ሸይኽ አልባኒ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፡

ጥያቄ፡- አንድ ሰው የተወሰነ ጥቂት ገንዘብን ወይንም ሌላን እቃ መንገድ ላይ ወድቆ ቢያገኝ ምን ማድረግ ነው ያለበት ?

መልስ፡- ሰውየው ያገኘው ገንዘብ ወይንም እቃ አንተ እንዳልከው የተወሰነና ጥቂት ከሆነ ፡ እና ይህ ሰው ዳሀ ሚስኪን ከሆነ ይህ ወድቆ ያገኘው ገንዘብ ወይንም እቃ ከሌሎች ዳሃወች ይልቅ ለሱ ለራሱ ላገኘው ነው ተገቢ የሚሆነው ፡ ይሄን ገንዘብ ወይንም እቃ ያገኘው ሰው ሀብታም ከሆነ ለሚያውቀው ዳሀ ሚስኪን ይስጠው ፡፡

ምንጭ፡- ሲልሲለቱል ሁዳ ወን ኑር ( 439 )

____________

2. ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ ፡

- አንድ ሰው በመንገድ ላይ ገንዘብ ወድቆ ካገኘ ቅድሚያ የገንዘቡን መጠን ይመልከት ፡

- ያገኘው ገንዘብ ሰወች ቦታ የማይሰጡት ጥቂት ገንዘብ ከሆነ፡ ይህ ገንዘብ ለሱ ለራሱ (ገንዘቡን ላገኘው) ነው የሚገባው ፡ የገንዘቡን ባለቤት መፈለግም አያስፈልግም ፡ ግን የገንዘቡን ባለቤት ያወቀው እንደሆን ሊመልስለት ይገባል (የገንዘቡ መጠን ጥቂትም ቢሆን) ፡፡

- ለምሳሌ ፡ ሰውየው አምስት ሪያል መንገድ ላይ ወድቆ አገኘ እንበል ፡ በአሁን ጊዜያችን አምስት ሪያል ምንም ቦታ የላትም ፡ ሰውም አምስት ሪያል ጠፋኝ ብሎ አያስባትም ፡ ስለዚህ ይችን መንገድ ላይ ወድቃ ካገኘሀት ብትወስዳት ችግር የለውም ፡

- ነገር ግን የዚችን አምስት ሪያል ባለቤት ያወቅክ እንደሆን ልትመልስለት ግድ ይለሀል ፡ የጠፋው ገንዘብ ባለቤት እስከታወቀ ድረስ የገንዘቡ መጠን ጥቂትም ሆነ ብዙ ፣ እንድትመልስለት ፈለገም አልፈለገም ይህ ገንዘብ ሊመለስለት ይገባል ፡፡

- ይህ ያገኘኸው ገንዘብ ብዛት ካለውና ሰዎች የሚፈልጉት ከሆነ ፡ (የዚህን አይነቱን ገንዘብ አንድ አመት ድረስ ይዘህ ባለቤቱን ልትጠብቅና ልትፈልገው ይገባል) ፡፡

ምንጭ፡- ኑሩን አለ ደርብ (254 )


Репост из: Bahiru Teka
👉 የዙል ሒጃ ዘጠነኛ ቀን ፆም
የዙል ሒጃ ዘጠነኛ ቀን ፆምን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መለሱ : –
عنْ أَبي قتَادةَ – رضي الله عنه – ، قال َ: سئِل رسولُ اللَّهِ ﷺ : عَنْ صَوْمِ يوْمِ عَرَفَة َ؟ قَال َ: " يكفِّرُ السَّنَةَ المَاضِيةَ وَالبَاقِيَة "
َ رواه مسلمٌ
" ያለፈውን አመትና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል "
🔹 በአቡ ቀታዳ ተወርቶ ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል ።
አብዛኛዎች የረመዷን ቀዳእ እያለ ሱና ፆም መፆም አይቻልም የሚሉ ሊቃውንቶች የዙል ሒጃን ዘጠነኛ ቀን ይፈቅዳሉ ከፊሎቹ ዘጠኙንም ቀን ይፈቅዳሉ በመሆኑም ቀዷእ ያለባቸው እህቶችም ይህን ቀን መፆም ይችላሉ ። ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከሌለ በስተቀር የዚህን አይነት ምንዳ ማስመለጥ አይገባም ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች!

