Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Экономика


የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Экономика
Статистика
Фильтр публикаций


ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች

የካቲት 24/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የታክስ ዓይነቶች ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡

ለዚህ ክፍፍል መሰረቱ ታክሱን ሰብስቦ ለመንግሥት የመክፈል ኃላፊነት እና ታክሱን የመክፈል የመጨረሻው ኃላፊነት የሚያርፍባቸውን አካላት መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ቀጥተኛ ታክስ የሚባለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በሚያገኘው ገቢ ላይ በቀጥታ የሚከፍለው እና ታክስ የመክፈል የመጨረሻ ኃላፊነቱ በዚሁ ታክስ ከፋይ ላይ ሲሆን ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/FePK1


በQR Cod የተደገፈ የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የህትመት ጥያቄያቸውን ማቀረብ እንደሚገባቸው ተገለፀ

የካቲት 24/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ካሣሁን ደመመ ሀሰተኛ ደረሰኝ የገቢ አሰባሰብ ተግባር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ መሆኑን እና ግብር ከፋዩን ባለተገባ መልኩ ለታክስ ማጭበርበር ወንጀል ሲዳርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍም የደረሰኝ አስተዳደር እና አጠቃቀም ሥርዓትን በማሻሻል በQR Cod የተደገፈ እና ሚስጥራዊ መለያ ያካተተ የደረሰኝ ህትመት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኑ በግብር አሰባሰቡ ላይ በጎ ውጤት እንደሚያመጣ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች እያጋጠሙ የነበረ መሆኑን እና በተያዘው በጀት ዓመትም በሀሰተኛ ደረሰኝ ምክንያት በ5 ድርጅቶች አለአግባብ ሊቀናነስ የነበረ 104 ሚሊየን ብር ገቢ በኦዲት ሥራ አማካኝነት ማዳን መቻሉን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ አዲሱ የደረሰኝ ህትመት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/b6O90


#ማስታወቂያ

የካቲት 23/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

#ለሽያጭ_መመዝገቢያ_መሳሪያና_ሶፍትዌር/ሲስተም_አቅራቢዎች_በሙሉ

የገቢዎች ሚኒስቴር የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝነት ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በቀጣይ ለመተግበር ባቀደው የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ላይ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ፣ ሶፍትዌር ወይም ሲስተም አቅራቢዎች በሚከተሉት አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ለማድረግ አቅዷል፦

1. ከገቢዎች ሚኒስትቴር የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ጋር ሶ
ፍትዌር/ሲስተም ለማስተሳሰር በሚጠበቁ ተግባራት ፤
2. ስለ ግብይት ምዝገባ እና ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ለገዥ/ከፋይ ስለማስተላለፍ፤
3. ከተሳታፊዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠት።

በዚህ ምክክር በነባሩ አሰራር መሰረት የካሽ ረጂስተር ማሽን ፣ ፖስ እና ሌሎች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በተጨማሪ በቀጣይ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ጋር በመተሳሰር ግብር ከፋዮች ግብይታቸውን መዝግበው ደረሰኝ እንዲያስተላልፉ የሚያስችሉ ሶፍትዌር ወይም ሲስተሞችን የማልማትና በገቢዎች ሚኒስቴር እውቅና የማግኘት እቅድ ያላቸው ድርጅቶችም እንዲሳተፉ ይበረታታል።

በመሆኑም እርስዎ በስራው ላይ ካሎት ተሳትፎ አኳያ በውይይቱ ላይ ለመገኘት ያለዎትን ፈቃደኝነት እስከ ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በተዘጋጀው የጉግል ፎርም ላይ እንዲገልጹልን እየጠየቅን፤ የውይይቱ መድረክ የሚካሄድበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት ፎርሙን በሞሉበት የኢሜይል አድራሻዎ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የመመዝገቢያ ፎርም፦ https://forms.gle/DUqR7V3t34ppK8757


334 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የካቲት 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከየካቲት 14 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው ክትትል 334 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ እና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በሞያሌ፣ በአዋሽ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 20 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 11 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ፡- የጉምሩክ ኮሚሽን


አድዋን እንዘክራለን፣ ግብርን በትጋት በመሰብሰብ የኢትዮጵያ አንድነት እናሻገራለን!!

