(ምኔ ነህ??)
ልጠይቅህ አለሜ ግራ የገባኝን
ልመልስ ፈልጌ ያወዛገበኝን
ልጠይቅህ እና መልስ አገኝለት
ያጨናነቀኝን መፍትሔ አበጅለት
ለኔ አንተ ምንድነህ❓እኔስ ላንተ ማነኝ❓
ምንስ ይፈጠራል ብታገኝ ብታጣኝ
መመለስ ከብዶህ እኔን ከጠየከኝ
መልሽልኝ ብለህ አጥብቀህ ከያዝከኝ
እንግዲህ ስማኛ አድምጠኝ ከልብህ
አንተ ካላወከው በቃ እኔው ልንገርህ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሳቅፍህ እኮ ሱሴ
ወደ ደስታአለም ትነጉዳለች ነብሴ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሁሉን እፈታለሁ
ያስከፋኝንም ሰው ይቅር እለዋለሁ
ላስጨነቀኝ ነገር መፍትሄ አገኛለሁ
የፈለኩትንም ሁሉን አደርጋለሁ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሁሉም ይቀርና ደስተኛ እሆናለሁ
እና የኔ ደስታ አንተ ለኔ ማነህ❓
ለምንድነዉ ከሰው ከሁሉ የተለየህ
መልሱን አላውቀውም ለኔ ምን እንደሆንክ
እንደሚመስለኝ ግን ደስታዬ ብቻ ነክ
ልጠይቅህ አለሜ ግራ የገባኝን
ልመልስ ፈልጌ ያወዛገበኝን
ልጠይቅህ እና መልስ አገኝለት
ያጨናነቀኝን መፍትሔ አበጅለት
ለኔ አንተ ምንድነህ❓እኔስ ላንተ ማነኝ❓
ምንስ ይፈጠራል ብታገኝ ብታጣኝ
መመለስ ከብዶህ እኔን ከጠየከኝ
መልሽልኝ ብለህ አጥብቀህ ከያዝከኝ
እንግዲህ ስማኛ አድምጠኝ ከልብህ
አንተ ካላወከው በቃ እኔው ልንገርህ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሳቅፍህ እኮ ሱሴ
ወደ ደስታአለም ትነጉዳለች ነብሴ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሁሉን እፈታለሁ
ያስከፋኝንም ሰው ይቅር እለዋለሁ
ላስጨነቀኝ ነገር መፍትሄ አገኛለሁ
የፈለኩትንም ሁሉን አደርጋለሁ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሁሉም ይቀርና ደስተኛ እሆናለሁ
እና የኔ ደስታ አንተ ለኔ ማነህ❓
ለምንድነዉ ከሰው ከሁሉ የተለየህ
መልሱን አላውቀውም ለኔ ምን እንደሆንክ
እንደሚመስለኝ ግን ደስታዬ ብቻ ነክ