የነገው የአንፎ ደርስ የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን በቀጣይ እሁድ የተለመደው ደርሣችን ይቀጥላል - በአላህ ፈቃድ።
ቴሌግራም ለማይጠቀሙ እየተደዋወላችሁ ለምታውቁት አድርሱልን። ሰዎች እንዳይንገላቱ መልክቱን አሰራጩልን።


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አንድ ነጥብ ለአስተውሎት
~~~~~~~~~
በጣም ከምንሸወድባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ በእውቀት የሚበልጡንን መሻይኾች ልንጠቀምባቸው አለመቻላችን ነው። በሃገራችን የመንሃጅ ግንዛቤ በጣም የሳሳ እንደሆነ ማንም የማይክደው ሐቅ ነው። ይሄ ክፍተት ደግሞ ብዙ መሻይኾች ላይ ይጎላል። ለወቅታዊ ኪታቦችና ለኢንተርኔት የቀረበው ወጣት #አንፃራዊ በሆነ መልኩ ትንሽ ሻል የሚልበት ሁኔታ አለ። በንፅፅር ነው እያወራሁ ያለሁት። ትንሽ እውቀት የራሱ ብዙ ድክመት አለበትና የማንክደው ብዙ ጣጣ እያመጣብን ነው። ሌሎችን ችግሮች ለጊዜው ልተውና በተነሳሁበት ጉዳይ ላይ ያለውን ላንሳ። ድርቅና (ዒናድ) ሳይሆን የግንዛቤ ችግር ያለባቸውን መሻይኾች መቅረብ እንጂ መራቅ ለሁሉም አይበጅም። ይሄ ማግለልና መግፋት ለነሱም፣ ለኛም፣ ለቆምንለት አላማም፣ ለወገናችንም የሚበጅ አይደለም፡፡ እና ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል እጅ መስጠት ካሸተትንባቸው ክፍተቶችን ብናይ እንኳ ከመራቅ ይልቅ መቅረባችን ነው የሚያተርፈን።

1ኛ:- ለነሱም ውለታ መዋል ነው። እኛ ችላ ስንላቸው በሌሎች አንጃዎች ይጠለፋሉ። ይሄ ከዚህ ቀደም በስፋት ተከስቷል። እኛ ስንርቃቸው የሌሎች ሲሳይ ሆነዋል። በራሳችን ላይ ጠላት አብዝተናል። ካለፈው ልንማር በቃ ልንል ይገባል፡፡
2ኛ:- ለሰፊው ህዝበ ሙስሊም፦ እነዚህ መሻይኾች ህዝብ ዘንድ የተሻለ ቦታ ስለሚኖራቸው የነሱ መጠንከር ለህዝብ ይተርፏል፡፡ እኛ ባግባቡ ካልቀረብናቸው ግን የሚጠልፏቸው አንጃዎች የሰለፊያን ዳዕዋ በጥላቻና በስጋት እንዲመለከቱ አድርገው ይሞሏቸዋል። ይሄ ደግሞ ዞሮ ዞሮ ዳፋው ለህዝብ ነው የሚተርፈው።
3ኛው:- ጥቅም ለራሳችን ነው፡፡ እኛ ትንሽዬ የመንሃጅ ግንዛቤ አለችን ማለት (ያውም ከኖረ) ከነሱ በእውቀት በለጥን ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ከነጭራሹ እውቀት አለን ማለትም አይደለም። እነሱ ዘንድ መንሃጅ ላይ የግንዛቤ ክፍተት መታየቱ እውቀት የላቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለሁለቱም ወገን የሚበጀው መቀራረቡ ነው። እነሱ ዘንድ ያለውን ክፍተት ከቻልን ኪታብ እየገዛንላቸው ፣ ካልሆነ እያዋስናቸው፣ የታላላቅ ዑለማዎችን ንግግር እያሰማናቸው፣ በአደብ እየተከራከርናቸው ለመሙላት መጣር አለብን። በተለይ ኪታብ መስጠት ያለው ዋጋ ቀላል አይደለምና በዚህ ላይ ልንረባረብ ይገባል። የኛን ጅህልና ደግሞ ቁጭ ብሎ በመማር መግፈፍ አለብን። ይህን ስናደርግ ለራሳችንም፣ ለመሻይኾቹም፣ ለወገናችንም ትልቅ ውለታ እንውላለን። ለደዕዋችን መፋፋትም ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ የማወራው ከላይ እንደገለፅኩት ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል እራስን ዝቅ ማድረግ፣ ቅንነት ስለሚታይባቸው መሻይኾች ነው። አላማዬ ጥቆማ መስጠት ነው። ሃሳቡን ይበልጥ ልታዳብሩት ትችላላችሁ። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። ኣሚን።

https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.

59

подписчиков
Статистика канала