የካቲት 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የዋናው መ/ቤት ሰራተኞች 129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል በፓናል ውይይት በደመቀ መልኩ አክብረዋል፡፡

በበአሉ አከባበር ላይ በመገኝት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ በመላው ጥቁር ህዝቦች በዓለም አደባባይ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ ያደረጉ አያቶቻችን ትልቅ መሰዋትነት በመክፈል ተፋልመዋል እኛም ይሄንን ድል አስቀጥለን እንድንሄድ ሀገራችን በኢኮኖሚ እራሷን የቻለች እንድትሆን በራሷ የምትተማመን ሀገር እንድትኖረን ግብርን በአግባቡ ሰብስበን እራሷ የምትተዳደር ሀገር መፍጠር አለብን ብለዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ ከአድዋ ልንማርበት የሚገባ አንድነታችንን አጠናክረን ስንሄድ ጠንካራ ሀገር እንገነባለን ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/Z4Q0u


"አደዋ የጥቁር ህዝቦች ድል"

የካቲት 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

እንኳን ለ129ኛውን የድል በአል አደረሳችሁ! አደረሰን!


የታክስ አይነቶችና የማሳወቂያ ጊዜያት

የካቲት 21/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

#ከመቀጠር_የሚገኝ_ገቢን_በሚመለከት
👉ከራስ ገቢ ላይ የሚቀንስ በየ3 ወሩ፣
👉ድርጅቶች በየወሩ፡፡

#ከቤት_ኪራይ_እና_ንግድ_ሥራ_ገቢ_ግብርን_በሚመለከት፤
👉ደረጃ “ሀ” ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30፤
👉ደረጃ “ለ” ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 5/6፤
👉ደረጃ “ሐ” ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30፤

#በሰንጠረዥ “መ” ሌሎች ገቢዎች ምድብ ስር የሚመደቡት የገቢ አይነቶች
👉ሮያሊቲ፣
👉የትርፍ ድርሻ፣
👉ወለድ፣
👉ከእድል ሙከራ የሚገኝ ገቢ፣
👉የቴክኒክ እና ሰራ አመራር ክፍያ፣
👉ግብሩ ተቀናሽ ካልተደረገ በስተቀር ገቢውን ያስገኘው ግብይት ከተደረገበት ቀን
ጀምሮ ባሉት ሁለት ወራት፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/eaeV3


ጉምሩክ ኮሚሽን የተሻለ የሕግ ተገዥነት ካላቸው አስመጪዎች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች ጋር መከረ

የካቲት 20/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ጉምሩክ ኮሚሽን ከሰማንያ በመቶ በላይ ከሆኑ እና የተሻለ የሕግ ተገዥነት ካላቸው አስመጪዎች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች ጋር የካቲት 20/2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሂዷል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/NjYiL


የንግድ ስራ ገቢ ግብር ምጣኔ

የካቲት 20/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የንግድ ስራ ገቢ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-

👉 ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣

👉 የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (ከመዝገብ ዋጋ በላይ ያለው ዋጋ)፣

👉 በዚህ አዋጅ መሠረት የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርገው የተወሰዱ ሌሎች ማናቸውም ገቢዎች፣

👉 የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ በሚገኘው ጥቅም ላይ ሁለት ግብሮች ሊወሰኑ ይችላሉ፡፡

- የንግድ ትርፍ ግብር

- የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር

👉ለንግድ ስራው ሃብት የተደረገው ወጪ ከንግድ ስራው ሀብት የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚበልጠው የገንዘብ መጠን በንግድ ስራ ገቢ ውስጥ የሚካተት ሲሆን ከወጪው በላይ የሚገኘው ጥቅም ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡


የንግድ ስራ ገቢ

ግብር የሚከፈልበት የንግድ ስራ ገቢ አወሳሰን

ግብር የሚከፈልበት የንግድ ስራ ገቢ የሚባለው በግብር ዓመቱ ውስጥ ከተገኘው ጠቅላላ የንግድ ስራ ገቢ ላይ በህግ የተፈቀዱ ወጪዎች ተቀንሰው የሚገኘው የተጣራ የገቢ መጠን ነው፡፡

የአዋጅ ድንጋጌዎች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ እና የሚኒስቴሩ መመሪያ እንደተጠበቁ ሆነው ግብር ከፋዩ የግብር ዓመቱን ግብር የሚከፍልበት የንግዱ ስራ ገቢ የሚወሰነው በፋይናንሻል ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት በሚያዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም የገቢ መግለጫ ላይ በመመስረት ይሆናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/jQWHV

Показано 10 последних публикаций.